መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ደብዳቤ ተላከላቸው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫውቸን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተውና ከአንድ ሳምንት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ድንበር ውስጥ ለሚያደርጓቸው ማናቸው እንቅስቃሴዎች ቅድመ ፈቃድ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡፡
በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች በተመለከተ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተቀመጠ የቅድሚያ ማሳወቂያ ፎርም ከሞሉ በኋላ መሆን እንዳለበት አመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተጻፈው ደብዳቤ ማስጠንቀቂያው ለሥራ ወይም ለግል ጉዳይ የሚጓዙትን እንደሆነ በግልጽ አያስረዳም፡፡
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ከዚህ ተመሳሳይ ድበዳቤ ተጽፎ የነበረ ቢሆንም፣ አንዳንድ ዲፕሎማቶች አሁንም ከፌዴራል መንግሥቱ ዕውቅና ውጭ ሲንቀሳቀሱ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዓመት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ ክልሎች በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ብቻ በተሰጠው የውጭ ግንኙነት ሥራ ላይ እየተሳተፉ በመሆኑ ፓርላማው ማሳሰቢያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር፡፡
ምንጭ: ሪፖርተር
@Addis_Reporter