ስነፅሁፍ በወንጌል - Gospel Literature


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


◉ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ላይ ፦
➫ #አጭር_እና_ረጅም_ልብወለዶች
➫ #መንፈሳዊ_ተውኔት
➫ #መንፈሳዊ_ትረካዎች
➫ #መንፈሳዊ_ግጥሞች
➫ #መንፈሳዊ_ፅሁፎች
➫ #መንፈሳዊ_ድርሰቶችያገኛሉ።
ሶሻል ሚዲያ አካውንት ለመሸጥ ለመግዛት እኔን ያናግሩኝ 👉 @wunu_pa
Buy ads: https://telega.io/c/Gospel_Literature
Since Thursday 11-9-2014

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


እውቀት ወለድ ክፍል አምስት
✍በ ቅድስት /@Kidymar1

ከፕሮግራም በዋላ ቲጂ ቀድማ ወታ" ጋይስ ሁልሽም ነገ ፈልግሻለው "
ፅናት : አረ ተረጋጊ ሰላም በይን ቅድሚያ
ቲጂ : እሺ ፅኑ love U ነገ እንገናኛለን bye
ቲጂ :ዮዮ አለህ ነገ ፈልጋችዋለሁ ለሚኪም ንገረው
ዮናስ : እንዴ ቲጂ ቾክለሻል
ቲጂ : አዎ ዮዮ ደዉልልኝ ባይ
እየዞረች ላሰበችው አላማ ይጠቅማሉ ያለቻቸውን ጓደኞችዋን ጋበዘች::በግዜ ለመነሳት በግዜ ተኛች ::

ሲነጋ በጠዋት ተነስታ እቅዷን ማከናወን ጀመረች በጠዋቱ ብዙ ስልኮች እየተደወሉ ቀጠሮ እያስያዘች ነው

ዮኒ: ለምን ይመስልሃል ቲጂ የጠራችን?
ሚኪ: ምን አዉቃለሁ ጠንከር ያለ ነገር ይመስላል
አንተ ደሞ እሷ ጠንከር ያለ ነገር ታቃለች?
እንዴት አታቅም?
ሲጀመር የቲማቸው ድምቀት እሷ አደለች?
ሲቀጥል ከፍቅር ጋር ስላንተ ምትሟገት እሷ አደለች?
ይሄን ካልነው ሃሳብ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ቁምነገር ብርቋ አደለም ለማለት ብዬ ነው
ቢሆንም የሆነች ቅልብልብ ነገር ስለ ሆነች ሙድ ልትይዝ እንዳይሆን ብዬ ነዋ
እሱን እንግዴ... ሄደን ነው ምናቀው
ሰዓቱ እንደዛው ነው ወይስ....
አዎ ምንም ያለቺኝ የለም ለዚህ በዛው ነው ሚሆነው
-------------
ሁሉም በየፊናው የራሱን ግምት እያስቀመጠ ከሌላው እየተከራከረ ወደ ተጠራበት ይፈሳል ምን ይሆን? ምን ልትል ይሆን? ምን አስባ ይሆን? እየተባባሉ እርስ በእርስ እየጠያየቁ ሁሉም መጡ ትዕግስትም እንደተዘጋጀቺው ሃሳቧን ማብራራት ቀጠለች
እንኳን ደና መጣችሁ ማርፈድን ለሙሽራ ብቻ ያለ ማነው? ብላችሁ ያረፈዳችሁ ደሞ ቆይ እንገናኛለን ዛሬ ግን የተገናኘነው ባንድ ሃሳብ ላይ አዉርተን እንድንወስን ነው::
እና ሃሳቡ ምንድነው ከዛሬ ጀምሮ እስክንመረቅ ድረስ ያለውን excess ወጪ በመቀነስ እንዲሁም በትርፍ ጊዜ ገቢ በማሰባሰብ ጉልበት ሲያስፈልግም በጉልበት በማገዝ አቅማችን እስከቻለ በማድረግ ነገ ለስራ ወይም ለጉብኝት ስንመጣ የምንኮራበት ነገር አስቤ ነው የጠራህዋችሁ እና ሃሳቤን እንዴት አያችሁት?

ይህን ስትናገር ፍቅር በመገረም ታያታለች ወይ ጉድ መድረክ ካገኘ ሁሉም ሰው የመስራት አቅም አለው:: ረባሽ:ፈጣን እና ቅልብልብ የተባለችው እንዲህ ባንዴ ትለወጥ? ይገርማል ትላለች በሃሳቧ

አረ እስኪ አንዴ ለቲጂ ( ሁሉም አንድ ላይ ሞቅ አርገው አጨበጨቡ)
ቲጂ በጣም ደስ የሚል ሃሳብ ነው እርግጠኛ ነኝ ሁሉም የሚስማማበት ሃሳብ ነው እኔም ይህን ዕድል በማግኘቴ ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ አለች አንዷ::
ሌሎችም በየተራ እየተነሱ ሃሳቡን ደግፈው ተናገሩ ወደድዋት አሞገስዋት አደነቋት ደስ አላቸው :: ከውይይቱ በዋላ ፍቅር ጋር ወደ ዶርም ሲመለሱ
ጀግኒት ደስ የሚል ፕሮግራም ነበር
ቲጂ : ወይኔ በስማም ካሰብኩት በላይ ደስ ይል ነበር ::
ፍቅር :ሁሉም እንደተናገሩት ከተገበሩት amazing ነው
ቲጂ : እንደ ጌታ ፍቃድ ይሁን
ስለ ብር ልጆቹ ያላቸው ሃሳብ ግን አይገርምም?
"ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ"ያለው ቤኪ እውነቱን ነው (ሞቅ ያለ ሳቅ )
አረ አንቺ ልጅ ከምነው ሃሳብ እንደሚመጣልሽ እራሱ የኔ ፈጣን
ያው ያንቺ እህት አደለሁ? አለመጎበዝ አልችልም
ፍቅር :ይሁንልሽ እንደዉም አስታወሽኝ ላይብረሪ ሰዓታችን ደርሶአል እኮ እንሂድ
ቲጂ :እሺ ልብስ እንቀይር
ፍቅር :አረ ይሁን ተይው እኔ አልቀይርም
ቲጂ :እሺ ተባብለው ወተው ሄዱ

