ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ልማዳዊ እምነቶችን በመሞገት እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የዓለም ሰላምን ማረጋገጥ

ኢማኑኤል ካንት  ፤ በ1795 ዓ.ም ባዘጋጀው አነስተኛ በራሪ ወረቀት (Pamphlet) ላይም እንዴት በዓለም ላይ ፍጹማዊ ፍጹማዊ ሰላምን ማስፈን ይቻላል በሚል ደረጃ በደረጃ አስረድቷል፡፡

አገራት ሰላምን ማስፈን ከፈለጉ ሊከተሏቸው የሚገቡ ሶስት መንገዶች ብሎ የጻፋቸውን እንመልከት፡-

1. ሪፐብሊክ መሆን (ህዝባዊ መንግስት መመስረት)-
ካንት ሁሉም የሀገሪቷ ህዝብ በህግ ፊት እኩል መሆን አለባቸው ይለናል፡፡ ህጉም በዜጎች የጋራ ፍቃድ ሊጸድቅ ይገባዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ይለናል ካንት፣ ህዝቦች መንግስታቸው እንዳይዋጋ ያግዱታል፤ ምክንያቱም ወደ ጦርነት ከተገባ ንብረት የሚወድምባቸው እና የሚሰደዱት እነርሱ ናቸውና፡፡ ሃብታሞች እና አምባገነን ባለስልጣናት ብቻ ናቸው ጦርነትን የሚያውጁት፤ በጦርነቱ ከሚያጡትም ይልቅ ትርፋቸው
ይበልጣል፡፡

2. የሪፐብሊኮች ፌዴሬሽን መመስረት  (ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ መንግስታትን በአንድ ማቀናጀት) -
በንግድ ይሁን በሌላም መንገድ በመንግስታት መካከል ግንኙነቶች ሊመሰረቱ ይገባል፡፡ የዚህ ህብረት አካል የሆኑ መንግስታትም ሉአላዊነታቸውን አሳልፈው መስጠት እና በአንድ ንጉስ የመመራት ግዴታ የለባቸውም፤ ይልቁኑ በምክንያት የሚመራ የንግድ ትሥሥርን ይዘረጋሉ፡፡

3. ኮስሞ ፖሊታኒዝምን መቀበል (ሁሉም ሰዎች እኩል ናቸው ብሎ ማመን)
ካንት ሁሉንም ሰው በአንድ መደብ መድቦ እኩል ናቸው አላለም፤ ይልቁኑ ሰዎች በመሃላቸው የጋራ መከባበር ሊኖር ይገባል ይለናል፡፡ ሌላውን ሰው እንደ አውሬ እያየን ወይም ከሰው በታች ዝቅ አድርገን እያንቋሸሽነው ሰላምን ማምጣት አንችልም፡፡

አሁን ላይ የካንትን እሳቤ የሚከተሉ የዓለም አገራት አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አውሮፓውያን በአውሮፓ ህብረት ስር የጋራ የሆነን የንግድ ትስስር መስርተዋል፡፡ በእነዚህ አገራት መካከልም ጦርነት የመከሰት እድሉ በእጅጉ አናሳ ነው፡፡

@Zephilosophy


አመስጋኝ እንሁን
ሙላ ናስሩዲን

@Zephilosophy
@Zephilosophy


የኛ ውብ ምድር
ኦሾ

@Zephilosophy
@Zephilosophy




ኢጎ እና ደስታ
✍️ኤካህርት ቶሌ

ብዙውን ጊዜ ደስታ ሠዎች የሚላበሱት ሚና እየሆነ ነው። ከሚስቅልህ ፊት ጀርባ ከፍተኛ ስቃይ አለ። የደስታ እጦት በፈገግተኛ ፊት እና በሚያምሩ ነጭ ጥርሶች ጀርባ ሲደበቅ ወይም ደስታ ማጣትህን ለራስህም ጭምር ሳትቀበል ስትቀር ድብርት ውድቀት ፣ጉስቁልና እና ግልፍተኝነት የተለመዱ ከስተቶች ይሆናሉ።

“ደህና ነኝ” የሚለው ኢጎ የሚላበሰው ሚና፣ "የተጎሳቆሉ መምሰል " የተለመደ በሆነባቸውና በማህበረሰቡም መደበኛ ከሆነባቸው ከሌሎች አገሮች ይልቅ በአሜሪካ ጎልቶ ይታያል። ምናልባት ግነት ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በአንደኛው የኖርዲክ አገር መዲና ውስጥ መንገድ ላይ ለማታውቀው ሠው ፈገግ ካልክ፣ ሰከረሃል ተብለህ ልትታሰር እንደምትችል ሰምቻለሁ።

መከፋት በውስጥህ ካለ በመጀመሪያ መኖሩን ልትቀበል ይገባል። “ደስተኛ አይደለሁም” ግን አትበል። ደስታን ማጣት ከማንነትህ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ይልቁንም “መከፋት በውስጤ አለ” ብለህ ከዚያ ነገሩን ለመመርመር ሞክር። ምናልባት ያለህበት ሁኔታ፣ ለዚያ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሁኔታውን ለመቀየር ወይም ከሁኔታው ለመውጣት እርምጃ መውሰድ የማትችል ከሆነ ደግሞ ያለውን ነገር ተጋፍጠህ “ደህና፣ በዚህ ሰዓት ነገሩ እንዲህ ነው፤ ልቀበለው ይገባል ” በል። የደስታ እጦት ዋነኛ ምክንያቱ የተከሰተው ነገር ሳይሆን፣ ለሁኔታው ያለህ ሃሳብ ነው። ስለዚህም ሃሳብህን አስተውል። ሁልጊዜ ገለልተኛ እና እንደነበር ከሚሆነው ክስተት ሃሳብህን ለይተህ ተመልከት። ስለሁኔታው ሃሳቦች እየጨማመርክ ነገር ከማወሳሰብ፣ክስተቱ ወይም እውነታው ይሄ ሲሆን ለሁኔታው ያለኝ ሃሳብ ደግሞ ይሄ ነው፤ ብለህ በእውነታው ላይ አተኩር።ለምሳሌ “አለቀልኝ” ካልክ አንተን የሚገድብና ተገቢ እርምጃ እንዳትወስድ የሚያደርግህ ታሪክ ነው። “በአካውንቴ የቀረኝ ሃምሳ ሳንቲም ብቻ ነው” ብትል ግን እውነታ ነው። እውነታውን መጋፈጥ ደግሞ ሁልግዜም ቢሆን ሃያል ያደርጋል። የምታስበው ነገር ስሜትህን ለማወክ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ልብ ብለህ አስተውል። በሃሳብህና በታወከው ስሜትህ መሃል የሚኖረውን ቁርኝት ተመልከት። ሁልጊዜ ታድያ፣ ሃሳብህንና ስሜትህን ከመሆን ይልቅ ከባሻገራቸው ያለውን አስተውሎ ሁን።

ደስታ ለማግኘት አታፈላልገው፤ ካፈላለግከው አታገኘውም፤ ምክንያቱም ማፈላለግ በራሱ የደስታ ጸር ነው። ደስታን ለመጨበጥ አዳጋች ነው። ከደስታ እጦት ነፃ መውጣት ግን፣ አሁኑኑ ማሳካት የምትችለው ነገር ነው። ይህ የሚሆነውም ለሚፈጠረው ሁሉ፣ ታሪክ ከማበጀት ይልቅ ነገሩን እራሱን በመጋፈጥ ነው። የደስታ እጦት ተፈጥሮአዊውን የደህንነት፤ የውስጣዊ ሰላምንና የእውነተኛ ደስታን ምንጭ ይጋርዳል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy


ኢጎ የአእምሮ በሽታ ነው
✍️ኤካህርት ቶሌ

አዕምሮአዊ ቀውሶች የተገነቡት በማንኛውም ጤናማ ሠው ላይ በሚሰሩ ተመሳሳይ ኢጎአዊ ባህሪዎች ነው። ልዩነቱ ከሚሰቃየው ሠው በቀር ለሌላው ሠው ሁሉ እጅግ ጎልተው መታየታቸውና በሽታዊ ባህሪያቸው ግልፅ መሆኑ ነው።ለምሳሌ፣ ጤናማ የሚባሉ ሠዎች በጣም አስፈላጊ መስለው ለመታየትና የተለዩ ለመምሰል በሌሎች አዕምሮ ውስጥ ያላቸውን ምስል ለማጎልበት እገሌን አውቀዋለሁ ፣ አንዲህ ነገር አሳክቻለሁ፣ ይህን እችላለሁ፣ይሄ አለኝ እና ማንኛውንም ኢጎ ሊዛመድበት የሚችለውን ነገር በመጠቀም በየጊዜው ይዋሻሉ። አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በኢጎ የጎዶሎነት ስሜት እና የማግኘት ወይም ተጨማሪ ብዙ በሚለው ፍላጎቱ ተነድተው፣ እንደ ልምድ ከፍቃዳቸው ውጪ ይዋሻሉ። ስለራሳቸው የሚናገሩት ብዙ ነገር (ታሪካቸው)፣ ባጠቃላይ ምኞትና ኢጎ ታላቅና ልዩ ለመሆን ለራሱ የቀመረው ምናብ ነው። ለራሳቸው የፈጠሩት አስደማሚና የተጋነነ ምስል፣ ለጊዜው ሌሎችን ሊያጃጅል ይችላል። ትንሽ ቆይቶ ግን የፈጠራ ታሪክ እንደሆነ በብዙዎች ይደረስበታል።

ፓራኖይድ እስኪዞፍሬኒያ ወይም ባጭሩ ፓራኖያ  እየተባለ የሚታወቀው የአዕምሮ በሽታ፣ በመሰረቱ የኢጎ የተጋነነ ገፅታ ነው። በአብዛኛው የተገነባው አዕምሮ ከጀርባው ለሚሰማው ጠንካራ ፍራቻ ትርጉም ለመስጠት በፈጠረው ምናባዊ ታሪክ ነው። የታሪኩ ዋናው ክፍል፣ የሆኑ ሠዎች (አንዳንዴም ብዙ ሠው ወይም ሁሉም ሰው) በኔ ላይ ሊያሴሩብኝ ነው” ወይም “እኔን ለመቆጣጠር ወይም ለመግደል እያደቡ ነው” የሚል እምነት ነው።

ተረኩ ወጥነት ያለውና ምክንያታዊ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንዴ ሌሎችን ሰዎች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። አንዳንዴ ድርጅቶችና አገሮችም ጭምር ከስራቸው የዚሁ የፓራኖይድ ሲስተም እምነት አላቸው። “የኢጎ ፍራቻና ሌላውን አለማመን፣ የሌሎችን “ሌላነት” በሚያየው ስህተታቸውና ይህንንም ስህተት ማንነታቸው በማድረግ ላይ ትኩረት መስጠት ባህሪው ምክንያት፣ የተወሰነ እርምጃ በመውሰድ ሌሎችን ኢ-ሰብዓዊ ጭራቆች ያደርጋል።
  ኢጎህ እየጠነከረ ሲመጣ፣ ሌሎች ሠዎች የህይወትህ ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ወደማመኑ ትመጣለህ። አንተ ደግሞ ይበልጡኑ ለሌሎች ህይወትን ከባድ ታደርግባቸዋለህ።.. በርግጥ ይህንን መመልከት አትችልም። ሁልጊዜ የሚሰማህ ሌሎች አንተ ላይ እያደረጉ እንደሆነ ነው።

