Hakim


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ጃፓኖች ሁሉም ነገር ላይ እጅግ ስነ ስርዓት አላቸው ይባላል። በቀደመ ህይወቴ ጃፓናዊ ነበርኩኝ መሰለኝ እኔም ስርዓት አበዛለሁ።😄 በእርግጥ የኔ የጤና አይደለም። በፀበልም በፀሎትም የማይድን OCD (Obsessive Compulsive Disorder) አለብኝ። የችግሩ አንደኛው ምልክት ነገሮች ሁሉ በስርዓት እንዲደራጁ አለቅጥ መሻት ነው። እኔም የሚታይብኝ ይሄኛው ምልክት ነው።

የተዛነፈ ነገር ማዬት አልችልም። የማላውቀው ሰው ኮሌታ ራሱ ካልተስተካከለ እጄን ይበላኛል። የምግብም ይሁን የቡና ሱፍራ ዘርፍ አሁንም አሁንም ሳስተካከል፣ ሲኒ ሆነ ብርጭቆ በልክ ስደረድር፣ ምንጣፍ ለማንጠፍ መስመር ሳሰምር ላዬኝ ድሮዊንግ ተጨንቆ እዬሰራ ያለ ሲቪል ኢንጂኒዬር ነው የምመስለው።

የተዝረከረከ ነገር አልወድም። አልጋ ሳነጥፍ ውጥር አድርጌ ነው። መጅሊስም ይሁን ፍራሽ ሰው ተቀምጦ በተነሳ ቁጥር ነው የማስተካክለው። ጫማ ሲቀመጥ ከተንሻፈፈም ከተደራረበም ተነስቼ አስተካክላለሁ። ደርቆ የገባ ልብስ ቶሎ ካልተጣጠፈ የሆነ የተሸከምኩት ነገር ያለ እስኪመስለኝ ነው የሚከብደኝ። ያልተተኮሰ ልብስ በተዓምር አልለብስም።

ልብሴ ላይ ትንሽ ጠብታ ነገር አርፎ ማስወገድ ካልቻልኩ ትኩረቴ እዛ ላይ ሆኖ ይውላል። አብሮ የማይሄድ ወይም ከላይም ከታችም የተዥጎረጎረ አለባበስ ያቅለሸልሸኛል። ዲዛይነር ብሆን የሚዋጣልኝ ይመስለኛል። የብር ኖት የባንክ ሠራተኛ እንኳን እንደኔ አያስተካክልም። ፅሁፍ ላይ ግድፈት እንዳይኖር በጣም እጠነቀቃለሁ። አለቆች ትንሽ ካወቁኝ በኋላ "መቼም አንቺ አትሳሳቺም" እያሉ ሳያነቡ መፈረም ይጀምራሉ። እምነታቸው በበሽታዬ ላይ ኃላፊነት ያሸክመኛል።

🤦‍♀️ እንኳን ቢሮ ፌስቡክ ላይም ስፅፍ የአንዲትም ፊደል ስህተት አልፈልግም። ለአፃፃፉ ግድ የሌለው ሰው ራሱ ይገርመኛል። የቢሮ ጠረጴዛዬ ላይ አንዲት ወረቀት ያለ አግባብ አትገኝም።

ፎቶ ሳነሳ ባለሙያ ይመስል አንግል፣ ሴንተር፣ ፎከስ እላለሁ። የተጣመመ ፎቶ የማይረብሻቸው ሰዎች ታድለው። የምቀርፃቸውን የኸሚስ ቪድዮዎች ያዬ አንድ ጓደኛዬ እንደውም እንቅስቃሴ ካለመኖሩ የተነሳ በስታንድ ካሜራ ነው ወይ የምትቀርጪው ብሎኛል። ለነገሮች ውበትና Details ስጨነቅ አርክቴክት ይቀናብኛል።

