የዘላቂ ፍቅር ሚስጥር
============
"ፍቅር ይዞኝ አልበላ፣ አልጠጣ አለኝ። ሁሌ ስለ እሷ ነው የማስበው፤ በየቀኑ ካርድ እሰከምንጨርስ ነው የምናወራው።" ያላችሁን ሰው ከሁለት አመት በኋላ ብታገኙት የያዘው ፍቅር ለቆታል። ምክኒያቱም ስሜታዊው ፍቅር እድሜው ከሁለት አመት ስለማይበልጥ። በፊት ያለ ምንም ማንገራገር ስትጠራው ወዲያውኑ "አቤት" ስትልከው ወዲያውኑ "ወዴት" ይል የነበረው የያዘው ፍቅር እየነዳው ነበር። አሁን ፍቅሩ ለቆታል። (በተለምዶ "ፀባዩ/ይዋ መለወጥ ጀመረ።" የሚባለው እዚህኛው ደረጃ ላይ ሲደረስ ነው።)
በፊት እንደሚፈቀሩ እርግጠኛ የነበሩ ሰዎች አሁን ቅር ቅር እያላቸው ይመጣል። እንደዚህ ከተሰማቸው ያሉት አማራጮች ሶስት ናቸው። የበፊቶቹ ትውልዶች ፍቅር ባይሰማቸውም፣ ደስተኛ ባይሆኑም (አንዳንዶቹ ለልጆቻቸው ሲሉ) ተቻችሎ መኖር። እንደ ባል ሳይሆን እንደ ደባል። የአሁኑ ትውልድ ደግሞ ደስተኛ ሳይሆን ሲቀር ቶሎ ወደ መለያየት። አሁን አሁን ሰዎች ልጆች ቢኖራቸውም በፍቅር ህይወታቸው ደስተኛ ካልሆኑ ይለያያሉ።
ጥሩ ዜና አለ! ከሁለቱ የተለየ ሶስተኛ አማራጭ አለ። የዘለቂ የፍቅር ቁልፍ የሆኑትን አምስቱን የፍቅር ቋንቋዎች ማወቅና መናገር። አንዳንድ ሰዎች ለፍቅራቸው ሲሉ ብዙ ነገር አድርገውም ምንም ውጤት አይኖረውም። ለዚህ ምክኒያቱ እነሱ በሚያውቁት የፍቅር ቋንቋ ፍቅራቸውን በደንብ እየገለፁ ነው። ነገር ግን አጋራቸው የሚሰማው ሌላ የፍቅር ቋንቋ ነው። ስለዚህ የነሱ ጥረት ውጤት የሌለው ይሆናል። ልክ ጃፓንኛ ብቻ ለሚሰማ ሰው በፈረንሳይኛ ቅኔ እየዘረፍሽ፣ ውብ ግጥም እየገጠምሽ ፍቅርሽን ብትገልጭለት ለሱ ትርጉም የለውም። እንደውም ሊያናድደው ሁሉ ይችላል።
"የዘላቂ ፍቅር ሚስጥር" መፅሀፍ ላይ የራሳችንን እንዲሁም የአጋራችንን የፍቅር ቋንቋ በመለየትና አነጋገሩን በማወቅ ዘላቂ የፍቅር እንዲኖረን አዲስ ምልከታ ያሳያል።
መልካም ንባብ
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
✈️@Enmare1988