ነሲሃ ቲቢ ተዘግቶ አይዘጋም! የሙስሊሙ ህብረተሰብ ኪስ ይበዘበዝበታል እንጂ!!
—————ክፍል አንድ
የሙመይዓ - ኢኽዋኑ ነሲሃ ቲቢ ተዘጋ በሚል ሙሾ አውራጅና አስለቃሽ ጭፍን ተከታዮች በየ ማህበራዊ ሚዲያው በዝተው እየተመለከትኩ ነው። የኢኽዋንና የሙመይዓ የጥምር የጥመት ቡድኖች የሆነው ነሲሃ ቲቢ መስኮት አንዳንድ ምስጢሩ ያልገባቸው ሰዎች በገንዘብ እጥረት ተዘጋ ሲባሉ እውነት መስሏቸዋል። አብዘሃኞቹ ደግሞ አፈቀላጤ የሆኑ ጭፍን አራጋቢ ሙሪዶችን አዘጋጅተው እያስጮሁ ስለሆነ ተጨባጩ ቢነገራቸውም እውነት ብለው ለመቀበል ሊከብዳቸው ይችላል።
በቅድሚያ ነሲሃ ቲቢ እውነት በገንዘብ እጥረት ነው የተዘጋው ወይ? በሚለው ነጥብ ላይ የተወሰነ ልበል።
ነሲሃ ቲቢ በየትኛውም ስሌት በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ አይችልም!!።
ምክንያት አንድ:- በተለያየ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንቅልፍ የማይተኙ በመርከዟ አመራርነት ደረጃ የተቀመጡ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ ባለ ሀብቶችን እና በየ ደረጃው የሚገኙ ነጋዴዎችንና በደሞዝ የሚተዳደሩ ደሞዝተኞችን ሳይቀር በተለያየ መንገድ በማጥመድ ለቲቢዋ ድጋፍ እንዲያደርጉ ከስራቸው አድርገዋል። ከነዚያ ባለ ሀብቶች ከፊላቸው በየ ወሩ መዋጮ በማድረግ ከፊላቸው ደግሞ በየ አመቱ ከፍተኛ የሆነ (ተራ ብር እንዳይመስላችሁ እያንዳንዱ ባለ ሀብት በሚሊየን ቤት) መዋጮ እንዲያደርግ አድርገዋል። ልብ በሉ! ገንዘቡ ሳይሰበሰብ እንዳይቀር ሰዎቹ ፖለቲካዊ ጫወታው ላይም የተዋጣልን አካሄድና የብር መሰብስብ ብቃት ያለን ብልጦች ነን ብለው ስለ ሚያስቡ ለባለ ሀብቶች ባለ ሀብት አስተባባሪዎችን ነው ያሰማሩት። ለሌሎች ደግሞ በየ ደረጃቸው በዘመድ፣ በአከባቢ ልጅነት፣ በየ ደርስ ቦታው… ወዘተ በየ ደረጃቸው ተመድቦላቸዋል። የተሰማሩ ባለ ሀብቶች ደግሞ በመሪያቸው ፍቅር ያበዱ የእነሱ ቀንደኛ ተላላኪና እራሳቸው ከፍተኛ የሆነን ገንዘብ ነይተው ሌሎችን በፉክክር የሚያስነይቱ ናቸው። ከባለ ሀብቶቹ ስለ ሚንሃጅ ብዙም ግንዛቤ የሌላቸው ኢኽዋኑም ሙመይዓውም… ሌላውም ለመልካም ነገር (ለዲን) ነው በሚል ስም እንዳሻው የሚያልባቸው አሉ፣ ከጅህልናቸውም ጋር በተለያየ ፊክራ የተዘፈቁ አሉ፣ ከነዚህም ውስጥ በኢኽዋን ፊክራ የተዘፈቁ ሆነው የመርከዙ ሰዎች ከእኛው ጀመዓ (ከኢኽዋኑ) ጋር አንድ ሆነዋል መደገፍ አለብን በሚል ስሜት የሚደግፉ አሉ፣ ቀደም ሲልም መርከዟን ባለ በሌለ ሀይላቸው ለዚህ ደረጃ እንድትበቃ ያደረጉ ለደዕወቱ ሰለፊያ ጉጉት የነበራቸው አሁን የመርከዙ አመራሮች ሲቀልጡ ይዘዋቸው የቀለጡና የሟሙ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች አሉ። አይደለም እንዲህ ተረባርበው ይቅርና ብቻቸውን የቲቢውን ወጪ መሸፈን የሚችሉ ጠንካራ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች ባሉበት "በገንዘብ እጥረት ተዘጋ" ብለው አስለቃሾችን ቀጥረው ሙሪዶችን አደራጅተው ማስጮሃቸው አሁንም ምስጢራቸውን ያላወቀውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ "ና! አይንህን ጨፍንና እናሙኝህ" እያሉት ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!!
