ነሲሃ ቲቢ በገንዘብ እጥረት ተዘግቶ አይዘጋም! የሙስሊሙ ህብረተሰብ ኪስ ይበዘበዝበታል እንጂ!!
—————ክፍል ሁለት
በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ስር የሚተዳደረውን ነሲሃ ቲቢን አስመልክቼ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደማይችልና ሰዎቹ ምን ያህል የህዝበ ሙስሊሙን ገንዘብ ሰብስበው ህዝበ ሙስሊሙ አማና እንዳስቀመጠባቸው ዘንግተው አማና እየበሉ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ህዝቡ በግልፅ በሚመለከተው ማስረጃ ተንተርሼ በክፍል አንድ የተወሰነ ፅሁፍ ፅፌያለሁ።
በሚከተለው ሊንክም ያገኙታል።
https://t.me/IbnShifa/2604
ይህ ሁሉ የገንዘብ አቅም እንዳላቸውና በተገቢው መልኩ እንዳልሰሩበት ብዙዎች አያውቁም። ከፊሎቹ እውነታውን ቢያውቁም አያስተውሉም። አንዳንዶች ደግሞ እያወቁም በጭፍን ተከታይነት ስለታወሩ በማስረጃ ሲተቹ "ለምን ተነኩብኝ? ለምን ቀደም ሲል በዲናዊም ሆነ በዱኒያዊ ነገር እራሳቸው እንኳን ሲተቹት እንደነበረው አይነት መጅሊስ ቢሆኑ እንኳን ዝም አይባሉም?…" አይነት ጭፍን አስተሳሰብ ውስጥ ገብተው በመነካታቸውና እውነታው በመውጣቱ ስሜታቸውን በመንጫጫትና በተለያየ አይነት የባለጌ ስድብ ሲገልፁ ተስተውሏል። ይህ ብዙ ጊዜ የጭፍን ተከታይ ቲፎዞዎች የተለመደ ባህሪ ነው።
➥ ገንዘብ ማግበስበሱንና ከዱኒያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምንም እንኳን ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ከዲኑ ጋር ትስስር ያለው ቢሆንም ለአብነት ያህል ክፍል አንድ ላይ በፃፍኩት ላቁመውና ቀጥታ ወደ ዲናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ለማድረግ ልሞክር። አለያማ ሰውን የሰለፊያን ካባ ለብሰው በዲኑ እንዳጭበረበሩት ሁሉ በዱኒያዊ ጉዳዩም በእጅጉ ነው ያጭበረበሩት!፣ "በሸሪዓዊ ጉዳዮች አማካሪው ኢልያስ አህመድ ነው፣ ከሌሎች በተሻለ መልኩ ሸሪዓን ጠብቀን እንሰራለን…" እያሉ ህዝበ ሙስሊሙን በመሸንገል ገንዘቡን እያፈሰሰ አክሲዮን እንዲገዛ ካደረጉት በኋላ ደብዛው የጠፋው የዛድ ባንክ አጀንዳም ሌላ ጉድ ነው፣ ለህዝቡ የሚሰጠው ምላሽና እውነታውም የየቂል ናቸው። እንዲሁም የሁለቱ ሪልስቴቶች ውጥንቅጥና በሰው ሰራሹ ኩፍር በሆነው (ቀዋኒን አል-ወድዒይ) እስከ መካሰስ ያደረሳቸው ጉድ ሌላ ነው።
· ገንዘቡ ጠፍቶ ሳይሆን እውነታው የህዝበ ሙስሊሙን ገንዘብ በዲን ሽፋን እየሰበሰቡ መፎካከር ላይ ናቸው።
ከዐምር ቢን ዐውፍ አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
فواللَّهِ ما الفَقرَ أخشى عليكُم، ولَكِنِّي أخشى عليكُم أن تُبسَطَ الدُّنيا عليكُم، كما بُسِطَت على مَن كانَ قبلَكُم، فتَنافسوها كما تَنافسوها، فتُهْلِكَكم كما أَهْلَكَتهُم
“በአላህ እምላለሁ! በናንተ ላይ ድህነትን አልፈራላችሁም። ነገር ግን የምፍራላችሁ ዱኒያ ከናንተ በፊት ለነበሩት ሰዎች ተዘርግታ እንደነበረችው ለናንተም ተዘርግታ ከዚያም እነርሱ እንደተፎካከሩት እናንተም ተፎካክራችሁ እነሱን እንዳጠፋቻቸው እናንተንም እንዳታጠፋችሁ ነው።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]
