እንማር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
   ለ Promo - @Kiya988
https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ሁሌ ቤቴንግ መበላት ከሰለቸህ  ይሄን ቻናል ተቀላቀል ሁሌ ነው አሸናፊ እምትሆነው Ethiopia  ውስጥ  ይሄ ብቻ ነው እውነተኛ ቻናል ስለዚ ሳያመልጣህ አሁኑኑ ተቀላቀል




የብልፅግና ሳይንሳዊ መንገድ.pdf
42.4Mb
📔ጊዜ የማይሽረው ጥበብ ፤ በተግባር የታገዘ እና ደረጃ በደረጃ የሚሰጥ የብልፅግና ፕሮግራም ተሻጋሪ መፅሐፍ)

🟢ደራሲ- ዋላስ ዲ. ዋትልስ

📖📔ተርጓሚ- ኢዮብ ካሣ

ከመፅሐፉ ውስጥ የተወሰዱ

*የእውነት መበልፀግ ማለት በትንሹ መርካት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን የበለጠ መጠቀምና ማጣጣም እየቻለ፣ በትንሹ መርካት የለበትም፡፡ ምን አለፋችሁ --- በትንሹ መርካት ሃጢያት ነው! የተፈጥሮ ዓላማ፣ የሀይወት እድገትና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለህይወት አቅምን፣ ሞገስን፣ ውበትንና መትረፍረፍን ለማጎናፀፍ የሚያግዙ ነገሮች ሁሉ ሊኖሩት ይገባል፡፡ ለምን ቢሉ --- ሁሉም የመበልፀግ መብት አለውና፡፡

*ተፈጥሮ የተሰራችው ህይወትን ለማሳደግ ነው፡፡ የሚያነሳሳት ዓላማም ህይወትን የማሳደግ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለህይወት ምቾት የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተትረፍርፎ ይቀርባል፡፡ ፈጣሪ ራሱን መቃረንና የራሱን ሥራዎች ማውደም ካልፈለገ በቀር፣ የምንም ነገር ችግር ወይም እጥረት አይፈጠርም፡፡

*እናንተ ስለድህነት አታውሩ፤ ስለድህነት አትመራመሩ፤ ስለድህነት አትጨነቁ፡፡ የድህነት መንስኤ አያሳስባችሁ፡፡ ድህነትን ጉዳያችሁ አታድርጉት፡፡ እናንተን አይመለከታችሁም፡፡ እናንተን የሚመለከታችሁ መፍትሄው ነው - መድሃኒቱ! በርትታችሁ ሃብታም ሁኑ! ድሃውን ለመርዳት የተሻለው መንገድ ራስን ማበልፀግ ብቻ ነው::

*ህልማችሁን እውን ለማድረግ የሚስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ በውስጣችሁ አለ፡፡ ተነግሮ የማያልቅ፤ የትየለሌ አቅም አላችሁ፡፡ የፈጠራ አቅም የለንም ብትሉም ፤ ቀደም ሲል ሳይሳካላችሁ ቢቀርም፤ ሁሉንም ሞክራችሁ ምንም የቀራችሁ እንደሌለ ብታስቡም እንኳን —— ለዚህ መፅሃፍ አዕምሮአችሁን ከፈቱ፡፡


⭐⭐@Enmare1988
⭐⭐@Enmare1988


ከመፅሐፉ ውስጥ የተወሰዱ

*የእውነት መበልፀግ ማለት በትንሹ መርካት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን የበለጠ መጠቀምና ማጣጣም እየቻለ፣ በትንሹ መርካት የለበትም፡፡ ምን አለፋችሁ --- በትንሹ መርካት ሃጢያት ነው! የተፈጥሮ ዓላማ፣ የሀይወት እድገትና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለህይወት አቅምን፣ ሞገስን፣ ውበትንና መትረፍረፍን ለማጎናፀፍ የሚያግዙ ነገሮች ሁሉ ሊኖሩት ይገባል፡፡ ለምን ቢሉ --- ሁሉም የመበልፀግ መብት አለውና፡፡

*ተፈጥሮ የተሰራችው ህይወትን ለማሳደግ ነው፡፡ የሚያነሳሳት ዓላማም ህይወትን የማሳደግ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለህይወት ምቾት የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተትረፍርፎ ይቀርባል፡፡ ፈጣሪ ራሱን መቃረንና የራሱን ሥራዎች ማውደም ካልፈለገ በቀር፣ የምንም ነገር ችግር ወይም እጥረት አይፈጠርም፡፡

