እውነትን ፍለጋ
በሃይማኖታዊ አስተሳሰብ የሰው አቅምና ምኞቱ የሚስተካከሉት በእምነት ውስጥ ሲኖር ብቻ ነው:: "እምነት" ይላል ቅዱስ ጳውሎስ ፤
"እምነት ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ በሌለን ነገር ፣ ተስፋ ባደረግነው ነገር ፣ እርግጠኛ የሚያደርገንና ነገንም የማያስረዳን ነው ፤ "
ዕብራ 11፡1
ለሳይንሱ ግን እምነት ብቻውን የስንፍና መፈልፈያ፣ የንቃተ ህሊና ዝቅተኛ ደረጃ፣ተስፋ ለቆረጠ ሰው የሚሰጥ ሃሳባዊ ዳቦ ነው፡፡ ካርል ማርክስም "ሃይማኖት የህዝቦች አደንዛዥ ዕጽ ነው፤" ይላል። ሰዎች ከጥንት ዘመን ጀምሮ በብዙ ነገሮች ሲያምኑ ነበር፤ አብዛኛው እምነታቸው የተፈጥሮኝ አደጋዎች መቆጣጠር ካለመቻላቸው የተነሳ የተፈጠሩ ነበሩ፡፡ ተፈጥሮን መቆጣጠር ሲችሉና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችንም እያበለፅጉ ሲሄዱ ግን የበፊት እምነቶቻቸው ከንቱ እንደነበር ደረሱበት፥ ስለዚህም የጦርነት፣ የአውሎ ንፋስ፣ የጎርፍ፣ የፍቅር፣ የፀሐይ... አምላኮቻቸውኝ ሁሉ ገደሏቸው::
እንደሌሎች የወቅቱ የዓለም ህዝቦች ሁሉ የብሉይ ኪዳን እስራኤላውያንም ሳይንሳዊ ዕውቀታቸው ዝቅተኛ ስለነበር እያንዳንዱን ተፈጥሯዊ ክስተት እነሱ ከአግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት የተፈጠሩ አድርገው ያስቡ ነበር፡፡ በዚህም ለምጽን ሀጢያተኛ ሰዎች ላይ የሚመጣ የእግዚአብሐር ቁጣ ያደርጉታል፤ አስቀድሞ የነበረውን የኖራ ዲንጋይ የሎጥ ሚስት ወደ ጨው ሃውልትነት ተቀይራ ነው ይላሉ፣ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሴቶችን የወር አበባ የእግዚአብሔር እርግማን ነው ይሉታል፤ የፀሀይ ግርዶሹን የነቢዩ ኤልያስ ተአምር ነው ይላሉ፤ በራሱ ተፈጥሯዊ ሂደት የሚፈጠረውን ቀስተ ደመና ለኖህ የተሰጠው ቃል ኪዳን ነው ይላሉ፤ የተፈጥሮን ክስተቶች ሕጋቸውን፣ አመጣጣቸውንና አካሄዳቸውን ስለማያውቁ እግዚአብሔር የትየለሌ የሆነውን ፍጥረቱንና ሌሎች የዓለም ህዝቦችን ሁሉ ትቶ ከእነርሱ ጋር ብቻ በፈጠረው ግንኙነት ውስጥ እነዚህ ነገሮች እንደተከሰቱ ያምናሉ፡፡ ስፒኖዛ "የተፈጥሮን ክስተቶች ከራሳችን እምነትና ስሜት አንጻር ብቻ በተናጥል አንመልከታቸው፤" የሚለው እንደዚህ አይነት ስህተት ላይ እንዳንወድቅ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ እምነቶች ታዲያ ስህተት መሆናቸውን ያጋለጠው የሳይንስ እድገት ነው፡፡
በፊት ሁሉን ነገር የሚያንቀሳቅሰው እግዚአብሔር እንደሆነ ይታመን ነበር ፤ በኋላ ላይ ግን ጋሊሊዮና ኒውተንን የመሳሰለሉ ሊቃውንት Force, Gravity, Motion ... የመሳሰሉ የተፈጥሮ ህጎች ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በመንስዔ - ውጤት አንድ ጊዜ የተወሰኑ ቋሚ የተፈጥሮ ሕጎች መሆናቸውን ሲያስረዱ እግዚአብሔርም ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነት (ጣልቃ ገብነት) ውስን እንደሆነ ግንዛቤ ተወሰደ። ስለሆነም ሰዎች ሁልጊዜ ከንቃት ህሊናቸው ኋላቀርነት የተነሳ ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ነገር በእግዚአብሔር የስልጣን ክልል ስር እያደረጉት በዚህ በኩል ያለው ሕይወታቸውን በእምነት ይሞሉታል፡፡ ስለሆነም ሰዎች በእምነታቸው ምክንያት ላለፉት ብዙ ዘመናት እየተታለሉ ኖረዋል፤ ወደፊት ለሚመጡትም አያሌ ዘመናት እየተታለሉ ይኖራሉም ነው - የሳይንሱ ስጋት። ስለዚህ እውነትን በማፈላለግ ሂደት ውስጥ የስሜት ህዋሶቻችን ላይም ሆነ እምነታችን ላይ ያለን ተስፋ የሞተ ነው::
ሃይማኖቱ ግን ይሄንን አባባል፣ "ወደ ቁሳዊ ህይወት ያደላ ጥራዝ ነጠቅ አመለካከት ነው፤" ይለዋል፤
