2.1.45.12 ደም መርጋት (Deep Vein Thrombosis) /DVT
ደም መርጋት ችግር የምንለው ደም በስውነታችን ውስጥ በሚገኙ የደም ስሮች ላይ መቋጠር ወይም መርጋት ሲፈጠር ማለት ነው። ይህም በአብዛኛው የሚከሰተው በእግራችን አካባቢ በሚገኙ የደም ስሮች ላይ ነው። የደም መርጋት ችግር በአብዛኛው ጊዜ የሚታየው ደምን ከሰውነት ወደ ልብ በሚመልሱ ደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ የተቋጠረ ደም መርጋት ሲፈጠር ነው። ብዙ ጊዜ በታፋና በጭን ውስጥ ገባ ብለው በሚገኙ ተለቅ ባሉ ደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ ነው የሚከሰተው።
የደም መርጋት መነሻ ምክንያት/መንስኤው
የደም መርጋት የሚፈጠረው በደም መላሽ የደም ስሮች ውስጥ ደም መዘዋወርን የሚቀነስ ወይም የሚቀየር ሁኔታ ሲፈጠር ነው።
📌 ለረዥም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ መሆን በተለይም እንቅስቃሴ የሌለበት
📌 ከቤተሰብ የሚመጣ/በዘር የሚተላለፍ በቤተሰብ አባላት ላይ የሚታይ ከሆነ
📌 ከወሊድ በኋላ እስከ ስድስት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ
📌 በቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገና ህክምና መደረግ
📌 በተለያዩ ምክንያቶች ከመጠን በላይ የደም ሴሎች መፈጠር
📌 እድሜ ከ60 በላይ
📌 ከመጠን በላይ ውፍረት
📌 ሲጋራ ማጨስ
📌 ለረጅም ጊዜ መቀመጥ
📌 በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ አለመኖር
📌 እርግዝና
📌 የእርግዝና መከላከያ እንክብል ለብዙ ጊዜ ማቅረብ
📌 የሆርሞን መተካት ህክምና ከተደረገ
📌 ካንሰር
📌 በተፈጥሮ የገዛ ሰውነትን የሚፃረሩ በሽታዎች ለምሳሌ (ሉፖስ)
የደም መርጋት ምልክቶች
ደም መርጋት ከላይ እንደተጠቀሰው በታፋ እና በጭን በሚገኙ ተለቅ ባሉ ደም መላሽ የደም ስሮች የሚፈጠር ሲሆን በብዛት የሚታየው በአንድ በኩል ብቻ ነው። የተፈጠረው የደም መርጋት ደም ዝውውርን ስለሚዘጋ የሚከተሉት ስሜቶች ይታያሉ።
የቆዳ ቀለም መቅላት
የእግር ህመም ስሜት
የታመመውን እግር በሚነኩበት ጊዜ የሙቀት ስሜት ይኖረዋል።
የታመመው እግር በኩል እብጠት መታየት
ለምርመራ በሚቀርቡበት ጊዜ ያበጠና የቀላ ሲነኩት የህመም ስሜት የሚፈጥር እግር ወይም ጭን ይታያል።ይህ ሁኔታ ሲፈጠር በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው።
የደም መረጋት ችግር ዋነኛ ምልክት ሊሆን የሚችለው
📌 የእግር ማበጥ
📌 በተጠቃው ወይም በተጎዳው የአካል ክፍል የመሞቅ ስሜት መኖር
📌 የቆዳው ቀለም መቀየር
📌 የህመም ስሜት መኖር
ምርመራዎች
በብዛት በመጀመሪያ ደረጃ የሚሰሩ ምርመራዎች ሁለት ናቸው
የደም ምርመራ
እግር ላይ የተቋጠረውን ደም ለማየት ዶፕለር አልትራሳውንድ /Doppler Ultrasound የተባለ ምርመራ ይደረጋል።የደም መርጋት መኖሩ እንዳለ ከታወቀ የደም መርጋት ለመፈጠሩ ምክንያቶችን ለማወቅ ተጨማሪ የደም ምርመራዎች ይደረጋሉ።
ህክምና
ደምን ለማቅጠን የሚረዱ መድሃኒቶችን መውሰድ አንቲ ኮአጉላንት(Anti coagulant)
ቀዶ ጥገና ህክምና
ከመድሀኒት በተጨማሪ በእግር ውስጥ የደም ዝውውርን ለመጨመር ስቶኪንግ ሊታዘዝ ይችላል።
በተጨማሪም የረጋው ደም ወደ ላይ ወደ ሳንባ እንዳይሄድ ለመከላከል በደም ስር በኩል የማጣሪያ ወይም የማጥለያ ወንፊት ሊቀበር ይችላል።አንዳንድ ጊዜም የረጋውን ደም ለማስወገድ ወይም ለመበተን የሚያስችሉ መድሀኒቶች በቀጥታ ደሙ ወደረጋበት ቦታ በመርፌ በኩል ሊሰጡ ይችላሉ።
መፍትሄ
📌 ለረዥም ሰዓታት የሚቀመጡ ከሆነ እግርን በየጊዜው ማንቀሳቀስ ተገቢ ነው።
📌 ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ
📌 ውሃ አብዝቶ መጠጣት
📌 ውሃ አዘል ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መጠቀም
📌 የምንቀመጥበትን ሰዐት መቀነስ
📌 በእግር ውስጥ የደም ዝውውርን ለመጨመር የሚደረጉ የሚያጣብቁ ልብሶች (ስቶኪንግ) መጠቀም
ምንጭ፦Tena Ethiopia እና Dr.Alle health groups
ከመ/ር ሸዋፈራ Medical Note/የጤና ማስታወሻ/ ገጽ 304-305 የተወሰደ
ለጓደኛዎት ሼር ማድረግ አይረሳ ከታች ያለውን 👇👇👇 ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➪ https://t.me/+TiEdr8WudAsnLqzh
➪https://t.me/+BUoXJAYu-HozY2U0
➪https://t.me/ShewaferaGetaneh