Merkato Online Services


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


Trusted digital market

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


باب العلم dan repost
በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ተቀርተው ያለቁ 10 ደርሶችን ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ይገኛሉ

🕹 ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ

1 አል ጀዘሪያ الجزرية
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20528

2 " ሪሳለቱል-ሒጃብ  "
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20560

3 የአሕባሾ እምነት በሚዛን ላይ (መግቢያ)
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20573

4 የሰፊነቱን'ነጃት ማብራሪያ
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20686

5 የሰፊነቱስሰላት ማብራሪያ
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20735?single

6-የኡሱል አል-ኢማን(የእምነት መሰረቶች
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20739

7 📚የቁርዓን ተፍሲር ማብራሪያ
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/20771

8 ላሚይ-የቱ ኢብኒል- ወርዲይ
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/22622?single

9 አልኡሱሉ_አሥሠላሣህ 
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/22627

10 አልቀዋዒዱል_አርበዕ 
↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Babul_Et/22656?single


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የወተት ሲኒ
በ 0932889327 ላይ ያገኙናል


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ማይካ ሲኒ የማይሰበር የማይመነችክ በብዛት (ከአንድ ካርቶን ጀምሮ) ለምትፈልጉ በ 0932889327 ላይ ይደውሉልን

https://vm.tiktok.com/ZMryX4Xba/


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የሾርባ ማንኪያ
በብዛት ለምትፈልጉ ብቻ ማለትም ከአንድ ካርቶን ጀምሮ

https://linktr.ee/merkato10


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Coming Soon

Merkato Online Services

Trusted digital market

https://linktr.ee/merkato10


Merkato Online Services

Trusted digital market

https://linktr.ee/merkato10


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
tiktok.com/@merkato.online.se






ሸኽ ሰዒድ ጫሌ

ሸኽ ሰዒድ ጫሌ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ጫሌ በመትባል ቀበሌ ከ1872-1948 ዓም እንደኖሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለአባታቸው ሸህ ኢብራሂም ያሲንና ለእናታቸው ወሮ ዘቡራ ሙሃመድ ብቸኛ ልጅ እንደነበሩና ወላጆቻቸውን በልጅነታቸው በማጣታቸው ሳቢያ የየቲም ልጅ ሁነው ማደጋቸውን የታሪክ ማህደራቸው ያሳያል፡፡


ሸኽ ጫሌ

ሸኽ ጫሌ በርካታ ሊቃውንቶችን ተክተዋል፡፡ ወደ ሰላሳ ማዕከል የከፈቱ ሊቃውንቶችን አፍርተዋል፡፡
ሸኽ ሙሃመድ ዓሚን አላማጣ ፣ ሸኽ ሙሃመድ ሃጂ ፣ ሸኽ ሙሃመድ ሸህና ሸኽ ዓሊይ ዘከሪያ የሚባሉት ከሸኽ ጫሌ ደረሶች ከጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ሸኽ ሙሃመድ ራፊዕ የቀሩባቸው ሸኽ ዑስማን ቂልጦ ሸኽ ጫሌ ላይ ነው የቀሩት፡፡


‹‹ፈሩትና አስፈራቸው
፤ ››

ሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ

በነሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ ዘመን እንዲህ ሆነ ፤ እርሳቸውን ጨምሮ እነ ሀጅ ራፊዕ ፣ ሸኽ ሰይድ ሙሀመድ ሳዲቅና ሌሎችም ታላላቅ ዐሊሞች በተገኙበት አንድ ለቅሶ ላይ የዳንዮች ልጅ ሸኽ አህመድ በሻሻ ሲገቡ በወግ ደምቆ የነበረው ድንኳን ፣ እንዳትተነፍሱ የተባለ ይመስል በአንድ ጊዜ ጸጥ ረጭ አለ ፡፡

