ናይጄሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በአምስት አየር መንገዶች ላይ በተሳፋሪዎች መብቶች ጥሰት ማዕቀብ ጣለች‼️
የናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በአምስት አየር መንገዶች ላይ ደንብ ቁጥር 19 ስር የተካተቱ የተሳፋሪዎች መብት በመጣሳቸው የማዕቀብ እርምጃ ወስዷል።
በባለሥልጣኑ የህዝብ ጉዳዮች እና የደንበኞች ጥበቃ ዳይሬክተር የሆኑት ማይክል አቺሙጉ የተፈጸሙት ጥሰቶቹ፤ “በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተመላሽ ገንዘብ አለመክፈል፣ የሻንጣ መጥፋት፣ ተገቢ ባልሆን ሻንጣ አያያዝ የሚደርስ ውድመት፣ በሻንጣ ውስጥ የተካተቱ እቃዎች መጥፋት እና የበረራ መዘግየት እና መሰረዝን ያካትታሉ” ብለዋል።
"ዛሬ የምንጀምረው የማስፈጸሚያ እርምጃዎች አየር መንገዱ ጥፋተኛ ነው ተብሎ በታሰባባቸው ጉዳዮች ላይ ነው። የሚበልጠው ይቀጥላል” ብለዋል። ምንም እንኳን ባለሥልጣኑ የአየር መንገዶቹን ስም በይፋ ባይጠቅስም ምንጮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሮያል ኤር ማሮክ፣ አሪክ ኤር፣ ኤሮ ኮንትራክተርስ እና ኤር ፒስ መሆናቸውን ገልጸዋል።
@Esat_tv1