ንባብ ለ ሕይወት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደ አንተ ይመጣሉ። ንባብ ህይወት ይሰጥካል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ብቻ ነው።
ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇
@Nibab_lehiwot
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቅያ ስራ ያዋሩኝ👉 @Tesh5050

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ትግርኛ አትችልም "አባቴ ይሙት !" አለችኝ እየሳቀች። እውይ ጥርሶቿ ታይተው አይጠገቡም። የውበት አምላክ በጥንቃቄ የደረደራቸው የቀይ ባህር ዕንቁዎች ይመስላሉ።

"ይህ ጉሮሮ የሚፍቅ ቋንቋ ! መጓጉጥ ነው። አልኳት
"እንጥላችሁ ስላልተቆረጠ ይሆናል "
"እሰኪ መቶ በይ "
"ሞቶ "
" እስኪ አንተ በይ "
"አንቴ "
" አንቺም አማርኛ አትችይም አባቴ ይሙት " አልኳትና መጠጧን ላመጣላት ሄድኩ።

መጠጧን አመጣሁላትና " ሕራይ ትግርኛ ክትምህርኒ እሺ " ሺ እምበአር ? ጸጋዬ ኃይለማርያም እባላለሁ " አልኳትና መጠጧን ቀምሼ ሰጠኋት። እውነትም ጥሩ መጠጥ ነው።

"በቲቪ አውቅሀለሁ አንተም አማርኛ ታስተምረኛለህ "አለች ፡ ጠጉሯን እየነሰነሰች ፈገግታዋ ይናፍቃል።
" ማን ብዬ ልጥራሽ ሰሜናዊት ጽብቖቲ ?" ብዬ ስሟን ጠየኳት ሳቀችና "ፊያሜታ ጊላይ እባላለሁ " ብላ ስሟን ነገረቺኝ። ስሟ ደንቆኝ ቅንድቤን ከፍና ዝቅ ሳደርግ አይታኝ "ምነው አለች።

" እንግዳ ስም ነው ...."
"የጣሊያን ስም ነው ...."
"ምን ማለት ነው ? "
"ትንሽ ነባልባል ...."

"እውነት አንቺን ከሩቅ መሸሽ ይሻላል "አልኳት "
"ለምን አለችኝ "
" ስምን መላክ ያወጣዋል ይባላል። እንደ ስምሽ ከሆንሽ አደገኛ ነው። በትንሽ ነበልባል ተቃጥሎ ማለቅ ደግ አይደለም። እንደ ስምሽ እንዳልሆንሽ ተስፋ አደርጋለሁ አልኳት።
"ነኝ አባቴ ይሙት "አለች ስቃ"
#ኦሮማይ
#በዓሉ ግርማ


መጋቢት 27/2015 ዓ.ም
==================
የ9 ዓመት ሴት ልጁን የደፈረው አባት በ15 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!!

ነዋሪነቱ በቡታጅራ ከተማ እሪንዛፍ ክ/ከተማ ቀበሌ 04 ልዩ ስሙ ገበያ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው አቶ አክሊሉ ግዛው የ9 ዓመት ዕድሜ ያላትን ታዳጊ ህፃን ልጁ ወላጅ እናቷ አዳሯን ዘመድ ጥየቃ በሄደችበት አጋጣሚ ተጠቅሞ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም በዕለተ ቅዳሜ ለሊት በመድፈሩ በጎረቤት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ምርመራ በመረጃና ማስረጃ በመረጋገጡ ወንጀለኛው እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የቡታጅራ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ወስኗል።

ፍርድ ቤቱ ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው አገልግሎት፤ የህፃናት ጥቃትና አስገድዶ መድፈር ወንጀል በመሆኑ በዚህ ረገድ ከቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት እና ከቡታጅራ ከተማ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት መስራታቸው ህግንና ማስረጃን ተንተርሶ በአጭር ጊዜ ለውሳኔ እንዲበቃ ማስቻሉን የቡታጅራ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ዳኛ አቶ አወቀ ሰይፉ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት የቅጣት ዋንኛ አላማው ማስተማር ፣ ማረምና ሌሎችን እንዲማሩ ማድረግ እንደሆነ በመግለፅ ሁላችንም የሰው ፍጥረት ነንና ህብረተሰቡ ነቅቶ ልጆቹን መጠበቅ እንዳለበትና ድርጊቱ ከተከሰተም ፈጥኖ ለህግና ለፍትህ አካላት መጠቆም እንዳለበት ገልፀዋል።

ከከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጉዳዩን ሲከታተሉ የቆዩት ወ/ሮ ሀና አላምረው እንደተናገሩት ድርጊቱ በተፈፀመ በ4ኛው ቀን ላይ ጎረቤት የልጅቷን ምግብ አለመውስድና አለመጫወት ከሁኔታዋ በመረዳትና በመጠርጠር ጥቆማውን እንዳደረሷቸው ፈጥነው በመድረስና ህፃኗም የምስክርነት ቃልዋን በመስጠቷ ጉዳዩን የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ከከተማው ፖሊስ ጋር ተቀናጅተው በመስራታቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ፍርዱን ሊያገኝ መቻሉን ገልፀዋል።

መረጃው የቡታጅራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው!!


መጋቢት 27/2015 ዓ.ም
==================
የ9 ዓመት ሴት ልጁን የደፈረው አባት በ15 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!!

👇👇👇👇👇
ሶስት ሰዓት ለይ ይጠብቁን

ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈

🗣 @Tesh5050


እኔ #ኢትዮጵያዊያንን_አላምንም!

🗣እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ።
#በጭንብል_ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም #ሰምና_ወርቅ ነው ...

🗣በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት
#መለኪያ የለንም፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን #የግል_ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው #ተንኮል_የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው።

ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው
#መርህ_አንድ ብቻ ነው፤ #የግል_ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው...

🗣ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ
#ህሊናችንን_ቅንጣት_ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል?

🗣ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን፤ የስጋ ዘመድን አይለይም
#ቅናት_ባህላችን ነው።

🗣ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም?

በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው።

በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ፣ ከምቀኝነት፣ ከተንኮል፣ ከቅናት፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!

🗣
#በዓሉ_ግርማ_የቀይ_ኮከብ ጥሪ፥ ገፅ 234


እኔ ኢትዮጵያውያንን አላምንም።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


         
                 
#ስለ_ጊዜ

ኒዉዬርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡

አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን አሪፍ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል።

አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ50 አመቱ ሲምት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሁኖ እስከ 90 ዓመት ይኖራል።

ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ70 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኅላ ቀር አያደርገዉም።

ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡ ፈጣሪ በግዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል ፡፡ ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ! ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን

                       ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉
@Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Ni
bab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈

🗣 @Tesh5050


የሕፃኑ ሙዚቀኛ ማልቀስ ምስል በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በጣም ስሜታዊ ከሆኑት ፎቶግራፎች ውስጥ አንዱ ተመድቧል። ይህ ፎቶ የተነሳው የ12 አመቱ ብራዚላዊ ልጅ (ዲዬጎ ፍራዞ ቱርካቶ) በመምህሩ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ቫዮሊን ሲጫወት ከድህነት እና ወንጀል ያዳነው። በዚህ ምስል ውስጥ የሰው ልጅ በዓለም ላይ በጣም ጠንካራ በሆነ ድምጽ ይናገራል: "በልጅ ውስጥ ፍቅርን እና ደግነትን ያሳድጉ የርህራሄ ዘሮችን ለመዝራት. እና ከዚያ በኋላ ብቻ ታላቅ ስልጣኔን, ታላቅ ሀገርን ይገነባሉ ". ( ፎቶግራፍ አንሺ፡ ማርኮስ ትሪስታኦ )


ባለቤቴ ከአጠገቤ ተኝታለች...
በድንገት የፌስቡክ ማሳወቂያ (notification) ደረሰኝ... ካንዲት ሴት ከእኔ ጋር ጓደኛ እንድትሆነኝ የሚጠይቅ ነበር እኔ ተቀበልኳት።

ቀጥዬም እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩላት
እሷም

3.8k 0 23 20 89

አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከ አማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ። አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል። ልጅም አባቱን ማነው ሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል። አባትም በር ለይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነሱ ናቸው ይለዋል። ልጁም ይገረምና ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል። አባትም የኮረኮሩት ያህል ይስቅና፦
እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም ! ብሎ መለሰለት።
___________________________________

#ደራሲው
( በዓሉ ግርማ )


የምትፈራው የማታውቀውን ነገር ነው!