-----------
በሱ : እንዴት ነሽ? ቲጂ
ቲጂ : ሰላም በሱ ፍቃድ
በሱ :ግን እንደዚህ አሪፍ ሃሳብ ይሆናል ብዬ አልጠበኩም ነበር በጣም አሪፍ ነው
ቲጂ :አረ እኔም አልጠበኩም ከዛ በዋላ ብዙ ስልክ እየተደወለ ነው ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ እና ሊሳተፉ እንደሚፈልጉ እየነገሩኝ የነበረው
በሱ :በእዉነት? በጣም አሪፍ ነዋ
ቲጂ : አዎ አሁን ላይብረሪ እየገባሁ ነው ስወጣ ስለ ሃሳቡ በዝርዝር እናወራለን
በሱ : መልካም ነይ
ቲጂ : እሺ


ዮኒ:አንተ የዛሬው ሃሳብ ግን አልገረመህም?
ሚኪ :ቀላል በፊትም የናካት አንተ ነህ እንጂ ልጅቱ ጎብዛለች
ዮኒ:ንቀት ሳይሆን ቁምነገር አታቅም ብዬ ነው
ሚኪ :ዛሬ አሳመነችካ!
ዮኒ: በደንብ!ተገርሞአል ዮናስ ምክንያቱም ለሷ የሰጣት ቦታ ከፍ ብላ ስላገኛት ሲጀመር እንዲው ነው ዛሬ ካገኘኘነው ሰው ጀምሮ እድሜ ልክ እስከምናቀው ሰው ድረስ ከልባችን ቦታ እነሆኝ ብለን እንሰጣለን ከዛ ከፍ ብለው ስናገኝ ሱርፕራይዝ እንሆናለን ከዛ ወርደው ስናገኝ ደሞ እንናደድባቸዋለን ::

ስራውን ቲጂና በሱ በበላይነት እየመሩ ሁሉንም ሞራል እየሰጡ ተጀመረ:: ለሁሉም ኃላፊነት ተከፋፈለ ግማሹ ገቢ አሰባሳቢ ግማሹ ሪሰርች ሰሪ ግማሹ የወረቀት ጉዳዮችን አስፈፃሚ ግማሹን ዕቃ ገዢ ግማሹ ሂሳብ ተቆጣጣሪ አድርገው ሁሉንም ግን በጉልበት አጋዥ እንዲሆኑ አስቀምጡ በየግዜው እየተገናኙ አስፈላጊውን ማሻሻያ ያደርጋሉ:: በዚህ ምደባ ዮናስም ፍቅርም ጥናት መስራቱ ላይ ነው የተመደቡት ዮኒ ፍቅርን የሚያገኝበት ሰፊ በማግኘቱ እጅግ ደስ ብሎታል ቲጂ እና በሱ ተገናኝተው ለመወያየት እንዲመች ሁለቱም ሂሳብ ተቆጣጣሪ ቡድን ውስጥ ገብተዋል::

ከታሰበው በላይ ሆነ::ከክርስቲያን በወጣ ሃሳብ ብዙዎች ተጠቅመዋል የአለም ብርሃን የምድር ጨው ማለት ይሄ ነው:: ተማሪው ካለው ብቻ ሳይሆን ያለውን ያመጣል ማቲዎስ በቅርቡ የማሳትመው ገቢው ለዚህ አላማ ይዋል አለ :: ሌሎችም ቤተሰብ ከሚልክላቸው እንዲሁም እዛው የሚሰሩ ከሚሰሩት እነኤልዱም አገልግሎት ሄደው ካገኙት ለመስጠት አልሳሱም እግዚአብሔር ይመስገን የብዙ ሰዎች ቤት ታደስ የብዙ ሰዎች ስራ ተስተካከለ የብዙዎች ህብረት ጠነከረ አረ
በዚህ ስራ እንደ ዮናስ የተደሰተ ግን አልነበረም ምክንያቱም ሲተኛም ሲነሳም ሲበላም ሲጠጣም ሕልሙ የሆነችው ሴት አብራው ትውላለች ፍቅርም ቢሆን ለዮኒ ያላት ቦታ ጨምሮአል እሱን መስማት እና ማየት ደስ የሚለው ስራዋ ሆኖአል:: እንደውም አንድ ቀን የአንድ አዛውንት ቤት ለማደስ ሲያፈርሱ ዮናስ እጁ ይቆረጣል::ፍቅር ደነገጠች አለቀሰች አበደች ስታለቅስ ያያት ሰው ሞቶ እንጂ እጅ ተቆርጦ አይመስልም በዛ አጋጣሚ እንደወደደችው ታዋቀባት እሷ ግን ግድ አልሰጣትም እሱ ላይ አተኮረች እሱስ ሚፈለገው ያን አደል በደንብ ፍቅሩን አሳያት::ሳታስበው እንዳፈቀረችው ታወቀባት ግድ አልሰጣትም :: አ ጧ እቅዳቸው በመሳካቱ ትግስት እና በሱፍቃድ ደስታችቸው ወደር አቶአል እየተገናኙ ሂሳብም ይሰራሉ እቅድም ያወጣሉ ከዛ ወደ ተግባር በሁለት ወር ተአምር የመሰለ ስራ ነው የተሰራው ከዛ ማጠናቀቅያ አከባቢ ሪፖርት ማዘጋጀት የነሱ ስራ ነበር:: እና እያዘጋጁ ቢሮ ተቀምጠው እየሰሩ እየሳቁ እያለ ድንገት ሰላም ቢሮው አከባቢ ስትደርስ
"አንቺ ጎበዝ ሴት ነሽ አንቺን በማወቄ እድለኛ ነኝ የእዉነት አመሰግናለሁ "
"ኦው በሱዬ ቴንኪው ባንተ እንዲህ መባል እንዴት ደስ እንደሚል " የሚል ድምፅ ትሰማለች እየሳቀች ወደ ኃላ ተመለሰች::
ይቀጥል?




ስለምትሰጡኝ አስተያየት አመሰግናለሁ ::
https://t.me/Gospel_Literature
https://t.me/Gospel_Literature


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
New platform Valero Energy
Many people have made money by joining Valero Energy, so what are you waiting for? Join Valero Energy and make money at home at any time. Welcome to the new energy company Valero Energy. Prepare for tomorrow with Valero Energy. It is actually very simple to make money online.
Choose the best company to cooperate with, and you will succeed.
If you encounter any problems, please contact the online customer service directly, we are always at your service. Join Valero Energy and find your own financial freedom. Register now to get 50 ETB, there will be a cash treasure box every day, which can be withdrawn directly
🌐Official registration address: https://www.valerosn.com/?invitation_code=44F8E
🌐Official Telegram channel https://t.me/Valero1


እውቀት ወለድ ክፍል አራት
✍በ ቅድስት /@Kidymar1


ያው ልወያይ ነዋ እናቴ ለቁምነገር ምንፈለግ ሰው ሆነናል ስልሽ?ህህህህ የአሽሙር ሳቅ ሳቀች ሁሌም እንዲህ ነው ተናቁረው ሲያበቁ አሸናፊው አሽሙር ሳቅ ይስቃል:: ቲጂም ባሸናፊነት መንፈስ ዶርም ለቃ ወጣች የቸርች ደርሳ ቢሮ ስገባ ከበሱፍቃድ ጋር ተገናኙ:: ሳይገናኝ እንደቆየ ሰው ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጡ ዉይይቱ ተጀመረ....


ሰላም :እናንተ? የምር ቲጂ ግን የት ሄዳ ነው?
ምህረት: ቀጠሮ አለኝ ብላ ነበር ከበድ ያለ ሳይሆን አይቀርም
ፍቅር : ዉይ ቲጂ ከኛ ተለይታ? አረ አታረገውም ሱቅ ምናምን ነው ሚሆነው
ሰላም :አረ አንቺ አልጠበሽም እና እሷም አትጥበስ?
ምህረት : በእየሱስ ስም ከምኔው ወደዛ ሄድሽ
ሰላም : አረ ባክሽ ጨዋ ነች ምንም አታቅም ልትሉኝ ባሎነ?
ፍቅር: አረ አንቺ ልጅ ምን ይሻልሻል? ሁሌ ጭቅጭቅ?
ሰላም : እና ማይመስል ነገር አታውሩዋ
ምህረት : አረ ተዉት ስትመጣ ትነግረን የለ?
ፍቅር : ሰሊማ የሷ ደህንነት ሁሌም በጣም ያሳስባታል :: ብላ ከት ብለው ሳቁ ለምን እንደሆነ የሁሉም ልብ ያቀዋል ::



ዮናስ : ሚኪ በናትህ በግዜ እንውጣ
ሚኪ : ምን? ለምን
ዮኒ: ኤጭ አንተ ደሞ በዚህ ጉዳይ አታላግጥ አላልኩህም አፍጥነው ና እንሂድ
ሚኪ : በለው ቁጣም አለው ዛሬ በገዛ ስልኬ ልትቆጣ ባሎነ እንደውም ቻው አልሄድም
ዮኒ: ሚኪ በጌታ? ለምን አትረዳኝ ቆይ
ሚኪ : አረ ስቀልድ ነው መጣሁ ተዘጋጅ እና ጠብቀኝ
ዮኒ : ተዘጋጅቻለው
ሚኪ : እሺ መጣሁ :: ስልኩን ዘግቶ ጌታ ሆይ እባክህ እኔንም ከጭቅጭቅ እሱንም ከጭንቅ ገላግለን

ቲጂ ከመቼውም በበለጠ ዝምተኛ ሆናለች ዛሬ ለካ እንዲህ ነው እንዴ? ሰዉ ከራሱ ጋር ሲሆን ከሰው የሚያወራው ይቀንሳል? ዝምተኛ እሚባሉት ሰዎች ለካ ሚያወሩት ሲያጡ ሳይሆን ሚያወሩለት ሲመርጡ ነው ቲጂም ዛሬ ምታወራው እያለ ምታወራለት አታ ዝም አለች
ፍቅር : ምነው ቲጂ ምን ሆነሻል?
ቲጂ : ምንም
ድሮስ ምን ትበላት?ከበሱ ፍቃድ ጋር እንዳሰብነው አንቺን ከዮኒ ጋር እንዴት ማገናኘት እንዳለብን እያቀድኩ ነው ትበላት? ሆ ማይሆነውን ወይስ አንቺም ዮናስም ሳታቁ እንድታወሩ ልናደርግ ነው ትበል እኮ ይሄ ምን ተብሎ ይነገራል
ፍቅር : አረ አንቺ ልጅ ያለወትሮ ዝጋታም ሆንሽ እኮ ደሞ ልንገርሽ ባንቺ አያምርም ወይስ ችግር አለ?
ቲጂ: ምንም አልሆንኩም አልኩሽ እኮ
ፍቅር : ቲጂዬ እኔ ማውቃት ቲጂ እኮ እቺ አደለችም ባህሪሽን አቃለሁ ካኮረፍሽ ዞር ነው ምትይው እንጂ ከኔ ጋር ሆነሽ ዝም ማለት አትችይም ታዲያ አዲስ ፀባይ ከየት አመጣሽ?
ቲጂ : የኔ እናት ልቅም አርገሽ አዉቀሽኛላ እኔማ በሱ ያልተነበብሽ መፅሐፍ ነሽ ሲል ፈርቼ ነበረ
ፍቅር : ማን በሱ ነው? አረ አውቆ ሲቀልድ ነው ከሆነም እኔ አንብቤሻለው ይጠይቀኝ ሃሃሃሃ ብላ ሳቀች
ቲጂ : አረ ባክሽ? ቀልደኛ ባይሆን የሆነ ነገር ልንገርሽ
ከማለቷ ወደ ፍቅር ስልክ ቴክስት ገባ ፍቅር ስልኩን ብድግ ስታረግ
ቲጂ : ዮናስ ነዋ?
ፍቅር : አዎ ነው
ቲጂ : አረ ፍቅር ግን ለምንድነው እሺ የማትው ቆይ
ፍቅር : text በገባ ቁጥር? አይሰለችሽም ግን?
ቲጂ : ስለ ምወድሽ እና ፀፀትሽን ማየት ስለማልፈልግ ነዋ
እንደ ሌላው ግዜ ፍቅር አላሾፈችም ዝም አለች ::ባይሆን ልነግርሽ የጀመርኩት ነገር ነበረ አደል?
ፍቅር : አዎ ምንድነው
ቲጂ : ከግቢ ስንወጣ እንዳንረሳ ለምን አንድ ቁምነገር እዚህ በምንቆይበት ግዜ አንሰራም
ፍቅር : የምርሽን ነው? አንቺ ተአምር የማያልቅብሽ ልጅ ሁሌም እንዳስደመምሽኝ ነዋ?
ቲጂ : ምን ተአምር አለው ብዙ ግዜ አስቤ አቃለሁ ግን free ስላልሆንን እና ብዙ ተማሪ ጋር መግባባት እንዳለብን አስቤ ነው የተውኩት አሁን ግዜው ነው ብዬ አሰብኩ ከዛ ነገርኩሽ
ፍቅር : በፊት ለምን ሳትነግሪኝ?
ቲጂ : አረ ባክሽ? ባንቺ አመል? ብነግርሽ የዋህ ጎንሽ ተነክቶ ደሞ ትምህርትሽ ላይ ጣጣ ልታበዥ?
ፍቅር : እንደዛማ አላረግም እሺ ግን ምን ያህል አሰብሽበት?
ቲጂ : መች ማሰቢያ ግዜ ሰጠሽኝ ገና ላስብ ስል አደል? ለምን አሰብሽ ብለሽ ምጨቀጭቂኝ?
ፍቅር: እንኳን ይሄን የመሰለ ሃሳብ መች ትነግሪኛለሽ ዝም ብልሽ
ቲጂ : ይሁንልሽ ያው ሰብሰብ ብለን አዉርተን እንወስናለን ብዙ ሰዉ ያስፈልጋል:: አረ እንውጣ ተነሺ ይሄን ግዜ ተጎልተዋል ብላት በሩን ዘግተው ወጡ::