*እናንተ ስለድህነት አታውሩ፤ ስለድህነት አትመራመሩ፤ ስለድህነት አትጨነቁ፡፡ የድህነት መንስኤ አያሳስባችሁ፡፡ ድህነትን ጉዳያችሁ አታድርጉት፡፡ እናንተን አይመለከታችሁም፡፡ እናንተን የሚመለከታችሁ መፍትሄው ነው - መድሃኒቱ! በርትታችሁ ሃብታም ሁኑ! ድሃውን ለመርዳት የተሻለው መንገድ ራስን ማበልፀግ ብቻ ነው::

*ህልማችሁን እውን ለማድረግ የሚስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ በውስጣችሁ አለ፡፡ ተነግሮ የማያልቅ፤ የትየለሌ አቅም አላችሁ፡፡ የፈጠራ አቅም የለንም ብትሉም ፤ ቀደም ሲል ሳይሳካላችሁ ቢቀርም፤ ሁሉንም ሞክራችሁ ምንም የቀራችሁ እንደሌለ ብታስቡም እንኳን —— ለዚህ መፅሃፍ አዕምሮአችሁን ከፈቱ፡፡


አትሳሳት ጓደኛዬ........


ዝቅ የሚሉት ለህሊናቸው ያልተገዙ ሰዎች ብቻ ናቸው..ዝቅ የሚሉት ክብር ባለሌለው ቦታ ላይ የተገኙ ሰዎች ብቻ ናቸው......ዝቅ የሚሉት አይምሯቸውን ከልባቸው ጋር  ያላዋዱ ሰዎች ናቸው...

ታዲያ ለምንድን ነው እኔ ማፍረው?

ለምንድን ነው ዝቅ የምለው?

ለምንድን ነው ራሴን የምከሰው?


መጀመሪያ ራስህን አፅዳ.....ውስጥህ ያሉትን መጥፎ ልማዶች ሁሉ በደምብ አፅዳ.....መሲሑንም ይቅር በለኝ በለው.....ቀን-ከሌት ራስህን በመገንባት አሳልፍ.....መቼም ቢሆን ራስህን ከመግዛት ወደኃላ እንዳትል...ክብር ባሌለውም ቦታ ላይ አትገኝ....ከዛ ሁሉም ሰው አንተን የማያከብርበት መንገድ ያጣል.....ይሄ ነው ቀና ብሎ መሄድ ማለት...ይሄ ነው ሰላማዊ ሰው ማለት...❤️✍✍


🎙ለዮቱበሮች ና ለቲክታከሮች ለቪዲዮዋቹ ጥርት ያለ ድምፅ የምትቀዱበት 🎙#K9 ዋይርለስ ማይክ በ 1 ካርቶን 2 ማይኮች የያዘ  #20_ሜትር_ ርቀት_ድረስ_የሚሰራ   ጫጫታ ቦታ ውስጥ ቮይስ ብትቀዱም  የናንተን ድምፅ ብቻ በጥራት ለይቶ የሚቀዳ ከስልክ ቮይስ የበለጠ ጥራት ያለው  ማይክ ለገብያ  አቅርበንላቹሀል ይደውሉልን 📞 0777403952
      0941546755  

👇በውስጥ መስመር
@Laday_33


"ንፋስ አልወድም"....አለቺኝ ካዘነበለችበት ሳትነቀል....

"ለምን"....ጠየቅኩ....

"ስለማይረጋ...ባንድ አቅጣጫ ስለማይነፍስ...ወዲህ ብቻ ገፍቶ ስለማይተው...ወዲህም ወዲያም ስለሚያደርግ...አቋም ስለሚያሳጣ....አንዴ ሽው ካለበት ስለማያድር...."....በረጅሙ ተነፈሰችና ቀጠለች....

"ገፍቶ ከጣለህ በኃላ ደግፎ ሊያነሳህ ስለማይመጣ....ከመጣም ደግሞ ደጋግሞ ሊያፈርስህ ስለሚመጣ....ታውቃለህ ንፋስ ደካሞች ላይ እንደሚበረታ....ብቻ ምን አለፋህ የወደቀ ላይ ምሳር ለማብዛት ስለሚመጣ ያስፈራኛል...."

"አትፍሪ እኔ አለሁልሽ...."....አልኳት በልበ ሙሉነት....

"ከግዑዝ ነገር ፀብ የለኝም...ስለ ንፋስ ሳወራ ራስህን ታያለህ ብዬ ጠብቄ ነበር...."

"ማለት...."

"ከግዑዙ ንፋስ እዚ ፊቴ ያለኧው ንፋስ ታስፈራኛለህ...."

"ማለት...."

"ንፋስ ነህ እያልኩህ ነው...."

"አይደለሁም...."

"ነህ...አንተ ግን እያባበልክ አለሁ እያልክ ነው የምትጥለው...ግዑዙ ንፋስ አያባብልም...ሁሌም የቻለውን ሊያፈርስ እንደሚመጣ አውቃለሁ....የሰው ንፋስ ከጣለ መነሳት ቅዠት ነው...እና እሱን ንፋስ ነህ"....


በረጅሙ ተንፍሳ አቆመች....እኔም ደግሜ አልጠየቅኳትም....



✍Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka


ልፈልግም ስትለኝ እምባዬ እንዳይመጣ ታግዬ ፈገግ አልኩኝ ። ለእምባዬ ፊት መስጠት አልፈለኩም ። የሄደን ሰው እምባ አይመልሰውም ብዬ ነው መሰለኝ !

ግን ከፋኝ ፦

ተደግፌባት ነበር ። አደጋገፌ በጥርጣሬ አልነበረም ። ከኔ እሷን አምናት ነበር ፣ እንዳልጎዳት ስጣጣር ነበር ። እንዳላሳዝናት ሁኔታዬን ሁሌ አየው ነበር !

አልፈልግህም ስትለኝ ....

ጭር አለብኝ በግርግር ውስጥ ጭርታ ስሜት እንዴት ይወለዳል ? ጭርታው አስፈራኝ ጭርታው ድብርት ወለደ ። ስታብራራ መልስ መስጠት አልፈለኩም ። እንዲ ስለው እንዲ ይላል ብላ ምላሽ ተሸክማ እንደመጣች ገብቶኛል ።

ምላሽ ካጠና ሰው ጋር ውይይት ትርፍ የለውም ። ማን ለማን ብሎ ከማን ጋ ይሆናል ? ይሄ መስቀል ሳላጉረመርም የምሸከመው ነው !!

ግን ይሄን ሁሉ ሲሰማኝ ፈገግ ብዬ ነበር ።

እሷም አልፈልግህም ስለው ፈገግ ብሎ ነበር ትል ይሆናል ።
©Adhanom Mitiku

4k 0 25 4 108

'' አንዳንድ ታሪኮች ርእስ የላቸውም ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ ። አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም _ ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ ።

አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም _ የባከኑ መሥዋትነቶች ይባላሉ። አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ

አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል _ ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን አንቀጥላለን። አንዳንድ ሕዝቦች በውል ተረስተዋል _ ለመታሰቢያነት የቀረላቸው ምንም የለም።

አንዳንድ ኮቴዎች በመረሳት ተጠቅተዋል አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል። ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሦስት መሃላ ተክደዋል። ....''


...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።

የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።

"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ

መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''

ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።

ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።

ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።

አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም

በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።

አለመኖር 📚

6.5k 0 113 7 172

''የአንዲት ሴት ዓይኖች ቅፅበታዊ ዕይታ የዓለማችን ደስተኛ ሰው ሊያደርግህ ይችላል...❤

5.4k 0 28 17 111

አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች...

ቤቴን አጽድቼ ካስተካከልኩ በኋላ ወንድሜ ደወለ...ከባለቤቴ ጋር ልንጠይቅሽ እንመጣለን ኣለኝ። ኩሽና ገባሁ ለእንግዶቸ ያለኝ ላዘጋጅ።

ለመስተንግዶ ምንም አላገኘሁም! አንድ ነገር ላቀርብላቸው ብፈልግ፡ ምንም ማግኘት ኣልቻልኩም ጥቂት ብርቱካን ብቻ አገኘሁ… እናም ወዲያውኑ ሁለት ብርጭቆ ቀዝቃዛ ጭማቂ አዘጋጀሁ።

ወንድሜ እና ሚስቱ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኘችን ያለው የወንድሜ ሚስት እናት ከሳቸው ጋር ነበረች።

