የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ‼️
ምክር ቤቱ እያካሄደው ባለው 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን ተጨማሪ ረቂቅ በጀት መርምሮ አጽድቋል።
ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በጀቱ የሚውልባቸውን ዋና ዋና ዘርፎች ዘርዝረዋል።
ይህም ለመደበኛ ወጪ 393 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ 70 ቢሊዮን ብርና ለወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ 119 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን በዝርዝር ሲያስረዱም፥ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ 185 ቢሊዮን ብር፣ ለማኅበራዊ ድጎማ 208 ቢሊዮን ብር፣ ለማኅበራዊ ሴፍቲኔት ማስፋፊያ 60 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስተካከያ 10 ቢሊዮን ብርና የወጪ አሸፍፈን ማስተካከያ ለማድረግ 119 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፥ ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ተወያየቶ በሦስት ተቃውሞና በአምስት ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ተጨማሪ በጀቱን አጽድቋል።
@Esat_tv1