የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገራችን "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በድምቀት አከበረ፡፡
በዓሉ ዶክተር እመቤት መለሰ፣ የባንኩ ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበራት የኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ አንተነህ ግርማ፣ የባንኪንግና ፋይናንስ ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ የምሥራች አለምነህ እና ሌሎችም የባንኩ ሴት ሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች፣ እንዲሁም ተጋባዥ የባንኩ ሥራ ኃላፊዎች በታደሙበት ሰፊ መድረክ የተከበረ ሲሆን፣ ባንኩ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝዳንት መሪው አድርጎ እያሠራ ባለበት ጊዜ መከበሩ በዓሉን ልዩ አድርጎታል፡፡
በዚሁ በዓል ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት ዶክተር እመቤት መለሰ ‹‹ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት የሴቶችን ተሳታፊነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ያሉ ሲሆን ‹‹ሴቶች ወደ አመራር በመጡ ቁጥር የተቋማት ውጤታማነት እንደሚጨምር በተግባር የታየበት ወቅትም ነው›› ብለዋል፡፡
በበዓሉ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ሠራተኞች ማኅበራት የኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ አንተነህ ግርማ በበኵላቸው ሴቶች ሁሉም ቀን የሴቶች እስኪሆን ድረስ መታገልና መትጋት እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን፣ የፋይናንስ ተቋማት የሴት አመራሮችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ አሳስበዋል፡፡
የባንኩ የሴቶች ተወካይ ወ/ሮ ዓለም ስዩም ‹‹በዓሉን በባንካችን እያከበርን ያለነው ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዝዳንት የተሾሙበት እና በተሾሙ ማግስትም በሴቶች የአመራርነት አቅም ግንባታ ላይ ሰፊ ሥራ ለመሥራት የሚያስችሉ ሥልጠናዎች በተከተታይ እየተሰጡ ባለበት ጊዜ መሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል›› ብለዋል፡፡
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃም “For ALL women and girls: Rights. Equality. Empowerment.” በሚል መሪ ቃል ለ114ኛ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡-
www.dbe.com.etፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/dbethiopiaቴሌግራም፦
https://t.me/DBE1900ትዊተር፡-
https://twitter.com/DBE_Ethiopiaሊንክድኢን፡-
https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ዩቱብ:-
https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopiaየኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!