ሁለት ብርጭቆ ለሚስቱና እናትዋ ኣቀረብኩላቸው። ኣንድ ብርጭቆ ውሃ ደግሞ ለወንድሜ። 7up እንደምትወድ ኣቃለሁ ኣልኩት።

ትንሽ ጠጣና ውሃ መሆኑን ኣወቀ። እናትየዋ እኔ 7up ነው የምፈልግ ለሆዴ ይመቸኛል እና ስጡኝ.. ትላለች። ግራ ገባኝ ደነገጥኩ …

ወንድሜ እንዲህ ሲል አዳነኝ: - አዲስ ብርጭቆ ከኩሽና ኣመጣለሁ ብሎ ብርጭቆውን ይዞት ሄደ። ከዚያም የጠርሙሱ መሰበር ድምፅ ሰማን፡

እናም ተመልሶ መጥቶ አማቱን እንዲህ አላት... የሚያሳዝነው ከኔ ወድቆ ብርጭቆውን ተሰበረ.. ግን ምንም አይደለም ሌላ ላመጣሽ ወደ ግሮሰሪ እሄዳለሁ... ኣላት።
አማቹ አያስፈልግም አለች...

ሲወጡ ወንድሜ ሲሰናበተኝ፡ አቅፎ በእጄ ገንዘብ አስጨበጠኝና እና እንዲህ አለኝ: ​​-ከኩሽናው 7up ማጽዳት እንዳትረሺ፡ ጉንዳኖችን እንዳያመጣ! ብሎ በፈገግታ እና በፍቅር ተሰናበተኝ..።
ራስሺን ተንከባከቢ ኣለኝ።
በዚህ መንገድ... ወንድሜ ጭንቀቴንና ጉድለቴን ሸፈነልኝ.. ስሜቴን ጠበቀልኝ..

ወንድማማችነት እንዲህ መሆን ኣለበት...Happ

6.7k 0 54 8 437

''ቀድሞ የተዘጋጀ ማንነት ይዛችሁ አልተወለዳችሁም። በግንባራችሁ ወይ በመዳፎቻችሁ መስመር ላይ የሆነ ነገር ተፅፎባችሁ አልተፈጠራችሁም።

ወደዚህ አለም ስትመጡ ምንም እንዳልተፃፈበት ባዶ መፅሀፍ ሆናችሁ ነው። ዕድላችሁን የምትፅፉት፣ ዕጣ ፈንታችሁን የምትፅፉት ራሳችሁ ናችሁ ፤ ስለዚህም ራሳችሁን መሆን አለበችሁ...❤

6.1k 0 25 14 102

⭐️ ከኮንዶም እና ሲጋራ ውጪ ገዝቶኝ አያቅም!!እኔ ደሞ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ገና ሲመጣ እራሱ ሰውነቴን ውርር እስኪያደርገኝ ያስጠላኛል።ሌላ ቦታ አይገዛም?? ደሞ በዚ ድህነቱ ላይ ሲጋራ ኮንዶም...ምናለ ቀንስራ ለላጠው እጁ ባዝሊን ቢገዛ??ምናለ ፀጉሩን ቢቆረጥ?? ምናለ ዳቦ ቢገዛበት??ሞጋጋ.....(ብስጭት እያልኩ ጓደኛዬ ላይ እነጫነጫለሁ
እኔ ምለው ረዱ ምን አገባሽ ቆይ ሽቀላሽ አደል እንዴ??


አረ የሱ 10 ብር በአፊንጫዬ ይውጣ!!
እንደው ቆይ ይሄንን ጉድሽን ባየሁልሽ...ሆ..ሰው እንዴት ከመሬት ተነስቶ ሰው ይጠላል...?
ዳኑ በግርምት እያወራችኝ ሰፈራችን የሚመረቀው አዲሱ ስላሴ ቤተክርስትያን በር ላይ ደርሰን
ተሳልመን ገባን።

መቼስ የምእመናኑ ብዛት ጠጠር አያስጥልም።ሰፊው የስላሴ ግቢ ውስጥ ነጭ ኩታ የተነጠፈ እስኪመስል በአሉ ድምቅ ብሎ ታቦታቱ ወጥተው ዝማሬው ጫፍ እስከጫፍ ያስተጋባል።ዳኑ ደሞ በማህበር የሚዘምሩትን ወጣቶች ስለምትወድ ተከታትለን ወደ
ዘማርያኑ እንደቀረብን ነበር ቀና ስል ከዛ ሰይጣን ጨብራራ ሱሰኛ ልጅ ጋ አይን ለአይን የተጋጠምነው...