ድንቅ ግዜ ድንቅ አምልኮ ሁሉም ችግሩን ሃዘኑን ሃሳቡን ጭንቀቱን ጥሎ ከእግዝአብሔር የተገናኘበት ግዜ አቢጊያ ዘምራ ማቲዎስ ነበር ቃል ያካፈለ እግዚአብሔር ትልቅ ነው በሚል ርዕስ ነበር የእግዚአብሔርን ትልቅነት እንዲሁም ጥልቀት በዝርዝር ሲያስተምር ቆየ ለምንድነው ግን ስለእግዚአብሔር ትልቅነት
መቼም የትም ሲነገር ማይሰለቸው ከማቲ ቅልጥፍና ጋር ደሞ እግዚአብሔር በርሱ ያነጋገር ችሎታ እና እንቅስቃሴ እራሱን ሲገልጥ እንዴት ደስ ይላል :: ማስደነቅ ማይሰለቸው ጌታ ሲያስደንቃቸው አመሸ :: ከፕሮግራም በዋላ ቲጂ ቀድማ ወታ" ጋይስ ሁልሽም ነገ ፈልግሻለው "
ፅናት : አረ ተረጋጊ ሰላም በይን ቅድሚያ
ቲጂ : እሺ ፅኑ love U ነገ እንገናኛለን bye
ቲጂ :ዮዮ አለህ ነገ ፈልጋችዋለሁ ለሚኪም ንገረው
ዮናስ : እንዴ ቲጂ ቾክለሻል
ቲጂ : አዎ ዮዮ ደዉልልኝ ባይ
እየዞረች ላሰበችው አላማ ይጠቅማሉ ያለቻቸውን ጓደኞችዋን ጋበዘች:: በግዜ ለመነሳት በግዜ ተኛች ::
ሲነጋ በጠዋት ተነስታ እቅዷን ማከናወን ጀመረች በጠዋቱ ብዙ ስልኮች እየተደወሉ ቀጠሮ እያስያዘች ነው...
ይቀጥል?


አረ አስተያየት ስጡኝ? ተዉ ግን ሳምንት ሙሉ 4 ሰዉ ብቻ?

https://t.me/Gospel_Literature
https://t.me/Gospel_Literature


1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:10-11 አማ05
📌‼️The foundation of Christianity is Jesus Christ.


ሀጥያት የሰው ዘርን ከፋፈለ ክርስቶስ ግን በመንፈሱ አንድ አደረገ


ባንተ መሸነፍ ማሸነፍ ነው አንተን ይዞ መዘግየት ቀድም ከመውጣት በላይ ነው
የኔ ድል ያለኝ ነገር የምትሰጠኝ አይደለም የኔ ድል እጄን ላንተ አንስቼ ስሸነፍ ነክተኸኝ ስለወጥ ብቻ ነው. forwarded message from YouTube comments


#እፈራለሁ🤲🥹
✨ከሰፋው የምህረት እቅፍህ ውጪ #በራሴ_የቅጠል_ካባ ልሸሸግ ስሞክር
✨ያለ መገኘትህ ሙላት ለመኖር ስዘጋጅ
✨ከድምፅህ ምሪት ቀድሜ በራሴ ማስተዋል ስደገፍ
✨ከአንተ ለይቶ ለራሱ ሊያደርገኝ ከከጀለኝ ጠላት ስወዳጅ
✨አንተን ባላማከለ ሃሳብ ስጠለፍ
✨ካላንተ ልጎብዝ ስሞክር፤ጥገኝነቴን ስሽር
#እፈራለሁ!!!
አምላኬ ሆይ ለዘላለም የአንተ ጥገኛ ነኝ መቼም አልችልም🙌🥹
ይለናል በሴ


ዋጋዬ ስንት ነው?