የሚያስፈራህ ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ ሳይሆን አንተ እንድትፈራ በአዕምሮህ ያመንከው እውነት መስሎ የቀረበ የውሸት ማስረጃ ስለተቀበልክ ነው! በሕይወትህ ምን ያስፈራሃል? የምትፈራው ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ ነው ወይንስ ሌላ? ራስህን ፈትሽ ፍርሃትን ለማሸነፍ ሁለት መንገዶች አሉ አንደኛው የምትፈራውን ነገር አጥናው እወቀው ከዚያም ተጋፈጠው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን

#dawitdreams #dreams #motivation #morning #mindset #fear


• ፍፁም ለመሆን መሞከር-በፍፁም ሊሆን የማይችል ግብ ማስቀመጥ

• ቁርስ መዝለል- መኪናን ያለቤንዚን ለማስነሳት መሞከር እንደማለት ነዉ

• እኔ አልችልም ወይም አልስማማም አለማለት- የማንፈልገዉን ነገር “አልፈልግም” ብሎ አለመናገር ዉስጥን ያደክማል

• በጣም መጨነቅ-በአለም ላይ ያሉ ችግሮችና መጥፎ ነገሮች እኛ ላይ እንደሚሆኑ ማሰብ

• ለመለወጥ አለመፈለግ-ያለንበትን ሁኔታ “ለመለወጥ አልችልም” ብሎ ባሉበት ሁኔታ መኖር


እንባ አምላክ አለው....
እንባ ሲወርድ ውሃ ነው
ሲመለስ ግን እሳት ነው
እንባ ሲወርድ ይበርዳል...ያረፈበትን ግን ያቃጥለዋል እና ሰዎች ሲያለቅሱብህ ፍራ...

ፍርዱን አትችለውምና።

ፈራጅ አትሁኑ።

ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉
@Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Ni
bab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈

🗣 @Tesh5050


" ምን እየተደረገ እንደሆነ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ወሰደብኝ፡፡ ስለመደፈር ሲወራ እሰማለሁ፡፡ አንድ ቀን እኔ ላይ እንደሚደርስ አላስብም ነበር፡፡ ስዞር አፌን ለአፍታ ያክል ለቀቀኝ፡፡ ደግሜ ጮህኩ፡፡ ምን ነበረበት አቢ ቡና ቢጠጣ? ግራ እጁ በትከሻዬ ዞሮ መልሶ አፈነኝ፡፡ በአፍንጫዬ ከላይ ከላይ እተነፍሳለሁ። በቀኝ እጁ ሁለት እጆቼን አስሯል፡፡ በሰውነቱ ከግድግዳው ጋር አጣብቆ ያዘኝ። ሊያጠቃኝ የተዘጋጀ ደም የወጠረው ገላው ቂጤ ላይ ይሰማኛል፡፡ ምን ነበረበት ደስታ ዘመዶቿ ጋ በጠዋት ደርሳ ብትመጣስ? አፉ አንገቴ ላይ ነው። ያለከልካል። የዚህ ልጅ ድፍረቱ ሁለት ነው፡፡ ከግድግዳው ጋር በሰውነቱ አጣብቆ ያዘኝ፡፡ ደፍሮ ቤቴ ይገባል? ግራ እጁ አሁንም አፌን አፍኗል፡፡ ደፍሮስ እንዲህ ያደርገኛል? አየር እያጠረኝ ነው፡፡ በፈጠጠ ዐይኔ በጉንጬ የተደገፍኩት አረንጓዴ የግድግዳ ላይ አፍጥጫለሁ፡፡ ጠረጴዛው ላይ የእናቴ ፎቶ ይታየኛል፡፡ አባዬ ትዝ አለኝ፡፡ ላቤ ችፍ ብሏል፡፡ ልቤ ይደልቃል፡፡ አማራጭ አጥቼ እፈራገጣለሁ፡፡ ቀኝ እጁ እጆቼን ለቆ ወደ ደረቴ መጣ፡፡ የቀኝ ጡቴን በኃይል ጨበጠ፡፡ ሊፈርጥ ሁሉ መሰለኝ፡፡ የታፈነ የሕመም ድምፅ አወጣሁ። "

" መሐረቤን ያያችሁ "
የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ
ሙሉጌታ አለባቸው
ሁለተኛ ዕትም

የአዳም ረታ ዓይነት የአጻጻፍ ስልት ለማንበብ የናፈቃችሁ ተደራሲያን ይኸው አዳም ራሱ አድንቆ የመሰከረለትን መጽሐፍ አንብቡ ::

ጃዕፈር መጻሕፍት

ፎቶ :- Gebrela Shewakena


ነገ ብትሞቱ ምን ታደርጉ ነበር?

ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ200ሺ እስከ 300ሺህ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል። ስለዚህ ነገ ሞት ቢመጣ ሳትሸበር ምን እድርገህ ታልፍ ነበር?

የ21 ቀን ፓራዳይም ሺፍት ስልጠና ለመመዝገብ በ+251938252525 ይደውሉ!
መልካም ቀን ተመኘን!

#dawitdreams #abrshdreams #dreams #life #Ethiopia


ቤንጃሚን ፍራንክሊን በወጣትነቱ ተከራካሪና እዉነቱን በግድ ለማሳመን የሚጥር ሰዉ ነበር።ታዲያ አንድ ቀን ከጓደኞቹ ጋር ሲከራከር አንድ ፌዘኛ ጓደኛዉ እንዲህ አለዉ።
       "ቤን አስቸጋሪ ሰዉ እኮ ነህ።የሚቃወምህን ሰዉ በነገር ጥፊ ታጮለዋለህ።ጥረትህ  የሰዎችን እምነት ለመቀየር ስለሆነ ማንም ሊሰማህ አይፈልግም።እንደዉም እንዳየሁት ከሆነ ጓደኞችህ ተዝናንተው የሚጫወቱት አንተ ሳትኖር ነዉ።እርግጥ ነዉ ብዙ ታዉቃለህ።ስለዚህም አንተን መምከር ያስቸግራል።እንዲያዉም ማንም ሰዉ ምንም ሊያስረዳህ አይሞክርም ምክኒያቱም ሀይለኛ ክርክር እንደሚገጥመዉ አስቀድሞ ያዉቃል።ስለዚህም ከዚህ በኋላ ባለህ እወቀት ላይ የምትጨምር አይመስለኝም።የምታወቀዉ ደግሞ ትንሽ ነዉ።"ነበር ያለዉ
   ቤንጃሚን አዋቂና ትልቅ ሰዉ ስለነበር ይህን የጓደኛዉን ትችት እንደ ዉርደት ከመቁጠር ይልቅ በፀጋ ተቀበለዉ።
     "ከዚያ ቀን በኋላ "ይላል ቤንጃሚን የጓደኛዉ ንግግር እንዴት እንደቀየረዉ ሲናገር  "የሰዎችን ሀሳብ ከመቃወምና እንደመጣልኝ በቃላት ከመዘርጠጥ ተቆጠብኩ።እርግጠኝነትን የሚገልጹ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ 'እንደሚመስለኝ'፣'እንደምረዳዉ'፣'ሳስበዉ'የመሳሰሉ ቃላትን መጠቀም አዘወተርኩ።እንዲያዉም ከዚያ ጊዜ በኋላ ለ50አመታት ምንም አይነት ግትርነትን የሚገልጹ ቃላትን ተጠቅሜ አላዉቅም።" ነበር ያለዉ።

    እኔ ብቻነኝ አዋቂ፣እኔ ብቻ ነኝ ትክከል፣እኔ ብቻ ነኝ ተናገሪ ብለዉ የሚያስቡ ሰዎች ካላቸዉ እዉቀት በላይ አይጨምሩም።ስለዚህም በሀሳብ ልዕልና እንመን!!!!!

     ይህ ባህሪ ከአንባቢያኑ ዉስጥ አንዱን ይወክል ይሆናልና በቅንነት ሸር እናድርግ!!!!!!!!!!


ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈

🗣 @Tesh5050


ለቅዳሚታችሁ

አንድ ሰዉ በእግዚሀብሄር ፊት ቆመና

"ጌታዬ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሀን ናቸዉ ደም አላፈሰሱም፣የሰዉ ገንዘብም አልቀማሁም" አለ።

እግዚሀብሄርም መለሰለት "ልጄ ሆይ አዎን እጆችሕ ንፁሀን ናቸዉ ነገርግን እጆችሕ ባዶዎች ናቸዉ"።አለዉ አሉ ፈጣሪ..
ንፁህ ሆኖ ባዶ ከመሆን ይሰዉርህ። ንፁህነት ብቻዉን አያድንህምና ንፁህ እጅ ግን ባዶ እጅ
ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ እጅ ፣
ያልሰረቀ እጅ ግን ያልመፀወተ እጅ፣በፈጣሪ ፊት ሞገስ የለዉምና ተጠንቀቅ!
ፓሊስ ነዉ ንፁህ እጅን የሚፈልገዉ እግዚያብሄር ግን ሙሉ እጅህን አጥብቆ ይሻል።

መልካምነት ማለት ላንተ ክፉ ሳያስቡ መኖር ማለት ብቻ ሊሆን ይችላል?

ግን አትሳሳት እዉነተኛዉ መልካምነት የሚመጣዉ መልካም በማድረግም ጭምር ነዉ።

የሚጎዳህን መተዉ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎች ጥቅምም መድከምን ማወቅ አለብህ።

የሚወዱህን ብቻ መዉደድህ አንተን ከግብዞች ምን ለየህ ።

ማወቅህን ሳትጠላ አጥብቀሕ ተግባርህን ጨምርበት እጆችሕ ከመንካት ባለፈ ይዳስሱ።

ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈
👉👉 @Nibab_lehiwot 👈👈

🗣 @Tesh5050 ነኝ


የሚጠብቀን አይተኛም !

ሁላችንም የፈጠረን ፈጣሪ እጅ ላይ ነን በራሳችን የቆምን አደለንም የምድር ባለቤት የሁላችን ፈጣሪ ሁሌም እኛን ለመጠበቅ አይተኛም አያንቀላፋም ስለዚህ ምንድነው ታድያ የሚያስፈራን ?

ቤታችንን ከሌባ ለመጠበቅ ዘበኛ ወይም አደገኛ አጥር ወይ ደግሞ ውሻ አስቀምጠን ነፃ ሆነን ያለስጋት እንተኛ የለ ታድያ ከሁሉ በላይ ሁሉን የፈጠረ ፈጣሪ እየጠበቀን ካለ ምንም ነገር ሊያሸንፈን እንዴት ይቻለዋል ?


❤ፍቅር ነው ያስረጀን!❤

ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው መሆን ይቀድማል
ታላቁ ሲታዘዝ ታናሹ ይሰማል።

ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው ማለት
ትርጉሙ አይደል መሄድ ቆሞ
ለእውነት መኖር
ነው እንጂ የአንዱን ህመም ታሞ።

ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
መች እንዲህ ነበረ
ጊዜውስ መች ከፋ?
ያንቺ ቤት ሞልቶ ከኔ ቤት ቢጠፋ ,,

ችግር እና ሀዘን ደስታና መከራ
ስንቱን አሳለፍነው ተሳስበን በጋራ።

በልባችን የታተመ ፍቅር ስላበጀን
አምላክ እድሜ ሰጥቶን ,,,
ይኸው ሳንለያይ እንደዚህ አረጀን።
"ተ መ ስ ገ ን!"

👌ገጣሚ ዘሪሁን ከ አሰላ
መጋቢት 14/2015


የባሌ ቤተሰቦች በትዳሬ ጣልቃ እየገቡ ተቸገርኩ

እኔ ከ ፍቅረኛየ ከተዋወቅን ቶሎ ነዉ ኣብረን መኖር የጀመርነዉ እና ከኔ በፊት ሚስት ነበረችው ግን እንደተለያዩ ነዉ የነገረኝ ፣
ግን ፍቺ ኣላረጉም ነበር እና ዋሸኝ ፣የተለያዩት እስዋ መዉለድ ስለማትችል ነበር እና ካረገዝኩ ቡዋላ ሰማሁ፣

እኔ ቤተሰብ ነግሬ ቀለበት እንድናስር ግን እሱ መጀመርያ ፍቺ መፈፀሙ ኣለበት እስዋ ሌላ ሃገር ናት እና ቀለበቱ ቀረ አንድ ልጅ አለን፣
ልጄ በህክምና እርጉዝ እያለሁ አሞኝ ሐኪሞቹ እንዲወለድ አልፈለጉም ነበር ፣ለኔ ጤና ብለዉ ግን እኔ ልጎዳ ልጄ ይወለድ ብዬ በስንት ስቃይ በ እመቤታችን ብርታት ወለድኩ፣ እኔም ደናነኝ ልጄም ተገላገልኩ፣
ግን ከ ባለቤቴ ጋር ብዙ ደስተኛ አይደለሁም ምክንያቱም ቤተሰቦቹ ትዳራችን ለይ ጣልቃ እንዲገቡ ቦታ ይሰጣቸዋል በሁሉ ነገር በሃሳብ ባለው ንብረትም ለኔ ያለው ፍቅር በጣሙን እየቀነሰ ነዉ ፣