እርሳቸው ዱዐ አድርገውና
ሀዘንተኞችን አጫውተው ፣ ፈቃድ ጠይቀው ገና እግራቸው ከድንኳኑ እንደወጣ ሰዎች መተንፈስ ጀመሩ ፡፡ የተቋረጡ ወጎች ቀጠሉ ፡፡ ሁኔታውን በትዝብት ሲከታተሉ የነበሩት ሀጅ
ሙሀመድ ወሌ ፡- «አሁን ማን ዝም በሉ ብሎን ነው እርሳቸው ሲገቡ ለመተንፈስ እንኳ
ያልደፈርነው?» በማለት በግርምት ጠየቁ ፡፡ የሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ መልስ ጥበብ አዘል
ነበር ፡፡ « ፈሩትና አስፈራቸው » አሉ ፡፡

አዎ ፣ አላህን የፈራ ሁሉም ይፈራዋል ፤ የአላህን ትእዛዝ ያከበረ ሁሉም ያከብረዋል ፡፡
ዑለሞቻችን በየማህበረሰቦቻቸው ዘንድ ያተረፉት ክብር አላህን የመፍራታቸው ውጤት
እንደሆነ ጥርጥር የለውም ፡፡

ከዚህ ውጭ ሌላ ምን ትርጉም ሊሰጠው ይችላል ?
መሻኢኾችን በእጅጉ የሚያከብረው ክርስቲያን ማህበረሰብ ተራውን ሙስሊምም ከልብ ያምን ነበር ፡፡ ከርሱ ዘንድ አደራ ያስቀምጣል ፡፡ «ሙስሊም አይዋሽም ፤ አደራ አያጎድልም
፤ ቃሉን አይበላም » የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ክርስቲያን ማህበረሰብ የዘመናት አምነት
ነበር ፡፡

ሙስሊም ዋሸ ፣ ቃሉን አጠፈ…ማለት ለአገሬ ክርስቲያን 8ኛው ሺ ደረሰ ፤ ዘመን ጠለሸ ፤
ጊዜ ተበላሸ ማለት ነው ፡፡

ይህን ዕምነቱን ከገለጸባቸው ሥነ-ቃሎች መካከል አንደኛው ፡-
«እስላም ካበለ ቀኑ ዘነበለ» ይላል ፡፡ ‹‹ሙስሊም ከዋሸ ዘመን ተበላሸ›› ማለት ነው ፡፡

የጥንቶቹ ሙስሊሞች በሌላው ወገን ዘንድ የነበራቸውን መታመን የጥንቱ የጎንደር አዝማሪ
በግጥሞቹ እንዲህ ገልጾታል ፡-

እስላም አልኩሽ እንጅ እጁ የሚታመን ፤
ሸማኔማ ሞልቷል ደግሞ ለመሸመን፤

ከኑረዲን ዒሳ ‹‹የባንዴራ ታሪክ›› ግጥም የተቀነጨበች ፡፡

በዳኖች ዘመን ዑለሞች እስልምናን በወጉ ተገበሩ ፤ እንዲህም ገዘፉ ፤ ህዝባቸውንም
አስተምረውና አስተግብረውም አስከበሩ ፡፡ ያን የማህበረሰባችንን ገጽታ ፣ ያን የታሪካችንን
ከፍታ እንዴት እንመልሰው ?
ሚስጥሩን ሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ በጥቂት ቃላት አጠቃለውታል ፡-

‹‹ፈሩትና አስፈራቸው
፤ ›› አላህን ፈርተን ፣ ትዕዛዙን አክብረን የምንከበር ያድርገን ፡፡

ታሪካችንን የመረዳት ጥበብም ይስጠን ፡፡ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እንዳሉት፡- ‹‹ታሪኩን የማያከብር ትውልድ ታሪክ አይሰራምና›› ታሪካችንን አክብረን ታሪክ ለመሥራት ያብቃን ፡፡ ወይም በኔ መረዳት ፡-

‹‹ትላንት የሌለው ነገ የለውምና›› ነጋችን እንዲያምር ትላንታችንን በወጉ አላህ ያሳውቀን

Copy

@ethio_mus


ምን ትወዳለህ አለው አንዱን

"ትንሽ ወሬ ብዙ ስራ"

ብሎ መለሰ


🎈ዒድ ሙባረክ 🎈
«ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል»።


🍁ሸህ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢቢ

→ክፍል-1

መጅሊስን ያቋቋሙት ሼህ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢቢ ልጃቸውን ደርግ ገድሎባቸዋል ። ግን
እሳቸው ከመንግስቱ ጎን ይቀመጣሉ ለምን ይሆን