"በምናየውና በቤተሙከራ በሚገኘው ነገር ብቻ ከተመካን ሕይወታችን ውስን፣ አመጣጣችንን በደንብ የማያስረዳ ፣ ቁሳውያን፣ ሞተን በስብሰን የምንቀር፣ ፈጣሪያችንን የሚያስረሳን፣ ግብረኃብነትንም የሚያጠፋ ነው" ይላል። "እምነት ግን ለዚህ ዓለም ሕግጋት ላልተገለጡ ሆኖም ግን የሕይወታችን መነሻም ሆነ መድረሻ የሆኑ ጉዳዮችን እንድናውቅና በእነርሱ እርግጠኛ እንድንሆን ያደርገናል ፤ " ይላል ሃይማኖት በበኩሉ።
ጀርመናዊው ፈላስፋ ኒቼ ግን "በሃይማኖት በኩል ለዚህ አለም የምንሰጠው ፍቺ ዘመኑ አልፎበታል" ይላል። አሁን ሃይማኖት አርጅቶ እየሞተ ነው፤ እየሞተ ባለ ነገር ደግሞ ዓለምን መተርጎም የራስ ሞትንም ያስከትላል፤ ከእውነትም አያደርስም። የአይሁድ - ክርስትና ሃይማኖት ከ2000 ለሚበልጡ ረጅም ዓመታት የዚህ ዓለምና ሞራላዊ እሴቶች መተርጎሚያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ይህ ሃይማኖት ስለዚህ ዓለምና ስለሰው ልጅ አመጣጥ እንዲሁም ማኅበራዊ ኑሮና የመጨረሻ የህይወት ግብ ላይ በሰጠው ትንታኔና ተስፋ የሰውን ልጅ ከተስፋ መቁረጥና ከስርዓት አልበኝነት ተከላክሎ እዚህ አድርሶታል፡፡
አሁን ግን በሳይንሳዊ አስተሳሰብ የዳበረ ንቃተ ህሊና፣ በቴክኖሎጂ የተፈጥሮን አደጋዎች መቆጣጠር የቻለ ንቃተ ህሊና፣ ማህበረሰባዊና ግለሰባዊ ደህንነቱን በዲሞክራሲና በሀብት ክምችት ማስጠበቅ የቻለ ንቃተ ህሊና የአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ሀይማኖት መሰረት የሆኑትን "ፍርሃትን ጉስቁልናን፣ድንቁርናንና እምነትን" እየገደላቸው ነው፡፡ የእነዚህ መሰረቶች መሸርሸርን ተከትሎ ብዙ ቁጥር ያለው ሰው በአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ውስጥ የተሰበከው እግዚአብሄር ላይ ጥርጣሪያቸውን ማንሳት ጀምረዋል፡፡ ለዘብተኝነት የእንደዚህ አይነት የህይወት አኗኗር እንዱ መገለጫ ነው፡፡ ኒቼም የሚለው ይሄንኑ ነው።
"በየቀኑ ሰዎች ፣ ሁላችንም እግዚአብሄርን እየገደልነው (እየተውነው) ነው፤ በዚህም ምክንያት የአይሁድ - ክርስትና - እስልምና ሃይማኖት እንዲሁ በየቀኑ እየሞተ ነው፡፡ እሱ የተረጎመልን አለምም ከእርሱ ጋር አብሮ እየጠፋ ነው፡፡ በመሆኑም እየሞተ ያለ ሃይማኖት ወይም እምነት የዚህን ዓለም የመጨረሻ እውነት ሊነግረን አይገባም፤ ደግሞም አይችልም፡፡ ሃይማኖቱ የሰጠን እሴቶችም እንደገና መከለስ (revaluation of values) አለባቸው፡፡"
የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ፓትሪያርከ ቤኔዲክት 16ኛም ክርስትና ከህዝብ መድረኮች እየጠፋ መሆኑን አምነው፤ ሆኖም ግን ይህ ክስተት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን እንግሊዝን በመስከረም 2010 በጎበኙበት ወቅት መናገራቸውን ቢቢሲ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ዘግቦታል፡፡ ፓትሪያርኩ በዚሁ ንግግራቸው የአውሮፓ ስልጣኔና ዲሞክራሲ የተገነባው በክርስቲያናዊ ስነምግባርና አስተምህሮ ላይ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሆኖም ግን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ግፊት ህዝቡ ውስጥ እየተስፋፋ ያለው ቅጥ ያጣ ቁሳዊነትና አምልኮት ሸቀጥ የዲሞክራሲያችንን መሰረት እያናጋው መሆኑን ጠቅሰዋል:: Aggressive secularism and commodity feitishism are becoming threat to our democracy. በመሆኑም በሳይንስ መታበያችን ከጋራ ጥፋት በስተቀር ሌላ የምናተርፈው ነገር የለም፡፡
መፅሀፍ፦ ፍልስፍና ፩
ደራሲ ፦ ብሩህ አለምነህ
@Zephilosophy