ድሮኖቹ‼️
ድሮኖቹ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ #እርምጃም መውሰድ ይችላሉ ተባለ‼️
👉የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታና የትራፊክ ፍሰት ለመቆጣጠር ይሰማራሉ የተባሉ ድሮኖች ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን እርምጃም እንደሚወስዱ ተገለጸ።
የትራፊክ ፍሰት እና በበዓላት ወቅት የከተማዋን ጸጥታ ለመቆጣጠር በርካታ ድሮኖች መግባታቸው እና የሚቆጣጠሯቸው ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ሰልጠና አጠናቅቀው በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
ድሮኖቹ የከተማዋን ፀጥታ ሁኔታና የትራፊክ ፍሰት ከመቆጣጠር ባሻገር እርምጃም እንደሚወስዱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በቅርብ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ታላላቅ ፕሮግራሞችን ቁጥጥር ማድረግ የሚችሉ የድሮኖች ስምሪት እንደሚደረግ፣ የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል ከቀናት በፊት መግለጹ ይታወቃል፡፡
አሁን ላይ በርካታ ድሮኖች አገር ውስጥ መግባታቸውን እና የሚቆጣጠሯቸው ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ስልጠና አጠናቅቀው በቀጣይ ጥቂት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ አስታውቀዋል፡፡
ድሮኖቹ ቀድሞ ስምሪት ተሰጥቷቸው ለዋናው መስሪያ ቤት መረጃ የሚያቀብሉ ሲሆን መረጃ ከመስጠት ባሻገር ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፈጣን እርምጃ እንደሚወስዱም አቶ ጄይላ ተናግረዋል፡፡
ከመደበኛ የካሜራ ድሮኖች የተለዩ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው ለፖሊስ ወንጀል መከላከል፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሰሩ ናቸውም ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ህዝባዊ እና ኃይማኖታዊ በዓላት ላይ በድሮኖች የጸጥታ ሁኔታ ክትትል ይደረግ እንደነበር የገለጹት አቶ ጄይላን፣ የተለየ ነገር እንደማይፈጠር እና ህዝብን በማይረብሽ መልኩ ስራው እንደሚከናውን አመላክተዋል፡
@ET_SEBER_ZENA