አንድ አንድ ጊዜ መሆን ምንፈልገውና ምንሆነው ለየቅል ነው። ምንአልባት ሂወት መንገድ አስቀይራን ምንፈልገውን እንደማያስፈልገን ትነግረናለች።
ጥያቄው
ለምን ?
የሚል ይሆናል
ዞር ብለን ህይወታችንን ካየነው የፈለግነውን ነገር ሁሉ አግኝተን ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ አንገኝም ነበር። የፈለግነው ነገር አያስፈልገንም ምክንያቱም ዋጋችን የፈለግነው ነገር ላይ ወድቆ እኛነታችንን ያሳጣን ነበር። ከሰውነት ተራ ያወጣን ነበር። ሂወት ግን በስቃይ እና በህመም ልታስተምረን ትመጣለች። ዋጋችሁን ፈልጉት ትለናለች። የሚገባቹን ኑሩ የሚገባቹ ቦታ ቁሙ ትለናለች። ምክንያቱም እኛ ዋጋችን በደም የታተመ ነው። እሱን በማይገባን ቦታ ቆመን አናርክሰው! በመኖራችን ብቻ ደስታን የሚጎናጸፉ ሰዎች አሉን ቤተሰብ፥ የትዳር አጋራችን አሊያም ጓደኛ ሊሆን ይችላል። ደስታችንን እያሳየን መሆን ምንፈልገውን ሳይሆን ሚያስፈልገንን ሞገስ ተላብሰን ደስታችንን እያሳየን ፍቅርን እናልብሳቸው።
ለሱ ደሞ ዋጋችንን እንወቅ
ምንቆምበትን ምንራመድበትን  ቦታ እንምረጥ
የኛ ዋጋ የት ነው?
ዋጋችንስ ስንት ነው? እንበል

     ✍በ ሚልካ


እውቀት ወለድ ክፍል ሶስት
✍በ ቅድስት /@Kidymar1

እስኪ የእግዚአብሔርን ፍቅር ደሞ አስቡት
ይወደናል - ይረዳናል
ይወደናል- ያግዘናል
ይወደናል - ይሰጠናል
ይወደናል - ይሞትልናል
ይወደናል - ከኛ ምንም አይፈልግም
እየበደልነው እንኩዋን ይፈልገናል
ባንመጥነውም አይንቀንም ብኖደውም ባንወደዉም ይወደናል::እዉነተኛ ፍቅር እንደዚ ነው የአሳን ለአሳ ትታቹ ሰውን እንደ ቃሉ ዉደዱ እሺ ጉዋደኞቼ?
ዮናስ : በጣም አመሰግናለሁ ትልቅ ነገር ነው የነገርከኝ 10q በጣም::
በሱ : ቺግር የለውም
ሚኪ :አሁን ግን ምንሄድበት አለን ብሎ ተነሳ ዮኒም ተነሳ ካፌዉን ለቀው ወጡ ::


"እኔማ በዋላ እዉነተኛ ፍቅርን ከሃሰተኛ ፍቅር መለየት አቅቶሽ እንዳይቆጭሽ ነው"::ያለቺው የትግስት ንግግር ከአይምሮዋ ሊወጣ አልቻለም "ልክ እኮ ናት ምን አልባት አስቤ አመዛዝኘው ያልወሰንኩት ነገር ነገ እንዳይፀፅተኝ!" አለች ስልኳን አንስታ ደወለች::

ሀለው ፍቅር
ሄለው በሱ
እንደምን ነሽ
አለሁ እንዴት ነህ
ደና ነኝ ደዉላለው እያልኩ ሳልደውል ቀደምሽኝ ደሞ ዮኒ በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው ::
እንዴት? ማለት? ማለቴ አወራችሁ?
አረ ቀስ
ጉጉቷ ስለታዋቀባት አፍራ ዝም አለች
አይዞሽ ነግርሻለው ዮኒ እንዳንቺ እና እንደአሳ የምወደው የለውም እ ብሎ ሳቀ
ደስ አላት " ያው ቢሆንም እኔ ማስቀድማቸው መስፈርቶች አሉኝ " አለች ቆፍጠን ብላ
ልክ ነው በሂደት ምናየው ይሆናል ::
እሺ
በቃ ነገ ቢሮ ነይና እናወራለን
እሺ መጣለሁ
እሺ ቻው
ቻው

በቀጣይ ቀን ከክላስ በዋላ ወደዚያው አመራች ሰላምታ ተለዋውጠው ተቀምጣ መነጋገር ጀመሩ
በሱፍቃድ : ይሄውልሽ ፍቅር እስካሁን ያለው አካሄድሽ ልክ ነው ከዚህ በዋላ ግን ማስተዋል አለብሽ በደፈናው ከመግፋት የእግዝአብሔር ፈቃድ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ አለብሽ ያን ደሞ በሂደት እናደርጋለን
ፍቅር : በጣም አመሰግናለሁ በሱ አባትም ወንድሜም እኮ ነህ ግን ምን አስተዋልክ ከሱ?
በሱ : በጣም የገረመኝ እንደ ወደደሽ ያስታውቅበታል ስምሽ ሲነሳ ስሜታዊ ይሆናል
የመስማት ችሎታው ደስ ሲል
በመሃል ፍቅርን ሲያስተዉላት ምስጥ ብላ ታዳምጣለች
በሱ :ወሬውን ቅይር አርጎ በኤልኤዘር ወሬ ይስሀቅን የወደደችው ማን ነበረች?
ፍቅር : እ? እሱዋን መሆኑን ሲገባት ሳቀች አፍራ በቃ ልሂድ አዲስ ነገር ሲኖር ደዉልልኝ ብላ ተነሳች
በሱ : ይሻላል? እሺ ደዉላለው ቻው
ፍቅር : ቻው