ሲበዛ ቀጠሮ አከብራለሁ። ሌላው ቀርቶ ፖስት ራሱ በተሸራረፈ ሰዓት መፖሰት አልወድም። 1 ሰዓት 5 ሰዓት እንደዛ። የአንድ የሁለት ደቂቃም ልዩነት አልፈልግም። በምንም ነገር ፐርፌክሽን ያስደስተኛል። ግድየለሽነት፣ ቸልተኝነት ያናድደኛል። የቱንም ያክል ቢበዛ ከቢሮ ሥራ ጨርሼ ነው የምወጣው። ካልሆነ ልቤ እዛው ተንጠልጥሎ ነው የሚያድረው። ልሠራው ያሰብኩት 5 ነገር ኖሮ አንዱ እንኳን ከጎደለ ይደብረኛል። ጓደኞቼ "ሞራልሽ የወታደር ነው!" ይሉኛል። አቡዳቢ እያለሁ ጂም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ሊዘጋ እኔ 6 ሰዓት ሄጄ አውቃለሁ። ምክንያቱም ቀድሜ አስቤዋለኋ።🤣 ያሰብኩትን ነገር ካልፈፀምኩ የአዕምሮዬ መንገድ ይጨናነቃል። የሰውም ጉዳይ ቢሆን ሳላሳካ መተው አልችልም። በነገራችሁ ላይ ይሄ ችግር ቀላል እንዳይመስላችሁ። በዚህ ሰበብ የፈረሱ ትዳሮች ሁሉ አሉ። ደግነቱ እኔ እየመረረኝም ቢሆን ራሴ አስተካክላለሁ እንጂ ሰው አልጫንም። ቢያመኝም ቢደክመኝም ለዚህ ሲሆን አልሰንፍም። ምናልባት ልጆች ሲኖሩኝና ቤቱን እያመሳቀሉ ጢምቢራዬን ሲያዞሩት እንደ ኩፍኝ ካልወጣልኝ በቀር ነገርዬው በዋዛ የሚተውም አይደለም። ለማንኛውም መስመር የያዘች ቅድዬ ተመኘሁላችሁ!

ፏ_ያለች_ቅድዬ!♥♥♥

By: Atiqa Ahmed Ali

@HakimEthio


Willingness_of_caregivers_to_have_their_daughters_vaccinated_against.pdf
1.3Mb
Willingness of caregivers to have their daughters vaccinated against human papilloma virus and associated factors in Jimma Town, Southwest Ethiopia

Anebo Getachew, Susan Anand and Tilahun Wodaynew

https://www.frontiersin.org/journals/global-womens-health/articles/10.3389/fgwh.2024.1400324/full

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio


frph-1-1491617.pdf
3.4Mb
The magnitude of casual sex and associated factors among students at Debre Berhan University

Tsega Mathewos, Esubalew Tesfahun,Muluken Tessema Aemiro and Tadesse Mamo Dejene

doi: 10.3389/frph.2024.1491617

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio


I wanted to take a moment to express my heartfelt gratitude and appreciation to Dr. Godana Jarso (Abba Liban), who was an incredible mentor, guide, and now elder brother.

I have known Dr. Godana for more than a decade, and what sets Dr. Godana Jarso apart is his unwavering dedication. Dr. Godana has a unique ability to make even the most challenging topics understandable and engaging. Beyond academics, I learnt the importance of perseverance, curiosity, and kindness from him.

He is a leader, academician, researcher, and businessman. His encouragement and support have made a lasting difference in my confidence and growth. I am truly honored to have been mentored by such an exceptional academician, and I will always cherish the wisdom and inspiration he has shared with me

Watch his life journey with http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

Dr. Beshada Z. Woldegeorgis, MD, Public Health Specialist, Internal Medicine resident

@HakimEthio


Urology Graduates of Tikur Anbessa, 2024

@HakimEthio


ONCO Pathology Diagnostic Center arranged and provided Professional Customer Handling Training provided to its staff members, aiming to equip the team with enhanced skills to deliver professional customer service to our valued clients. The training was conducted by Addis Hesabe Consulting Services far Embilta Hotel from December 17-20,2024.

📞0949045555 | 0945606969 | 0945003664📞
ኦንኮ የፓቶሎጂ ምርመራ ማእከል በአሳለፍነው ሳምንት (ታህሳስ 8-11፡2017) የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል አልሞ ለሰራተኞቹ “የደንበኞች አገልግሎት ስልጠና”፡ ሰጥቷል፡ ስልጠናው የተሰጠው በአዲስ ህሳቤ ኮንሰልቲንግ ሰርቪስስ በእምቢልታ ሆቴል ነው።

#ONCOPathology #CustomerService #StaffTraining #AddisHesabe


እርጋታ እና ማስተዋል መልካቸው እሱን ነው ሚመስለኝ!!!

