ፈተናውን ሙሉ በሙሉ ደፍኖታል
ሳህሌ ነጋሲ የተባለው የ17 አመቱ ታዳጊ በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ተማሪ ሲሆን የዘንድሮውን የኮሌጅ መግቢያ ፈተና ወይንም ሳት (SAT) የወሰደ ነው፡፡ በውጤቱም 1600 ነጥብ ማምጣት ችሏል፡፡ ይህም ማለት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ ደፍኖታል፡፡
በመላው አሜሪካ በሚሰጠው በዚህ ፈተና እንዲህ አይነት ውጤት እንብዛም አይመጣም፡፡
የሳት ፈተናን መድፈን የሚችሉት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከአንድ ፐርሰንት በታቹ ብቻ ናቸው፡፡ ማለትም በየአመቱ የሚደፍን ተማሪ የማይኖር ሲሆን ከአመታት በኋላ አንድ ተማሪ ደፍኖ ይገኛል፡፡ ሳህሌ ነጋሲ ከእነዚህ ጥቂት ተማሪዎች መካከል ዘንድሮ ተገኝቷል፡፡
በኒውዮርክ ተወልዶ በኒው ጀርሲ ያደገው ይህ ተማሪ ለዚህ ፈተና ዝግጅት ያደረገው በትምህርት ቤት በሚሰጠው ትምህርት ብቻ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡ ከኢንተርኔት ላይ በነፃ የሚሰጡ ትምህርቶችን መከታተሉ እንደጠቀመውም አስረድቷል፡፡

በቀጣይነት በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት እንዳለው ያስረዳው ሳህሌ ጨምሮም ‹‹ከአስር አመት በኋላ በዚህ ፈተና ካመጣሁት ውጤት የበለጠ ትልቅ ነገር እሰራለሁ›› በማለት ህልሙን አስታውቋል፡፡
የዚህ ተማሪ መረጃ ከትላንት ጀምሮ ይፋ ከሆነ በኋላ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ተማሪው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ኤርትራዊያን በበኩላቸው ደግሞ የአገራቸው ዜጋ መሆኑን እየገለፁ ናቸው፡፡ #Zehabesha
@Ethiopian_Digital_Library