በሱ ፍቃድ እያንዳንቸውን ጉዋደኛሞች አስተዋለ
ትዕግስት => ፈጣን ቀልጣፋ መልስ እማታጣ
ሰላም = > ችኩል ነገረኛ ጠብ በደላላ
ምህረት => ዝምተኛ አይን አፋር ለጓደኞችዋ ስትል ምንም የምታደርግ
ፍቅር => በራስ መተማመን ያላት ማድረግ ምትፈልገውን የማድረግ አቅም ያላት
እዉነትም ዮኒ መምረጥ ትችላለህ አለ በሃሳቡ በሰውኛ ምርጥ ጥንድ ነው እግዚአብሔር ያሳካላችሁ እንጂ ብሎ መረቃቸው አንድ ነገር አስቦ ለትዕግስት ደወለ
ትዕግስት : ሄለው
በሱ : ሄለው ቲጂ
ወዬ
ደና ነሽ?
ደና ነኝ እንዴት ነህ?
አለሁ ክላስ እንዴት ነው
ተያይዘናል እንግዲህ
አንተስ ያዝከው? ወይስ ይዞሃል?
ሃሃሃሃ ልይዘኝሲል አመለጥኩት አሁን እኔ ነኝ የያዝኩት
ተሳሳቁ
ቲጂ አንድ ነገር ላማክርሽ አስቤ ነበር የደወልኩት
በለው እኔ አንተን መካሪ ሆኘ? ይሁና
ቀላል አንቺ እኮ ያልተነበበ መፅሐፍ ነሽ ሁሉም ርዕስሽን አይቶ ነው ሚፈራሽ
አስፈሪ ርዕስ ውስጡ ባዶ ገፅ በለኛ ልታነብ ስትገባ ሚነበብ አጣክ አደል? ህህህህ
በጭራሽ እንዴ ወሰብሰብ ያለ ይዘት ስላለሽ ነው ሪፍረንስ ያሌለው አይረዳሽም
እንዴ ቁምነገር ይሁና ስንት ሰዓት እንገናኝ?
ከፕሮግራም በፊት መምጣት ትቺያለሽ?
እሺ መጣለው
መልካም ነገ እንገናኛለን
እሺ ቻው ስልኩ ተዘጋ

በነጋታው ስለ ፍቅር እንደሆነ ስለገባት በጊዜ መዘጋጀት ጀምራለች
የት ነው ደሞ በጊዜ ጠየቀች ሰላም
ልነበብ ማለቴ ልወያይ
ምን
አዎ ምነው
ልወያይ ማለት?
ያው ልወያይ ነዋ እናቴ ለቁምነገር ምንፈለግ ሰው ሆነናል ስልሽ?ህህህህ የአሽሙር ሳቅ ሳቀች ሁሌም እንዲህ ነው ተናቁረው ሲያበቁ አሸናፊው አሽሙር ሳቅ ይስቃል ቲጂም ባሸናፊነት መንፈስ ዶርም ለቃ ወጣች የቸርች ደርሳ ቢሮ ስገባ ከበሱፍቃድ ጋር ተገናኙ ሳይገናኝ እንደቆየ ሰው ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጡ ዉይይቱ ተጀመረ....


https://t.me/Gospel_Literature
https://t.me/Gospel_Literature


ጥበበኞች ነን ቢሉም፣ ሞኞች ሆኑ፤'.....


ለምን ደስታ ራቀኝ?  ለምን ማስመሰል ጀመርኩ? ለምን? ለምን ? ለምን? በጣም ብዙ ጥያቄ

ወደኃላ ስመለከት ለካ በጣም ብዙ ከ እግዚአብሔር ያልመጡ ነገሮች ዙርያዬን ከበዋል። ከእርሱ ያልሆነ ምንም ነገር በዙርያህ ካለ ምንም ደስተኛ የሆንክ ብትመስልም እዉነተኛ ደስታና ሰላም ግን በእርግጠኝነት ልታገኝ አትችልም። ከእግዚአብሔር ያልመጣን ነገር ማስወጣት ስትጀምር እወነተኛ ደስታ ሰላም መረጋጋት ወደ ህይወትህ መምጣት ይጀምራሉ።

#መኩሪያ ነኝ


እውቀት ወለድ ክፍል ሁለት
✍በ ቅድስት /@Kidymar1

ለተወሰነ ደቂቃ ዝም ካላት በዋላ ዝምታዋ ገርሞት ምን ልታማክሪኝ ነው እስኪ ንገሪኝ?ፍቅር : እሺ ብላ ድጋሚ ወደ ሃሳብ ሰመጠች ፈገግ ብሎ ፍቅር በእውነት ትክክለኛ ዉሳኔ እንደ ወሰንሽ ልነግርሽ ፈልጋለው :: ብዙዎች አንድ ነገር ሲገጥማቸው በነገሩ ላይ እዉቀት ያለው ሰው ከማማከር እና እንደ እግዚአብሔር ቃል ከመፈተሽ ይልቅ ሌላ አማራጭ ይወስዳሉ አንቺ ግን ልባም ነሽ ::
ፍቅር : ቀና ብላ አይታው አመሰግናለሁ ብላ ጉዳይዋን ልታብራራ ገባች
ከቸርች ሲወጡ ተፈላልገው ተገናኙ እንደ በፊቱ ፍቅር አብራቸው አለመኖሯ ገርሞአቸው ነበር ሲያገኝዋት
ሰላም :አንቺ ምን በልተሽ ጠግበሽ ነው ትተሽን የመጣሺው እኛ አንቺ በመፈለግ ስንንከራተት ማየት አምሮሽ ነው?
ትግስት :አብሬሽን መምጣት ካልፈለግሽ ቅድም ለምን ሳነግሪኝ?
ምህረት : ወረዳቹባት እኮ አረ ተፋቱዋት በቃ መብትዋ እኮ ነው?
ክሳቸውን ሲጨርሱ እያወሩ ወደ ግቢ ሄዱ ::

ሁሌ ፍቅር እና ትግስት ዶርም ዉስጥ አልጋቸው ላይ ተቀምጠው እንዳሉ : ወደ የፍቅር ስልክ text ይገባል::
ሁሌ :ትግስት : ማነው?
ፍቅር : አቤት አንች
ትግስት :ዮናስ ነዋ?
ፍቅር :አዎ
ትግስት : አረ አንቺ ልጅ ግን ነው ምትለው ምክንያትዋን አጠይቅም ይወድሻል ነው በቃ
ፍቅር : ለምን?
ትግስት : ወይ ጉድ ስንት ዓመት ነው ምነግርሽ?
ፍቅር :አይ ለኔ ያልታየው እንዴት ታየሽ ብዬ ነዋ 😂
ትግስት :አረ ባክሽ? አዉቀሽ እንጂ ሳይገባሽ ቀርቶ ነው?