ከተማሪነት ግዜ አንስቶ እስከ አሁኗ አብሮ የመስራት አድል ያስተዋልኩት በጊዜ ብዛት የማይቀየር ፅናት ፣ ስራ ወዳድነት ፣ ስነምግባር እና የተደራጀ እውቀት የተላበሰ አስተማሪ፣ ሀኪም ፣ መሪ እና አባት መሆኑን ነው !(አንተ አንድለው ስለሚፈቅድልኝ ነው 😊)

ፊልም በሚመስል ግን ደሞ በተኖረ ልጅነትና ወጣትነት፣ በተከፈለ መስዋዕትነትና አልሸነፍ ባይነት የተገኘ ስኬት እንዲ በኩራት ሲነገር በብዙ ውጣውረድ ውሰጥ ላለን ጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ወጣቶች በዓላማ መፅናት የግዜ ጉዳይ እንጂ ዉጤት እንዳለው ማሳያ ነው።

ዶ/ር ጎዳና ከሰዎች ማንነት ይልቅ ባላቸው አቅም እና ስነምግባር መዳኘት የሚችል ፣ ያለ ስስት አውቀቱን የሚያካፍል ፣ በቀላሉ ቀልቡን ማትይዘው ፣ በድርጊት እና ስራህ ብቻ ምታሳምነው ድንቅ ሰው ነወ። ይህ ማንነቱን ነው መኮረጅ ያቃተኝ 😁

ከ ዶ/ር ጋር ባለኝ የስራ ግኑኝነት አዲስ ነገር ያልተማርኩበት ቀን አይታወሰኝም በተለይ ፈታኝ አና ውስብስብ በሆኑ የህክምና ጉዳዮች ላይ ያለው የተለየ እይታ እና የመፍትሔ ጥቆማዎቹ የተለየ ችሎታውና መሠጠቱ ናቸወ።

በግሌ ስለሰጠኸኝ እውቀት ፣ አክብሮት ፣መረዳት ፣ አብሮ የመስራት እድል አንዲሁም በገንዘብ ማይተመኑ የስራ ልምዶችና ገንቢ ምክሮች ከልብ አመሠግናለሁ።

የዶክተር ጎዳና ጃርሶን (አባ ሊበን) የህይወት ተሞክሮ እና የህክምና ህይወት እንድትመለከቱና እንድትማሩበት እጋብዛለሁ ፧ https://www.youtube.com/watch?v=Z0mnjg8xpII

ዶ/ር አለኝታ በቀለ

@HakimEthio


12872_2024_4389_OnlinePDF.pdf
1.7Mb
Determinant factors of the longitudinal pulse pressure among hypertensive patients treated at Assosa general hospital, Western Ethiopia

Berhanie Addis Ayele, Maru Zewdu Kassie, Haymanot Berelie Berhan and Seyifemickael Amare Yilema
https://doi.org/10.1186/s12872-024-04389-7

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio


We hope you are proud to know that your efforts are making a lasting difference in the lives of our patients and their families. We are truly fortunate to have you with us.

Dear Dr. Shukuria Lemma
I would like to express my sincere gratitude for your exceptional support and dedication during our recent surgical procedures. Your willingness to communicate openly and your willingness to help us with your training has made a huge difference to our entire operating theater team.

Your commitment to staying with us, even in the most difficult of circumstances, demonstrates your unwavering commitment to our growth and success. Your training has not only improved our skills but also fostered teamwork and confidence among all of us.

Now our fracture patients are treated here in their own communities with free, American-made technology that is shipped to us regularly. They can walk and work within days.

Dear Dr. Lewis Zerkle, as the owner and founder of the SIGN nail program, we would like to thank you again for your generosity and vision. On behalf of our patients, we thank you for giving opportunity to Professor Biruk for helping us and for what he has accomplished.
Sincerely

Dr. Abreham Gebre, MD, Assistant professor of Orthopedics, Welkitie University

@HakimEthio


ተወርቅጥየ ዩኒቨርስቲ እናምሰግኑ/ናትሸኩኔኩ
ፕሮፈሰር ብሩክ ላምቢሶ በሙራ ጉራጌም በቀያ ባነቦ ሰብ ሽም ናትሸኩኔኩ።

ጎይታ በዴንጋሁ ያስራሁምታ እንም ወሄ ዘንጋ ኧዘዎ ። ኧትክንዳ ዶ/ር ሽኩሪያ ለማ (አሁ አስተማርሁምታ ፤ ተኽታተርሁምታ ኧዝ አሰናሁያ) አት ኧዶ/ር ሉዊዝ ዘርክልም በአመሪካን ባነሁኴ መደር  ሹኩርተንዳ  የስራሁ፡፡