ቤተሰቦቹ በጣም ጣልቃ ይገባሉ ፣እኔ ነገርኩት ብዙ ጊዜ ግን ምንም ሊስተካከሉ አልቻሉም እንዳውም ነገሮች እየተባባሱ ነዉ ምን ላደርግ? እባካችሁ ሀሳብ ስጡኝ ፣
ስሜ እንዳይጠቀስ አደራ


ሰላም እንዴት ናችሁ? ትንሽ በ ሂወቴ ላይ ግራ የገባኝ ነገር እየተፈጠረ ስላለ ላካፍላቺሁ ብዬ ነው. ባለትዳር እና ሁለት ልጆች አሉኝ. ባለቤቴ ያው ለልጆቹ መልካም አባት ነው.ነገሩን ባጭሩ ላርገዉና... ባለቤቴ በፊት በጣም የሚወዳት ሴት ነበረች. እና ብዙ ነገር ካሳለፉ በሁዋላ.... ያው ፍቅራቸዉን ሳይጨርሱ እሱዋ ወደ ዉጭ ሄደች ግን ሄዳ አልተመለሰቺም. በዚህም የተነሳ በጣም ተጎድቶ ነበር... ለረጅም ጊዜ ሴት አልቀረበም ነበር ቢያንስ ለ 7 አመታት ትመጣለች ብሎ እየጠበቃት ነበር. ግን ፈጣሪ አልፈቀድዉምና አልሆነም. በዚህ መሃል ነበር ከኔ ጋር የተዋወቅነው. ከዛ ቢያንስ 3 ዓመት ከቆየን በሁዋላ እኔ አንቺን ማግባት እፈልጋለሁ.. ሲለኝ እኔም ጥሩ ሰው ስለሆነና ስለወደድኩት እሺ ብዬ ተገባን. እሱን ሳገባ እኔ ሌላ ወንድ አላዉቅም ነበር. ድንግል ነበርኩ 😊በቃ እንዲህ እያልን እየኖርን... ስልክ ተደወለ ድንገት እና እንደመጣች ነገረቺው.. 😔እና ያው እንዳገኛት ሄዶ ደርሼበታለው ግን ስጠይቀው ዋሸኝ. ከዛ በሁዋላ ስልኩን ማየት ጀመርኩ. እና ልጅ ዉለጅልኝ ስልሽ አንቺ እንቢ አልሽ.... የወለድኩት ካንቺ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር... 😔😔 ብዙ የማይረሱ ጊዜ አሳልፈናል መቼም አረሳሺም... 😔.. በህልሜ አየሁሽ የኔ እመቤት... እነዚህ እንኩዋን አሁን በቅርብ ያነበብኩት ነው.. ዉዶቼ እና ቆይ እኔን ሳይወደኝ ነው ማለት ነው ያገባኝ... የጎደለበትን ነገር እንድሞላለት ማለት ነው? ብዬ በቃ ማልቀስ ሆነ ስራዬ. በዛ ላይ እሱ 47 ዓመቱ ነው እኔ ደሞ 27 አመቴ ነው. በቃ ሁሌ እኔ በሱ አይን ስህተት እንደሰራሁ ነው... ጥሩ ነገር ሰራሁ ስል በሱ አይን ጥፋት ሆኖ ይታየዋል. ይቆጣል... አሁን አሁን ጭራሽ ያመናጭቀኛል እና በቃ ይከፋኝ ጀመር. ሳይወደኝ ነው ያገባኝ ብዬ አስባለሁ 😔በዛ ላይ የድሮ photo እቤት ሰብስቦ አስቀምጦ እሱን ባየሁ ቁጥር ያመኛል.የድሮ ደብዳቤ አግንቼ አንብቤ ምን ያህል ይወዳት እንደነበር ያስታዉቃል. እኔ ለምን ወደዳት ሳይሆን በቃ የተቁዋረጠ ነገር እንዴት ሰው ትዳር እና ልጆች አፍርቶ ስላለፈ ታሪክ እና ሰው እንዴት ይታሰባል. በቃ እኔን የፈለገኝ በትዳር እራሱን አስሮ ለመኖር ነው በቃ ብዙ ሴቶች ጋር ወሲብ እንዳይፈትጽም በአንድ ተወስኖ ለመኖር እንጂ እኔን ከልቡ አፍቅሮኝ እንዳልሆነ እያሰብኩ ነው.... 😔😔😔. ባጠቃላይ ድብርት ዉስጥ ነኝ ዉዶቼ ምን ባደርግ ይሻለኛል?

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

30 704

obunachilar
Kanal statistikasi