በኃይልና ጥበብ | ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ
በኃይልና ጥበብ ትልቆቹን ትቶ
ንጉስ አደረገው ደሀውን ቀብቶ
በእረኝነት ሜዳ ልቡን መረመረው
እደልቡ ሆኖ ዳዊትን ቢያገኘው/2/
ምንም ታናሽ ቢሆን አካሉ ቢኮስስ
የተገባ ነበር በእግዚአብሔር ፊት ሊነግስ
የሰው አይን ያልሞላው ትንሽ ብላቴና
አባት ሆኖ ነበር በእግዚአብሔር ህሊና/2/
የጌታችን እናት ታላላቅ ቅዱሳን
ይልቁን ጌታችን የሰው ልጆች መድኅን
በአለም ሊወለድ ከዳዊት በሥጋ
ተስፋ ተሰጥቶታል እንዲሁ በፀጋ/3/
የዋህ ስለነበር ዳዊት በህይወቱ
ከበሩ ሲገባ ፈላለት ዘይቱ
ሳሙኤል አክብሮ በእግዚአብሔር ፊት ቀባው
አምላኩ ቢወደው ታላቅ አደረገው/2/
የምስጋና ሀብቱን ከንግሥና ጋራ
አጣምሮ ሰጥቶታል መልካም እንዲሰራ
ሌትና ቀን ሳይል ሲመገብ ምስጋና
እየደረደረ መሰንቆ በገና
ራዕይ ተሰጥቶት ከላይ ከደመና
ድንግልን አሳየው አንገቱን ሲያቀና/2/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
በኃይልና ጥበብ ትልቆቹን ትቶ
ንጉስ አደረገው ደሀውን ቀብቶ
በእረኝነት ሜዳ ልቡን መረመረው
እደልቡ ሆኖ ዳዊትን ቢያገኘው/2/
አዝ
ምንም ታናሽ ቢሆን አካሉ ቢኮስስ
የተገባ ነበር በእግዚአብሔር ፊት ሊነግስ
የሰው አይን ያልሞላው ትንሽ ብላቴና
አባት ሆኖ ነበር በእግዚአብሔር ህሊና/2/
አዝ
የጌታችን እናት ታላላቅ ቅዱሳን
ይልቁን ጌታችን የሰው ልጆች መድኅን
በአለም ሊወለድ ከዳዊት በሥጋ
ተስፋ ተሰጥቶታል እንዲሁ በፀጋ/3/
አዝ
የዋህ ስለነበር ዳዊት በህይወቱ
ከበሩ ሲገባ ፈላለት ዘይቱ
ሳሙኤል አክብሮ በእግዚአብሔር ፊት ቀባው
አምላኩ ቢወደው ታላቅ አደረገው/2/
አዝ
የምስጋና ሀብቱን ከንግሥና ጋራ
አጣምሮ ሰጥቶታል መልካም እንዲሰራ
ሌትና ቀን ሳይል ሲመገብ ምስጋና
እየደረደረ መሰንቆ በገና
ራዕይ ተሰጥቶት ከላይ ከደመና
ድንግልን አሳየው አንገቱን ሲያቀና/2/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All