ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ ለስርቆት ተዳርጓል‼️
🗣የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ባለፉት አስር ቀናት በአዋሽ - ወልዲያ - ሃራ ገበያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር ለስርቆት መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
በአዋሽ - ወልዲያ - ሃራ ገበያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንደተናገሩት ባለፉት አስር ቀናት ከመተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ ድረስ በቡድን በተደራጀ ሁኔታ 78 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ዝርፊያ ተፈጽሟል።
ከባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ ሁለት ድረስ ደግሞ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ በዘራፊዎች መወሰዱንም ነው የጠቆሙት።
በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በዱዱብ እና ዶሆ ቀበሌዎች ሁለት ጊዜ እንዲሁም በዱለሳ ወረዳ በቡሩቱሊ እና ኢስኪለሊ ቀበሌዎች አንድ ጊዜ በተፈፀመ የስርቆት ወንጀል ሳቢያ ከ758 ሺህ ዶላር በላይ እና በብር ከ6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱንም ተናግረዋል።
የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ወደ ሥራ እስኪገባ ድረስ በ33 እና 15 ኪሎ ቮልት በጊዜያዊነት ኃይል ይዞ እንዲቆይ ለማድረግ ከሥራ ተቋራጩ ጋር ምክክሮች እየተደረጉ ባሉበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል።
@Esat_tv1