Jafer Books 📚


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ
ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok
ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL
ለዌብሳይት www.jaferbooks.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


እግዜር ሸማኔ ነው።
ይሸምናል ሕይወት
ይቋጫል ነጠላ
ዳሩ አይመሰገን እጁ በሽመና
አዳውሮ መተርተር ልማዱ ነውና።

ይህ የእንጉርጉሮ ውዳሴ በሲጋራ ሽታ እና በሁካታ ድብልቅ በተሞላው ጠጅ ቤት ውስጥ በአንድ አዝማሪ ልሳን ለመለኮት የቀረበ ዝማሬ ነው፡፡ አዝማሪው  ከሁካታው በላይ ድምፁን ጎላ አድርጎ እያንጎራጎረ፣ መሰንቆውን እየተጫወተ ዓይኑን ባዶው ቦታ ላይ ያንከራትታል፡፡

ግንባሩን ቁጥር እና አገጩን ከፍ አድርጎ ዙሪያውን ይገረምማል፡፡ በጠጅ ቤቱ ውስጥ የተሰባሰቡት በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች አፍላአፍ ገጥመው ወጋቸውን መጠረቅ ይዘዋል፡፡ ልጅ እግሩ አዝማሪ ከሁሉም በላይ ድምጹን ከፍ አድርጎ ማንጎራሩን ቀጠለ፡፡ ድምፁ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስተጋባ ኃይለኛ ቢሆንም የቅዳሜ ከሰዓቱን የጠጅ ቤት ግለት እና ሁካታ ማሸነፍ የሚችል አልነበረም፡፡

ይህ ልጅ እግር አዝማሪ ስሙ ጥጋቡ ይሰኛል፡፡ በጥንቱ ዘመን ነገሥታቱን ከሚያጫውቱ በትውልድ አዝማሪዎች ከሆኑ ቤተሰቦች ይወለዳል፡፡  አዝማሪዎች ለዘመናት ነገሥታቱን እና መሳፍንቱን የሚያገለግሉ፣ ፖለቲካውን የሚሸረድዱ፣ ለድሃው የልቡን በሰምና ወርቅ በዜማ አዋዝተው የሚናገሩ፣ የሰላ ማኅበረሰባዊ ነቀፌታ የሚሰነዝሩ አስቂኝና ቧልተኞች ብቻ ሳይሆኑ የማኅበረሰብ ሐያሲዎች ነበሩ፡፡

ለዘመናት ለዙፋኑ ቅርብ ሆነው አንዳንድ ጊዜም ከዙፋኑ ተጋፊዎች ጎራ ተሰልፈው የአጫዋችነቱን ሚና ወስደው ባህልን በማሳለጥ፣ በማጎልበት ሂደት ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡

ጥጋቡ ከጠጅ ቤት ወደ ጠጅ ቤት ይንከራተታል፡፡ የሰከሩ ደንበኞች ቢጎነትሉም ወይም ለዜማ ጥሪው ትኩረት ቢነፍጉትም በጽናት አዝማሪነቱን ቀጥሎበታል፡፡ መጀመሪያ የጨዋታ ማሟሻ ይሆነው ዘንድ ወዲያውም የአዝማሪነት ችሎታውን ለመግለጥ የእግዚአብሔርን ኃያልነት፣ የሕይወትን ኃላፊ ጠፊነት የሚያመሰጥር ግጥሙን በዘለሰኛ እንጉርጉሮ ለታዳሚዎቹ አቀረበ፡፡

ቀስ በቀስ ስልቱን እየለወጠ ወደ የፍቅር ዝማሬ፣ ጎንደር ከተማንና ጎንደር ያፈራቻቸውን ታላላቅ ሰዎች የሚያወዳድሱ እዚያው በዚያው የተሰናኙ ግጥምና ዜማዎች ወደ ማቅረብ ተሸጋገረ፡፡ ደንበኞች የቱንም ያህል በሚያቀርባቸው ዜማዎች ቢፈነድቁ አዝማሪው ግን ስሜቱን ገዝቶ መጫወቱን ይቀጥላል፡፡
-
-
-
-

(የፒያሳ ቆሌዎች፣ የአዝማሪው እግዚኦታ፣  ገጽ 27-28)

ተጻፈ፣  በኢተሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር)