ሚኪ እና ዮናስ እንደ ሁሌው ሁሉ ዛሬም አብረው ናቸው
ዮኒ :ሂሳብ ዛሬ አንተጋ ነው ሚሊየነር
ሚኪ : ከፍላለሁ ደሞ ለአሳ
ዮኒ: ስንት ቦታ ህህህህ

ተሳሳቁ... ሲሰማቸው የቆየ አንድ ሰው
አገልጋዩ : እዚጋ ልቀመጥ?
ተቀመጥ ባንድ ድምፅ ::
አመሰግናለሁ በሱ ፍቃድ እባላለሁ
ሚኪ :እኔ ሚክያስ እባላለሁ
ዮን:እኔ ዮናስ እባላለሁ
በሱፍቃድ :ከንግግራቹ ስረዳ አሳ የምትወድ ይመስላል አለ ወደ ዮናስ እያየ
ሚኪ: ከራሱ በላይ ነዋ አለ ሚኪ
ዮን :ስለሚጠቅመኝ ነዋ
ሚኪ: እንደ ፍቅር እና እንደ አሳ የሚወደው የለም በሳምንት 2ቴ /3ቴ ካልበላ እሚሞት ነው ሚመስለው
ዮን : አረ አጋነንከው አበባ ስለማይበላ እንጂ እንደ ሴት አደል ምትመሰጥበት? ነው እያሳጣሀኝ ነው?
በሱ:ቺግር የለውም ነፃ ሁኑ
ዮን:አረ ተወው እኔን ለማብሸቅ ነው

ምግቡ መጣ መመገብ ጀመሩ

በሱፍቃድ አሳውን ሲያይ ቆይቶ ቀና አለና :ምን እንደ ሚገርመኝ ታቃላችሁ? ያንዳንድ ሰው ፍቅር ልክ እንደዚ ነው ::አይን አይናቸው እያየ ንግግሩን ቀጠለ
. አሳን የማይወው ሰው እንዲኖር ሲተወው እሚወደው ይገለዋል::አንዳንድ ሰዉም እንደምወድህ እየነገረህ ይጎዳሃል:: ወይ እንድትጠቅመው ብቻ ይፈልጋል መጠበሳችሁ: መቃጠላችሁ መቀቀላችሁ ከጠቀመው ያረገዋል::
አሳውን ትወደዋለህ -ታጠምደዋለህ
ትወደዋለህ - ትገለዋለህ
ትወደዋለህ - ትጠብሰዋለህ
ትወደዋለህ - ትበላዋለህ
ይወደኛል ብሎ አንተ ጋር ሲመጣ ታሪኩ ያበቃል::
እስኪ የእግዚአብሔርን ፍቅር ደሞ አስቡት
ይወደናል - ይረዳናል
ይወደናል- ያግዘናል
ይወደናል - ይሰጠናል
ይወደናል - ይሞትልናል
ይወደናል - ከኛ ምንም አይፈልግም
እየበደልነው እንኩዋን ይፈልገናል
ባንመጥነውም አይንቀንም ብኖደውም ባንወደዉም ይወደናል::እዉነተኛ ፍቅር እንደዚ ነው የአሳን ለአሳ ትታቹ ሰውን እንደ ቃሉ ዉደዱ እሺ ጉዋደኞቼ?
ዮናስ : በጣም አመሰግናለሁ ትልቅ ነገር ነው የነገርከኝ 10q በጣም::
በሱ : ቺግር የለውም
ሚኪ :አሁን ግን ምንሄድበት አለን ብሎ ተነሳ ዮኒም ተነሳ ካፌዉን ለቀው ወጡ ::

አይቀጥል?
https://t.me/Gospel_Literature
https://t.me/Gospel_Literature


እውቀት ወለድ ክፍል አንድ
✍በ ቅድስት /@Kidymar1


ፍቅር እና ትግስት ዶርም ዉስጥ አልጋቸው ላይ ተቀምጠው እያወሩ: ወደ የፍቅር ስልክ text ይገባል::
ትግስት : ማነው?
ፍቅር : ተረጋጊ
ትግስት :ዮናስ ነዋ?
ፍቅር :አዎ
ትግስት : አረ አንቺ ልጅ ግን ለምን ጥያቄዉን አትቀበይም?
ፍቅር : ለምን?
ትግስት :ዮናስ እኮ ይወድሻል :በዛ ላይ እንደ ስሙ የዋህ ነው ::
ፍቅር :ህህህ በስም ሆነ እንዴ? በስም ከሆነ አደፍርስ እና አስጨናቂ ምን ይዉጣቸዋል ደሞ ጉዋደኛችን ሰላምም እንደስሟ ሰላም መሆን ነበረባት አንቺም እንደ ስምሽ ትግስ...
ትግስት :ተይው ተይው በቃ አንቺን ማን ይችላል ::
ፍቅር : ህህህህ አንቺ አደለሽ ያነሳሽው?
ትግስት :እኔማ በዋላ እዉነተኛ ፍቅርን ከሃሰተኛ ፍቅር መለየት አቅቶሽ እንዳይቆጭሽ ነው::
ፍቅር :ምንም አልመለሰችም ዝም አለች
ትግስት : በይ ተነሽ ፀጉር ቤትሽ ሂጂ ብላት ተነሳች ዶርሙንም ለቃ ወጣች::





ዮናስ ካፌ ተቀምጦ ወደ ምጠብቀው ሚኪ ሲሄድ እንደ ደበረው ነው
ሚኪ :ዮዮ ጭር ብለህሃል
ዮን :ተወኝ ባክህ
ሚኪ : ዛሬም?
ዮን :አዎ
ሚኪ :ለምን አትተዋትም?
ዮን : አንተ ደሞ እወዳታለሁ እኮ
ሚኪ :እሺ እሺ ቁርስ እንብላ እንዳታለቅስ ብሎ ሳቀበት