ፓራኖያ የምንለው የምንለው የአዕምሮ በሽታ፣ በሁሉም ኢጎ ላይ የሚታይ ሌሎች መገለጫዎች አሉት። ምንም እንኳ በፖራኖያ ላይ በጣም የጎላ ቢሆንም። በሽተኛው እራሱን በሌሎች እንደሚጨቆን፣እንደሚሰለል፣ እንደሚያስፈራሩት ሲያይ  ሁሉም ነገር በሱ ዛቢያ እንደሚሽከረከር፣ የብዙ ሠዎችን ትኩረት የሳበ ምናባዊ ቁልፍ ሠው እንደሆነ በማሰብ፣ ልዩና አስፈላጊ ሠው እንደሆነ የተጋነነ ማንነት ስሜት ይሰማዋል። የተበዳይነት ስሜቱና ብዙዎች በስህተት ተመለከተውኛል ማለቱ በጣም ልዩ እንደሆነ እንዲሰማው ያደርገዋል። ቅዠታዊ መዋቅሩን በፈጠረው ታሪክ ውስጥ እራሱን የሚመለከተው ኣንድም እንደተበዳይ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ አለምን ለማዳን ወይም እነዚህን የጥፋት ሃይሎች ለማሸነፍ አቅም እንዳለው ጀግና ሠው ነው።

@Zephilosophy
@Zephilosophy


"የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንኳንስ ውለታን መክፈል፣ ራሱን ውለታንም አታውቅም።"
ልደቱ አያሌው

የእኛዋ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የ1960ዎቹ የእነ ጥላሁን ግዛው ኢትዮጵያ፣ ወይም የ1960ዎቹ የእነ ኒኖይ አኲዪኖ ፊሊፒንስ፣ወይም የ2010ቹ የእነ መሐሙድ ቡዓዚዝ ቱኒዚያ እንዳልሆነች ብዥታ የለኝም። የእኛዋ ኢትዮጵያ የታጋይ መስዋዕትነት ተራ እና “ደመ ከልብ” ሆኖ የሚቀርባት ኢትዮጵያ ናት። በተቃራኒው የሚሊየን ሕዝብ ደም በእጃቸው ላይ ያለ ፖለቲከኞች ከተጠያቂነት ነፃ ሆነው በድሎትና በክብር እንቅልፍ እየተኙ የሚኖሩባት አገር ነች ኢትዮጵያ።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንኳንስ ውለታን መክፈል፣ ራሱን ውለታንም አታውቅም። አገዛዝን በፀጋ አንቀበልም ብለው የሚታሰሩና የሚገደሉ ዜጐች አርዓያ፣ አርበኛና ባለውለታ ተደርገው ከመታየት ይልቅ ሰላማዊ ትግልን ለማጣጣል ማስፈራሪያና መፈራረጃ ተደርገው የሚቀርቡባት አገር ነች። በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙ እና በትግሉ ሒደት ተገለው ሜዳ ላይ የተጣሉት “ሰማዕታት” እኛን ለማጀገን የሚወሱ አርዓያዎች መሆን ሲገባቸው፣ በተቃራኒው እኛን በሰላማዊ ትግል ተስፋ ለማስቆረጥ የሚቀርቡ ማስፈራሪያዎች ሆነዋል። የእኔም የነገ ዕጣ-ፈንታ ከዚህ የተለየ የሚሆን አይመስለኝም። “ስንመክረው አልሰማ ብሎ ነው፣ ይገባዋል!” ብባል ብዙም አይደንቀኝም።

በአጠቃላይ በራሳችን የህይወት ዘመን ደጋግመን እንዳየነው አገራችን አስመሳዮች፣ ጥቅመኞች፣አላዋቂዎች፣ ክፉዎችና ከፋፋዮች ባለ ክብርና ባለ ዝና ሆነው እየተሞካሹ የሚኖሩባት ነች።

ዛሬ ላይ የሕዝቡን አይንና ጀሮ የተቆጣጠሩትና ድጋፍ የሚጐርፍላቸው ሰዎች የሕዝብን ጊዜያዊ ስሜት በመኰርኰር የተካኑ ብልጣ-ብልጥ ብሔርተኞችና ጥቅመኞች ናቸው። በአንፃሩ አዋቂዎችና ሀቀኞች፣ አገርና ሕዝብ ወዳዶች፣ ጨዋዎችና ሰላማዊ ዜጐች ተንቀውና አንገታቸውን ደፍተው የሚኖሩባት የጉድ አገር ነች- ኢትዮጵያ።

@zephilosophy


"ብሔርተኛነት ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ ነው።"

በብሔርተኛነት ላይ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ኤሪክ ሆብስቦውንን /Eric Hobsbawn/፣ እና ፍራንዝ ፋነንን /Franz Fanon/ የመሳሰሉ ምሁራን እንደሚሉት “ብሔርተኛነት የተካረረ ልዩነትንና ቅራኔን በመፍጠር አንድን ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ አነሳስቶ ስልጣንና ሀብትን ለመቆጣጠር በመሳሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል ርዕዮት ነው። የውጪ ጥራዝ- ነጠቅ ርዕዮት ሰለባ በመሆን ጤናማ የሆነውን የባሕልና የቋንቋ ወይም የብሔር ማንነታችንን አውዳሚ ወደሆነ የፖለቲካ መሳሪያነት በመቀየር አስተሳሳሪ ማንነታችንን በጣጥሰን ጥለነዋል። አሁን በእጃችን ላይ የቀረችው ስጋና ደሟ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ተነጥቃ በአፅመ-ቅሪቷ ብቻ በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተንገዳገደች የምትገኘው አገረ-ኢትዮጵያ ነች። አገረ-ኢትዮጵያም የግንባታ ሂደቷ ከመቆምም አልፎ በመቀልበሱ ምክንያትም አሁን የምትገኝበት ደረጃ በከፍተኛ የህልውና የአደጋ ቋፍ ላይ ነው። ዓለም-አቀፍ እውቅና ኖሯት በስምና በካርታ ላይ ከመኖሯ በቀር ለህልውናዋ ዋስትና የሚሰጡ እጅግ ብዙ አስተሳሳሪ እሴቶቿን አጥታለች።

ብሔርተኛነትን በርዕዮትነት እንደማራመድ ለአገር አንድነትና ሰላም ብቻ ሳይሆን ለብሔር-ብሔረሰቦች የእኩልነት መብት መከበርም ፀር የሆነ የፖለቲካ አመለካከት የለም። አንድ ኃይል ራሱን በአንድ ብሔር ስም አደራጅቶ ለፖለቲካ ስልጣን ከታገለና ስልጣን ከያዘ በኋላ የሁሉንም የአገሪቱን ሕዝብ ጥቅምና ፍላጐት የሚያስጠብቅ የእኩልነት ስርዓት ሊመሰርት አይችልም። ብሔር የመሬት ወይም የግዛት ባለቤት ከሆነም ከዚያ ብሔር ውጪ ያሉ ዜጐች መጤና ሁለተኛ ዜጐች ተደርገው ከመታየት ሊድኑ አይችሉም።

በአገራችን በተግባር እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። አልበርት አንስታይን /Albert Einstein/ በጥሩ አባባል እንደገለፀው ብሔርተኛነት “ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ” /Infantile Disease/ ነው።

የኢትዮጵያዊነትን መሸነፍ እንደ ጥሩ ውጤትና ድል በመቁጠር የሚኩራሩ የዘመናችን ብሔርተኞች ብዙዎች ሆነዋል። ይህ መኩራራታቸው የሚመነጨው ግን ብሔርተኛነት ሄዶ ሄዶ የአጥፍቶ-ጠፊነት ውጤት እንደሚያስከትል ካለመረዳት ነው። ጆን ግሬይ /John Gray/፣ በርትራንድ ረስል /Bertrand Russell/፣ ሃናህ አረንት /Hannah Arendt/ እና መሰል ፀሐፍት እንደሚሉት “የብሔርተኝነት ትግል ሲጀመር በፍጥነት የሚያድግና የሚጠናከር ሲሆን፣ በሒደት ግን በውስጡ በሚፈጥረው የጥላቻና የመከፋፈል አዙሪት ባልተቋረጠ ሁኔታ እየተበተነና እየተዳከመ የሚሄድ ነው። ብሔርተኛነት በቆየና የበለጠ በተጠናከረ ቁጥር ሁሉጊዜ የሚፈጥረው ሌላ ከሱ የባሰ ጠባብና አክራሪ ብሔርተኛነትን ነው። ከዚህ የተለየ ሌላ የእድገት ዑደት የለውም። እድገቱ ቁልቁል ነጓጅ /Degenerative/ ሒደት ነው።

አንድ ጊዜ የጋራ መተሳሰሪያችን ከሆነው ከኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜግነት ማንነታችን መነቀል ከጀመርን በኋላ አሁን ላይ ንዑስ-ብሔርተኞች ሲሉ እንደሚሰማው ከብሔር ማንነታችን አውርዳችሁ አድዋና ተንቤን፣ ወለጋና አርሲ፣ ወይም ጎንደርና ጎጃም ወዘተ... ብላችሁ አትከፋፍሉን ብሎ ሌሎችን ማማረር ትርጉም የለውም። እንዲህ ዓይነቱ አባባል የብሔር ፖለቲካን መነሻ እንጂ መድረሻን አስቀድሞ ካለማወቅ የሚመነጭ ድክመት ነው። በዜግነት ደረጃ ያልጠበቅነውን መተሳሰር ወደ ብሔር ደረጃ ከወረድን በኋላ አስጠብቀን የማስቀጠል ዋስትና ሊኖረን አይችልም። አንድ ጊዜ የብሔርተኛነት ፖለቲካን የተለማመደ ሕዝብም የራሴ የሚለውን አገር ከመመስረት ባነሰ በሌላ ማናቸውም ዓይነት ውጤት የመርካት ዕድል የለውም። ሁልጊዜም ብሶተኛ፣ ነጭናጫና ጠባጫሪ ሆኖ የሚኖር ነው።

ተዋቂው ፀሀፊ ኤሪክ ሆፈር /Eric Hoffer/ እንደሚለው፣ “ማንኛውም የግለሰቦችን መብት ለቡድን ጥያቄ አሳልፎ የሚሰጥ የቡድን እንቅስቃሴ ሕዝብን ለጊዜው በብሶት፣ በስሜትና በጥላቻ ከማነሳሳት ባለፈ አገርንና ስርዓትን በጋራ የመገንባትና የማስቀጠል ሚና የለውም”። ባለፉት 33 ዓመታት በአገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ሲሆን እንደታየው የብሔር “ነፃ አውጪ” ድርጅቶች ዕጣ-ፈንታ እየተበተኑ ከመሄድ የተለየ አልሆነም። የራሳቸውንም ሆነ “ነፃ እናወጣሀለን” የሚሉትን ሕዝብ ሕይወት ከመኖር ወደ አለመኖር ሲቀይሩት እንጂ ችግሩን ሲፈቱለት አልታዬም። የኦነግ፣ የብአዴን፣ የኦህዴድም ሆነ የ50 ዓመታቱ የሕወሓት የብሄርተኛነት ጉዞ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ብሔርተኛነትን በአገር ደረጃ በፖለቲካ ርዕዮትነት ማራመድ ከጀመርን በኋላ በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መጠን በሚሊየኖች ስንፈናቀልና በጭካኔ ስንጨፈጨፍ በገሃድ እያየንም ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ የተለየና አዲስ መፍትሄ ማሰብ አልቻልንም። በመረረ ጥላቻ፣ በአጉል እልህና ፉክክር ሕሊናችን ስለተጋረደ “የጅል ዘዬ ሁሌ አበባዬ”እንዲሉ ዛሬም “ብሔርተኝነት ወይም ሞት!” በማለት የጥፋቱን መንገድ የበለጠ አጠናክረን ቀጥለንበታል።

ከልደቱ አያሌው ገፅ የተወሰደ

@zephilosophy
@zephilosophy


ቴሌቭዥን

ምንጭ ፦ አሁናዊ ሀይልን ማግኘት
ትርጉም ፦ ሙሉቀን ታሪኩ

በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ የሚመርጠው መዝናኛ ቲቪ መመልከት ነው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን ከ60 ዓመት እድሜያቸው 15 ዓመታትን ቲቪ በማየት ያሳልፋሉ። የሌሎች አገራትም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው።

ለብዙዎች ቲቪ መመልከት “ዘና ያደርጋል”። በእርግጥ የቲቪ ስክሪን ላይ አፍጥጣችሁ ሳላችሁ የማሰብ ተግባራችሁ ይቋረጣል። የትኛውም ዓይነት ፕሮግራም ስትመለከቱ አእምሮ ምንም ዓይነት ሃሳብ አያፈልቅም፤ ችግሮቻችሁን ትረሳላችሁ፤ እንዲሁም ለአጭር ጊዜም ቢሆን ከራሳችሁ ነፃ ትሆናላችሁ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ?