ትርጉም፣ በያዕቆብ ብርሃኑና ዓለማየሁ ታዬ




#Quotes

TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


#ሰው_እንዴት_ይሄንን_ሁሉ_መከራ_አልፎ_ሰው_ይሆናል?
***
👉15 ስደተኞች በአንዲት ትንሽ ጀልባ ላይ
👉11 ቀናትን ያለ ምግብና ውሃ በሜዲትራኒያን ባህር እምብርት
👉1 ብቻ ተራፊ ሰው - እርሱም የዚህ ታሪክ ታሪክ ባለቤት ነው!
👉12 ዓመታትን ያለ ፍላጎቱ በትጥቅ ትግል ያባከነበው መሀመድ እንዴት ብቻውን ተረፈ? ምን በልቶ ህይወቱን አቆየ? አሁንስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

“የኢብራሂም አስክሬን የባህሩን ወለል እንደነካ በመጀመሪያ ከውሃው ንቅንቃቄ ጋር አብሮ ወዲያ ወዲህ ይዋልል ጀመር፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ በዝግታ በጀልባዋ ዙሪያ ክብ ሰርቶ ወደነበረበት ተመለሰ፡፡ አሁንም ፍጥነቱን እየጨመረ እንደገና ጀልባዋን ደግሞ ዞራት፡፡ ሁላችንም አስፈሪውን ትርኢት እያስተዋልን መተከዝና መደነቅ ጀመርን፡፡ ኢብራሂም ትቶን ለመሄድ የደፈረ አይመስልም፡፡ ወይንም የእኛንም መጪ እጣፈንታ በቅኔ እያሳየን መሰለን፡፡ ትርዒቱ እጅግ አስፈሪ ነበር፡፡

ልክ እንደ አስማታዊ ነገረ ስራ በጀልባዋ ዙሪያ በተሽከረከረ ቁጥር አይናችንም አስክሬኑን ተከትሎ ይዞራል፡፡ ወርደን እንዳንገፋው አቅም የለንም፡፡ ያለን አማራጭ መጨረሻውንማየት ብቻ ነበረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች የእሽክርክሪት ትርዒቱቀጠለ፡፡ ሁላችንም አዕምሯችን የተነካ መሰለን፡፡ ሳናውቀው እኛንም ያዞረን ጀመር፡፡ ዳንኤል የተሳሰረ አንደበቱን እንደምንም አስገድዶ “ሂድ ኢብሮ! እባክህ ሂድ! በቃ ሂድ… ቻው ወንድሜ!” አለ ከደረቅ ለቅሶ ጋር፡፡

ወዲያው አስክሬኑ የሚዞርበትን ክበብ እያሰፋ ሄዶ ከጀልባዋ መራቅ ጀመረ፡፡ ምህዋሩን እያሰፋ ሄዶ በዝግታ ተሰወረ፡፡ ሁላችንም በሀዘን ተውጠን እስከመጨረሻው በዓይናችን  ሸኘነው፡፡”

በእርግጥ ለማመን ይከብዳል! ብዙዎች ባያምኑም ታሪኩ እውነተኛ ነው። ቢቢሲ፥ ስካይ ኒውስ፥ ዘ ጋርዲያን እና አልጀዚራን ጨምሮ  ከ15 በላይ ዓለማቀፍ ሚድያዎች የመሀመድን ታሪክ ዘግበውት ዓለም ተነጋግሮበታል። የሰው ልጅ ምንያህል ብርቱ ፍጥረት እንደሆነ ገልቦ ያሳያል።

ድካምና ብርታት፥ ውሳኔናጸጸት፥ ሞትና ትንሳኤ የተዋሃዱበት ታሪክ ነው። የጦርነት፥ የትጥቅ ትግል፥ የስደት፥ የሀገር ክህደት፥ የይቅርታ፥ የእንደገና ጅማሬ ታሪኮች በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ያልፋሉ። ሰው እንዴት ይሄንን ሁሉ መከራ አልፎ ሰው ይሆናል?

የሰሙት እንባቸውን በመዳፋቸው ሰፍረዋል። ያዘኑለትም ያዘኑበትም ነበሩ። የፈረዱለትም ፈረዱበትም ብዙ ናቸው። እሱ ግን “ወደ ፈተና አታግባኝ” በሉ ይላል።  ስጋ ሲፈተን፥ ነፍስ ከሞት ጋር ስትጋፈጥ ሁሉም ሰው ሁሉንም ያደርጋልና “አትፍረድ” ባይ ነው።

ዓለምን ያነጋገረውና ያስደነገጠው የመሐመድ ዓደም ኦጋ ታሪክ በሆሊውድ ደረጃ በፊልም ከመውጣቱ በፊት “አትፍረድ” በሚል ርዕስ በአማርኛ ለአንባቢያን ቀርቧል።




አዲስ መጽሐፍ ።

እመጓ፣ ዝጎራ ፣ መርበብት ፣ ሰበዝ ፣ ሚተራሊዮን በተሰኙት መጻሕፍቱ እጅግ ዝናን ያተረፈው ደራሲና ተመራማሪ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ " ፍካሬ " የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ያበቃል ::


#4ኪሎ_ቅርንጫፍ
አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ፊትለፊት ድንቅ ስራ ህንፃ ስር
ይምጡና ይጎብኙን!!
TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


#Quotes

TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


ምህላ ፩

ሁሉም ነገር የድምጽና የንዝረት ውጤት የመሆኑን ነገር እያሰላሰልኩ በደንብ አየር ሳብኩና ደወሉንም ደወልኩት፡፡ ከመቅደሱ የሚወጣው የደወል ድምጽ በመንደሯ በሙሉ ተሰማ፡፡ በጫካው ውስጥ የከተመች ታላቂቱ የገዴ ወፍ ለደወል ድምፁ ምላሽ ሠጠች፡፡ ከዚህች የተቀደሰች ገዴ ወፍ የወጣው ድምጽ ግን የሕማም፣ የድንጋጤ አይመስልም፡፡ የመንደሯ ውሾች የደወል ድምጹን መስተጋባት ተከትሎ በደስታ ጮኹ፡፡ የደወሉ ድምጽ በተራሮች ገመገም አማካኝነት ከተስተጋባ በኋላ ወደ ሞገድ ተለውጦ ከሰመ፡፡ ደወሉን ደግሜ  ደጋግሜ  ደወልኩት፡፡ ጊዜውን ጠብቆ ደወሉን መደወል ልጅ እያለሁ ዘወትር የማከናውነው ተግባር ነበር፡፡ የደወሉ ድምጽ ንዝረት ሰውነቴንም በረቂቅ ሁኔታ ይንጠው ጀመር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ የደወል ድምጽ ልክፍት ጎንደር በሕዝብ መሃል ስረማመድ፣ በማንቸስተር ከተማ የደቡብ ሕንድን ምግብ ቤቶች ስታደም፣ ወይ በሰንሪ ቹኦ የባቡር ጣቢያ በኩል ሳልፍ ይይዘኛል፡፡ ድምፁ ቀጭንና ሰርሳሪ ነው፡፡ ግን ደግሞ  የለምለም አረንጓዴ ሸለቆን ሽታ፣ የትኩስ አፈርን ጠረን፣ የወንዝ ዳርን መዓዛ እየነዛ ያልፋል፡፡ ገመዱን በሁለት እጆቼ ይዤ ደወሉን የደወልኩበት የገመዱ የመሰርሰር ስሜት እጆቼ ላይ ይሰማኛል፡፡

ልጅ እያለሁ ሴት አያቴ ስለ ወንድ ቅድመ አያቴ የነገረችኝ የሆነ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡ አያቴ በሁሉም የሚወደድ ንቁ መነኩሴ ነበር አሉ፡፡ የዚህ ቅድመ አያቴ ታላቅ ወንድም  ጃፓን ከሩሲያ ጋር ባደረገችው  ጦርነት ተገደለ፡፡ ቀድሞ  ባይሞት ኖሮ ከቅድመ አያቴ ይልቅ የቤተመቅሱ ጠባቂ የሚሆነው እርሱ ነበር፡፡ ልክ ከምሽግ አንገቱን ብቅ ሲያደርግ ጭንቅላቱን እንደተመታ ይነገራል፡፡ እና የቤተ መቅደሱን አገልጋይነት የተቀበለው ቅድመ አያቴ የነተበ የምንኩስና ልብሱን ለብሶ በባዶ እግሩ እየተመላለሰ በአካባቢው በእጅጉ የሚወደደውን ሱትራ (የዘወትር ጸሎት) ያነበንብ ነበር፡፡ ወንዙን ሲሻገር የጸሎት መነባበንቡን አቁሞ  ከንጹሁ  ውኃ ጠጥቶ ወደ ሌላኛው  አጎራባች  ጎጥ  ይጓዛል፡፡

በአብዛኛው በሚሄድባቸው ቦታዎች የሚያከናውናቸው የጸሎተ ፍታት ሥርዓቶች እስከ እኩለ ሌሊት ያቆዩታል፡፡ በውድቅት ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ ግን ብቻውን አይመጣም፡፡ ያማ  እያለ የሚጠራውን ከውሻ ትንሽ ከፍ ያለ እንሰሳ አስከትሎ ይመጣል፡፡ ያማ በጃፓንኛ ተራራ ማለት ነው፡፡ አያቴ እንደነገረችኝ እንሰሳው አስፈሪ ጭራቅ የሚያስመስለው  ከአፉ እስከ ጆሮው የዘለቀ ከባድ ሽንትር ጠባሳ አለበት፡፡ ቀስ በቀስ እንሳሰው  ቅድመ አያቴን ተለማምዶ ቤተኛ ሆነ፡፡ ቅድመ አያቴ እንሰሳውን ሲጠራው ራሱ ‹ያ› የምትለው ቃል ላይ ጠንከር ያለ አጽዕኖት ይሰጣል፡፡ ይህ እንሰሳ የዱር ውሻ ዝርያ ይሁን የተኩላ የሚታወቅ ነበር አልነበረም፡፡

የቅድመ አያቴንና የያማን ታሪክ የነገረችኝ አያቴ በአሁኑ ጊዜ አልጋ ላይ ውላ ኑሮዋ በአዛውንቶች መጦሪያ ውስጥ ነው፡፡ የመጀመሪያ ወንድ ልጇን አባቴን እንኳን አታስታውሰውም፡፡ የቅርብ ወዳጇ የሆነች እኩያዋ ሴት ግን አሁንም በመንደራቸው አቅራቢያ ትኖራለች፡፡ የአዛውንትነት ዕድሜ ላይ ብትሆንም አሁንም  በእርሻ ማሳዎች ላይ አንዳንድ ሥራዎችን ታከናውናለች፡፡ ይህችን ሴት ስለ ያማ  ታሪክ የምታውቀው ነገር ካለ ብጠይቃት ምንም የምታስታውሰው ነገር እንደሌለ ነገረችኝ፡፡ ያኔ ቅድመ አያቴ ለአገልግሎት ወደ አጎራባች መንደሮች ይረማመድበት የነበረው ተራራ ምናልባት ዛሬ ለኮንክሪት የሚያገለግል ማዕድን ፍለጋ በግራቨል ማይኒንግ  የሚቆፈረው  ተራራ  ሳይሆን አይቀርም፡፡

ቅድመ አያቴ አንድ በጣም ያረጀ እና የደበዘዘ ፎቶ ብቻ አለው፡፡ ፎቶው ወደ ፓስፊክ ለጦርነት የዘመተውን የጦር ጓድ ተከትሎ የቤተመቅደሱ ደወልም አብሮ ሲዘምት ለማስታወሻ የተነሳ ነበር፡፡ ከደወሉ ጎን የቤተመቅደሱ ግድግዳ ላይ የተጻፉ የቡድሂስት ጽህፈቶችና ምልክቶችም አብረው ይታያሉ፡፡ ከደወሉ ፊት ለፊት ሁለት መነኮሳት ቆመዋል፡፡ አንደኛው ቅድመ አያቴ ሲሆን ሁለተኛው ከአጎራባች ቤተ መቅደስ የመጡ መነኩሴ ናቸው፡፡ እኒህ ጽኑ እና ኃያል የሚመስሉ ውብ የመነኮሳት አልባሳትን የተጎናጸፉ ግዙፍ ሰው አሮጌ የተሸበሸበ የመነኩሴ አልባሱን ለብሶ አንጎንብሶ የተዳከሙ የሚመስሉ ዓይኖቹን ሩቅ ተክሎ ከቆመው አያቴ ጎን ተሰትረዋል፡፡

በፎቶው ላይ እንደማየው የቅድመ አያቴ የመኖር ምኞት የሰለለ የነበረ ይመስላል፡፡ እናም ጦርነቱ ከማብቃት ጥቂት ዓመታት በፊት ድንገት ተዝለፍልፎ ወደቀና ሞተ፡፡ እንግዲህ ይህ ፎቶ ምናልባት በዕድሜው አመሻሽ የተነሳ መሆን አለበት፡፡ ፎቶው ላይ ከደወሉ ጀርባ የእርሱ ጎረቤት የነበሩ ሀምሳ ያህል መንደርተኞች ይታያሉ፡፡ በልጅነቴ አንዳንዶቹን ደርሼባቸዋለሁ፡፡ በዚያ ጊዜ እኔ ሳውቃቸው ፎቶው ላይ የሚታየው ወዘናቸው ተሟጧል፡፡ በእርግጥ  ዘመኑ ብዙ ነበርና እንዲያ ቢሆን የሚገርም  አይሆንም፡፡

በዚህ ፎቶ ላይ የምትታየው  ሴት የሴት አያቴ ጓደኛ ናት፡፡ አያቴ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለች እዚህች ወዳጇ ቤት ትመላለስ ነበር፡፡ ሴት አያቴ በሜጂ ዘመን ነበር የተወለደችው፡፡ ስሟ  ዩሳን ይባላል፡፡ አንድ ምሽት ለቤተ መቅደስ በስለት የተሰጠሁ ልጅ ስለመሆኔ ነገረችኝ፡፡ በእያንዳንዱ ምሽት የቤተመቅደሱን ደወል ስሰማ  አንገቴን እሰብራለሁ፡፡ አንገቴን ድፍቼ ዓይኖቼን ጨፍኜ ድምፁ ወደሚመጣበት ዞሬ እጆቼን ለፀሎት አገጣጥሜ ጸሎቴን አነበንባለሁ፡፡ ልጅ  እያለሁ  ከእርጅና የተነሳ ፊቷ የተሰረጎደ አንዲት አሮጊት ሴት የደወሉን ድምጽ ተከትላ በመጸለይዋ ጸሎቷ እንደሚሰምር በማሰብ ወደ ደወል ድምጹ ዞራ ስትጸልይ ማየቴን አስታውሳለሁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ የቤተመቅደሳችን ደወል ተራራ፣ ወንዝ፣ ሀይቅ፣ ውቅያኖስ አቆራርጠው ተሸክመውት ወስደው አቅልጠውት ሰዎችን ለመግደል ለጦር መሳሪያነት አውለውት ይሆን እያልኩ አስባለሁ፡፡ የፓስፊክ ጦርነት ካበቃ በኋላ ለቤተመቅደሳችን አዲስ ደወል ተሰርቶ መጣ፡፡ ደግሜ ደጋግሜ የደወልኩት፣ የተወዳጀሁት፣ አብሬው ማለቂያ የሌለውን የሙሪዮጁኮ ሱትራን ያነበነብኩበት ይህ ደወል እንደ ቀደመው ደወል ዓይነት ዕጣ እንዳይገጥመው  ምኞቴ ነው፡፡

.
.
.

(የፒያሳ ቆሌዎች ገጽ 58-61 )




#Quotes

TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


ከ "ውብ" ገጾች!

"ትልቁ ፈተና ሰው ሁኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጅ!"

“ዓላማ ያለው ሰው የሚታገሰው ራሱ ስለፈለገ ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ስለሆነ ነው!”

"በህይወታችን ውድ የሚመስለን ያለን ሳይሆን ያጣነው የሌለን ነገር ነው!"

“መጀመሪያ ራስሽን ውደጂው። ራሱን የገዛ፣ የወደደና ያሸነፈ ሰው ዓለምን መውደድ፣ ማሸነፍና መግዛት ይችላል። “

“ሁሌም ሰዎች በሚያገኙት መልካም ነገር ተደሰት እንጂ አትከፋ።”

“ስትወድ እንደዚህ ነው። የወደድከው ምን ያህል በዳይ ቢሆን ምን ያህል መጥፎ ፊት ቢኖረው ነገ የተሻለ እንዲሆንለት ከፊቱ ትቀድማለህ።”


#Quotes

TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


New book alert.


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


#Quotes

TelegramFacebookInstagramTiktokWebsite


New book ALERT

" MARVEL SCHOLASTIC APTITUDE TEST "
FOR GRADE 11-12


Features:

Section by section explanations EXAM SPECIFIC

Example with detailed UP-TO-DATE

Lucid presentation concepts EASY TO USE

Solved problems (2003 E.C-2016E. C)ETHIOPIAN UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION

Exercises with answers
E 5 Model exams with answers
Letter Writing.

Common Interview Questions and Answers.


Features:
Section by section explanations EXAM SPECIFIC
Example with detailed UP-TO-DATE
Lucid presentation concepts EASY TO USE
Solved problems (2003 E.C-2016E. C)ETHIOPIAN UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION
Exercises with answers
E 5 Model exams with answers
Letter Writing.
Common Interview Questions and Answers.


በደሴ አዳም የተደረሰው " ውብ " የተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ ይገኛል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት !


ተወዳጁን " A LITTLE LIFE " መጽሐፍ አስገብተናል ::

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.