በስመአብ አረ ይኼንን ሰይጣን ማላይበት የት ልሂድ!!?? (በስጭት ስል ድምፄን መሠሠት የሚያቅተኝ ነገርስ? አንባረቅኳ!!
አረ ቀስ በይ ረዱ..ማነው?ምንድነው??
ያ ሲጋራ የሚገዛው ልጅ ነዋ...እዚህም አየሁት። ደሞ አለማፈሩ...!! (አልኳት ንዴቴ ብሶ ድምፄን ለመቀነስ እየታገልኩ

የታለ በናትሽ አረ አሳዪኝ...
ዳኑ ተሰብስቦ በሚዘምረው ምእመን መሀል በጥፍሯ ቆማ አንገቷን አስግጋ ስታማትር ቆይታ ድንገት ዘጭ ብላ ቆማ ደርቃ ስትቀር ነገሯ አስደንግጦኝ እኔ ፈዝዤ አየኋት..
አንቺ ምን ሆነሻል???ምንድነው
ሚያፈዝሽ??....አትናገሪም እንዴ???አንቺ ዳኑ??

(ትከሻዋን እየነቀነቅኩ ብዙ ከጠሯኋት በኋላ በቆምኩበት ጥላኝ ወደኋላ ዞራ ስትራመድ ተከታትለን ሄዴን አንድ ጥግ ቁጭ አለን
ምንድነው ዳኑ???ይሄ ምን አይነት የተረገመ ሰይጣን ነው???ቆይ አንቺም ታቂዋለሽ ማለት ነው!!??

እረፊ ረዱ ሰይጣን አትበይው!! እረፊ ክፉ አትናገሪ!! በረከት እኮ ነው ረዱዬ በረከ....(ነጠላዋን አይኗ ላይ ሸፍና ተንሰቀሰቀች
ማነው በረከት??ምንድነው???የት ታቂዋለሽ??

በረከት ነዋ.....አንድ ጊዜ ስለሱ ነግሬሽ አልነበር? በረከት ዲያቆኑ...ማለቴ እኔና እሱ...(ዳኑ ፀጥ ስትል ከሆነ አመት በፊት የተፈጠረው ክስተት ትዝ ብሎኝ በቆምኩበት ቁልቁል ተዘረፈጥኩ
አላምንሽም ዳኑ!!!

⭐️አዎ ተቀይሯል!!እሱን አይመስልም!!ግን እኔ መልኩ አይጠፋኝም!!ይሄ ሁሉ የኔ ስህተት ነው።ታውቂ የለ ያፈቅረኝ ነበር... ይወደኝ ነበር...የመጀመርያውም የመጨረሻውም እኔ እንደሆንኩ ነበር የሚያምነው።ግን እኔ አልረባም... እስካሁን ከሱጋ የተገናኘንበትን ቀን እረግማታለሁ!!!እሱን አፈቅርሀለው ብዬ የዋሸሁበትን ቀን እረግማታለሁ!!!

ለሊት ከሌላ ወንድ ጋ አድሬ ነጠላውን ተከናንቦ ከማህሌት ሲመጣ የተገናኘንባትን ቀን ረግማታለሁ....ከዛች ቀን
ወዲህ ነው ዲያቆኑ ትሁቱ አገልጋዩ በረከት የጠፋው፤ሱስ የጀመረው፤መስከር የለመደው...ይቅር በለኝ እለዋለሁ
እያልኩ ስፈልገው ኖሬያለሁ ግን ከአባቱ ጋ ሰፈሩን ለቆ እንደወጣ ከሰማሁ ወዲህ...
ዳኑ እንባዋ እንደ ጅረት ከአይኖቿ ሲወርድ የበረከትን ሁኔታ አሰላሰልኩት ከዚህች ቤተክርስትያን በር አይጠፋም።

አንዳንዴ ሲያልፍ ከዛ ሲወጣ አይቼው አውቃለሁ። ብዙ ጊዜ እዛው ቆሞ ሲጃራ ለኩሺልኝ እያለ ላይተር በሚይዝባት እጆቹ ዳኑ ብሎ ክንዱ ላይ የተነቀሰው ትዝ ብሎኝ አንገቴን አቀርቅሬ...
ዳኑዬ ይገባኛል ግን ደሞ አንዴ ሆኗል... በረከት ከቤተመቅደሱ አገልግሎት ይራቅ እንጂ ከክርስቶስ ልጅነት አራቀም።