አስተናጋጅዋን ጠሩ..... መጣች
ምን ልታዘዝ?
ሚኪ: ዛሬም አሳ ነው?
ዮን: እና
ሚኪ :ለኔ እንቁላል አምጪልኝ ጥቂት ቆይቶ ምግቡ መጣ
መመገብ ጀመሩ ::ተመግበው ሲያበቁ ወተው እዛው ከተማ ወደሚገኘው የጉዋደኞቻቸው ቤት ሄዱ ይሄ የዘወትር የቅዳሜ ጠዋት ስራቸው ነው


ፍቅርም ለቅዳሜ ከሰዓት fellowship program ለመሄድ በጊዜ ፀጉርዋን ለመሰራት ተጣጥባ ተነሳች ልብሱዋን እንደ ነገሩ ለብሳ ወጣች በርግጥ ብዙ ቅዳሜዎችዋ ተመሳሳይ ናቸው አራት ዓመት እንዲሁ ታደርግ ነበር:: ዛሬ ግን አንድ ሃሳብ ላይ መወሰን እንዳለባት እየተሰማት ፀጉር ቤቱ በር ላይ ደረሰች::በካክስ ዉስጥ የሚጠበሰው ፀጉርዋ ሳይሰማት ታሰላስላለች :: አንድ ነገር ለማድረግ አሰበች+:ጨርሳም ስትወጣ ምሳ ለመብላት ወደ ካፌ ተመለሰች



ከምሳ በዋላ እንደ በፊቱ ጉዋደኛዋጋ አልደወለችም ይልቅ ሌላ ቦታ ነው የደወለችው::ሰዓት እስኪደርስ አልጠበቀችም::ብቻዋን ከሰዓቱ ቀድማ ወደ ቸርች ገሠገሠች:: ቸርች ስትደርስ የደወለችለት ሰው ቢሮ እየጠበቃት ነው ገብታ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ በዝምታ ተቀመተች ለተወሰነ ደቂቃ ዝም ካላት በዋላ ዝምታዋ ገርሞት ምን ልታማክሪኝ ነው እስኪ ንገሪኝ?

ይቀጥል?
https://t.me/Gospel_Literature
https://t.me/Gospel_Literature


አሁንም ማርከን አባ❤❤


አቤቱ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት ማፅናናትህ ነብሴን ደስ አሰኛት


❗️ቃሉ
ስለ ሕይወት ጅማሮ 

❗️ቃሉ
በክርስቶስ ስለሚገኝ ሕይወት

❗️ቃሉ
በክርስቶስ ስላለ ሕይወትና አኗኗር

❗️ቃሉ
ስለ ፍጻሜያችን

መመሪያችን መማሪያችን ነው!!

👉 ከቃሉ በመራቅ ሕይወቴን ሕይወት በሌለበት ነገር አልጠምድም!!

👉 ሕይወት የናፈቃችሁ ኑ ወደ ቃሉ

👉 የጠማችሁ ኑና ቃሉ በሚሰጠው እርካታ ደስ ተሰኙ፣
የተራባችሁ ኑ ና ብሉ በሚያጠግበው በእግዚአብሔር ቃል ጥገቡ!

❗️ከቃሉ በመራቅ ነፍሳችሁን አታስርቡ!!


አቤቱ ስለ ቸርነትህ ስለ ይቅር ባይነትክ የቱ ቃል አንተን ይገልፅክ ይሆን?


ሰላም ማጣትን የመሰለ ህመም የለም ውጫዊ ጩኸትን ሰው ይገታልሀል ሀይ ባይ አለ የነብስን ጭንቀትና ጩኸት ግን ማንም ዝም አያሰኝም ከክርስቶስ በቀር እኔ ምሰጣቹ ሰላም አለም እንደምሰጠው አይደለም አለ አለም የስጋ ሰላም ምናልባት ልሰጥ ትችላለች የነብስም የስጋም ሰላም የሆነው የዘላለም ጌታችን ይባረክ
እህታቹ ኤደን ነኝ


የእግዚአብሔር ምህረት ከማንኛውም ስህተት የበለጠ ነው.


ለጌታ ነገር በተጋው መጠን ፈተና ይበዛብኛል ለምትሉ ሰዎች!

ዓለም አጥበቀው ከጌታ ጋር ሕይወት ለመኖር ለሚናፍቁ ሰዎች ምቹ አይደለችም የእኛ ምቹ መኖሪያ ስፍራ ሰማይ ነው።

ከጌታ በኖርክ መጠን ዓለምን ጨለማዋን ትገልጥባታለህ ስለዚህ ወዳጇ ሳትሆን ጠላቷ ነህ ቢመስልህም ባይመስልህም በግልጥ ወይ በስውር ትዋጋናለች።

ስለዚህ በመጠን ኖረን ጨለማዋን መግለጥ ካልቻልን ልታስርን በምትፈልገው ሁሉ አስራን ባርያ ታደርገናለች አልያም ፍቅሯን በመስበክ ወዳጇ ታደርገንና ያላትን ትሰጠናለች የወደደች መስላ የእግዚአብሔር ጠላት ታደርገናለች።

ፈተናው በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መታመንና መውደድ ማስጣል ነው።  ፈተናውን ማለፍ ካልቻልን ባርያ መሆን ግዴታችን ይሆናል።

በአጭሩ በፈተና ጽና አይዞህ ወዳጄ ለጌታ ለመኖር በታገለ መጠን ተሰነካክሎ በፈተና የወደቀ እንደ እኔ ምስክር አታገኝምና ጽና አይዞህ መንገዳችን ረጅም ነው መዳረሻው ሰማይ ነው።

ተራራውን ሸለቆውን  ጭንቀት መከራውን ሳቅና ደስታውን ድልና ሽንፈቱን አልፈን ሰማይ እንገናኛለን ምክንያቱም መዳራሻችን ሰማይ ነው።

“በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።”
  — ያዕቆብ 1፥12


በርታ አይዞህ!!
በአጭሩ በፈተና ጽኑ!!

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.