ኢትዮጵያ የያዘችውን ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ ለማሳካት የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ዕውን ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
አርባ ምንጭ:-ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የያዘችውን ብልጽግናን በሀገርና በቤተሰብ ደረጃ የማረጋገጥ ጉዞ ለማሳካት የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ዕውን ማድረግ ወሳኝ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሲቪል እና በቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፣ከፌደራል እና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እና አጋር አካላት ጋር በአገራዊ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ላይ ያተኮረ ውይይት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የመድረኩ ዋና ዓላማ በሀገራችን የተጀመረውን የማንነት ሥርዓት ግንባታ በተሟላ ደረጃ ዕውን ለማድረግ በቅርብ የጸደቀውን የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ አስመልክቶ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ እና አዋጁን ለማስፈጸም በተዘጋጁ ረቂቅ ደንብና የአፈጻጸም መመሪያዎች ላይ ውይይት በማድረግ ግብዓት ለማሰባሰብ የለመ መሆኑንን ጠቁመዋል ፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ መንግሥስት የተያዘውን ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ዘመናዊ የመረጃ ምንጭ የሆነዉን የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ዕውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ዶ/ር ደምሴ አድማሱ ተቋሙ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለዜጎች ተደራሽ ለማድግ በማለም አርባምንጭ ከተማ አዲስ የአገልግሎት ማዕከል ለማስጀመር የወደውን ውሳኔ በማድነቅ ለተቋም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በአሁኑ ሰአት የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1370/2017 እና ረቂቅ ደንብ እየቀረበ እንደሆነ ተገልፆል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/