ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ሊጀምር ነው‼️
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ በሚል ማስተላለፍ የጀመርነው ተወዳጁ ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘው ተከታታይ ፊልም በብዙዎቻችሁ የተወደደ መሆኑን አይተናል።
ኮርፖሬሽኑ ይህንን ስራ የባለቤትነት መብቱን ጠብቆ ካቆየው ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ፊልም የመስራት መብቱን በሕጋዊ መንገድ በመግዛት የደራሲውን ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ሕልም ሊያሳካ በሚያስችል፣ ክብራቸውን እና የተመልካቹን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ ከፍተኛ ወጭ በመመደብ ፊልሙ እንዲሠራ አድርገናል።
ይህ እንደ ብሔራዊ ጣቢያ ታሪክ ሰንዶ የማቆየት፣ የማስተላለፍ እና የማሳደ ይህንን የሕግ፣ የሞራል እና ሀገራዊ ሓላፊነታችንን እየተወጣን ባለንበት ወቅት የክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ወራሽ ነኝ በሚሉ ሰዎች የፊልሙን መተላለፍ በፍርድ ቤት እንዲታገድ አድርገዋል።
ተቋሙ የደራሲውን ሥራ በወጋየሁ ንጋቱ ትረካ ከፍ ያደረገ እና በዚህም በይፋ ደራሲው ያመሰገኑት ተቋም ነው። አሁንም የደራሲውን ህልም የሚፈታ እና በህጋዊ እና እውቅና ባለው ይሁንታቸው የተላለፈውን መብት መነሻ በማድረግ ፊልሙን ለእይታ አብቅተናል።
ይሁንና አሁን የተከሰተው አይነት ጉዳይ ሲያጋጥም ችግሩን በሕግ አግባብ መፈታት አስፈላጊ በመሆኑ በፍርድ ቤት ስንከራከር ቆይተን እግድ የሰጠው ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ሲያይ ቆይቶ ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ክርክሩ በስር የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲታይ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰጠው እግድ እንዲነሳ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መነሻ በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የፍቅር እስከመቃብር ፊልም በኮርፖሬሽኑ የመዝናኛ ቻናላችን ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚጀምር መሆኑን አንገልፃለን።
©EBC
@Esat_tv1