➣ በእርግጥ ከአማናዎች ሁሉ ትልቁና ከባዱ አማና አላህ በሰዎች ላይ ያስቀመጠው የዲን አማና ነው። ሰዎች ካልጠበቁትና ኀላፊነቱን ካልተወጡት አላህ ይጠብቀዋል። በመቀጠል ከግለሰቦች ከሚበላው አማና ይልቅ የብዙሃን አማና ከባድ አማና ነው። ህዝበ ሙስሊሙ (በተለይ ሰለፊዩ ክፍል) እንደ ኢትዮ አቆጣጠር ከ1998 አካባቢ ጀምሮ ነበር ሰለፊዮች ከተለያዩ አል-ኢኽዋኑል ሙስሊሙን ከተቆጣጠሩዋቸው መሳጂዶችና መድረሳዎች በነፃነት ደዕዋ ከማድረግና ከማስተማር ሲባረሩ (ሲከለከሉ) ናጂያ ኢስላማዊ ማህበርን (የአሁኑን መርከዝ ኢብኑ መስዑድን…) መስርተው ብቅ በማለታቸው አምኗቸው በሁሉ ነገር እነሱን ተከትሎ ለሰለፊያ ደዕዋ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ሆኖ የቀጠለው። ይህን የዲን አማና ነው ከሰለፊዮች ከገንዘባቸውም ጭምር የበሉት።
ከባድ የሆነውን የዲን አማና በአመራርነት ደረጃ ያሉ አካላት ካለ መወጣታቸውም ባሻገር በአቋማቸው ጠንካራ የሚባሉ ኡስታዞችንና ዳዒዎችን በተለያየ መንገድ አሸማትረዋል።
· ከሰዎች በዲን ስም ገንዘብ ሰብስቦ መብላት፣ ከአላህ ዲን ሰዎችን ለማራቅ ወጪ ማድረግ፣ ስለ እምነቱ እውቀት ያላቸውንና አስተማሪ የሆኑ ሰዎችን በገንዘብ በመደለል ከአላህ መንገድ መዝጋት እነዚያ አይሁድና ክርስቲያኖች የተወቀሱበት የአላህና የመልእክተኛው ﷺ ጠላት የሆኑ ሰዎች መገለጪያ ነው። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ كَثِيرًا مِّنَ الْأَحْبَارِ وَالرُّهْبَانِ لَيَأْكُلُونَ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۗ وَالَّذِينَ يَكْنِزُونَ الذَّهَبَ وَالْفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸት በእርግጥ ይበላሉ፡፡ ከአላህም መንገድ ያግዳሉ፡፡ እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው፡፡» አት-ተውባ 34
ልክ አል-ኢኽዋኑል ሙስሊሙን አይሁድን እና ክርስቲያኖችን ተከትለው የእውቀት ባለ ቤቶችን በገንዘብ እየደለሉ አቅጣጫ እንደሚያስቱት ሁሉ እነዚህም የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ አመራሮች ጠንካራ የነበሩ ኡስታዞችንና ዳዒዎችን ከአቋማቸው ለማሸማተር ኢልያስ አህመድ ሀገራችን ውስጥ ከበተናት የተምይዕ አስተሳሰብ ጋር በማጣመር እርምጃ በእርምጃ በመከተል በገንዘብ አሸማትረዋል።
➲ ይህን ተቋም ሰለፊዮች በተለያየ መንገድ እየረዱት ለጥሩ ደረጃ ካበቁት በኋላ ነው በወቅቱ በተምይዕ ፊክራ እንደተመቱ ሳይነቃባቸው ከ 8/9 አመታት በፊት ጀምሮ ገንዘብ ለመሰብሰብና ከኢኽዋን በአመለካከት ያልተለዩ የእራሳቸውን ጀመዓ ለማግኘት ሲለፉ የቆዩ በሚመስሉ መልኩ ነበር ጠንካራ ሰለፊይ ኡስታዞችንና ዳዒዎችን ከመርከዟ አካባቢ በማራቅ አንዳንድ ሱሩሪዮችንና የሱሩሪያ አስተሳሰብ ያላቸውን ከኢኽዋኖች ያልጠሩ ሰዎችን ወደ መርከዙ በማስጠጋት መሰግሰግ የጀመሩት።
ከዚያ በፊት በነበሩ ጊዜያት ግን በተለይ አዲስ አበባ ላይ ብዙ (ነጋዴ) ሰለፊዮችን ጨምሮ ከቢድዐ ባለ ቤቶች ከመለያየታቸውና እራሳቸውን ከማጥራታቸው የተነሳ በንግድና በተለያዩ ጉዳዮች የነበራቸውን ግንኙነት ከቢድዓ ባለ ቤቶችና በንግዱ አለም ከሚገናኟቸው ከቲፎዞዎቻቸው ሳይቀር (ተመዩዝ በማድረግ) በሚገባ ተራርቀው ነበር።
➥ ይህ ሁሉ ጥንካሬ የነበራቸውን ዛሬ ላይ አብዘሃኛዎችን ጭፍን ተከታይ እንዲሆኑ ያደረጓቸውን የቀድሞ ሰለፊዮችን በምን መልኩ አቀለጧቸው?! የሚለውን ወደ ኋላ መለስ ብለን የመርከዟን ባለ ቤቶችና አመራሮች ጉዞ መቃኘቱ ለወደፊቱ ትምህርት ይሆን ዘንድና አሁንም በጉያቸው ላሉ ከእንቅልፋቸው ላልነቁ እንዲነቁ ይረዳል።
1ኛ, በተለያዩ ጠንካራ ኡስታዞችና ዳዒዎች የሚሰጡ የነበሩ ጠንካራ (መንሀጅ) ነክ ሙሃዶራዎችን ህዝቡ በጉጉት እየጠበቀ ሳያሳትሙ ማዘግየት፣ ባስ ሲልም ህዝቡ በተደጋጋሚ እየጠየቀ እስከነ መጨረሻው ሳያሳትሙ ማስቀረት። ልብ በሉ! (በወቅቱ እንዳአሁን ጊዜ ማህበራዊ ሚዲያ ስለ ሌላ ሰለፊዮች ደዕዋቸውን የሚያሰራጩበት ብቸኛው መንገድ ካሴትና ኦዲዮ ሲዲ ነበር)