#Update
32 ኢትዮጵያዊያን ከታይላንድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
በማይናማር ታግተው ከቆዩ በኋላ ከሳምንታት በፊት ወደ ታይላንድ ተሻግረው ከነበሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 32ቱ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።
32 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መድረሳቸውን ከተመላሾቹ አረጋግጠናል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ 32 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን አስታውቋል።
ተመላሾቹ እንደሚሉት ከሆነ፤ የታይላንድ መንግስት አልቀበላችሁም ያላቸው ወደ 300 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ካምፕ ገና አልወጡም።
ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩት መካከል ደግሞ ወደ 5 ልጆች ተመልሰው ተወስደዋል።
ወደ 29 የሚሆኑ ኢትዮጵውያን ደግሞ ማይናማር ውስጥ "ዋልዋይ" የሚባል ቦታ የከፋ ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ።
ታይላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው፣ "ሌሎች በርካቶች በሌሎች ካምፓች ስቃይ እየደረሰባቸው ነው" ብለዋል።
@ThiqahEth