ረቢዕ ማለት ደግ ነው❤️❤️
የአህባቦቹ ሰርግ ነው❤️❤️
የመዲናዉ የሀዲስ አዋቂ ዶ/ር ሙሀመድ ኢብን አልዐለዊ በመካና በመዲና ለዘመናት የቆየዉንና እስከአሁንም በቤተሰባቸዉ የቀጠለዉን የታላቁን ነብይ የአሽረፈልኸልቅ የመዉሊድ ክብረበአል
አፈጻጸምን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ደስታና ብርታት በሚሰማን በየትኛዉም ቀንና አጋጣሚ የነብዩንﷺ መዉሊድ እናስባለን… በርሳቸዉ የመወለድ ጸጋ እንደሰታለን…ይህ መደሰታችን ሰኞ ቀንና በተወለዱበት በወርሀ ረቢዐል አወል መጠኑ ይጨምራል❤️… ጤነኛ አዕምሮ ያለዉ ሰዉ ‹በኢስራእና በሚዕራጅ ባለቤት ለምን ትደሰታላችሁ?›› ብሎ ሊጠይቀን አይችልም፡!!!!ይህ ጥያቄ በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በነብዩ ሙሀመድﷺመልዕክተኛነት ከመሰከረ ሙስሊም አንደበት ሊወጣ ይችላልን? እርባናቢስ ጥያቄ ስለሆነ መልስ አያሻዉም፡፡ ቢሆንም፡ ‹ሙእሚን ስለሆንኩ ነብዩንﷺ እወዳለሁ ፤ ስለወደድኳቸዉ በርሳቸዉ እደሰታለሁ፤ ደስታዬንም
ዘወትር እገልጻለሁ›ካልኩ በቂ ነዉ፡፡››
ይላሉ🥰🥰❤️
የሀገራችንን የመዉሊድ ሂደት ስናጠና ከላይ ሸኽ አልዐለዊ ከሰጡት ገለጻ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የነብዩﷺ ልደት በሳምንታዊ፣በወርሀዊ ወይም በቀናት ዑደት ዓመቱን ሙሉ ይታሰባል፡፡ ሆኖም በረቢዐል አወል ይህ ደሰታ ይጨምራል፡፡ ከወሩ ዉስጥ ከ9-12 ባሉት ቀናት ደግሞ
እርሳቸዉን የማሰቡና ገድላቸዉን በጋራ እያወሱ የመመሰጡ መጠን ይበልጥ ያይላል፡፡
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በየትኛዉም የዓመቱ ቀን ድሆችን ደግሶ የማብላቱ ክንዉን መዉሊድ ይባላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሶደቃዎች ላይ ምንጊዜም የነብያችንﷺ ገድል ይነበባል፡፡ በርሳቸዉ ላይ በብዛት ሶለዋት ይወረዳል፡፡ እርሳቸዉን የሚያወድሱና የሚያሞግሱ መንዙማዎች ምንጊዜም ይደመጣሉ፡፡ በዋነኛነት በእዉቁ ዓሊም በአህመደ ዳኒ (ዳንዩል
አወል) የተደራጀዉ ‹‹ራምሳ› እና ‹ተራ መንዙማ› የተሰኘ ሙሉ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ ይህ የመዉሊድ ሂደት በሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች የተለመደ ነዉ፡፡
ስለዚህ መዉሊድን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚከናወን ሂደት አድርጎ ማሰብ ስህተት ነዉ።
እንኳን ለቆንጅየው ለምርጡ ለጣፋጩ ነብዬ አለይሂ ሰላት ወሰላም ዊላዳ ወር ረቢዑል አወል አደረሳችሁ❤️❤️❤️❤️❤️
#ትንሹ አሚር
❀በቴሌግራም
❀ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢🍀🍀🍀
👇👇👇
💚💛❤️
@Tenshu6793 💚💛❤️
💚💛❤️
@Tenshu6793 💚💛❤️
💚💛❤️
@Tenshu6793 💚💛❤️