በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋም እየተካሄደ ያለው የሪፎርም ስራ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው- ዶ/ር ዲማ ነገዎ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያከናወነ ያለው የሪፎርም ስራ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያከነወነ ባለው አጠቃላይ ስራ ላይ ከተቋሙ ሃላፊዎች ገለፃ ቀርቦለታል።በዚህም ተቋሙ በ2016 ዓ.ም ያከናወናቸው የስራ እንቅስቃሴ፣ የ2017 በጀት ዓመት የስራ እቅድና የእስካሁን አፈፃፀም እንዲሁም የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ላይ ለቋሚ ኮሚቴው ገለፃ ቀርቧል።የቋሚ ኮሚቴ አባላቱም በተደረገላቸው ገላፃ ላይ ጥያቄና ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀው በተቋሙ የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) ተቋሙ በተለይም ብልሹ አሰራሮችን በመዋጋት ፣ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋትና ሙስናን በመከላከል ረገድ እያከናወነ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይም የሚያደርገውን የክትትልና ድጋፍ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ተቋሙ እያከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራ በብቃት እንዲወጣ የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።ተቋሙ ከነበረበት ውስብስብ ችግር አሁን ወዳለበት ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንዲሸጋገር ከቋሚ ኮሚቴው በተጨማሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎችም የመንግስት ተቋማት ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተያዘው የስራ ዘመንም በተቋሙ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማስቀጠል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
በመድረኩ አስተያየታቸውን የሰጡ የቋሚ ኮሚቴው አባላትም ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ባደረገው የሪፎርም ስራ ላስመዘገበው ውጤት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/