ጋዜጠኛ Zekeriya
Mohammed


አላህ በጀነቱል ፊርደውስ ያኑራቸውና ታላቁ አሊም ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፣ በደርግ
ሥርዓት የቀይ ሽብር ዘመቻ ልጃቸው ተገድሎባቸዋል። የልጃቸውን አስከሬን ደግሞ
እግቢያቸው በር ላይ ነበር የጣሉላቸው። በዚህም ምክንያት ሐጅ ሳኒ ዕድሜ ልካቸውን
ግቢያቸው ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በጠባቧ በር ነበር የሚጠቀሙት። የልጃቸው አስከሬን የተጣለበትን ቦታ በእግራቸውም ሆነ በመኪና አይሻገሩትም ነበር። ሐዘናቸው ቀላል አልነበረም።

ከዚህ በመነሳት የቅርብ ወዳጃቸው ሐጅ በሽር ዳውድ (አላህ የጀነት ያድርጋቸው) አንድ ቀን ለሐጅ ሙሐመድ ሳኒ፣ "ሐጂ፣ ለምንድነው ከልጅዎ ገዳይ (ከመንግስቱ ኃ/ማርያም) ጎን
የሚቀመጡት? … ሰው ምን ይልኋል?!" ሲሉ በግሳፄ መልክ ጠየቋቸው

የሐጅ ሙሐመድ ሳኒ መልስ

"በእኔ እዚያ መቀመጥ ሰበብ፣ አላህ ለኢትዮጵያ ሙስሊም መልካም ነገር ቢያመጣለት ብዬ እንጂ፣ ሌላ ምን እፈልግ ኖሯል?!" የሚል ነበር።

ይቀጥላል...


ይህን ፒቲሺን በመሙላት የእስራዔልን ወረራ በመቃወም ከፍልስጤም ወንድሞቻችን ጎን እንቁም‼

አሁን 406, 600 ደርሷል። የሚያስፈልገው 500,000 ፊርማ ነው።
ለሌሎችም ሼር እናድርገው!
👇👇👇
http://chng.it/RpmK5yWXDd


🍀ሸይኽ ሰይድ ኢብራሒም ጫሌ ረሂመሁሏህ
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂

→ክፍል ሁለት

ሐበሻ የርሳቸው አይነት በጣት የሚቆጠሩ እንጂ አልተቸረችም ቢባል ማጋነን አይሆንም። እስኪ ስለሳቸው አንድ ወንድም የከተበውን ላካፍላችሁ:

የሼህ ጫሌ አዋቂና ሊቅነት ፤ በአማርኛ የመራቀቅ አቅም ፤ ገጣሚነት ፤
በግጥሞች ላይ የሚታየዉ ሀሳብና አተያይን የመሻትና የማክበር ፤ የበሰሉ መልዕክቶችና
ያልተደዘደዙ ቃላቶች ተሰባጥረዉ ያለበሷቸዉ የገጣሚነት ግርማ ሞገስ እንዲሁም ለዚች
አለም የነበራቸዉ ግድ-የለሽነትና ሁለ ነገራቸዉ ተደማምረዉ ቀልባችንን በናፍቆት እንጥልጥል ያደርጓል ፡፡


ሼህ ጫሌ ነፍስን ጥግ ድረስ የማላጋት ሀይል ደራርበዉ ለብሰዋል ። ተአምር ባጀበዉ
ብዕራቸዉ ብዙ ትዝታዎችን ቀስቃሽ ፤ ለነፍስያችን ምግብ እየፈተፈቱ አጉራሽ ፤ ካለፉትም
ከኛም ላይ ሙቶና ደንዞ የነበረዉን የሐቢቢን ፍቅር ከተቀበረበት ምሰዉ ህያዉ ማድረጋቸዉ
በተከሰተልን ጊዜ ፤ የጨለመዉ አስተሳሰባችን ላይ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ተፈትልኮ ወገገን ይዘሩብናል፡፡
የነተበዉ አጥንታችን እንደ ዉሃ ዳር ቄጤማ ይለመልማል ፡፡ተስፋችን
ተንሰራርቶ ይፍረመረማል ፡፡ ድብርታችንን ፀዳላማዉ ስራቸዉ አሙለጭልጮ ፍግምግም
ያደርግልናል ፡፡
.
የሁልጊዜም ንግግራቸዉ ከገዛ እዉነታችን የተቀዳ ነዉና ኪታባቸዉን ባየን ጊዜ ፤ ራሳችንን
ህዝብና ሃገራችንን እየታዘብን እንቆጫኘለን ፤ እንደመማለን እንደገና አስበንም እንተክዛለን ፡፡
በዚህ መሃል ተስፋችን ሊመነምን ሲባጅ ፤ ዳግም የነርሱን ስራ አስተዉሎ ይቆዝማል ፡፡

እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተደራርበዉ ነዉ ፤ ሞተዉ ትዝ የሚሉ ብቻ ሳይሆን ፤ የሚናፈቁም
ያረጋቸው !

━━━━━━━━━━


አርበኛ ወ ብዕረኛው ሸህ
★★★★★★★★★

ሸህ ሰይድ ጫሌ በ1870ዎቹ መጀመሪያዎቹ አካባቢ ከአባታቸው ሸህ ኢብራሂም ያሲን እና እናታቸው ወ/ሮ ዘቡራ ሙሀመድ ይማም ተወለዱ። ሸህ ሰይድ ኢብራሂም ፣ እጅግ ሲበዛ ሊቅ ፣ ፈጣን አእምሮ የነበራቸው እና ከፍተኛ የሆነ የግጥምና የዜማ ችሎታ የነበራቸው ሰው ነበሩ።
እድገታቸው በራስ ወሌ ቤት ከእትየ መነን ጋር ሲሆን በጊዜው ከነበሩ የአካባቢ ገዥዎች ጋር ያደረጉት ትግል ፣ ከጣሊያን ጋር ያደረጉት ትግል እንዲሁም የአረብኛ እና የአጅም ፁሁፎቻቸው ሰርተዋቸው ያለፉት በርካታ ናቸው።
.
በፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግሉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ግለሰብ ሙስሊሞችና ታዋቂ የእስልምና ሊቃውንት ቁጥር እጅግ በጣም በርካታ ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጸሀፍት ስማቸው እስካሁን ተነስቶ ከማያውቁ ሊቃውንት መካከል «ከበላይ ዘለቀ» ጋር በመሆን ጣሊያንን ተዋግተው ያዋጉት ውስጥ «የጫሌው ሸህ ሰይድ ኢብራሂም» የሚጠቀሱ ናቸው።
.
ከጣሊያን ጋር በተደረገ ትግል ጋር ተግባራቸው ጎልቶ መነገር ካለበት የእስልምና ሊቃውንት መካከል የጫሌው ሸህ ሰይድ ኢብራሂም አንዱ ናቸው። እነ ሸህ ጫሌ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያኖች ትኩረት ውስጥ የገቡት ሰዎች ሁሉ ለጣሊያን ገዥዎች እጅ እየነሱ የሚያልፉበት ቦታ ላይ ከበቅሎዋቸው ላይ ሳይወርዱ እና ለጣሊያን ገዢዎች ሳያጎነብሱ በማለፋቸው ነበር።
.
የጣሊያን ገዥዎች «ይህ ሰው ማን ነው እጅ ሳይነሳ የሚያልፈው?» ብለው እንደጠየቁ ከኤርትራ የመጣው ኑራ ሁሴን የሚባለው ባንዳ እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች «ይህ ሰውማ እንኳን እጅ ሊነሳ ዙፋን ለመያዝም ይከጅላል» ማለታቸውን በጊዜው የነበሩ አባቶች ይናገራሉ። ይህ የሸህ ጫሌ ለጣሊያን እጅ ባለመንሳት እና ከበቅሎ ባለመውረድ ያሳዩት ልበ-ሙሉነት እንዲሁም ለራሳቸው እና ለህዝባቸው የነበራቸው ክብር ለጣሊያን ገዥዎች አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ በተደጋጋሚ እንዲገደሉ ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር። ነገር ግን ከነበራቸው ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ተቀባይነት አንፃር እርሳቸውን ይዞ ለመግደል ቀላል ሆኖ አልተገኘም።
.
ይዞ ለመስቀል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን መደበኛ ያልሆኑ ድርድሮች ነበሩ። ሸህ ኦራ የሚባሉት ታላቅ ሊቅ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሸህ ጫሌ ከጣሊያኑ ገዥ ጋር ለመገናኘት እና ለመነጋገር ቀጠሮ ያዙ። በቀጠሮው መሰረት በወሎ ወረባቦ አካባቢ ሲገናኙ ጣሊያናዊው ገዥ ከነ ልጁ እንዲሁም ኤርትራዊው ባንዳ ኑር ሁሴን በተገኙበት ቤት ውስጥ እንዲገኙ ተደረገ። ሸህ ሰይድ ጫሌ ወደ ቤት ሲገቡ ኤርትራዊው ባንዳ ሰይፍ በእጁ ይዞ ከጣሊያናዊው ገዥ ፊት ለፊት ቆሞ ነበር።
.
በግንኙነታቸውም ወቅት የባንዳውን ሁለት እጅ በመያዝ ሰይፉን ከቀሙት በኋላ «ሰው እየያዘልህ ነው የምታርደው በጀግንነት?» ብለውት ከቤት በመውጣት በበቅሏቸው ግቢውን ለቀው ሄዱ።
በወቅቱ ጣላናዋዊ ገዥ እና ባንዳዎቹ በመደናገጣቸው በነበሩበት ቤት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ዝምታ ሰፈነ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የገዥው ልጅ ከበር በመውጣት እርሳቸው በሄዱበት አቅጣጫ ጥይት ቢተኩስም ሳያገኛቸው ቀረ። ይሁንና ሸህ ሰይድ ጫሌ ለፈፀሙት ተግባር እንደምንም ተይዘው እንዲሰቀሉ በድጋሜ አዋጅ ተላለፈ።
.
.
ከዚህ ጊዜ በኋላ የሸህ ጫሌ መልስ ለየት ያለ እና በወቅቱ ሊታሰብ የማይችል ነበር።
ሸህ ሰይድ ኢብራሂም ጫሌ ያላቸውን ከፍተኛ የሆነ የግጥም እና የዜማ ችሎታ በመጠቀም ብዕራቸውን በመምዘዝ ጣሊያንን እና አገዛዙን በይፋ የሚያወግዝ የዱዓ መንዙማ ጻፉ፤ በይፋም አዜሙት።