ይህ ማለት ቲቪ መመልከት ውስጣዊ ስፍራን (Inner Space ) ይፈጥራል?አሁናዊ ንቃተ-ኅሊና ላይ ያደርሰናል? በእርግጥ ይህንን አያስችለንም። ቲቪ ስትመለከቱ አእምሮአችሁ ሃሳብ ማመንጨት ቢያቆምም ከቲቪው የሃሳብ ተግባራት ጋር መጣመሩ አይቀሬ ነው። በመሆኑም አእምሮ የቲቪውን ሃሳብ ማሰላሰሉ ይቀጥላል። በቲቪ የሚያየውን ምስልና ድምፅ እየመጠጠ ይመለከታል። ይህም መፍዘዝና የቀረበውን ነገር መቀበልን ያስከትላል። ፖለቲከኞችና የማስታወቂያ ሰዎች ብዙ ሚሊየን ከፍለው በቲቪ የሚጠቀሙት የተመልካቹን ሕዝብ ቀልብ መያዝ ስለሚችሉ ነው። ወይም ሕዝቡ ያለማስተዋል የቀረበለትን ስለሚቀበል ነው። በዚህም ሃሳባቸውን የተመልካቹ ሃሳብ ማድረግ ያስችላቸዋል።

እንደ አልኮልና እፅ ኹሉ ቴሌቭዥን መመልከት ከሃሳብ በላይ መቆም ሳይሆን ከሃሳብ በታች መውደቅ ያስከትላል። ለጊዜው ከአእምሮ ፋታ ቢሰጣችሁም ዋጋ ያስከፍላችኋል። ዋጋው ደግሞ ንቃተ-ኅሊና ማጣት ነው። በዚያ ላይ ደግሞ እንደ እፅ ሁሉ ቲቪም ሱስ ይሆናል። አንዳንዴ ሪሞት አንስታችሁ ቲቪ ለመዝጋት ትዘጋጃላችሁ። ይሁንና ሳታውቁት ለሰዓታት ቻናል እየቀያየራችሁ ታያላችሁ። ጣታችሁ የማይነካው የመዝጊያውን ቁልፍ ብቻ ይሆናል።

የተሻለ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞች መመልከት የቲቪን ተፅዕኖ ለመቀልበስ ያስችላል። አንዳንድ ፕሮግራሞች እጅግ ጠቃሚ ናቸው። የብዙሃንን ሕይወት የቀየሩና ለንቃተ-ኅሊና ያበቁ ይገኛሉ። ኮሜዲ ይዘት ያላቸው ጭውውቶች ሳያስቡት ንቃተ-ኅሊናን ይቀሰቅሳሉ። ኮሜዲ የሰውን ልጅ ኢጎ ማጋለጥ ይችላል። በዚያ ላይ ተመልካቹን እያሳቁ ሕይወትን በቀላል እይታ እንዲመዘን እና ምንም ነገር ከባድ እንዳልሆነ ያሳያሉ። ይሁንና ቲቪ በኢጎ የበላይነት ቁጥጥር ስር ባሉ ሰዎች የሚመራ ኢንዱስትሪ በመሆኑ ድብቅ አጀንዳቸው እናንተን ማስተኛትና ከንቃተ-ኅሊና ማራቅ ነው። ይህም ሆኖ ግን በርካታ ያልተረጋገጡ ጥቅሞች አሉት።

በከፍተኛ ፍጥነት ምስል የሚቀያይሩ ማስታወቂያዎችንና ተመሳሳይ የቲቪ ፕሮግራሞችን አትመልከቱ። የዚህ ዓይነት ትዕይንት ተመልካቹን ለትኩረት ማጣት (attention deficit disorder) ያጋልጣሉ። በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት የዚህ ችግር ተጋላጭ የሆኑት በቲቪ ምክንያት ነው። ቲቪ መመልከት ካለባችሁ ግን ዘወትር ውስጣችሁ ንቁ ሆኖ ተመልከቱ። በየመሃሉ ዓይናችሁን ከቲቪው ላይ በማንሳት ረፍት ስጡት። ቲቪውን እንደዘጋችሁት ወደ መኝታ አትሂዱ። በተለይ ደግሞ ቲቪ እያያችሁ በዚያው መተኛት ጉዳት ያስከትላል።

@zephilosophy
@zephilosophy

6k 0 29 6 54

አሁንን የመኖር ሀይል

በመጀመሪያ አሁን የጊዜ አካል አይደለም። ጊዜ እንዲኖር ያለፈው ወይም የወደፊቱ መኖር አለበት። አሁን የጊዜ አካል ሳይሆን ዘላለማዊ (eternal) ነው። ልብ ብላቹ ካሰባችሁት ጊዜ ያለው አእምሮአችን ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም ምናስባቸው ሀሳቦች በጊዜ ውስጥ ማለትም በባለፈው እና በወደፊቱ ጊዜ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። እስኪ ምታስቧቸው ሀሳቦች ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ለማተኮር ሞክሩ፤ ከዚያ አእምሮአችሁ በባለፈው(past) እና በወደፊቱ(future) ላይ ተጠምዶ ታገኙታላቹ።

ስለ አሁን(present) ማሰብ አትችሉም። አሁን ላይ ማሰብ ሳይሆን መኖር (አእምሮ አልባ መሆን) ነው ምትችሉት። እስኪ ስለአሁን ለማሰብ ሞክሩ ምን ሀሳብ ወደ አእምሮአችሁ መጣ? በርግጠኝነት ምንም ማሰብ አልቻላችሁም፤ ስለዚህ ሀሳብ የሚያርፍበት ጊዜ ይፈልጋል ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ምንም የማያስብ ስራፈት ትሆናላችሁ ማለት አይደለም። አሁን ላይ መኖር ስትጀምሩ ከአእምሮአችሁ በላይ መሆን ትጀምራላችሁ። ስለዚህ አእምሮአችሁን ምን ማሰብ እንዳለበት የምትወስኑት እናንተ መሆን ትጀምራላችሁ ማለት ነዉ። ነገር ግን አእምሮ ካለናንተ ፍቃድ በራሱ ማሰብ ያቆማል። አእምሮአችሁ እናንተ ሳትፈልጉ በሀሳብ የሚጠመድ ከሆነ ግን አሁን ላይ እየኖራችሁ አይደለም ማለት ነው።

አሁን ላይ ለመኖር ተደጋጋሚ የተመስጦ (meditation)  ልምምድ ያስፈልጋችኃል፤ ምክንያቱም ከአእምሮአችሁ ካልተላቀቃችሁ አሁንን መኖር አትችሉም። ተመስጦ (meditation) ማለት ደግሞ ምንም ሳይሆን እራሳችንን ከአእምሮ ቁጥጥር የምናላቅቅበት መንገድ ማለት ነው። ከአእምሮአችሁ ስትላቀቁ ህይወትን ከዳር ቆማችሁ እንደ ተመልካች መታዘብ ትችላላችሁ።

ህይወትን በሙላት መኖር ከፈለጋችሁ ከኢጎ (ከአእምሮ ቁጥጥር) መላቀቅ ይኖርባችኃል። ኢጎ ከሌሎች የተሻላችሁ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ እና ሌሎችን እንድትጨቁኑ ይነግራችኃል። አለማችን ላይ የምናየው ጦርነት፣ ክፉት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ፅንፍ የወጣ ሀይማኖትን ተገን ያደረገ የሰዎች ጭፍጨፋ በሙሉ የኢጎ ውጤቶች ናቸው። ሁላችንም ውስጥ አይነቱ ይለያይ እንጂ የሆነ አይነት ኢጎ አለ። ኢጎ አሁንን እንዳንኖር የሚገዳደረን ቀንደኛ ጠላታችን ነው።

ሁላችንም ኢጎን አሽቀንጥረን መጣል ይኖርብናል። አለበለዚያ ሰዎች በሰላም የሚኖሩባት የተዋበች ምድር ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን ከኢጎ መላቀቅ እንደምናስበው ቀላል አይደለም። ከህፃንነታችን ጀምሮ የሆነ የኢጎ ማንነት ስንገነባ ኖረናል። ኢጎአችን ትክክለኛ ማንነታችን እስኪመስለን ድረስ ከስብዕናችን ጋር ተጣብቋል። አንዳዶቻችን የብሔር ማንነትን፣ ሀይማኖትን፣ ግለሰባዊ አስተሳሰብን፣ የበላይነት ስሜትን፣ የቆዳ ቀለምን እና የመሳሰሉትን እንደ ተፈጥሮአዊ ማንነት በመቁጠር ከሌሎች ጋር እስከ መጋጨት እና መተላለቅ የሚያደርሱን የኢጎ ገፅታዎች አሉን። እነዚህ ኢጎዎች ከፍ ሲሉ በሀገራት ደረጃ አሁን የምናየውን ጎራ ለይቶ መጠፋፋት ያስከትላል።

አእምሮአችን ህይወትን ውስብስብ አድርጎብናል። ህይወት ግን በጣም ቀላል ናት። አእምሮአችን ማፍቀር አይችልም፤ አእምሮአችን የሚችለው ማስላት ነው። ህይወት አሁን ናት። ከአሁን ወጪ ማድረግ ምትችሉት ነገር አለ? መኖርስ? ያለፈው እና የወደፊቱ ጊዜ ቅዠት ብቻ ናቸው። ያለፈ የምንለው ጊዜ ስንኖርበት አሁን ነበር፤ የወደፊቱም አሁንን ሆኖ ነው ሚመጣዉ። አሁን ላይ መኖር ስትችሉ ከሁለንተና ጋር ትዋሀዳላችሁ።

ብዙ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ለምሳሌ፦ ተራራ መውጣት፣ ከፍተኛ ህመም፣ ከባድ የህይወት ፈተና ሲያጋጥማቸው አሁን ላይ የመገኘትን አጋጣሚ አግኝተዋል። ነገር ግን አሁን ላይ ለመገኘት የግድ እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎች መጠበቅ የለባችሁም። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ አሁን ላይ መገኘት ትችላላችሁ።

@zephilosophy
@zephilosophy

8.6k 1 57 10 96

ኢጎ እና አእምሮ

የሰው ልጅ ለደረሰበት ስልጣኔ እና ብዙ ሳይንሳዊ እውቀቶች ምክንያት አእምሮዉን በሚገባ መጠቀሙ መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን አእምሮአችን በጣም አስፈላጊ የመሆኑን ያህል አውዳሚም ሊሆን ይችላል። እንዴት?

