ሰላም ጋይስ ፡
አብዛኛዎቻችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት እና እኔም አስቀድሜ ቃል በገባሁት መሰረት በተቻለኝ ከአሁኑ በመጪው የአልት ሲዝን የተሻለ ትርፍን ማስገኘት የሚችሉ ተብለው የሚታሰቡ ኮይኖችን በመለየት በተለይ ከፈንዳመንታል አናሊስስ አንፃር ጥሩ የሆነ እምቅ የማደግ እድል ያላቸውን ቶክኖች እንደየናሬቲቫቸው እየከፋፈልኩ ላካፍላችሁ እሞክራለው። ይህን ሳደርግ ግን ከናንተ አንድ ሀላፊነት እንድትወስዱ የምፈልገው ትልቅ ነገር አለ። ይኸውም ብዙዎች እንደሚመስላቸው የቡል ማርኬት ዝም ብሎ ብር የሚዛቅበት ብቻ ሳይሆን ብራችንንም የምንበላበት ነውና በተለየ ሁነት የምትገዟቸውን ኮይኖች የራሳችሁን የሆነ የመጨረሻ ጥናት በማድረግ እንድታደርጓቸው እና የሪስክ ማኔጅመንት ህጋችሁንም በጠበቀ ሁኔታ ትከተሉ ዘንድ ለማሳሰብ እወዳለው። በእነዚህ ጥሪዎች ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች በአንድ ቀን ወይም ሳምንት ልዩነት የምታዩባቸው ሳይሆኑ ካፒታላችሁን በመከፋፈል ከመካከለኛ እስከ ረጅም ጊዜ እቅድ ከ50 እስከ 100 እጥፍ ድረስ ልታገኙባቸው የምትችሉ እና በጣም የተለቀ ትእግስትን የሚጠይቁ መሆኑንም ለማስታወስ እወዳለው።
ማሳሰቢያ፡ በዚህ የትዊተር ትሪድም ሆነ በቀጣይነት ይዘንላችሁ የምንቀርባቸውን የትኛዎቹንም የኮይን ጥቆማዎች በምንም አይነት ሁነት እንደፋይናንሲዊ ምክር ሊወሰዱ የማይገባቸው እና የፀሀፊውን እይታ ብቻ የያዙ ሀሳቦች መሆናቸውን በዚህም ሊመጣ የሚችለውን ማንኛወንም አይነት ሪስክ ተገበያዮች ራሳቸው በራሳቸው መውሰድ የሚኖርባቸው እና ኮሚዩኒቲያችንም ምንም አይነት ሀላፊነት የሚወስድበት እንዳልሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ይህን ያህል እንደመግቢያ ካልን በቀጣዩ መስፈንጠሪያ በምታገኙት የትዊተር መስፈንጠሪያ የኮይኖቹን ዝርዝር ማግኘት የምትችሉ ይሆናል። እግረ መንገዱንም መሰል የኮይን ጥቆማዎች እና ጥናታዊ ዘገባዎች ከተመቿችሁ ፖስቱን BookMark🔖 ማድረግ እንዲሁም ሌሎች ቢያዩት ሊጠቀሙ ይችላሉ ብላችሁ ካሰባችሁ ደግሞ ላይክ ReTweet እና ኮሜንት በማድረግ ተደራሽነቱ ይሰፋ ዘንድ የበኩላችሁን ትወጡ ዘንድ ለመጠየቅ እንወዳለን። መልካም ምሽት።
🔗የትዊተር #Thread ሊንክ ፡
https://twitter.com/CryptotalkEt/status/1870903268089417896