የኌሪም ኀማ ሆስፒታለንዳ የብዘ አጥም ሱረር ነቦ ሰብ ያጓኪር  ቃሩ፡፡ ዝም ኸረምታ  የዝ ኢፍቴ የህክምና ግብር   አነፐረንደ ኧኽሬ ያጥም ሱረር የሰናቦ ሰብ ብዘም ቃር አናጌከነ። እድሜ ያሁ ኧኋ ጭን SIGN Nail program በሆስፒታለንዳ በቅርሶት ተህ ጅጓረ ተጊያፈነ። ተሂነንዴ ሳረንደምታ  በዝ ወሄ ዘንጋ ያሰናሁንደ አሁትንሁ ፕሮፌሰር ንቃር ናትሸኩኔኩ። ዝህ ይኸሬ ኧቄጥሁ አሁ ዘበራሁ የትባረክ፡፡

ናማጂንደ ፕሮፈሰር ብሩክ ላምቢሶ
በገነንዳ በብዘ  ሆስፒታል  ኧቾትሁዊ ኸማ ቢናሜ ዝህ SIGN Nail program ንቀርስኔ ኧቄጥሁይ ቂጭናሁ ተጌቴ ንኸበዊ። ዝህ ንቅ ዋጋ  በሚሊዮን ብር ቢኸርም ካሽተዊታኤረህዊ ግብር በነጻ አቸነሁምታ ሜና ቀነስነ፣ ኢና ኧሃኪም ፎያት ኧታማሚ ፌነት ነከዉነም። በአለም በትራቆ ገነ አንዝወነ ኸማ በሰዉ አሰናሁንደም የሳርሁ ንቃር ሳረንደም።
ፕሮፍ ኢና ቢኧር ኧታካሚየንዳ አነናሁ ንቅ መደር  ብንመንዳ በኦርቶፔዲክስ  ኻኪምኤትረሳ ወሄ ዘንጋ ቾትሁንደም። እን ግዚየ ወሄ ሜና ንቾትን ኸማ ወሄ ኤማ አትየሸሁንደም።

SIGN nail ንኸዎተንዳ ታማሚ ህም ተህም ፈዘዘም፤ ካች ባረም ኧሜናቴ  ያር ኸማ ኤፐንም። በዝ የጀፐርሁይ ግዚየ፣ አወጣሁዊ  ቂጭነር ፣ ፍራንክ ፤ ዘንጊተዊ ኤጀፑሪ እክም  ጎይታ እካስነሁ በሮቱ ባኸሬ። ዝህ እንም ኢና ኧጉራጌ አነነሁ ንማጀ ተጠነቆታሁ ያቲየሽ።

ናማጂየንዳ ዶ/ር ሽኩሪያ ለማ
ዶ/ር አኽ የቾትኺ ወሄ ዘንጋ ንቃሩ፣ ተሄ በሻዋ ተዝራኸሂም ሜናኽ ቸሂም ዝህ ይብስ  ባሂም ተረንሳሂም ግብር ሁታ ጠበጥሂም ቸነሂም፣ ይንመንዳ ኦኦፐሬሽን  ክፍል ሰብ ኤፐሂ ወሄ ዘንጋ ጎይታ እንም ወሄ ዘንጋ አተዥኺ። ኼት ሳምት ስነጋ ቲና ቸናኺም ቤትሸከት መደር ኧክስሂም  ኦፐረሽን ቲና ኤፐኺም በታማሚም በሆስፒታልም ሽም ሽኩር ኧስራኺ ። በቃ ታማሚ በዝም በቀያህኖ ኧረቔ ቴያሮም ይታከሞቴ  ሳረንደም የሳርኺ።

ናማጂየንዳ ዶ/ር ሉዊስ ዘርክል
የSIGN nail program መስራችም ባለቤት ኤፐኾን እንም ወኼ ዘንጋ ንኸብ ባርነ ዳርኔክ። በመጨረሻም እንም የሆስፒታል ሰብ እንም ሳረንደም የሳርሁ፡፡

ዶ/ር አብርሃም ገብሬ: አጥም ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር : ተወርቅጥየ ዩኒቨርስቲ

Thank you from Gurage-Wolkite University

Professor Biruk Lambiso, on behalf of the entire Gurage and surrounding communities. May God bless you with your children.

Our deepest gratitude goes to our daughter Dr. Shkuria Lemma (whom you taught and mentored and made her a success) and Dr. Lewis Zerkle for their time in the United States.