አእምሮ በውስጡ ወደ 100 ቢሊየን የሚጠጉ ኒውሮኖች ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ በቀን (24ሰአታት) ውስጥ ከ 40,000 እስከ 60,000 ሀሳቦችን ያስባል። ከነዚህ ሀሳቦች ውስጥ 75% የሚሆኑት መጥፎና አውዳሚ (negative thoughts) ሲሆኑ 95% ደግሞ ተደጋጋሚ (repetitive thoughts) ናቸው። ስለዚህ ከነዚህ ሁሉ ምናስባቸው ሀሳቦች ውስጥ ቀና እና መልካም (positive thoughts) የሚባሉት 5%ቱ ብቻ ናቸው።

ተመስጦ (meditation) የማድረግ ልምድ ካላችሁ ይህንን መረዳት ትችላላችሁ። አእምሮአችን በአብዛኛው ምንም ለህይወታችን ፋይዳ በሌላቸው ሀሳቦች ሲባክን ይውላል። ነገር ግን ይህን ለመረዳት መጀመሪያ አእምሮአችሁን መታዘብ መጀመር አለባችሁ። ይህንን ካላደረጋችሁ ግን የምታስቡት እናንተ እንጂ አእምሮአችሁ ላይመስላችሁ ይችላል። አብዛኛው ሰዉ የሚያስበው አእምሮ መሆኑን አይረዳም፤ የሚያስበው፣ የሚያስታውሰው፣ የሚያሰላስለው አእምሮአችሁ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ይህንን ለማረጋገጥ ጭንቅላቱ ላይ አደጋ የደረሰበትን ሰው መመልከት በቂ ነው፤ ጭንቅላታቸው የተጎዱ ሰዎች ያለፈ የህይወት ታሪካቸውን እና ያከማቹትን እውቀት የሚረሱበት አጋጣሚ አለ።

አእምሮአችን እንድናስብበት እና እንዲያገለግለን የተሰጠን ድንቅ ገፀ በረከት ቢሆንም በተቃራኒው እኛ እራሳችን የአእምሮአችን ባርያ ነን። ነገር ግን አእምሮን በአግባቡ ከተጠቀምንበት መጥፎ ጌታ ከመሆን ይልቅ ጥሩ ባርያ ማድረግ እንችለላለን። አእምሮአችን ማስላት ይወዳል፤ እራሱን ከሌሎች ያነፃፅራል።

አእምሮ የኢጎ ማእከል ነው። ኢጎ እራስን በሆነ አይነት ማንነት ለሰዎች ለመግለፅ መሞከር እና ከሌሎች የተሻለ መሆኑን ለማሳየት የሚሞክርበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ፦ የብሔር ማንነትን፣ የትምህርት ደረጃን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ሀይማኖትን፣ ግለሰባዊ አመለካከትን እንደ ራስ ማንነት በመቁጠር ከሌሎች የተሻሉ መሆንን ለማሳየት የሚደረግ ጥረት የኢጎ የተለያየ ገፅታ ነው። አንድ ሐኪም ለሙያው ካለው ፍቅር የተነሳ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ጤናማ ቢሆንም፤ የህክምና እውቀት መያዙ ከሌሎች ሰዎች የተሻለ እንደሆነ እንዲሰማዉ የሚያደርገው ከሆነ እና በየአጋጣሚው ስለሱ የሚያወራ ከሆነ ግን ይህንን ኢጎ ልንለው እንችላለን።

ኢጎ ራስን ከሁለንተና የመነጠል ውጤት ነው። አእምሮአችሁ ከሁለነተና ጋር አንድ እንድትሆኑ አይፈልግም። ምክንያቱም ከሁለንተና (universe) ጋር አንድ ከሆናችሁ ከአእምሮ በላይ ትሆናላችሁ፤ ማሰብ በምትፈልጉበት ሰአት ታስባላችሁ ካልፈለጋችሁ ደግሞ አእምሮን እንዳያስብ ማድረግ (shutdown) ትችላላችሁ። አሁን ግን እየሆነ ያለው የተገላቢጦሽ ነው፤ አእምሮአችን በያንዳንዷ ሰከንድ ያለኛ ፍላጎት ያስባል። ይህም ማለት እጃችን ያለኛ ፍላጎት ቢንቀሳቀስ ማለት ነው፤ አእምሮአችን ግን ይህንን ያደርጋል። ሰዎችም ይህንን የአእምሮአቸውን ጫጫታ ለመርሳት በተለያዩ የአልኮል እና አደንዛዥ እፆች እራሳቸውን ይጠምዳሉ።

እዉነታው ግን እኛ ከሁለንተና የተለየን አይደለንም። አእምሮአችን ከእውነተኛ ውስጣዊ ተፈጥሮአችን በታች ነው። ይህንን ውስጣዊ ተፈጥሮአችንን ለማግኘት ከኢጎ (አእምሮ) የበላይነት መላቀቅ ይኖርብናል። አእምሮ ማለት ምንም ሳይሆን ያለፈ እና የወደፊት ህይወታችን የሀሳብ ጥርቅም ማለት ነው። ከአእምሮአችን ቁጥጥር ለመላቀቅ አሁንን መኖር ይኖርብናል፤ ምክንያቱም አሁን(now) የጊዜ አካል አይደለም። ሀሳብ እንዲኖር ያለፈ ወይም የወደፊቱ ጊዜ መኖር አለባቸው።

@zephilosophy
@zephilosophy

8.5k 0 60 22 89

2.ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)

በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ሳለሁ ለሁሉም ሰው፣ ለምንም ነገር ግድ እንደሌለኝ እናገር ነበር፡፡ እውነቱ ግን በጣም ለብዙ ነገር ግድ ያለኝ መሆኔ ነበር፡፡ ሌሎች ሰዎች እኔ ሳላውቅ የእኔን አለም ያዙበት ነበር፡፡ ደስታ እጣ ፈንታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ፍቅር ዝም ብሎ የሚከስት እንጂ የምትሰራው እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ አሪፍነት ራሳችን የምንፈጥረው ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች የምንማረው እንደሆነ አስብ ነበር፡፡

ከመጀመሪያ የሴት ጓደኛዬ ጋር ሳለሁ እስከ ዘላለም አብረን እንደምንሆን አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግንኙነታችን ሲያበቃ፣ ስለ ሴቶች በፍፁም በድጋሚ በተመሳሳይ መንገድ እንደማይሰማኝ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ለሴት እንደገና ያን አይነት ስሜት ሲሰማኝ ደግሞ ፍቅር ብቻ በቂ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግን እያንዳንዱ ግለሰብ “በቂ” የሚለውን መወሰን እንዳለበትና ፍቅር ደግሞ እንዲሆን የፈቀድንለትን ሊሆን እንደሚችል ተረዳሁ፡፡

በመንገዴ በየትኛውም ደረጃ ተሳስቼ ነበር፡፡ ስለሁሉም ነገር ተሳስቼ ነበር፡፡ ህይወቴን ሙሉ ስለ ራሴ፣ ስለ ሌሎች፣ ስለ ማህበረሰቡ፣ ስለ ባህል፣ ስለ አለምና ስለ ሁሉም ተሳስቼ ነበር፡፡

እና በቀሪው ህይወቴም ሁኔታው ያው መሆኑ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡ የአሁኑ እርማት የባለፈው እርማት የነበረውን እያንዳንዱን ግድፈትና ስህተት ወደ ኋላ ተመልሶ ሊመለከት እንደሚችል ሁሉ፣ የወደፊቱ እርማትም አንድ ቀን የአሁኑን ግምቶችና ተመሳሳይ ግድፈቶችን ወደኋላ የሚመለከት ይሆናል፡፡ እና ያ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም አድጌያለሁ ማለት ነው፡፡

ደጋግሞ ስለመውደቅ የሚገልፅ የማይክል ጆርዳን ጥቅስ አለ፡፡ እና ስኬታማ የሆነውም ለዚያ ነው፡፡ ጥቅሱ “ስለ ሁሉም ነገሮች ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ተሳስቻለሁ ህይወቴ የተሻሻለውም ፤ለዚያ ነው” ይላል፡፡

ትክክል ህግ ወይም ፍፁም የሆነ የፖለቲካ ዘይቤ የለም፡፡ ያለው ነገር የአንተ ተሞክሮ ለአንተ ትክክል የሚሆነው የቱ እንደሆነ ያሳየህ ብቻ ነው፡፡ እና በዚህም ላይ ያ ልምምድ ራሱ ምናልባት በሆነ ሁኔታ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ እና እኔ፣ አንተና ሁሉም ሰው የተለያዩ የግል ፍላጎቶች፣ የግል ታሪኮችና የህይወት ሁኔታዎች ያሉን በመሆኑ ሁላችንም ስለ ህይወታችን ትርጉምና እንዴት መኖር እንደሚገባን ወደተለያዩ “ትክክል” ወደምንላቸው መልሶች መምጣታችን የማይቀር ነው፡፡የእኔ ትክክለኛ መልስ አመቱን ሙሉ ብቻዬን ወደተለያዩ ቦታዎች መጓዝ፣ የተረሱ ቦታዎች ውስጥ መኖርና በራሴ ቀልዶች መሳቅ ያጠቃለለ ሊሆን ይችላል ወይም ቢያንስ እስከቅርብ ጊዜ የነበረኝ ትክክለኛ መልስ ይህ ነው፡፡ ያ መልስ ይለወጣል፣ ያድጋል፤ ምክንያቱም እኔም እያደግኩና ብዙ ልምዶች እያዳበርኩ ስመጣ እለወጣለሁ፣ አድጋለሁ፡፡ ምን ያህል የተሳሳትኩ መሆኔን እየሸራረፍኩ በየቀኑ ስህተቶቼን እያሳነስኩ እያሳነስኩ እመጣለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ሙሉ “ትክክል(ፍፁም)” ስለመሆን አጥብቀው ይጨነቃሉ፡፡ ግን በመጨረሻ አይሆኑም፡፡

አንዲት ሴት ያላገባችና ብቸኛ ናት፡፡ እናም አጋር ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን ከቤት አትወጣም፣ ግንኙነት ለመመስረት ምንም ነገር አታደርግም፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በጣም ጠንክሮ እየሰራ በመሆኑ የደረጃ እድገት እንደሚገባው ያምናል፤ ግን ያንን በፍፁም ለአለቃው ተናግሮ አያውቅም፡፡

እነዚህ ሰዎች ሽንፈትን፣ አይሆንም መባልን እንዲፈሩ ተነግሯቸዋል ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ያ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው አለመፈለግ ይጎዳል፡፡ ሽንፈት ያስጠላል፡፡ ግን ለአመታት ለህይወታችን ትርጉም የሰጡ እሴቶች አድርገን የያዝናቸው ለመጠየቅ የመፍራት ወይም ነገሮችን የመተው እርግጠኝነቶች አሉ፡፡ ያቺ ሴት ከቤት ወጥታ ከወንዶች ጋር መገናኘት ስለ ራሷ ተፈላጊነት ያላትን እምነት ለመጋፈጥ እንድትገደድ ያደርጋታል፡፡ ያ ሰውም እድገት መጠየቅ ይፈራል፤ ምክንያቱም ባለው ክህሎት ራሱን በእርግጥም ዋጋ ያለው አድርጎ ከማመኑ ጋር መጋፈጥ ይጠበቅበታል፡፡