ምክንያት ሁለት:- ይህ መርከዝ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ ገንዘብ ለማግበስበስ ሌት ከቀን እንቅልፍ በሌላቸው አመራሮቹ አማካኝነት ከፍተኛ የሆነ የእራሱ የገቢ አቅም አለው። ይህ የገቢ አቅምም አዲስ አበባ ላይ ብዙዎች የሚያውቁት አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር ነው። ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች ጠንከር ያለ ክፍያ እያስከፈ ከሌሎች የግል ትምህርት ቤቶች ጋር የሚወዳደር ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ት/ቤቶች አሉት። የእራሱን ቦታ ገዝቶ የገነባውን ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎችም አቅሞች ያሉት አክሲዮን ነው። ብዙ ሰዎች ይህን አክሲዮን ከመርከዙ ለይተው ሲመለከቱት ይስተዋላል። አይፈረድባቸውም 1ኛ, እነዚህ በመሪነት ደረጃ ያሉ አካላት ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች ካልሆነ በስተቀር ስሙን ከመርከዟ ጋር አያይዘው ማንሳት አይፈልጉም። 2ኛ, ብዙ ሰዎች አመሰራረቱንና አሁን ከሚያስተዳድሩት ሰዎች ጋር ምን ያህል ትስስር እንዳለው በቅርበት የሚያውቁት ነገር ስለ ሌለ እራሱን የቻለ የንግድ ተቋም አድርገው ይመለከቱታል።
መጋቢት 29/2010 ላይ 18 አካባቢ በሚገኘው በመርከዙ ዋና ህንፃ "ከመጅሊሱ ተቀላቅለን ልንሰራ ስላሰብን እንዲሁም ቲቪ ለመክፈት ፕሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን እያስገባን ስለሆነ ልናወያያችሁ አስበን ነው" የሰበሰብናችሁ በማለት ከተለያዩ ቦታዎች በኡስታዝነት ደረጃ ተቀምጠው በስራቸው የሚገኙ ሰዎችንና የሱሩሪያ ፊክራ የነበራቸውን ሰዎች በሰበሰቡበት ወቅት ከመርከዙ በዋና አመራርነት ከሚጠቀሱ ሰዎች አዩብ ደርባቸው የሚባለው አል-ዓፊያ አክሲዮንን አስመልክቶ የመርከዙ ዋና ሀብትና የገቢ ምንጭ መሆኑን ተናግሯል። ይህን መናገሩን ያስታውስ አያስታውስ አላውቅም እንጂ በወቅቱ ወንድሜ ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ከሀዋሳ መጥቶ ተሳትፎ ነበር። ይህን እውነታ በተጨማሪ አክሲዮኑ ሲመሰረት የነበሩ አንዳንድ በገንዘባቸውም ጭምር ያገዙ ባለ ሀብቶች አጫውተውኛል። ታዲያ ይህ ሁሉ አቅምና የገቢ ምንጭ እያለ ቲቢዋን ዘግቶ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ገንዘብ መበዝበዙ ለምን አስፈለገ? ህዝበ ሙስሊሙን መንሀጁንና ገንዘቡን አጭበርብረውት የት ሊያደርሳቸው ይሆን?!
በነገራችን ላይ በመጋቢት 29/2010 ስብሰባ ላይ የነበሩት አብዘሃኞቹ ተሰብሳቢዎች በቅርበት የማውቃቸው ሲያኮርፉና ሲያሻቸው ወደ ሱሩሪዮች ሲላቸው ወደ መርከዟ ልጥፍ የሚሉ የነበሩ የዛኔም ሚናቸውን ያልለዩ በሁለት ማሊያ እየተጫወቱ የነበሩ ሰዎች ነበር የሞሉት። እኔና ወንደሜን አቡ ሀመዊያን ጨምሮ አንድ ከሀረር የመጡ አሁን በትክክል ስማቸውን የማላስታውሳቸው ከመጅሊስ ስለ መስራት ሲነሳ በቁጣና በጩሀት አውግዘው ከተናገሩ በኋላ ጥለው የወጡ ሸይኽና ከባህር ዳር የመጡ በወቅቱ በእጅጉ አውግዘው በመናገር "ለምን እራሳችንን ችለን አንጓዝም?፣ ለሰለፊያ ደዕዋ እንዲህ ያለ መሰረት ካገኘን በኋላ (ህንፃውን ማለታቸው ነው) ለምን ትላንት ስናወግዛቸው ከነበሩት ከኢኽዋንና ከሱፊይ እንጨመራለን?!" በማለት ቁጣ አዘል ጥያቄ ያቀረቡ ሸይኽና በሰለፊያው ጀመዓ የሚታወቁ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው የነበሩት። ከስብሰባው በኋላ በተለምዶ (አባ ዱላ) በሚባለው በመርከዙ መኪና ወደ አየርጤና ስንሄድ ከመርከዟ አመራሮች አንዱ የሆነውን ኤልያስ አወልን በጠንካራ አቋማቸው የማውቃቸውን ሰዎች ስም ጠቅሼ ለምን አልመጡም?፣ ለምን አልተሳተፉም ወይስ አልጠራችኋቸውም ነው አልኩት? ምንም እንኳን ጥያቄ ምቾት ባይሰጠውም ሳይመልስልኝ ማለፍ አልቻለምና "እነ ባህሩ ተካን ማለትህ ነው አለኝ?" አዎ፣ ሌሎችም ብዬ የአሁኖቹን የአዲሶቹን ሙመይዓዎችንም ስም ጠቃቀስኩለት። "እነሱ ቢመጡም አንግባባም፣ ይልቁንም ሌላውንም ያስበረግጉብናል" አለኝ። እኔም:- ታዲያ በዚህ መልኩ መጓዝ ይሻላል? አልኩት። "አዎ በተለያየ ጊዜ እንወያይ ብለን ስንገናኝ ትርፉ ጭቅጭቅ ነው፣ ዝም ብለን ስራ ብንሰራ ይሻላል" አለኝ። እኔም ትዝብቴን ይዤ በጭንቅላቴ የሚመላለሱ ጥያቄዎችን ከዚህ በላይ መቀጠል ስላልፈለግኩ ዝምታዬን መርጬ አየርጤና ስንደርስ አውርዱኝ ብዬ ወደ ፉሪ ጉዟቸውን ቀጠሉ።