"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
📕 #ቅዱሳን አባድር እና #እኅቱ ኢራኒ 🌹🙇
📌•••ወር በገባ በ 28 የቅዱሳን #አባድር_እና_እኅቱ_ኢራኒ ወርኅዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው ሰማዕታቱ ቅዱስ አባድርና እኅቱ ቅድስት ኢራኒ፡- እነዚህም ሰማዕታት የመንግሥት ወገን የሆኑ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው፡፡
📌••••አባድር በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ቢሆንም እርሱ ግን በድብቅ ሌሊት በጸሎት ሲተጋ ያድራል፡፡ አንድ ሌሊት ጌታችን ተገልጦለት ‹‹የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ እኅትህ ኢራኒን ይዘህ ወደ ግብፅ አገር ሂድ፡፡
=> ስለ ሥጋችሁም እንዲያስብ ሳሙኤል የሚባለውን ሰው እኔ አዘዋለሁ›› ካለው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ጌታችን ለቅዱስ አባድር በስሙ ሰማዕት እንዲሆንና ለዚህም ወደ ግብፅ ሄዶ ክብሩን በከሃድያን ነገሥታት ፊት እንዲመሰክር ከነገረው በኋላ እንዲሁ ጌታችን አሁንም ለእኅቱ ኢራኒ ተለተልጦት ‹‹የወንድምሽን ቃሉን ስሚው፣ ትእዛዙንም አትተላለፊ›› በማለት እርሷም ከወንድሟ ጋር አብራ ሰማዕት እንድትሆን ነገራት፡፡ ኢራኒም ጌታችን ተገልጦላት የነገራትን ነገር ለወንድሟ አባድር ሄዳ ነገረችውና እጅግ ደስ አላቸው፡፡
=> ክብር ይግባውና ስለጌታችን ቅዱስ ስሙ ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሰማዕት ይኑ ዘንድ በአንድ ሀሳብ በቁርጥ ኅሊና ተስማሙ፡፡ የአባድር እናቱ ልጇ ሰማዕት ይሆን ዘንድ መዘጋጀቱን ስትሰማ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ጋር እንዳይጣላ ትማፀነው ጀመር፡፡ ወደሌላ አገር ሄዶ በሰማዕትነት እንደሚሞት ግን አላወቀችም ነበር፡፡
=> ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባድር ራሱንም ሳይገልጥ በድብቅ ልብሱን ቀይሮ በመውጣት ለእስረኞች ውኃ እየቀዳ እግራቸውን ያጥባቸዋል፡፡ እስከሚነጋም ድረስ እንዲሁ ያደርጋል፡፡ በር የሚጠብቀውንም ሰው ‹‹ይህን ለማንም አትናገር፣ ነገር ግን ይህንን ሥራ ብትገልጥ እኔ ራስህን በሰይፍ እቆርጣለሁ›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባድር እኅቱን ቅዱስት ኢራኒን ይዞ ወደ ግብፅ ሄዶ እስክንድርያ ደረሰ፡፡ በዚያም ያሉ ወታደሮች አባድርን ዐውቀውት ‹‹አንተ የሠራዊት አለቃ ጌታችን አባድር አይዴለህም እንዴ?›› አሉት፡፡
=> ነገር ግን አባድር ፈገግ ብሎ ‹‹ብዙዎች እንዲሁ ይሉኛል እኔ ግን እመስለው ይሆናል እንጂ እርሱን አይደለሁም›› አላቸው፡፡ ከዚያም ወደሌላ ቦታ ሄደ፡፡ በዚያም ያሉት ጭፍሮች እንዲሁ ማንነቱን ማለትም በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ መሆኑን ቢያውቁትም እርሱ ግን ‹‹በመልክ ተመሳስለን ነው እንጂ እኔ አይደለሁም›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ወጥቶ ወደታላቋ ምስር አገር ሄደ፡፡
=> በምስር አገርም ከአባ አበከረዙን ጋር ተገናኝተው አባድርና እኅቱ ከእርሱ ቡራኬን ተቀበሉ፡፡ ከዚያም ወደ እስሙናይን ደርሰው ከዲያቆን ሳሙኤል ጋር ተገናኙ፡፡ በማግስቱም ወደ እንጽና ከተማ ሄደው በከሃዲው መኮንን በአርያኖስ ፊት የጌታችንን ክብር መሰከሩ፡፡ መኮንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው፡፡ ሁለቱም በጽኑ ሥቃይም ውስጥ ሳሉ ጌታችን ነፍሳቸውን ነጥቆ ወስዶ የሰማዕታትን መኖሪያ የብርሃን ቤቶችን አሳይቷቸው አጸናቸውና ወደ ሥጋቸው መለሳቸው፡፡
=> አርያኖስም በመጨረሻ ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገታቸውን እንዲቆርጧቸው አዘዘ፡፡ አንገታቸውንም ከመቆረጣቸው በፊት አርያኖስ ቅዱስ አባድርን ‹‹በአምላክህ አማጽኜሃለሁ ማንነትህን ንገረኝ?›› አለው፡፡ አባድርም መኮንኑን ‹‹ማንነቴን በነገርኩህ ጊዜ ራሳችንን እንዲቆርጡ ያዘዝከውን ትእዛዝ እንዳትለውጥ አንተም ማልልኝ›› አለው፡፡ አርያኖስንም ትእዛዙን እንዳይሽር ካስማለው በኋላ ቅዱስ አባድር ‹‹የሠራዊት አለቃ እኔ አባድር ነኝ›› በማለት ማንነቱን ነገረው፡፡
=> መኮንኑ አርያኖስም በዚህ ጊዜ ‹‹ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ ጌታዬ ሆይ በአንተ ፈንታ እኔ ልሞት ይገባኛል፣ ይህን ሁሉ ጽኑ ሥቃይ እስከአሠቃየሁህ ድረስ አንተ ጌታዬ እንደሆንክ እንዴት አላስረዳኸኝም›› እያለ አለቀሰ፡፡ ቅዱስ አባድርም ‹‹በመጨረሻ አንተም እንደእኔ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ አለህና አትዘን አሁን ግን የእኔንና የእኅቴን ሰማዕትነታችንን በፍጥነት ፈጽምልን›› አለው፡፡ መኮንኑም የቅዱስ አባድርን ፈቃዱን ይፈጽምለት ዘንድ የአባድርንና የእኅቱን አንገት በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ በሰይፍም ራስ ራሶቻቸውን ቆረጧቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡
=> በተአምራቶቻቸው ያሳመኗቸው 3,685 ማኅበርተኞቻቸውም እንዲሁ በጌታችን አምነው ተሰይፈው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡
ጌታችን አስቀድሞ ለቅዱስ አባድር ‹‹ስለ ሥጋችሁም እንዲያስብ ሳሙኤል የሚባለውን ሰው እኔ አዘዋለሁ›› ብሎ እንደነገረው አሁን እነ አባድር ካረፉ በኋላ ዲያቆን ሳሙኤል የተባለው አገልጋይ የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስ ቅዱስ ሥጋቸውን ወደ ቤቱ ወስዶ በክብር አኖረው፡፡
=> በኋላም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ቅዱስ ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ፡፡ ከሥጋቸውም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡
የሰማዕታቱ የቅዱስ አባድርና የእኅቱ ቅድስት ኢራኒ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን
!ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/Orthodoxtewahdoc