ስለዚህ እነዚያን እምነቶች ፈትኖ እውነቱን ከማወቅ ይልቅ ሰዎች ማራኪ ሆነህ ከማያገኙህ እና ተሰጥኦህን ሳያደንቁልህ ቢቀሩ ከሚሰማህ የሚያሳምም እርግጠኝነት ይልቅ መቀመጥ ቀላል ይሆናል፡፡እንደዚህ አይነት እምነቶች በኋላ ላይ ደስታችንንና ስኬታችንን በመያዣነት ይዘው አሁን መካከለኛ የሆነ ምቾት እንዲሰጡን የተነደፉ ወይም የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አስቸጋሪ የረጅም ጊዜ ስልቶች ናቸው፡፡ ሆኖም እነርሱ ላይ ተጣብቀናል፡፡ ምክንያቱም ትክክል እንደሆንን እንገምታለን፡፡ ምክንያቱም ምን ሊከሰት እንደሆነ አስቀድመን እንደምናውቅ እንገምታለን፡፡ በሌላ አነጋገር ታሪኩ በምን አይነት ሁኔታ እንደሚያልቅ አስቀድመን እንገምታለን ማለት ነው፡፡
እርግጠኝነት የእድገት ጠላት ነው፡፡ ምንም ነገር ሆኖ እስኪገኝ ድረስ እርግጥ አይደለም፡፡ የዚያን ጊዜም እንኳን አከራካሪ ነው፡፡ የእሴቶቻችንን ፍፁም ያለመሆን በሚያጠራጥር አይነት መቀበል እየሆነ ላለው የትኛውም እድገት አስፈላጊ የሚሆነው ለዚያ ነው፡፡

ለእርግጠኝነት ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ስለራሳችን እምነቶች፣ ስለራሳችን ስሜቶች እዚያ ደርሰን ራሳችን እስክንፈጥረው ድረስ የወደፊቱ ህይወታችን ለእኛ ስለያዘው ነገር ምንነት ሁሉ የማያቋርጥ ጥርጣሬ ሊኖረን ይገባናል።ሁልጊዜ ትክክል መሆናችንን ከማየት ይልቅ፣ ሁልጊዜ እንዴት የተሳሳትን እንደሆንን (ያለ ጥፋተኝነት ስሜት) መፈለግ አለብን።ምክንያቱም መሳሳትን ማወቅ ወደ መለወጥ ወደ መቻል ይወስደናልና።

📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson

@zephilosophy


ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)

አንዳንድ እጅግ መጥፎ ወንጀለኞች ስለራሳቸው በጣም ጥሩ ይሰማቸዋል፡፡ ይህ ስለራሳቸው የሚሰማቸው ጥሩ ስሜት፣ በዙሪያቸው ካለ እውነታ ይልቅ ሌሎችን ለመጉዳትና ላለማክበር ምክንያት የመደርደር ስሜት የሚያሳዩበት ነው፡፡

ሌሎች ሰዎች ላይ በሚያደርጓቸው አሰቃቂ ድርጊቶች ምክንያታዊ መሆናቸው የሚሰማቸው ግለሰቦች በራሳቸው ጻድቅነት፣ በራሳቸው እምነቶችና ያንን ማድረግ የሚገባቸው መሆን ላይ የማይነቃነቅ እርግጠኝነት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ ዘረኞች፣ የዘረኝነት ስራ ይሰራሉ፡፡ ምክንያቱም ስለራሳቸው ዘር የበላይነት እርግጠኞች ናቸው፡፡ የኃይማኖት አክራሪዎች ራሳቸውን ይጎዳሉ ወይም ብዙ ሰዎች ይገድላሉ፡፡ ምክንያቱም በመንግስተ ሰማያት ሰማዕታት የመሆን ቦታ እንዳላቸው እርግጠኞች ናቸውና፡፡ ወንዶች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ ወይም ሴቶች ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በሴቶች አካል ላይ ባላቸው የበላይነት እርግጠኞች በመሆናቸው ነው፡፡ክፉ ሰዎች ክፉ መሆናቸውን አያምኑም፡፡እንዲያውም የሚያስቡት ሌላው ሁሉ ክፉ መሆኑን ነው፡፡

እዚህ ላይ ችግሩ እርግጠኝነት ሊደርስበት የማይቻል መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ጉዳዮች ላይ እርግጠኝነትን መከተል በአብዛኛው ወይም መጥፎ በሆነ ሁኔታ የማያስተማምን ነገርን የሚፈጥር መሆኑ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ስራቸው ላይ ባላቸው ችሎታ ወይም በሚያገኙት የደሞዝ መጠን የማይነቃነቅ እርግጠኝነት አላቸው፡፡ ያ እርግጠኝነት ግን መጥፎ እንጂ የተሻለ እንዲሰማቸው አያደርጋቸውም፡፡ ሌሎች ከእነርሱ በላይ እድገት ሲያገኙ ሲመለከቱ ትንሽነት ይሰማቸዋል፡፡ ያለመደነቅና እውቅና ያለማግኘት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

የወንድ ጓደኛሽን የፅሁፍ መልእክቶች በሚስጥር ማየት ወይም ሰዎችን ስለ አንቺ ምን እንደሚሉ ጓደኛሽን የመጠየቅ አይነት ቀላል ባህርያት እንኳን የሚነሱት ዋስትና ከማጣትና እርግጠኛ ለመሆን ካለን ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡

ከዚያ ውስጥ ውስጡን ስለሚበላን ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ስሜት ተጠቂ የምንሆነው በእነዚህ ዋስትና ማጣትና ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ጊዜያት ነው፡፡

ይህ ውስጥ ውስጡን የሚበላ የበላይነት ስሜት መንገዱን ለማግኘት ትንሽ ማጭበርበር እንደሚገባን፣ ሌሎች ሰዎች መቀጣት እንደሚገባቸው ፣ የምንፈልገውን አንዳንዴም በኃይል ማግኘት እንደሚገባን ማመን ናቸው፡፡
ይህ እንደገና ወደኋላ የመመለስ ህግ ነው፡፡ ያም ስለሆነ ነገር እርግጠኛ ለመሆን የበለጠ በሞከርን መጠን፣ የበለጠ እርግጠኛ ያለመሆንና ዋስትና ማጣት ይሰማናል፡፡

የዚህ ግልባጭም እውነት ነው፡፡ እርግጠኛ ያለመሆንና ያለማወቅን የበለጠ በያዝን መጠን የማናውቀውን ለማወቅ የበለጠ ፍላጎት ይሰማናል፡፡

እርግጠኛ ያለመሆን ሌሎች ላይ የምንሰጠውን ፍርድ  ያስወግድልናል፡፡ የሆነን ሰው በቴሌቭዥን፣ ቢሮ ውስጥ ወይም በመንገድ ላይ ስንመለከት የሚሰማንን አላስፈላጊ ኩረጃና አድልዎ ባዶ ያስቀርልናል፡፡ እርግጠኛ ያለመሆን በተጨማሪ ራሳችን ላይ ከመፍረድ  ያሳርፈናል፡፡ ተፈቃሪ መሆን አለመሆናችንን አናውቅም፣ ምን ያህል እርግጠኞች እንደሆንን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ስለእነዚህ ነገሮች እርግጠኛ ባለመሆን መቆየትና በልምምድ ለማግኘት ክፍት መሆን ብቻ ነው፡፡

እርግጠኛ ያለመሆን የሁሉም እድገትና መሻሻል ስር ነው፡፡ አሮጌው ብሂል እንደሚገልፀው ሁሉንም እንደሚያውቅ የሚያምን ሰው ምንም አይማርም፡፡ በመጀመሪያ የሆነ ነገር የማናውቅ መሆናችንን ካላወቅን ምንም ነገር ልንማር አንችልም፡፡ ምንም የማናውቅ መሆናችንን የበለጠ ባመንን መጠን፣ የበለጠ የመማር እድል እናገኛለን፡፡

እሴቶቻችን ፍፁም ያልሆኑና ያልተሟሉ ናቸው፡፡ ፍፁምና የተሟሉ እንዲሆኑ አድርጎ መገመት ራስን ከፍ አድርጎ ማየትና ሀላፊነትን ችላ ማለትን የሚፈጥር በአደገኛ ሁኔታ  ግትር አስተሳሰብ  ውስጥ ያስቀምጠናል። ችግሮቻችንን ለመፍታት ብቸኛው መንገድ በመጀመሪያ እስከዚህ ነጥብ ድረስ ያሉት እርምጃዎቻችንና እምነቶቻችን የተሳሳቱ ሊሆኑ እንሚችሉ ማመን ነው፡፡

የትኛውም እውነተኛ ለውጥ ወይም እድገት እንዲካሄድ መሳሳታችንን ለማመን ግልፅነት መኖር አለበት፡፡ ወደ እሴቶቻችንና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች መመልከት ከመቻላችንና ወደተሻለና ጤናማ ልንለውጣቸው ከመቻላችን በፊት፣ በመጀመሪያ አሁን ስላሉት እሴቶቻችን እርግጠኛ አለመሆን ይገባናል፡፡ እሴቶቻችንን በመከፋፈል መመርመርና ስህተቶቻቸውንና ተፅዕኗቸውን ማየት፣ ከቀሪው አለም ጋር እንዴት እንደማይገጥሙ መመልከት፣ አላዋቂነታችንን ፊት ለፊት አፍጥጠን ማየትና ማመን አለብን፡፡

እድገት ማለቂያ የሌለው ተደጋጋሚ ሂደት ነው፡፡ አዲስ ነገር ስንማር፣ የምንሄደው ከ “ስህተት” ወደ “ትክክል” ሳይሆን ከስህተት ወደ አነስ ያለ ስህተት ነው፡፡ አንድ ተጨማሪ ነገር ስንማር አነስ ካለ ስህተት ከዚያ በመጠኑ አነስ ወዳለ ስህተት እየሄድን ነው፤ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ ሁልጊዜ በፍፁም ወደ እውነትና ወደ ፍፅምና ባለመድረስ ወደ እውነትና ፍፅምና የመቅረብ ሂደት ላይ ነን፡፡ለራሳችን የመጨረሻውን “ትክክለኛ” መልስ ለማግኘት መፈለግ አይገባንም፡፡ በዚያ ምትክ ነገ ከዛሬ ይልቅ መሳሳታችን የቀነሰ መሆን እንድንችል ዛሬ ስህተት የሆንባቸውን መንገዶች ፈልገን ማግኘት ይገባናል፡፡

📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson

ይቀጥላል....
@zephilosophy


አይኖቹን ከደነና ረሀብና ጥም በትነውት የነበረውን አሳቡን ሰበሰበ። ፈጣሪ ወደ አእምሮው መጣ:: አሁን ረሀብም ሆነ ጥም የለበትም:: ስለ ዓለም ድህነት (መዳን) አሰበ፡፡ “የጌታ ቀን የሚመጣው በፍቅር ብቻ ከሆነ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል አይደል? ስለምን ተአምር ፈጥሮ የሰዎችን ልብ እየነካ እንዲፈካ አያደርግም? በየአመቱ ግንዶች፣ አረምና እሾኾችስ እርሱ ሲነካቸው ይፈኩ የለ? ታዲያ ምናለ አንድ ቀን ሰዎች ሲነቁ ውስጣቸው ፈክቶ ቢያገኙት?”

ኒኮስ ካዛንታኪስ
የመጨረሻው ፈተና

@zephilosophy


ሰው እና ተፈጥሮ
___

"Life in all its forms is interconnected, and the song of a bird is as vital to the melody of existence as the hum of the stars."

___

ሳይንስ ስለ ምልዓተ ዓለሙ የሚተነትነውን ሃቂቃ ይዘን cosmic በሆነ መነጽር ብንመለከት ሰው የሕላዌ ማዕከል እንዳልሆነ ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርስ ስፋትና አይመጠኔ አነዋወር አንፃር ምድር ራሷ 'ብናኝ' ለማለት የሚደፍሯት እንደሆነች ይገባናል... 


በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ያሉትን ጥቂት ፕላኔቶች እንደ ከረጢት ብንቆጥራቸው ኔፕቲዩን 57፣ ዩራነስ 63፣ ሳተርን 763፣ ጁፒተር 1321 እንዲሁም ጸሐይ 1.3 ሚሊየን ምድር በውስጣቸው መያዝ ይችላሉ... ይህ እንግዲህ ሌሎች በመቶ ቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዓለማትን ሳይጨምር ነው... 


በእኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ ያለችው ጸሐይ 1.3 ሚሊዮናት ምድር በውስጧ ማጨቅ በመቻል እጅግ ግዙፍ ትምሰል እንጂ እንደነ Betelgeuse፣ VY Canis Majoris፣ UY Scuti፣ እና Stephenson ካሉ ሌሎች ጸሐያት ጋር ስትወዳደር ከ 2 - 18 ያህል ጊዜ ስለምታንስ እርሷም ጢንጢዬ የመሆን ዕጣ ይወድቅባታል... [በእኛም ላይ 'አባይን ያላየ...' ታስተርትብናለች]


ከዚህ ሁሉ ግዝፈት አንፃር ታዲያ የሰው ልጅ ምንድነው?... ከብናኝ በታችስ ምን አለ?... 


[የከዋክብቱ ግዝፈት የእኛን ማንነት ያሳንሳል እያልኩ እንዳልሆነ ግን ልብ በሉልኝ... ትልቀታቸው ዝቅ አያደርገንም... ከራስ ባሻገር ላለ ሕላዌ ቦታ እንድንሰጥ ያደርጋል እንጂ... ከአንድ ዓይነት ንጥረ ስሪት የተገነባን አይደለን?...

አስትሮፊዚስቱ Neil deGrasse Tyson እንዲህ ይላል...

"We are part of this universe; we are in this universe, but perhaps more important than both of those facts is that the universe is in us... And for me, that is a deeply spiritual, inspiring experience."]


_

ዳር አልባ በሆነ ምልዓት ውስጥ ብቸኞች ነን ብሎ ማሰብ ከባድ ነው...

"We are not alone in the universe. We are members of a vast cosmic community, sharing the same atoms, stardust, and energy." – Carl Sagan


እኛ ብቻ የተመረጥን፣ እኛ ብቻ የተለየን፣ እኛ ብቻ ግዕዛን ያለን ብሎ መከራከርም ውሃ አይቋጥርም... ተፈጥሮን ጭብጣቸው አድርገው በተሰሩ በርካታ documentary ፊልሞች ውስጥ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ የእንስሳትና ተክሎችን ባሕሪያት አይተናልና... 


"The smallest creature is a masterpiece of nature, as intricate and essential to the balance as the stars in the sky." – Anonymous


ደርሶ የሕላዌ ማዕከላዊ ጉዳይ (Center of existence) እኛ ብቻ ነን ብሎ ማሰብም አይከይፍም... ጉራ ይበዛዋልና... 


ሰው ሁሉ ከምድሪቱ ላይ ጠፍቶ ምድር ሌሎች ፍጡራንን አቅፋ፣ ተንከባክባ መኖር ግድ ቢላት ፈጽሞ የምትቸገር አይመስለኝም... ከአጥፊ ባህሪያችን አንፃር እንደውም ሳይመቻት አይቀርም... ግና ለጥቂት ቀናት ውሃ ቢርቃት ሕላዌን ድርቅ ሊያረግፋት ይችላል... እና ከውሃ አንፃር ሲታይ ሰው ምንድነው?... 


"In the grand orchestra of the universe, humanity is but one instrument, playing alongside countless others." – Anonymous


ደጉ ነገር ያለንበት Ecosystem ቅድሚያ የሚሰጠውም ሆነ የሚያበላልጠው ፍጥረት የለውም... ሁሉም ለእርሱ እኩል ነው፣ ሁሉም የተፈጥሮን ሚዛን አስጠባቂ ነው...


የሰው ልጅ የሃሳብ ጥመትና የእኔ እበልጥ ትርክት ግን ችግር ፈጠር መሆኑ አልቀረም...

___

እንዴት?... 

___


፩) ተፈጥሮን የምንቀርብበትን መንገድ የተሳሳተ አድርጎታል፤ በዙሪያችን ያሉ ተዋንያንን አስተዋጽዎ ከሰው አሳንሰን ስለምናይ የምንሰጣቸውን ቦታ ዝቅ አድርጎታል፤ ብዙ ተረቶቻችንን ተመልከቱ በእንስሳት ንቀት ላይ የተዋቀሩ ናቸው...

ንቀቱ ታዲያ እንስሳቱ ጋ ብቻ አልቆመም፣ ሰው የምንመዝንበትን ሚዛን አባይ አድርጎታል፤ 'ከራስ በላይ ንፋስ' የሚል ልክ አበጅቷል፤

፪) የርህራሔ ድንበር አፋልሷል፣ እንስሳቱን በጭካኔ እንገድላለን፣ ተክሎችን በግድየለሽነት እናወድማለን... 

"The greatness of a nation and its moral progress can be judged by the way its animals are treated." – Mahatma Gandhi

ይህ ልምምድ በአንፃሩ ሰውን የምናይበትን ዓይን አንሸዋሯል... ሞቱን አርክሶብናል...

፫) ጊዜያዊ ችግር ለመፍታት ዘላቂ ችግር እንፈጥራለን... ከእኛ ተርፎ ለልጅ ልጅ የሚሻገር ሃብት መፍጠር ሲገባን በስግብግብ ቅኝት ከመጪው ትውልድ አፍ ነጥቀን እንጎርሳለን...

"We do not inherit the earth from our ancestors, we borrow it from our children." – Native American Proverb

____

እንዲህም እንላለን... 

"Man is not the lord of all beings. He is a being among beings." – Martin Heidegger

@bridgethoughts
@zephilosophy




ነገረ መለኮት ከሌላ ማዕዘን...


እኔ እንደ በርትራንድ ረስል ‹‹ሐይማኖት የፍርሃት ውጤት ነው›› አልልም፡፡ ይልቁንስ ምንነቱን እና ከየትነቱን የማያውቁት በቅጡ ያልተደመጠ፣ ምላሽ ያልተሰጠው ናፍቆት ወደ ማመን እንደሚመራን አስባለሁ፡፡ በእርግጥ የሕይወት፣ የአምልኮ ነገር ሲጀመር አደራረጉ እንደሞኝነት መሆን አለበት፡፡

አጀማመሩ ልክ ከፏፏቴ እንማውጋት፣ ለጨቅላ እንደማንጎራጎር፤ ምናልባት ለነፋስ እንደማፏጨት ስሜት የማይሰጥ ከሚመስል መዳዳት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገርግን መሰረታዊው ሰው የመሆን ቅጥም የተሰራው በዚህ የገርነት ቅኝት መሆን አለበት፡፡ ሰው የፍጥረት የበላይ (superior) የመሆኑን ቀቢጽ የሚሰብኩት ከራሱ መካከል ተከስተው ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ቅኝት እስኪነጥሉት ድረስ የንጽህና ልጅ ነበር፡፡

ለምሳሌ የላቲን አሜሪካ ቅዱስ ሕዝቦች ኮጊዎች (Kogi) የክርስቶስን አዳኝነት፣ የነብዩ መሐመድን መልዕከተኝነትን ለመስማት ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት የቅኝ ገዥዎችን መምጣት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ነገርግን ሰው መሆን አልጠፋባቸውም፡፡ እንኳን ለመሰላቸው ለመላው ግዑዝ ለሆነው ስነፍጥረት ሁሉ ይራራሉ፡፡ ለሺህ ዘመናት አማኞች ነበሩ፡፡ ለዚያውም የተፈጥሮን ሥሪት የተከሉ... ዛሬም ድረስ የጥንታዊ አያቶቻቸውን የአምልኮ እና አስተሳሰብ ዘይቤዎችን እያስቀጠሉ ዘመናዊውን የሰው ልጅ ሽሽት በኮሎምቢያ አይደፈሬ የተራራ ሰንሰለቶች ይኖራሉ፡፡

እነዚህ ሕዝቦች ለተፈጥሮ ካላቸው ጥንቁቅነት የተነሳ መንገድ ስንኳ ለመስራት አንዲትም ድንጋይ ከቦታዋ አያፈናቅሉም፤ አንዲትም ሀረግ አይነቅሉም፡፡ ሁሉንም ነገር የሚከውኑት የተፈጥሮን የልብ ምት በተከተለ መልኩ ነው፡፡ ሰሚ ባያገኙም ቅሉ ስህተተኛው ታናሽ ወንድማችን ለሚሉት ዘመናዊው የሰው ልጅ ተፈጥሮን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት በተከታታይ መልዕክቶችን ይልካሉ፡፡
እንዲህ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ ሰው ጨካኝ በሚመስለው ነገር ግን ፍትህና ርትዕ ሚዛኑ በሆነው ስሙር የተፈጥሮ ሰሌዳ ላይ ጊዜያዊያነቱን፣ አላፊ ጠፊነቱን በጸጥታ የተቀበለ ስኩን ፍጥረት ነበር፡፡ ተፈጥሮን ለመግዛት ለመግራት በበላይነት ስሜት ከመቋመጥ ይልቅ ተፈጥሮን መልበስ፣ መዋረስ ሰው የመሆን ደመነፍስን ያሰለጥን የለምን?

ሁሉም ነገር ሲጀመር የሰው ልጅ የመሆንን ነገረ ውል ለመካን ሙዝን ልጦ የመበላት ጥበብ ማወቅ ብቻ ይበቃው ነበር፡፡ ሲፈጠርም ጀምሮ ስሪቱ የተፈጥሮ ነው፡፡ በእርግጥም ያኔ የሰው ልጅ ደመነፍስ እንደመላዕክት፣ እንደመለኮቱ ጉልህ ‹እኔነቱ በስግብግብ ምሪት ያልደበዘዘ ገር (simplistic) ነበር፡፡

ሊዮ ቶልስቶይ የጻፈው በብዙዎች ዘንድ ሊታወቅ የሚችል አንድ አስገራሚ ተረት አለ፡፡ አሳጥሬ ልተርከው..

በአንድ ደሴት በብህትውና የሚኖሩ ሦስት ጻድቃን ነበሩ፡፡ አኗኗራቸው ተርታ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ስለቅድስናቸው በአጎራባቿ ከተማና በመላው ሀገሪቱ ዝነኞች ሆኑ፡፡ ሰዎች ወደ እነርሱ ይጎርፉ ጀመር፡፡

ይህ ያላስደሰተው የአጎራባቿ ከተማ የቤተክህነት አስተዳዳሪ አንድ ቀን ሊገበኛቸው በጀልባ ሄደ፡
እንደደረሰም ጠየቃቸው..

‹‹ዝናችሁ በከተማውና በሀገሪቱ ናኝቷል፡፡ ለመሆኑ ለቅድስና ያበቃችሁ የተለዬ የምትጠቀሙት ጸሎት አለን?

