❞الواسطة بين الحق والخلق ❝
❛አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ❜
【መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ ❺】
«ዑመር ኢብኑ ዐብዲል ዐዚዝ እንድህ ይላሉ» ፦ እኛ የምናስተካክለዉ ጉዳይ ከአላህ ዉጭ ምንም አጋዥ የለዉም። ታላላቆች አልቀዉበታል። ህፃናቶች ሸብተዉበታል። ባለሀገሮች ተሰደዉበታል። እምነት ነዉ ብለዉ ያስቡታል እርሱ ግን ከአላህ ዘንድ እምነት አይደለም። በዚህ ላይ አዲስ ነገር የለም፦ መልእክተኛዉ ﷺ እንድህ ሲሉ የእስልምናን እንግዲነት ተናግረዋል"እስልምና እንግዳ ሆኖ ጀመረ ፣እንደጀመረዉ ወደ እንግድነት ይመለሳል። ለእንግዶች ጡባ(በዱኒያ መልካም ኑሮ በአኼራ ያማረ መመለሻም) አላቸዉ። «ሙስሊም በቁጥር 145 ዘግበዉታል።»
መልክተኛዉ ﷺእንዲህ ይላሉ፦ "ለእንግዶች ጡባ አላቸዉ። እነዚያ ሰዎች ሲበላሹ የሚያስተካክሉ ለሆኑት። (አቡ ዑመር አድዳኒ ሶሒሕ በሆነ ሰነድ ዘግበዉታል)
መልእክተኛዉﷺጉረባእ ማለት ምን ማለት ነዉ ? ከተባሉ በኋላ እንዲህ አሉ፦ በመጥፎ ሰዎች ዉስጥ ያሉና ከሚታዘዛቸዉ ይልቅ የሚያምፃቸዉ የሚበዙ ጥሩ ሰዎች ናቸዉ አሉ። (ሐዲሱ ሶሒሕ ነዉ ኢማሙ አሕመድ ዘግበዉታል ሶሒሑል ጃሚዕ ቁጥር 3918 ይመልከቱ)
«ይህች ቡዲን በማስተካከሉ ዘርፍ ላይ ሙስሊሞች ነቅተዉ ወደ ትክክለኛ እስልምና እስኪመለሱ ድረስ የተሀዲሶን መብራት በ ማብራት ጠንክራ መስራት አለባት። ተፃራሪ ለሆኑ አጥፊዎች አላህ ለአምሳያዎቻቸዉ ያለዉን እንላለን፦
"መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን ? በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን። በአላህ ላይ ተመኪዎች ይመኩ።" (ኢብራሂም :12)
«አሁን "አል ወሳኢጥ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ" በተሰኘችዉ ምርጥ መልእክታቸዉ አል ወሳኢጥን እንድያብራሯት መድረኩን ለሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንተዉላቸዉ።
«ይች በወርቅ ብዕር ልትፃፍ ይገባል። ሙስሊሞችም በነብያትና በደጋግ ሰዎች ቀብር ዙሪያ መዞራቸዉን ትተዉ፤ በፍርሃትና በዉርደት በቆሻሻቸዉ መተባበስ ርቀዉ፣ ከእንቅልፋቸዉ ነቅተዉ፤ የሃይልን፣ የዲልን አድራጊነትን ምክንያት ይዘዉ በአጽንኦት እና በማስተንተን ላማሯት ይገባል።
«መልካም ነገሮችን ሁሉ አስተማሪ በሆኑት ነብያችን ሙሐመድ ላይ የአላህ ሶላት ይዉረድ በቤተሰቦቻቸዉ እና በባልደረቦቻቸዉ ላይ ይስፈን። የመጨረሻ ጸሎታችን ምስጋና ሁሉ ለአላማቱ ጌታ አላህ ይሁን ።(ሞሕሙድ መህዲ የቱሕፈቱል ዐሩስ ኪታብ ባለቤት)
✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል......!
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

« وَمَا لَنَاۤ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَاۤ ءَاذَیۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡیَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ »