መሐርኒ ድንግል


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በመለከተ ስለ ገድለ ቅዱሳን፣ መንፈሳዊ ጥያቄ ፣ ምክረ አበው እና የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ወደ እናንተ እናደርሳለን!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜




በቅርቡ ምስባክ ከዕለቱ ቀደም ብለን እንለቃለን ይጠብቁን !


"ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህ እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በብልህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ  ሳይሆን በሀሳብህ ላይ አሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡክ አድርግ።"

[ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ]
   
@mehereni_dngl




† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት" እና "ቅዱስ አቡሊዲስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

+ ቅድስት ማርያም +

=>ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለን በስምዖን ቤት የመድኃኔ ዓለምን እግር በእንባዋ አጥባለች:: በፀጉሯም አብሳ የ300 ብር ሽቱ ቀብታዋለች:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የቀደመ ኀጢአቷን ይቅር ብሎ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: (ሉቃ. 7:36-50)

+ስለዚህች ቅድስት ሙሉ ታሪክ:-
1.ትርጉዋሜ ወንጌልን
2.ተአምረ ኢየሱስን
3.ስንክሳርን እና
4.መጽሐፈ ግንዘትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል::

+እንት ዕፍረት (ባለ ሽቱዋ ማለት ነው) ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን (በዘመነ ስብከቱ) የነበረችና ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ሴት ነበረች:: ግን መልክ የመልካም ነገሮች ምንጭ ሲሆን አይታይም::

+በመልካቸው ማማር የጠፉና ያጠፉ ብዙ ሴቶችን ዓለማችን አስተናግዳለች:: ከክሊዎፓትራ እስከ ዘመናችን "ሞዴል" ነን ባዮች : እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ የሰይጣን መደሰቻ : የገሃነም መንገድ አድርገውት ማየት (መስማት) እጅግ ያሳዝናል::

+በአንጻሩ ደግሞ ብዙዎችን ያስደመመ መልካቸውን ንቀው : ሰማያዊ ሙሽርነትን የመረጡትን ቅዱሳቱን:- አርሴማን : ቴክላን : ጤቅላን : መሪናን : ጣጡስን : ሔራኒን : ኢራኒን : አትናስያን : ሶፍያን : ኢላርያን . . . ስናስብ ደስ ይለናል:: ዛሬም ጌታ በሚያውቀው ብዙ እናቶቻችን (እህቶቻችንም) ተመሳሳዩን በጐ ጐዳና መርጠው እየተጉዋዙ መሆኑን እናውቃለን::

+ቅድስት ማርያምም ከፈጣሪዋ በተሰጣት ቁንጅና ክፋትን ትሠራ ዘንድ ሰይጣን ሲያገብራት "እሺ" ብላ የእሱ ወጥመድ ልትሆን ተራመደች:: ለዘመናትም ዓይነ-ዘማ : ልበ-ስስ የሆኑ ወንዶችን ወደ ኃጢአት ጐዳና ማረከች::

+ለመልኩዋ ከነበራች ስስት የተነሳም ቶሎ ቶሎ ራሷን በመጽሔት (መስታውት ማለት ነው) ትመለከት ነበር:: መቼም አምላካችን ለሁሉም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና (የሚያስተውለው ቢገኝ) ለማርያም ጥሪውን ላከላት:: ጥሪው ግን በስብከት : በመዝሙር : በመጽሐፍ . . . አልነበረም::

+እንዳስለመደች ውበቷን ለመመልከት መስታውት ፊት ቆማ የራሷን ጸጉር : ግንባር : ዐይን : አፍንጫ : ጥርስ . . . እየተመለከተች ተደመመች:: ወዲያው ግን ይህ አካል አፈር እንደሚበላው የሚያስብ ልቡና መንፈስ ቅዱስ አምጥቶባት በጣም አዘነች:: የመኖር ተስፋዋ እንዳይቆረጥ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዜና ሰማች::

+መወሰን ነበረባትና ከሞት ወደ ሕይወት : ከጨለማ ወደ ብርሃን ልትሔድ ቆረጠች:: በአምላኩዋ ፊት የሚቀርቡም 3 ስጦታዎችን አዘጋጀች:: ሰይጣን ሊያጣት አልፈለገምና ወደ ክርስቶስ እንዳትደርስስ ብዙ መሰናክልን ፈጠረባት:: ግን ውሳኔዋ የእውነት ነበርና እያሳፈረችው ወደ አምላኩዋ ገሰገሰች::

+የስምዖን ዘለምጽ በረኞችም ሊያስቀሰሯት አልተቻላቸውም:: ወደ ውስጥ ዘልቃ የያዘችውን ሁሉ ለመድኃኒታችን ሰዋች::
1.ከውስጧ እንባዋን:
2.ከአካሏ ጸጉሯን:
3.ከንብረቷ ውድ የሆነውን ሽቱ አቀረበች::

+ብዙ ወዳለችና ብዙ ኃጢአቷ ተሠርዮ ቅድስት እናታችን ሆነች:: ብዙ አዝማናትን ከሐዋርያት ጋር አገልግላም በዚህች ቀን ዐርፋለች::

+ ቅዱስ አቡሊዲስ መምህረ ኩሉ ዓለም +

=>የዓለም ሁሉ መምህር:
- ባለ ብዙ ድርሳንና ተግሣጽ:
- የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ:
- 38 ሕግጋትን የደነገገ:
- ስለ ቀናች እምነት የተጋደለ:
- መራራ ሞትን በደስታ የተቀበለ:
- የቀደመችዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረና:
- ሐዋርያትን የመሰለ አባት ነው::

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ያበራው ይሀን ኮከብ ካቶሊካውያን ክደውታል:: እነርሱ "አቡሊዲስ የሚባል ዻዻስ አልነበረም" ቢሉም ምክንያታቸው ግን ከሰይጣን ነው:: ሃይማኖታቸውን ከመለወጣቸው 250 ዓመታት በፊት ስለተናገረባቸውና አንድ ባሕርይን ስላስተማረ መሆኑን ዓለም ያውቃል::

+አባታችን ቅዱስ አቡሊዲስ የተገደለ የካቲት 5 ሲሆን የካቲት 6 ሥጋው የተገኘበት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ከቅድስት ማርያም ንስሃዋን : ከአባ አቡሊዲስ ምሥጢረ ቅድስናውን ያድለን::

=>የካቲት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
2.የዓለም ኁሉ መምሕር ቅዱስ አቡሊዲስ (ብዙ መንፈሳዊ ድርሳናትን የደረሰ ሊቀ ዻዻስና ሰማዕት)
3.ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ (ሰማዕታት)
4.ቅድስት አትናስያና 3ቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ቴዎድራ : ቴዎፍናና ቴዎዶክስያ)

ወርኀዊ በዓላት


1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>ከበረከተ ቅዱሳን ይክፈለን::

+ . . . አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም:: እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች:: ስለዚህ እልሃለሁ : እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአቷ ተሰርዮላታል:: ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል:: እርስዋንም:- 'ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል' አላት:: ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው:- 'ኃጢአትን እንኩዋ የሚያስተሰርይ ይህ ማነው' ይሉ ጀመር:: ሴቲቱንም:- 'እምነትሽ አድኖሻል: በሰላም ሒጂ' አላት:: +"+ (ሉቃ. 7:46)

[ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ]

@mehereni_dngl




† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

† አክርጵዮስ †

በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።

በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

" ቅዱስ ዕብሎይ "

=>አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ40 ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ40 ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

> (የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት)

" አባ ብሶይ (ዼጥሮስ) "

=>ብሶይ (ቢሾይ) በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም
ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ
ቅዱሳን (ከገዳማውያኑ) አንዱ የሆነው አባ ብሶይም
(አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል) የዘመነ ጻድቃን ፍሬ
ነው::

+ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን
ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች
ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን
በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት
እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::

+ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ :
ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው
ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ
በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል
ተከልለዋል::

+አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና
ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ
ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ
የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ
መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::

+የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን
ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ (አጋጣሚ) ነው::
ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ
ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት (ወደ ጸበሉ)
እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር
ይመስገን::

+ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ
ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ::
ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር
ፍጹም አስደነገጠው::

መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ
አለቀሰ::

+ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ4 ሲቆራርጣቸው ስላየ
ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ
እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ
ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ
አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::

+እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም
እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ
አስቄጥስ (ግብጽ) ለ38 ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ
በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::

+ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ 30 ቀን ያለ እህል ውሃ
ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም::
ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን
ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው
የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::

+ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና
ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ
ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት :
ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተቀብሏል::

አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !

=>የካቲት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
2.ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
3.አባ አክርዽዮስ
4."49" አረጋውያን ሰማዕታት (ፍልሠታቸው)
5.ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
6.አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

➡️ አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::

=>+"+ መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)

[ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ]

@mehereni_dngl




ፀሎት



"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድጸልይ ያስገድደናል።"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ለተዋህዶ ልጆች #share አርጉ

   
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl


በየቀኑ ገድለ ቅዱሳን ወደ እርሶ እናደርሳለን !




† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ †

† ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት (በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ) በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: (ሐዋ. 11:27)

በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው (መቃብሩ) ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች::

የአባታችን በረከት ይደርብን::

የካቲት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
2.አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር

† ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ

† "በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ::
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ::
እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" †
(ሐዋ. ፲፩፥፳፯)

† "ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን::" †
(ዕብ. ፲፫፥፲፰)

[ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ]

@mehereni_dngl


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አቤቱ ፈጠሪ ሆይ ይቅርበለን ማረን !


Logo  ለ telegram,tik tok,YouTube ለ group ወይም ለ channel  ማሰራት ከፈለጉ ?
በውስጥ መስመር 👉 @nice_creative_bot ያናግሩን !


እደዚህ አይነት አጠር ያለ ምክረ አበው እዳያመልጣቹሁ ለህይወታቹሁ ጠቃሚ ነው አደራ::


✝️✝️በክፉ ምኞት እና ሃሳብ ጊዜ ይህንን ወይም ያንን ውሰድልኝ አትበል ይልቁንም ግን እንዲህ ብለህ ጸልይ አቤቱ ጌታ መድኃኒት እየሱስ ክርስቶስ የነፃነት አምላክ መልሼ እንዳልበድል በአንተ ላይ አግዘኝ✝️✝️

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

@mehereni_dngl


ተመስገን


በሰላም አድረን በሰላም ስለተነሳን ተመስገን

ስንተ ተኝቶ ወደ ማይመለስበት ዓለም ሄዶል
እግዚአብሔር ሆይ ለንስሐ አብቃን

አሁንም በድጋሜ ተመስገን


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እስከዛሬ ለምትጠይቁት ጥያቄ መልስ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.