እኔም በረከትን ማውቀው እዚህ የስላሴ ህንፃ ሲሰራ ለቀንስራ ከመጣ ወዲህ ነው።ታውቂያለሽ....አንዳንዴ ህይወታችን እና ስራችን ይለዋወጥብናል።እግዚአብሔር ተጠቦ አክብሮ አስውቦ የፈጠረውን ታላቅ ቤተመቅደስ በውጪ አፍርሰን በሌላ በኩል ደሞ በገንዘባችን የተዋበ ቤተመቅደስ ሰርተን እልል ብለን እንመርቃለን።

⭐️ ወደኋላ ግን ስናስበው አፍራሾቹም ሰሪዎቹም እኛው ሆነን እንገኛለን።አየሽ ቤተመቅደስ የሚገነባው ለምእመናን አይን ማረፊያ፤ፎቶ መነሻ፤ሳይሆን የልባቸው ማረፊያ እና መሸሸጊያ እንዲሆናቸው ነው....ምንም ህንፃውን ብናስውበው የኛ ህይወት በእግዚአብሔር አባትነት ካልተዋበ ትርጉም የለውም።''እግዚአብሔር እየፈረሰ ቤቱን የሚያንፅ ሳይሆን.እየታነፀ ቤቱን የሚሰራ ትውልድ ነው ሚፈልገው"

⭐️ በረከት በዲቁናው ሰወችን ባያንፅ ሰወች የሚታነፁበትን ዛሬ የቆምንበትን መቅደስ ግን በላቡ በጉልበቱ ከማነፅ አልሰነፈም ፈጣሪ ደሞ በጎቹን ጥሎ አይጥልም አንዴ ቃሉን በልቡ የዘራ ከነቆሻሻውም ቢሆን ይመላለሳል እንጂ አይቀርም።ሁሌ አዲስ ቤተክርስትያን እንገንባ እነጂ እኛ ለክርስቶስ ነዘላለም አዳዲስ ህንፃወቹ ነን...አታልቅሺ በቃ በማርያም(እጇን ከአይኗ ላይ አንስቼ ላቅፋት ስል... ሂጄ አገኘዋለሁ ረዱዬ ....(ከተቀመጠችበት ፍንጥር ብላ ተነስታ ወደሚዘምሩ ምእመናንን እየገፋች ስታልፍ ተከተልኳት "በረከት ግን
ቆሞ በነበረበት ቦታ ላይ አልነበረም በረከት
ሄዳል....

✍️
ቻቻ

7.5k 0 31 7 190



የየሻረግን ቀልብ እና ፈገግታ ስለምን ነው የኖርኩት...!

የሻረግ የቤት ሰራተኛችን ነበረች ደግ ነች፤ ባለሙያ ናት፡ ዝምተኛ ነች ፤ ታዛዥ ነች ።

እናቴ አርፋ አመት እንደሞላት አባቴ የሻረግን አገባት ። የሰፈሩ ሰው ሁሉ አባቴን እና የሻረግን ወቀሳቸው ። እኔ በሂደት ነው የየሻረግ ሚና እና ቦታ እንደ ተቀየረ የገባኝ ።

የሻረግ እኔን ማዘዝ ስትጀምር ፣ ስትቆጣኝ ፣ ተጨማለቅክ ስትለኝ ፣ ትህትናዋ ፣ ደግነቷ ሲሰወርብኝ ፤ አባቴ ጋ መቃለድ ስትጀምር ፣ የልጅ አዕምሮዬ ግራ ሲጋባ ትዝ ይለኛል ።

ነፍስ ሳቅ ጀምሮ የታዘዘችኝ የሻረግ አዛኝ ያዘዝኩህን ቶሎ አልፈፀምክም ማለት ጀመረች ። ምግብ ብላ እያለች የምትለማመጠኝ የሻረግ "አሁን አይደል እንዴ የበላኸው?" ብላ መገልመጥ ጀመረች ።

ይሄን ማንነቷ አቅም ማጣት እንደደበቀባት ገባኝ ። ክፉ ልጅ ፣ የማልታዘዝ ፣ የምሳደብ አይደለሁም ለምን ጠላቺኝ እላለሁ ?