‹‹እውነቱን መናዘዝ ይኖርብናል፡፡ በሥላሶች፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከማመናችን የተለየ ምንም የምናውቀው ፀሎት የለም፡፡ ይልቁንስ የምንፈልገው መናገር ነው።ይፈጸምልናልም፡፡››

እንግዳው የቤተክህነት ሰው ሳቀ፡፡ ያለ ጸሎት የሚሆን ነገር እንደሌለ አስረድቶ ፀሎቱን አስጠናቸው፡፡

‹‹እባክህ እኛ የተማርን ሰዎች ባለመሆናችን ጸሎትህ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ ልናስታውሰው አልቻልንምና ድገምልን፡፡›› ባሉት ጊዜ እንደገና አስጠናቸው፡፡ ጸሎቱን ለሦስተኛ ጊዜ እንዲያጠኑት ረዳቸው፡፡

በአሸናፊነት ስሜት ወደ እናት ከተማው መመለስ ጀምሮ የሀይቁ መሀል ላይ ሲደርስ ግን ለማመን የሚከብድ ነገር ሆነ፡፡ ሦስቱ መናኒያን በውኃው ላይ በፍጥነት እየተራመዱ ተጠጉት...

‹‹እባክህ ያስጠናኸን ጸሎት ረጅም ስለሆነ እኛም የተማርን ባለመሆናችን ተረስቶናል እና ብትደግምልን፡፡›› ተማጸኑት፡፡

በውኃ ላይ እንደቀላል መራመድ በሚያስችል ቅድስናቸው የተደነቀው እንግዳው ጎብኚ ግን በውኃ ላይ እስከመራመድ የሚያስችል የመብቃታቸውን ተዓምር ከተመለከተ በኋላ ...
«በፍጹም!   ትክክለኛው ጸሎት የእናንተው ስለሆነ በዚሁ ቀጥሉ ብሎ አሰናበታቸው፡፡››

የሰው ልጅ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ እንደነዚህ ሦስት ጻድቃን ነበረ፡፡ በዘመን ሂደት ቀስ በቀስ ሰው መሆንን ረስቶ አውሬነትን ተለማመደ፡፡ ሰው የመሆን ውሉ ሲደናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሰሎሞንስ ስንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ እንደነሱ አልለበሰም›› የተባለላቸው የሜዳ አበቦች ግን አበባ መሆን እንግዳ አልሆነባቸውም፡፡ አበባ ለመሆን ብዙ ምርምር፣ ላቦራቶሪ አላስፈለጋቸውም፡፡ የጽጌ ጌጥነታቸውን ለመቀዳጀት የንጽህና ልጆች መሆን ብቻ ይበቃቸዋል፡፡

የሰውን ልጅ ግን እናውቅልሃለን በሚሉ በራሱ በሰው ልጆች የመላው ፍጥረት የበላይ መሆኑን እየተጋተ ልጅነቱን ካደ፡፡ በሚያምነው ፊት ምንምን፣ ጊዜንም ቢሆን የማይፈራ የነበረውን ፍጥረት በሂደት ድንጉጥ አደረጉት፡፡ ድንጋጤው ጭካኔን ወለደ፡፡

ለራሱ ለመላው ስነፍጥረት ሁሉ ጭካኔን የሚነዛ አረመኔ ሆነ፡፡ ከጊዜና ከቦታ ጽንፍ፣ ከራስ መዳዳት በላይ አልፎ ማሰብ የማይችል ድኩማን...


በፍም እሳት ማቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ

@Zephilosophy


የጠፋውን የሰው ልጅ ፍለጋ (Search for the lost human soul)

ዘመኑ 1950ዎቹ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ... ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ስካር የባነነው ዓለም ለሌላ ዓይነት ባርነት ራሱን ሲያዘጋጅ ተገኘ፡፡ ሥልጣኔውም አገዘው፡፡ የሥልጣኔ ቀዳሚው ተልዕኮ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ ደመነፍስ ማላመድ (taming human animalistic aggresion) ቢመስልም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡ ለኤሮፓዊ ፋውስታዊ የዛገ መዳዳቱ ስምረት ቴከኖሎጂው ረዳት ሆነለት፡፡

ዘመኑ ሰው ወደ አሻንጉሊትነት የሚያደርገውን የመምዘግዘግ ጉዞ አሀዱ ያለበት ሆነ፡፡ በአዲሱ ፈጠራ ቴሌቪዥን በመታገዝ "ፖፕ ከልቸር" ሰለጠነ፡፡ ሁሉም አብረቅራቂው ዘመን አመጣሽ ሳጥን ጋር ፍቅር ወድቆ ለአዲሱ ጊዜ ባርነት ራሱን አዘጋጀ፡፡ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ቴክኖሎጂው በቀኝም በግራም እኩል ይመነደጋል፡፡ ቫይረሱ እና አንቲቫይረሱ፣ ሚሳኤሉና ጸረሚሳኤሉ እኩል ይበለጽጋሉ፡፡

ዛሬ ከሰባ ዓመታት በኋላ በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ የቴሌቪዥኖች ዝግጅቶች ፣ ከ5 ቢሊዮን በላይ የሞባይል ስልኮች በሰው ልጆች እጆች ላይ ይገኛሉ። በአንጻሩ በሰው ልጆች የንባብ አትሮኖሶች ላይ እንደተዘረጉ የሚገመቱት መጻሕፍት ዓይነት ከ150 ሚሊዮን አይበልጥም፡፡

እነሆ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሞታችን ረክሶ ‹ላይቭ ስናየው ስንኳ ማስደንገጡ ቀንሷል፡፡ እንበላለን፤ ግን አናጣጥምም፡፡ እንዋሰባለን፤ ግን ፍቅርን ረስተናል፡፡ አብረን ሆነን ለብቻችንን ነን፡፡ አብረን እየኖረን አንዳችን ለሌላችን በዓድ፣ ሩቅ ነን፡፡ ወዳጅነት፣ ሣቅ፣ ፈገግታ፣ መታመን፣ ፍቅር፣ ፍትወት... ሸቀጥ ሆነው በገበያ ዋጋ ይቸበቸባሉ፡፡

ሰብዓዊት የማይቀለበስበት አስፈሪ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ አንዳንዶች ይህ አረዳድ ጭፍንነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አንዳንዶች ሀዘኑ ቤታቸው እስኪገባ ድረስ የመቃብር ደወሉ በየዕለቱ ለእነርሱ እንደሚደወል ይረሱታል፡፡

እናስ ኤሪክ ፍሮም እንዳስጠነቀቀው የሚቀጥለው ዘመን ሮቦቶች ለመሆን ምን ያክል ይቀረናል? በዚያ ዘመን (በ195oዎቹ አጋማሽ) የተነሱት እንደ ኤሪክ ፍሮም ዓይነት የሰው ልጅ ዕጣ ያስጨነቃቸው አሰላሳዮች ሰው ስለመዳረሻው እንዲጠነቀቅ አብዝተው ቢወተውቱም ሁሉም ከአጥበርባሪ ሳጥኗ ጋር ሲወዛወዝ ሰሚ አልነበራቸውም፡፡ ኤሪክ ፈሮም በ1955 እ.ኤአ በታተመ The Sane Society› በተሰኘ መጽሐፉ ላይ እንዲህ አለ፡፡

‹የ19ኛው ክፍለዘመን ጥያቄ፣ ትርክት ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል›› ነበር፡፡ የሀያኛው ክፍለዘመን ፈተና ግን የሰው ልጅ ሞቷል› ሆነ፡፡ በ19ኛው ክፍለዘመን ኢ-ሰብዓዊነት ማለት ጭካኔ ነበር፡፡ በ20ኛው ክፍለዘመን ግን ኢሰብዓዊነት ማለት መደንዘዝ፣ ስሜት ማጣትና መነጠል ሆነ፡፡ የትናንት ስጋታችን የሰውን ልጅ ወደ ባርነት እንዳይገባ ነበር፡፡ የነገ ስጋታችን ግን የሰውን ልጅ ከሮቦትነት የመታደግ ሆኗል፡፡››

‹‹ሁላችንም በዘመናዊው የምዕራብ ዓለም የምንኖር ሰዎች እብደት ውስጥ ነን፡፡ ራሳችን እያታለልን ላለመሆናችን ምን ዋስትና አለን?››

ዓለም መልክ የሌለው መገማሸር ውስጥ ገብታለች፡፡ ልክ አንደ ሁልጊዜው!... በዚህ ሂደት ሰው የመሆናችን ቀለም አጥተናል፡፡ ሰው የመሆናችን ውሉ በምን ይረጋገጥ? ከቅድመ አያቶቻችን የሚያስተሳስረን ፈትለነገር ከተቋረጠ ሺህ ዘመናት አልፈዋል፡፡ በሕንጻ ሰንሰለቶች መካከል እየተመላለስን ስንኳ ሕልማችን የተራራ፣ የሸንተረር፣ የአደን፣ የለቀማ ነው፤ እንደ ግዞተኛ ነን፤ ፊሊፒናዊ፣ ቼካዊ፣ ቱርካዊ... መሆናችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱስ ቁርዓን፣ ወይም የማናቸውም ቅኝት ሥሪት መሆናችን እውነታውን አይቀይረውም፡፡

እኔ ግን የዓይኑ ቀለም ያላማራቸውን በጅምላ ኮንነው ሰልፊ እየተነሱ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ ሕዝቦች ሀገር ዜጋ ነኝ፡፡ ያ ሁሉ የሺህ ዘመናት ወንጌል፣ ሥነምግባር፣ ሀፊዝ፣ ሥርዓት፣ ትምህርት፣ ግብረገብነት በቅፅበት ውኃ በልቶት መቅላት፣ እስከነፍስ ማቃጠል፣ መደፍጠጥ፣ ማሳደድ... ሁሉም በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሲከናወን አቅመቢስ ስዱድ፣ ዲዳ ሆኘ ተመልከቻለሁ፡፡ ታምሜያለሁ፡፡ ብዙ ኢፍትሃዊነት ባለበት ምንም ማድረግ ካለመቻል በላይ የሚያም ምንስ ነገር ይኖራል?

ለነገሩ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሰብዓዊነት፣ በአጠቃላይ በስነፍጥረት ላይ የሚቃጣ በደል ካላመመኝ የስካሩ አካል ሆኛለሁ ማለትም አይደል? አንዳንዶች ለዚህ መድኃኒቱ ዜግነትን ማስረጽ፣ ሕገመንግስት መቀየር... ዓይነት _ ጨዋ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ እሰማለሁ፡፡ ምንኛ የዋሆች ሆነዋል ጃል! የታመመው በአጠቃላይ የሰው ልጅ (ሰብዓዊነት) መሆኑን ማየትስ እንዴት ይሳናቸዋል? ይህ የሰብዓዊነት ማሽቆልቆል፣ ስርዓት በመቀየር፣ ደንደሳም ዴሞክራሲ በማስረጽ፣ በአዋጅ በማስነገር፣ ኢትዮጵያን እንደ አሜሪካ በማበልጸግ ብቻ ሊሻሻል አይችልም፡፡ እንዲውም ሁላችንም ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ ሰው ካላሰብን አንተርፍም፡፡


ዘመናዊው የሰው ልጅ ከቅድመ አያቶቻችን አንጻር የሁሉም ነገር ውስጥ መትረፍረፍ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ የአንድ አሜሪካዊ ቤተሰብ አማካይ የመገልገያ ቁሳቁሶች ብዛት እስከ 300,000 ይገመታል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 5000% እጥፍ ተመንድጓል፡፡ ዘመኑ በሁሉም ነገር የመትረፍረፍ (Abundance) ቅዠት ውስጥ የሚዳክር ይመስላል፡፡ ነገርግን መትረፍረፍ መቅሰፍት ሆኖብን ምኞታችን፣ እውነታችን፣ የሕይወት ትርጉማችን አሳክሮብናል፡፡ ምንም የማይፈይድልን የመረጃ ናዳ ያጥለቀልቀናል፡፡ በተሳከረ የመረጃ ቱማታ ተዋክበን እውነታችን ራሱ ዋጋ አጥቷል፡፡

ዘመኑ እንደየትኛውም ግልብ ዘመን ነበርና ኤሪክ ፍሮምና መሰሎቻቸው አድማጭ አላገኙም፡፡ እንደየትኛውም ዘመን... ዛሬ ለስሙ እንሰዋለን የሚሉ ቢሊዮናት ተከታዮች ያሉት መሲሁ በቁርጡ ቀን ከመስቀሉ ፊት ለፊት ለብቻው እንደነበረበት ዘመን፡፡ የሚያሳዝነው ዘመን ልብ መግዛት ሲጀምር ዕድሎች ቁጭት ሆነው ከተፍ ማለታቸው እኮ ነው፡፡

የሰው ልጅ የለየለት ዕብደት ውስጥ ገብቷል፡፡ ነጠል ብሎ ለሚታዘብ ተመልካች የሚታየው የሚሰማው  ሁሉ  አጃኢብ ነው፡፡ ሥልጣኔው ሁሉ በየዕለቱ የሚያስመዘግበው መካን፣ መራቀቅ የአውዳሚነት መሆኑ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ከጦር መሣሪያ ጋር ያልተነካካው ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራ ስንኳ በየዕለቱ ሰብዓዊነትን የሚያኮሰምን የመሆኑ ነገር ያስደነግጣል፡፡

ተመራማሪዎች በቅርቡ ሰው በማይደርስባቸው አስፈሪ የአርክቲክ አካባቢዎች ሳይቀር ብዙ ሺህ ቶን የሚመዝን የማይበሰብስ ቆሻሻ አግኝተዋል፡፡ የሰው ልጅ አሁን በተያያዘው ግዴለሽ ጎዳና ከቀጠለ ሩቅ በማይባል ዘመን ሕይወት ከውቅያኖሶችና ባህራት ተጠቃልሎ ሊጠፋ ይችላል፡፡


በፍም እሳት መቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ

ይቀጥላል
@Zephilosophy


ግለሰባዊነት

ምንጭ ፦ ከፍስሀ ጋር መወለድ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዩሐንስ አዳም

ሰዎች የሚኖሩት ግለሰባዊ ባልሆነ ዓይነት ህልውና ውስጥ ነው:: እነርሱ የሚኖሩት እንደ በጎች ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰባዊነቱ አመፁ ፣ ነፃነቱ ፣ የሚናገር ኢየሱስን ወይም ቡድሐን የመሰለ ሰው እዚያ ሲኖር መጠላቱ ወይም አለመወደዱ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ስብስቡ (መንጋው) ይፈራል መሰረታቸው ይነቃነቃል፡፡ ኢየሱስ ትክክል ከሆነ ከዚያም መላው የስብስቡ የህይወት ንድፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ብዙ ስራን ይጠይቃል ሰዎች ደግሞ በባርነታቸው ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡

የኢየሱስ መገኘት ወይም አሁናዊነት ሰዎችን የኪሣራ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ቡድሐን ባገኛችሁበት ቅፅበት ወደ በጣም አስቀያሚ ኢ-ሰባዓዊ ፍጥረት ዝቅ ትላላችሁ፡፡ ሁሉንም ክብር ታጣላችሁ፤ ኢ-ሰባዓዊ በሆነ መንገድ እንደታያችሁ ይሰማችኋል፡፡ ምጡቆች ከሆናችሁ የቡድሐን መገኘት እንደ ማንሠራሪያነት ትጠቀሙበታላችሁ፡፡ በአላዋቂነት ውስጥ፣ በእንቅልፍ ውስጥ ስትኖሩ እንደነበር የምታዩ ትሆናላችሁ:: እናም የቡድሐ መገኘት እና አሁናዊነት በጨለማው የነፍሣችሁ ሌሊት ውስጥ የብርሃን ጨረር እንደሆነ በመገንዘብ ለቡድሐ ታላቅ ምስጋናን ታቀርባላችሁ።

ዳሩ ያንን ያህል ምጥቀት ግን በጣም እያሰለሰ የሚገኝ ነው፡፡ ሰዎች ግትሮች እና ደደቦች ናቸው:: ወዲያውኑ ነው አፀፋ የሚሰጡት፡፡

ወደ ላይ ከማንሰራራት እና የቡድሐን (የነቃውን ሰው) ጫፍ ፈተና በመውሰድ ፋንታ ዳግም ማሸለብ ይችሉ እና ጣፋጭ ህልሞች ተብዬዋቻቸውን ያልሙ ዘንድ ቡድሐን፣ ኢየሱስን የመሰሉ ሰዎችን ያጠፏቸዋል፡፡

ለዚያ ነው ከእኔ ጋርም በተቃርኖ ውስጥ የሆኑት፡፡ እኔ የሆንኩኝ ረብሻ ዓይነት ነገር ነኝ፡፡ የእኔ መገኘት ችላ ሊባል አይችልም፡፡ አንድም ከእኔ ጋር መሆን አለባችሁ አልያም ደግሞ ከእኔ በተቃርኖ ውስጥ መሆን ይኖርባችኋል፡፡ የአንድን ሰው አሁናዊነት (መገኘት) ችላ ማለት ሣትችሉ ስትቀሩ መምረጥ ይኖርባችኋል፤ ታላቅ ትርምስም በፍጥረታችሁ ውስጥ የሚኖር ይሆናል - ምክንያቱም የትኛውም መምረጥ ቀላል አይደለም፡፡ መምረጥ ማለት ደግሞ መቀየር ማለት ነው::

ለሃምሣ ዓመታት በተወሰነ መንገድ ኖራችኋል እንበል፡- በነዚያ ዓመታት ውስጥ እነዚያ ልምዶች ሰምረዋል፡፡ አሁን በድንገት እኔ እዚህ ሆኜ እውነተኛ ህይወት ብላችሁ ታምኑበት ከነበረው መቃብራችሁ እየጠራኋችሁ ነው:: እኔ እዚህ ስትኖሩላቸው የነበሩት ሁሉንም ነገሮች፣ ሁሉም እሤቶቻችሁን፣ ግብረ - ገባዊነት ተብዬዎቻችሁ፣ ሁሉም ዕውቀቶቻችሁን፣ እየኮነንኩኝ ነው፡፡ በጣም ደፋር ሰዎች፣ በጣም የተመረጡ ሰዎች ብቻ ና፥ቸው በሁኔታው ማንሰራራት የሚችሉት እና ያላቸውን ሁሉንም ነገር ሊታይ ለማይችል ግን ዕምነትን ሊያሣድሩበት ለሚችል ነገር አደጋው ውስጥ ሊከቱ የሚችሉት፡፡ አሁን ይህ ለተራው መንጋ (ህዝብ) አስቸጋሪ ነው፡፡ ተራው መንጋ መወሰን የሚችለው ለታወቀ ነገር ነው፡፡ ኢየሱስ አንድ ያልታወቀ ነገር ነው፤ ቡድሐ ከባሻገሩ ያለ አንድ የሆነ ነገር ነው:: አሁን ጥያቄው አንድም የታወቀውን፣ አስተማማኙን፣ ምቹውን መምረጥ አልያም ይህንን ጅብዱ መምረጥ እና ካርታ ላይ ወዳልሰፈረው፣ ፈፅሞ እርግጠኛ ሊሆኑበት ወደማይችሉት መሆኑ አልያም አለመሆኑ ወደማይታወቅበት አንድ የሆነ ነገር
ውሥጥ ከቡድሐ ጋር መሄድ ይሆናል፡

ምናልባት ቡድሐ ራሱ ተሸውዶ ይሆናል ወይም ደግሞ ቡድሐ አታላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንኛው፣ ያንኛው የሚል ምልዑ የሆነ እርግጠኛ የሆነ ምንም መንገድ የለም፡፡ አንድ ሰው በጥልቅ ማመንታቱ፣ በጥልቅ ግራ መጋባቱ፣ በጥልቅ መንገዳገዱ ከቡድሐ (ከነቃው ሰው) ጋር መሄድ ይኖርበታል፡፡ እስካሁንም ወጣቶች የሆኑቱ ፣ አዕምሯቸው አቧራዎችን ያልሰበሰበው፣ የተደሞ ብቃት ያላቸው፣ የህይወት አክብሮት ስሜት ያላቸው፣ ፍፁም ያልተዘጉ፣ ከህይወት ጋር ያላቸውን ጉዳይ ገና ያልጨረሱ፣ እስካሁንም ድረስ ያልሞቱ ...እነዚህ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ከእኔ ጋር፣ ከኢየሱስ እና ከቡድሐ ጋር መሄድ የሚችሉት፡፡ ሌሎቹ ከእኔ፣ ከኢየሱስ እና ከቡድሐ ጋር በተቃርኖ ውስጥ ሊሆኑ ግድ ነው::

በተጨማሪም ሌሎች ምክንያቶች አሉ ሰዎች የቡድኖች አባል መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ቡድን አባል መሆን አንድ የሆነ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነኝ የሚል መፅናናትን እና እርካታን ዓይነት ነገር ይሠጣል፡፡

እውነት በመንጋው ተቀባይነት ልታገኝ አትችልም፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ መንጋው የሚኖረው በውሸቶች ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ እናም እነርሱ እነዚያ ውሸቶች ውሸቶች እስከማይመስሉ ድረስ ለረዥም ጊዜ ስለኖሩባቸው ውሸቶቹን የምር ያምኑባቸዋል፡፡ ከእነርሱ እምነቶች የተለየ ነገርን ስትናገሩ ግራ ይጋባሉ እናም ማንም ደግሞ ግራ እንዲገባው አይፈልግም፡፡ ውስጣዊ መነጋነግን ፣ ግራ መጋባትን በውስጣችሁ ትፈጥራላችሁ እናም ማንም ደግሞ በጥርጣሬ ውስጥ መሆንን አይፈልግም፡፡ እዚያ ግን ጥርጣሬ አለ፡፡ እውነትን አውቀው በነበር ምንም ፍርሃት አይኖርም ነበር፡፡ እነርሱ እውነትን አያውቁም፡፡ ብቻ ያምናሉ፡፡ በጥልቁ ነፍሣቸው ውስጥ ጥርጣሬ አለ፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ በተቃርኖ የሚሄድ አንድ የሆነ በምትናገሩበት ጊዜ ጥርጣሬ ማንሰራራት ይጀምር እና ከላይ ቦታውን መያዝ ይጀምራል፡፡ እናም እነርሱ ደግሞ በጥርጣሬ ውስጥ መሆንን ይፈራሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው እርግጠኝነትን ይፈልጋል፡፡ ለምን? ምክንያቱም እርግጠኝነት በራስ መተማመንን ይሠጣችኋል፡፡ ጥርጣሬ እንድትንቀጠቀጡ ያደርጋችኋል፡፡

እናም እኔ ደግሞ ብዙ ጥርጣሬን በውስጣችሁ እየፈጠርኩኝ ነው - ምክንያቱም በራዕዬ ውስጥ ጥርጣሬ ውሸት የሆኑ እርግጠኝነቶቻችሁን ካላወደው በስተቀር እውነተኛውን እርግጠኝነት የመቀዳጀቱ ዕድል አይኖርም፡፡ እውነተኛው እርግጠኝነት ከዕምነት አይመነጭም፡፡ እርግጠኝነት የሚመጣው ከልምድ ነው ፤እርግጠኝነት የሚመነጨው በራሣችሁ ማወቅ ነው::

@Zephilosophy
@Zephilosophy



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.