As you know, our hospital provides services to many patients with fractures. However, due to the lack of equipment, it was very difficult to provide proper care and treatment to patients with long fractures; however, today, with the launch of the SIGN nail program at our hospital, this problem is now history. Thank you very much, Professor. I would like to express my sincere gratitude to the sincere individuals who were the main actors in this success.

Dear Professor Biruk Lambiso, We are very grateful for your commitment to starting this program in our hospital, as you have done in many hospitals in our country. We are very grateful for your trust in us and for bringing these valuable items worth millions from American to our hospital and starting the work.

The impossible has become possible for us and we have succeeded! We are equal to the others! We are very happy

Prof. your place to our patients, for us and for your students has had a great impact on all of us as an orthopedic family. Your support and guidance have not only helped us overcome challenges but also inspired us to strive for continuous improvement in our work.

Thank you for being a wonderful leader and mentor. Your vision and support motivate us to grow in our profession every day and provide quality treatment. We sincerely thank you for your special support in coordinating the establishment of the SIGN nail program for long-term treatment of bone fractures at Wolkite University Hospital. Your dedication and efforts have made a significant impact on our ability to provide superior care to our patients.

The acquisition of the SIGN nail set will enhance our ability to effectively treat long bone fractures, resulting in better outcomes and early recovery for our patients. Your commitment to ensuring that we have access to this essential medical device demonstrates your deep concern for the well-being of the local community (Gurage) we serve.

We are deeply grateful for the time, money, and effort you have invested in this process. Your advocacy and coordination have been instrumental in making this possible, and we are grateful for your partnership in improving healthcare in our community.


ከጉራጌ-ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ምስጋና
("ናትሸኩኔኩ" "እናምሰግኑ")

አማርኛ | ጉራግኛ | English

ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶን በላቀ ሁኔታ በመላው ጉራጌና አከባቢው ሕዝብ ስም እናመሠግናለን። ፈጣሪ በልጆችዎ ይባርክዎ። ለልጃችን ዶ/ር ሽኩሪያ ለማ (እርስዎ አስተምረውና ተከታትለው ለዚህ ያበቋት) እና ለዶ/ር ሉዊስ ዘርክልም በአሜሪካን በያሉበት ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳቸው።

እንደሚታወቀው ሆስፒታላችን ለብዙ አጥንት ስብራት ላላቸው  ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጣል። ነገር ግን የዕቃ እጥረት ስላለብን ረዥም የአጥንት ስብራት ላለባቸው ታካሚዎች ተገቢውን እንክብካቤ እና ህክምና መስጠት በጣም አስቸጋሪ ነበር ፤ ዛሬ ግን  SIGN nail program በሆስፒታላችን በመጀመሩ ይሄ ችግር ከአሁን በኋላ ታሪክ ሆኗል። እጅግ እናመሠግናለን ፕሮፌሰር። ለዚህ ስኬት ዋነኛ ተዋናይ ለነበሩት ቅን ግለሰቦች ያለኝን ልባዊ ምስጋና እንደሚከተለው ማቅረብ እፈልጋለሁ።

ውድ ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ: በብዙ የሃገራችን ሆስፒታሎች ላይ እንዳደርጉት ሁሉ ለዚህ ፕሮግራም በሆስፒታላችን መጀመር ላሳዩት ቁርጠኝነት ታላቅ ምስጋና ይገባዎታል።
በኛ ተማምነው እነዚህን በጣም ባለሚልየኖች ውድ ዕቃዎች ከአሜሪካ ሆስፓታላችን ድረስ አስመጥተውልን ስራ አስጀመሩን እጅግ በጣም እናመሠግናለን።

የማይቻለው ሆኖልናል እኛም ተሳካልን! እኛም ከሌሎቹ እኩል ሆንን!ደስ ብሎናል። ፕሮፍ ለታካሚዎቻችን ለኛም ለተማሪዎቾ  ያሎት ቦታ በሁላችንም ላይ እንደ ኦርቶፔዲክ ቤተሰብ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል።

የእርስዎ ድጋፍና መንገድ መሪነት ተግዳሮቶችን እንድንሻገር ብቻ ሳይሆን በስራችን ላይ ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማድረግ እንድንጥር አነሳስቶናል። ድንቅ መሪ እና መካሪ ስለሆኑ እናመሰግናለን። የእርስዎ እይታ እና ድጋፍ በየቀኑ ራሳችን በሞያችን እንድናድግ ና ጥራት ያለው ህክምና እንድንሰጥ ያነሳሳናል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለረጅም ጊዜ የአጥንት ስብራት ሕክምና የ SIGN nail ፕሮግራምን ለማቋቋም በማስተባበር ላደረጋችሁት ልዩ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን  እናቀርባለን። የእርስዎ ቁርጠኝነት እና ጥረቶች ለታካሚዎቻችን የላቀ እንክብካቤ ለመስጠት ባለን አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል።