እናቴ ክፉ አልነበረችም ፣ ስትቆጣት ፣ ስትሰድባት ፣ ስታመናጭቃት አይቼ አላውቅም ለምን እንዲ በብርሃን ፍጥነት ተቀየረችብኝ??

በየምክንያቱ ሰራተኛህ መሰልኩህ ትላለች?

የየሻረግ ባህሪ መቀየሩ ከእኔ ችግር ስለሚመስለኝ እንደ ድሮ ጥሩ እንድትሆንልኝ በልጅነት አቅሜ እዳክራለሁ ። ያገኙትን ማጣት ከባድ እንደሆነ የሻረግ ሰጥታኝ የነበረውን እንክብካቤ ስትነጥቀኝ ነው የገባኝ ።

አባቴ ለውጡን እንዴት አያይም ?

አንድ ልጁን እንዴት አሳልፎ በዚህ ደረጃ ይሰጣል እል ነበር ።
አቤቱታ የማቀርብበት ግራ ስለሚገባኝ ምን ብዬ ፣ እንደምከሳት ግራ ስለሚገባኝ እንደ እሷ ቃላት ደርድሮ ማውራት ስለማልችል ።

እንደድሮ እንድትሆንልኝ እለማመጣት ነበር ። ያዘዘችኝን ቶሎ እሰራለሁ ፤ አቆላምጣት ነበር ። እኔ እና የሻረግ ቦታ ተቀያየርን ፤ እኔ ሰራተኛ እሷ እመቤት!

የሆነ ቀን ግቢያችን ውስጥ ወደቀች ፤ ስትሮክ ነው ተባለ ፤ የየሻረግ እጅ እና እግር እምቢ አለ ። የሻረግ ያኔ ሌላ ሆነች ፣ ምስኪን ሆነች ፣ አልቃሻ ሆነች ፣ ፀላይ ሆነች ፣ ተለማማጭ ሆነች ።

"ለግርድና ስለተሰራሽ እመቤትነት አልቻልሽበትም ነበር" እላት ጀመር ። "እባብ ልቡን አይቷ እግር ነሳው" እላት ጀመር ።" ተስፋም የለሽ እንዲ ሽንክልክል አልሽ ። ከዚህ በኋላ እግር እና እጅሽ እንደ እናቴ ሞቷል" እላታለሁ ።

የሻረግ ክፉ አትናገርም ነበር !

የድሮዋ የሻረግን : ትሁቷ የሻረግ ፣ ዝመተኛዋ የሻረግ ተለማማጯ የሻረግ ተመለሰች ። አለም ላይ እንደሁኔታው ራሱን እየቀያየረ እንደሚተውን የሚያክል ክፉ የለም !!

እያቆላመጥኩ አሾፍባታለሁ ፣ የማትወደውን ሙዚቃ ከፍ አድርጌ እየከፈትኩ እረብሻታለሁ ፣ ጓደኞቼ ሲመጡ ተዋወቋት የሻረግ ትባላለች
ሰራተኛችን ነች ፤ ቲያትርም ትሞክራለች እያልኩ አስተዋወቃታለሁ ።

ምኔን ነክታኝ ነው እንዲህ የቀየረችኝ ግን ??
ነገሩ ....
የክፉ ሰው ክፋት መበደሉ ብቻ አይደለም ማክፋቱ ጭምር እንጂ
!!


እጮኛዬን ከምከለክላት ከአንድ እስከሶስት ውስጥ ሶስቱም ካጠገቧ የሚከተላት እና የምታስከትለው የወንድ ቤስት ፍሬንድ ነው ።

ሳናዳት የሚያባብላት ፣እኔ ከሱ የተሻለ እረዳሻለሁ የሚል በሚያበሽቀው ሁሉ እየሳቀ የሚሰማት ፣ በሱ እንዳትመጣብኝ የምትል

በሱ ልትምል የሚቃጣት ፣ አክስቱ ታመሙ እኮ እያለች እምባዋ የሚመጣ ቴሌግራሟ ላይ ምስሉን እምትለጥፍ ፣ከከተማ ከሱ ጋ ወጥታ ልትንሸራሸር የምታቅድ ቤስት ፍሬንድ አልፈቅደም

እኔ ገገማ ነኝ ።

እስክጥልሽ ወይ እስክወድቅ የሚጠብቅ ይመስለኛል ። ስወድቅ ጠብቆ ፋይል የሚያደራጀብኝ ይመስለኛል ፣

ገገማ ነኝ ፦

በቅጡ እንዳትረጂኝ የሚከልለኝ ይመስለኛል ።በተጣላን ቁጥር ላንቺ የሚያግዝ ይመስለኛል ፕላን "B"ሽ ይመስለኛል ።

በምወድሽ ዙርያ ያለ ነገር እንደዋዛ አላይም። ሰው የሚጥለው በሚወድው በኩል ያለ ነገር ነው ።

እኔ አንፈቅድም ገገማ ነኝ ኣ?

አበጀው !! እንኳን ገገማ ሆንኩ !!
Adhanom Mitiku

7.9k 0 59 5 202

Thoughts dan repost
ለራሴ አዝዤ አላውቅም።

እሷ ስትበላ ራሱ ማየት ሀሴት ይሰጠኛል። እነገናኛለን ብዙ ምግብ አዝላታለሁ

መጀመሪያ ፀጥ ብላ እየተሻማች ቀጥሎ የምግቡን እያንዳንዱን ቅመም ለማዳመጥ በሚመስል አኳኋን አይኗን ጨፍና ስትመሰጥ ትቆይና

መጥገብ ስትጀምር ስለ ምግብ አስደሳች ተፈጥሮ lecture እያረገቺኝ በልታ ስትጨርስ ትንሽ አውርተን እንለያያለን።

ሁሉም ነገር በምግብ ካልተመሰለ ግር ይላታል።

አንድ ቀን እኮ ነው እንዲሁ ተገናኝተን እየበላች "ስሚማ" አልኳት "እ" አለቺኝ ቀና ሳትል

"ምን አይነት ወንድ ይመችሻል?" አልኳት እንደአንተ አይነት እንድትል ነበር

"እንደ ፈንዲሻ..." አላስጨረስኳትም ቱግ አልኩ
"የጠየኩሽ እኮ ስለ እኔ..." አመለጠኝ

"ማለቴ ስለ ወንድ ምርጫሽ ነው እንጂ ስለ ምግብ ምርጫሽ አይደለም።

"አስኪ አስጨርሰኝ ስለ ወንድ ምርጫዬ በምግብ አድርጌ እያስረዳውህ እኮ ነው" አለቺኝ"

የሆዳም ነገር እያልኩ"በሆዴ "ይሁን ቀጥዪ የሚል ፊት አሳየኋት
" እንደ ፈንዲሻ በደስታዬ ጊዜ ብቻ የሚኖር እንደ ንፍሮም በሀዘኔ ጊዜ ብቻ የማገኘው ሳይሆን
እንደ እንጀራ ሁሌ የሚያስፈልገኝ ስፈልገው የማላጣው እንዲሆን ነው" ብላኝ መብላቷን ቀጠለች።

"ወይ አንቺ ጉደኛ እንጀራ የሆነ ባል ይሰጠኝ እያልሽ ነው" እያልኳት እሷ ስተስቅ እኔ ስገረም አበቃን።

©nani


https://t.me/justhoughtsss
https://t.me/justhoughtsss
https://t.me/justhoughtsss

8.1k 0 28 2 103

"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው" አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ"
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?' አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

ይልቅ እንጠጣ እስኪ


ሰላም ለነሱ ❤

ለሚወዱን ፣ ስንዘጋቸው በቀላሉ ለማይዘጉን ፣ ስናጠፋ አፀፋውን ለመመለስ ለማይፈጥኑ ፣ ስተታችንን ለማያጎሉ ፣ ለሚሰሙን ፣ለሚያግዙን ፣ አሳልፈው ለማይሰጡን በዝቅታችን ጊዜ ከፍ ያልነውን ለሚያወሱ ፣

ሰላም ለነሱ ፦

በሆደ ሰፊነታቸው ላቀፉን ፣ ያላቸውን ላካፈሉን ፣ ደግ ደግ ነገራችንን ለሚያጮኹ ፣ አለመኖራችን ለሚታወቃቸው መጥፋታችን ለሚያሳስባቸው ።

ሰላም ለነሱ ፦🙏

መዘነጣችንን መክሳታችን ለሚያዩ ፣ የነገርናቸውን ጉዳዬ ለሚሉ፣ የማንወደውን ሃሳብ እየመዘዙ ትርፍ ለሌለው ነገር ለማያዝጉን ፣ ምቾታችንን ለሚጠብቁ

ሰላም ለነሱ ይሁን

9.1k 0 100 8 242
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.