ወሎ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር የእግር ኳስ ሻምፒዮን ሆነ
የዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ከዘጠኝ ዓመታት መቋረጥ በኋላ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡ ውድድሩ በአምስት የስፖርት ዓይነቶች ሲካሄድ ሰንብቶ አብዛኞቹ ተጠናቀዋል፡፡ ከእነዚህ ውድድሮች መካከል 45 ዩኒቨርስቲዎች የተሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር በወሎ ዩኒቨርስቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ከዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን ያደረገው ወሎ ዩኒቨርስቲ 1ለ0 አሸንፎ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ የታበትን የፍጻሜ ጨዋታ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ደረጄ እንግዳ( ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ማህበር ፕሬዚደንት አቶ አባይ በላይሁንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተከታትለውታል፡፡
ከፍጻሜው ጨዋታ ቀደም ብሎ በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ጎንደር ዩኒቨርስቲ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲን 3ለ2 አሸንፎ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
የ2017 የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ነገ ረፋድ ለአሸናፊዎች እውቅና፣ ሜዳሊያና ዋንጫ በመስጠት እንደሚጠናቀቅ አዘጋጆቹ አሳውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በክላስተር ደረጃ በአምስት ዞኖች ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡ #AMN
@Ethiopian_Digital_Library