የ SIGN nail set  ማግኘታችን ረጅም የአጥንት ስብራትን በብቃት የማከም አቅማችንን ያሳድጋል፣ ይህም ለታካሚዎቻችን የተሻለ የማገገሚያ ውጤት ያስገኛል።

ይህንን አስፈላጊ የህክምና መሳሪያ እንዳገኘን ለማረጋገጥ ያሎት ቁርጠኝነት ለምናገለግለው የአካባቢው ማህበረሰብ ደህንነት ያለዎትን ጥልቅ እንክብካቤ ያሳያል።

ችግራችንን ስንነግሮት ሰምተው መልስ ስላመጡልንና ቃልዎን ስለጠበቁ እናመሠግናለን። ዉድ የሆነዉን የርሶ በዚህ ሂደት ላይ ኢንቨስት ላደረጉት ጊዜ ገንዘብና እና ጉልበት ክብረት ይስጥልን ከልብ እናመሰግናለን። ይህ እንዲቻል የእርስዎ ጥብቅና እና ማስተባበር ጠቃሚ ነበር፣ እና በማህበረሰባችን ውስጥ የጤና እንክብካቤን ለማሻሻል ለምታደርጉት አጋርነት አመስጋኞች ነን። ጥረታችሁ በታካሚዎቻችን እና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ላይ ዘላቂ ለውጥ እንደሚያመጣ በማወቃችሁ እንደምትኮሩ ተስፋ እናደርጋለን። ከእኛ ጋር በመሆናችሁ በእውነት እድለኞች ነን።

ውድ ዶክተር ሽኩሪያ ለማ

በቅርብ በቀዶ ሕክምና ስራዎቻችን ወቅት ላደረጉት ልዩ ድጋፍ እና ትጋት ልባዊ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። በግልጽ ለመግባባት ፈቃደኛ መሆንዎ እና እርስዎ በሰጡትን ስልጠና፣ እኛን ለማገዝ  ያሳዩት ጥረት ለመላው የኦፕሬሽን ቲያትር ቡድናችን ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።

ከእኛ ጋር ለመቆየት ያለዎት ቁርጠኝነት፣ ለሳምንታት በማይመች ሁኔታ ውስጥም ቢሆንም፣ ለእድገታችን እና ለስኬታችን ያላችሁን የማያቋርጥ ትጋት ያሳያል። የእርስዎ ስልጠና ክህሎታችንን ከማሳደጉም በላይ በሁላችንም መካከል የቡድን ስራ እና በራስ የመተማመን ስሜትን አጎልብቷል።

አሁን የስብራት ታካሚዎቻችን እዚሁ በአካባቢያቸው ሆነው በነፃ በየጊዜው በሚላክልን አሜሪካ ሰራሽ ቴክኖሎጂ ይታከማሉ።በቀናት ውስጥ መራመድና ስራ መስራት ይችላሉ።

ውድ ዶክተር ሌዊስ ዘርክል፣

በSIGN nail program  ባለቤትና መስራች  ላደረጉልን ልግስና እና ስለ ራዕይዎ ደጋግመን እናመሠግናለን።ፕሮፌሰር ብሩክ እንዲረዳን ስላስቻሉትና ስላበቁት በታካሚዎቻችን ስም እናመሠግናለን።

ዶ/ር አብርሀም ገብሬ: የአጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት: ረዳት ፕሮፌሰር ወልቂጤ ዮኒቨርስቲ

@HakimEthio


በደቡብ የአገራችን አቅጣጫ ለምትገኙ ፣ በአቅራብያችሁ የነርቭ በሽታዎች ምርመራና ህክምና ማግኘት ከፈለጋችሁ፣ በሆሳዕና ከተማ በሚገኘው ዶ/ር ተገኝ የህክምና ማዕከል በመምጣት ፣ የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት(Neurologist) የሆኑትን ዶ/ር ተገኝን ማመከርና ፣ የተሟላ የነርቭ ምርመራና ህክምና ማግኘት ትችላላችሁ ።

አድራሻ፦ ሆሳዕና ከተማ ፣ ኢየሩሳሌም አደባባይ
ስልክ፦ 0911544732

@HakimEthio

12 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.