የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፣ ከተዋያየባቸው ጉዳዮች አንዱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት ለመወጣት፤ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት እንዲሁም ከፓስፖርት የቆይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ ያሉ ጥቄዎችን መፍታት እንዲችል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/