.

ሸህ ሰይድ ጫሌ መንዙማውን የጻፉት በአረብኛ ቋንቋ ቢሆንም ቢያንስ በዙሪያቸው ያሉ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎቻቸውና በመላ ሀገሪቱ ያሉ በርካታ ሺ የእስልምና ሊቃውንትን ግንዛቤ ለመቀየር የራሱን አስተዋጽኦ እንዳደረገ መገመት ይቻላል።
ከመንዙማው ግጥሞች የተወሰኑትን ስንኞች ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉም ለመመልከት ያክል መንዙማው የሚጀምረው በሚከተለው ርዕስ ነው።
.
.
» ህያው አሸናፊ የሆንከው አምላኬን » እለምንሀለው እንድታስወግደው ጭንቀቴን ስጋቴን
.
በዚህ ርዕስ የሚጀምረው መንዙማ በርካታ ስንኞች ቢኖሩትም ለምሳሌ ያክል በአማርኛ በቀጥታ በመተርጎም እንደሚከተለው ቀርቧል።
.
ከተንኮለኛ በዳይ ካህዲ በዙሪያው ካሉት ቆሻሾች ፍርድ ጠብቀን አላህ ሁላችንንም በአንድ እንደው ተሰብስበው አገሩን ወረሩ አንተን የማይፈሩ ገራፊዎች ሁሉ ስንቱን አቆሰሉ ስንቶቹን ገደሉ በየ አካባቢው ሰው እየሰለሉ በሩቅ ተንተግታጊ ጦር እየሰበቁ በነዚህ መናጦች ስንት ሰዎች አለቁ ስንቶቹ ህፃናት ያለ ወላጅ ቀሩ ስንት የተከበረን አዋርደው ሰቀሉ አገሩን በጉልበት በኃይል እየያዙ ስንት የተከበረን ባሪያ አድርገው ገዙ ወግ ልማዳችንን እያደፈረሱ ካገር ሊያባርሩን ሊገርፉን ተነሱ ወደ ሻም ወደ ሮም እንድንሄድ ደገሱ።
.
.
እነ ሸህ ጫሌ ይህን መንዙማ ግጥም ከሰሩ ከጥቂት ወራት በኋላ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ተጠቃሎ ወጣ።
በዚህ ኪነ-ጥበባዊ መሳሪያቸው በመጠቀም ሰዎችን ከጎናቸው በማሰለፍ ከጠላታቸው ጋር ተዋግተው ለድል መብቃታቸው ሳይዘከር ከተዘነጉ የእስልምና ሊቃውንት ገድል አንዱና ዋነኛው ነበሩ ማለት ይቻላል።
.
- ምንጭ
.
(ቀደምት ኢትዮጵያውያን የእስልምና ሊቃውንት እና ኪናዊ ትውፊቶቻቸው)ን ዋቢ አድርጎ "የኢትዮጵያ ዑለማዎች ታሪክ እና አስተምህሮ" የተሰኘው ገፅ እንዳተተው
🍀🍀🍀


በኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ ዘመን ተኩላዎች ፍየሎችን መብላት አቆሙ ምንድነው ምክንያቱ በማለት እረኞች ከየጫካው እየወጡ ይጠይቁ ጀመር

ምክንያቱን በአንድ የታሪክ ጨረፍታ ልዳስላችሁ

የኡመር ሚስት ፋጡማ የቀድሞው መሪ የአብደላህ ኢብኑ መርዋን ልጅ ነበረች አባቷ በተለያዮ ውድ ጌጣጌጦች አስውቧት አምራለች ታዲያ ኡመር ስልጣኑን ሲረከብ ጠራትና እንዲህ አላት
《 አባትሽ የሰጠሽን ጌጥ ለሙስሊሞች ግምጃ ቤት እንመልሳለን ካልሆነ እንለያያለን ስለዚህ አንዱን ምረጪ ጌጥሽን ወይም እኔን》
ፋጡማም
《አንተ የወደድከውን ጀነት እኔ የምጠላ ይመስልሀል አኼራንና ድህነትን መርጬ ካንተ ጋር እኖራለሁ 》 ብላ ጌጧን ሁሉ አውልቃ አስረከበች ቤተ መንግስቱን ሲቀይሩ ኻዲም ስላልነበራቸው ፋጡማ ጭቃ ታቦካለች ኡመር ይለጥፋል
እንዲህ አይነት ፍትህ ነው ተኩላ ፍየልን እንዳይበላ ያደረገው።


ታላቁ የህንድ አክተር ሰልማን ከሃን በአንድ ተወዳጅ የህንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት ነው። በመላው ዓለም የሚገኙ አድናቂና ወዳጆቹ በቀጥታ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ የሚተላለፈውን ይህን ፕሮግራም በጉጉት እየተከታተሉት ሳለ አንድ ያልታሰበ ክስተት ከቴሌቭዥን መስኮቱ ይታይ ጀመር።

ጋዜጠኛው ቃለ መጠይቁን እያደረገ ሳለ የሰላት ሰዓት ደርሶ ከአንድ መስጂድ የአዛን ድምፅ ተሰማ! ይህኔ ሰልማን ቃለ መጠይቁን አቋርጦ ለአዛኑ ክብር ዝምታን መረጠ። አዛኑም እንዳበቃ ሰላቱን ለመስገድ ወደ መስጅድ ከነፈ።
በዚህ የተነሳ የህንድን መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ ለሳምንታት ያህል መነጋገሪያ ሆነ።

የመጣህበት እንዳይጠፋህ የነበርክበትን አትርሳ አይደል የሚባለው ከአድናቂም ከዝናም ከምንም ይሉኝታ ሳይዘው ለጌታው ሱጁድ ሊያደርግ ወደ መስጅድ ሄደ።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

581

obunachilar
Kanal statistikasi