Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
🌿ሴትን መንካት ውዱእ ያፈርሳልን?🌿
~
♻️ ማሳሰቢያ፦
ለወንድ ሴትን መንካቱ ውዱእ ያፈርሳልን? የሚለውን ነጥብ ስናነሳ በተመሳሳይ ለሴት ወንድን መንካት ውዱእ ያፈርሳል ወይ የሚለው ታሳቢ ይደረጋል። ስለዚህ ጉዳዩ በአንዱ ፆታ ላይ የሚገደብ አይደለም።
ተቃራኒን ፆታ መንካት ውዱእ ያፈርሳል ወይስ አያፈርስም በሚለው ላይ ከኢስላም ምሁራን 3 ጎላ ያሉ የተለያዩ አቋሞች ተንፀባርቀዋል።
✅ አቋም አንድ ✅
በየትኛውም ሁኔታ ሴት መንካት ውዱእ ያፈርሳል የሚል ነው። ይሄ የኢማሙ ሻፊዒይ አቋም ሲሆን ማስረጃቸውም ተከታዩዋ የቁርኣን አንቀፅ ነች፦
(أَوْ لاَمَسْتُمُ النِّسَاء)
"ወይም ሴቶችን ብትነኩ (ሶላትን ራቁ)።" [ኒሳእ፡ 43]
ነገር ግን እዚህ ላይ የተጠቀሰው አካላዊ ንክኪ ሳይሆን የግብረ ስጋ ግንኙነት እንደሆነ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ በግልፅ ፈስረውታል። ተፍሲራቸው ከሌሎች የተሻለ ክብደት ይሰጠዋል። ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) "አላህ ሆይ! በዲን ላይ አስገንዝበው። ተፍሲርንም አሳውቀው" ብለው ዱዓእ አድርገውላቸዋልና። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
ኢብኑ ጀሪርም ይህኛውን ተፍሲር ነው የመረጡት። ስለዚህ የተጠቀሰውን ቁርኣናዊ መልእክት በአካላዊ ንክኪ መተርጎም ልክ አይሆንም።
✅ አቋም ሁለት ✅
ሴትን መንካት ከነጭራሹ ውዱእ አያፈርስም የሚል ነው። ይሄ የአቡ ሐኒፋህ አቋም ነው። በዚህ ላይ ያለው ማስረጃም፦
1ኛ፦ ጦሃራን በተመለከተ ግልፅ አፍራሽ እስከሚገኝ ድረስ መነሻ መሰረቱ የተደረገው ውዱእ ባለበት መኖሩ ነው። መጥፋቱን የሚጠቁም ግልፅ ማስረጃ እስከሚቀርብ ድረስ ባለበት ይዘልቃል። ሴትን መንካት ጦሀራን የሚያጠፋ ለመሆኑ ደግሞ ማስረጃ የለም። ስለዚህ ውዱኡ ባለበት ይቆያል ማለት ነው።
2ኛ፦ እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
كُنْتُ أَنَامُ بَيْنَ يَدَيْ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ وَرِجْلَايَ فِي قِبْلَتِهِ فَإِذَا سَجَدَ غَمَزَنِي فَقَبَضْتُ رِجْلَيَّ فَإِذَا قَامَ بَسَطْتُهُمَا
"ከአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ፊት ለፊት እተኛ ነበር። እግሮቼ በቂብላቸው በኩል ይሆናሉ። ሱጁድ ሲወርዱ ይቆነጥጡኛል እግሮቼን እሰበስባለሁ። ሲነሱ አዘራጋቸዋለሁ።" [ቡኻሪ፡ 382]
በነሳኢ ዘገባ ደግሞ "ዊትር ሊያደርጉ ሲያስቡ ጊዜ በእግራቸው ይነኩኛል።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
3ኛ፦ አሁንም እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
فَقَدْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ لَيْلَةً مِنْ الْفِرَاشِ فَالْتَمَسْتُهُ فَوَقَعَتْ يَدِي عَلَى بَطْنِ قَدَمَيْهِ وَهُوَ فِي الْمَسْجِدِ وَهُمَا مَنْصُوبَتَانِ ...
''የአላህ መልእክተኛን (ﷺ) በአንድ ሌሊት ከመኝታቸው አጣኋቸው። ስፈልጋቸው መስጂድ ውስጥ ሆነው እጄ በውስጥ እግሮቻቸው ላይ አረፈች። እነሱ (እግሮቻቸው) ተተክለው (መሬት ይዘው ቀጥ ብለው) ነው ያሉት። ..." [ሶሒሕ ሙስሊም]
በነሳኢይና በይሀቂይ ዘገባ ላይ ደግሞ "እሳቸው ሱጁድ ውስጥ ሆነው" የሚል ጭማሪ አለው።
በነዚህ ሐዲሦች ውስጥ ነብዩ (ﷺ) ሶላት ውስጥ ሆነው ዓኢሻን መንካታቸው ንክኪው ውዱእ አፍራሽ እንዳልሆነ ያሳያል።
♻️ ብዥታ፦
ሻፊዒያዎች ግን እጅ አይሰጡም። "ምናልባት ከቀጥተኛ አካላዊ ንክኪ የሚጠበቅ ነገር (ጨርቅ) ላይስ ቢሆን የነኳት?" ይላሉ። ሸውካኒይ በዚህ ላይ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፦ "ይሄ አጉል መድረቅረቅና ግልፅ ተቃርኖ ያለበት አረዳድ ነው።"
4ኛ፦ አሁንም እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፦
4- أن النبي ﷺ قَبَّلَ امْرَأَةً مِنْ نِسَائِهِ ثُمَّ خَرَجَ إِلَى الصَّلَاةِ وَلَمْ يَتَوَضَّأْ
"ነብዩ (ﷺ) ከሴቶቻቸው አንዷን ከሳሙ በኋላ ከዚያ ለሶላት ወጡ። ውዱእ አላደረጉም።"
ይህንን መረጃ በርካቶች ከሰነድ አንፃር ደካማ ነው ሲሉ ኢብኑ ጀሪር፣ ኢብኑ ዐብዲልበር፣ ዘይለዒይ እና አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። ዶዒፍ ነው የሚሉ አካላትን ውሳኔ ብናስቀድም እንኳ ያሳለፍናቸው መረጃዎች በቂ ናቸው።
✅ አቋም ሶስት ✅
በስሜት ከነካ ውዱእ ይፈርሳል። በስሜት ካልሆነ ግን አይፈርስም የሚል ነው። ይሄ የማሊኪያና የሐናቢላ አቋም ነው። ያደረጉት የቀደሙትን ሁለት አቋሞች መረጃዎች ለማጣጣም መሞከር ነው። ሴትን መንካት ውዱእ ያፈርሳል የሚሉት ወገኖች የሚያቀርቡት መረጃ ተፍሲራቸው ልክ እንዳልሆነ አሳልፈናል። ስለዚህ ይሄኛው ሃሳብ ልክ የሚሆነው የነዚያኞቹ ተፍሲር ልክ ቢሆን ነበር። ተፍሲሩ ልክ ካልሆነ ይሄኛው አካሄድ ውሃ አያነሳም።
ስለዚህ ሁለተኛው ውዱእ አያፈርስም የሚለው አቋም ያለ ተቃርኖ ይቀራል ማለት ነው። ስለሆነም በስሜትም ሆነ ያለ ስሜት፣ አስቦበትም ሆነ በስህተት፣ ቤተሰብም ትሁን ሩቅ (አጅነቢያህ) በየትኛውም ሁኔታ ሴት መንካት ውዱእ አያፈርስም የሚለው አቋም ትክክለኛ ነው ማለት ነው።
♻️ ማሳሰቢያ፦
1- በስሜት የነካ ሰው ፈሳሽ (መዝይ) ከወጣ በዚህን ጊዜ ውዱኡ ይበላሻል።
2- ንክኪው ብቻውን ውዱእ አያፈርስም ማለት ለወንድ አጅነቢያህ ሴትን ወይም ለሴት አጅነቢይ ወንድን መጨበጥ ይቻላል ማለት አይደለም። ክልክል ነው። ያወራነው ስለ ውዱእ ብቻ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 6/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor