ንፅፅር ላይ ለተሰማራችሁ ወገኖች አጭር ጥቆማ
~
1- በቀዳሚነት የማነሳው ስራችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ የሚል ነው። የግርግር ፈጣሪዎች ዋና አላማ ይህን ማሰናከል ስለሆነ ይበልጥ ትጋታችሁን ጨምሩ።
2- አቅማችሁን ይበልጥ አዳብሩ። በተለይም በቀዳሚነት የራሳችሁን ኢስላማዊ ግንዛቤ ከዐቂዳ ጀምራችሁ አጥሩ። እንደ አጠቃላይ ጥልቅ የሆነ ንባብና ጥናት ይኑራችሁ። ዘርፉ በደከመ አቅም የሚገባበት አይደለም። ወይ ባጭር ታጥቃችሁ ግቡ። ካልሆነ ይቅርባችሁ።
3- የሚቻል ከሆነ የጋራ መድረክ ቢኖራችሁ መልካም ነው። አካሄዱ ላይ የሚታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ነቅሳችሁ የምትነጋገሩበት፣ ተግዳሮቶች እና መፍተሄዎቻቸው ላይ የምትወያዩበት፣ ልምድ የምትቀሳሰሙበትና የምትተራረሙበት፣ መረጃዎችን የምትለዋወጡበት፣ ... የጋራ መድረክ ቢኖር መልካም ነው። የሚቻል ከሆነ ማለቴ ነው። በሆነ ምክንያት በተናጠል መስራቱ ከተሻለም እሰየው።
4- በውይይት ጊዜ፣ በአቀራረብ ላይ፣ ... ሊኖራችሁ የሚገባን አደብና አነጋገር ድባቡ የሚወስነው ሳይሆን ቀድሞ የተጠና፣ ጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ፣ ትንኮሳ የማይወዘውዘው እንዲሆን አድርጎ መቅረፅና ማነፅ ይገባል። ደግሞም አጀንዳ ተቀባይ አትሁኑ። መስመራችሁን አትልቀቁ፣ አታስለቅቁ። ካልሆነ ፍሬያማነታችሁን ሊቀንሰው ይችላል።
5- በተቻለ መጠን ከደዕዋው መስክ አትጥፉ። ሰዎች ናችሁና ሁሌ አይደላችሁም። የማይመች ሁኔታ ሊገጥም ይቻላል። ቤተቻለ መጠን ግን ከደዕዋው ዘርፍ አትራቁ። በመሀል እልም ማለት ሞራላችሁንም፣ አቅማችሁንም፣ ተፅእኗችሁንም ያቀዘቅዘዋል። ቆይታችሁ ስትመለሱ ነገሮች እንዳሰባችኋቸው ላይሆኑ ይችላሉ።
አላህ ያበርታችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor