የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
ጃሂሉ ማህበረሰብ የእውቀት ባለቤቶችን አጥብቆ ይጠይቅ ፤ የእውቀት ባለቤቶችን ይከታተል ፤ ማን ነው ወደመልካም የቀረበው? ማንነው ወደቀጥተኛ እና ትክክለኛው የቀረበው? የሚለውን ይመልከት፤ ስለአላህ ሸሪኣ ይጠይቅ፣ እነርሱም በኪታብና በሱና የእውቀት ባለቤቶች በተስማሙበት መሰረት ያስተምሩታል ፣ ወደሀቅ ይመሩታል፤
ትክክለኛ የሸሪዓ አሊም በትግስቱ ፣ አላህን በመፍራቱ ፣ አላህ እና ረሱል ግዴታ ባደረጉት ነገር ላይ በመቸኮሉ ፣ አላህና ረሱል ሀራም ካደረጉት ነገር በመራቁ ይታወቃል።
የሸሪዓ እውቀት ባለቤቶች በዚህ አለም ምርጦቹ እነርሱ ናቸው ፤ የአላህ መልክተኛ እንደተናገሩት የህብረተሰብ እረኞች ናቸው ፣ ህብረተሰብ ወዳልሆነ አቅጣጫ እንዳይጓዝ ጠባቂዎች እነርሱ ናቸው።
የአላህ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል
"كلكم راع وكلكم مسئول عن رعيته"
“ሁሉም እረኛ ነው፤ ከሚጠብቀው ነገር ተጠያቂ ነው፡፡”
የእውቀት ባለቤቶች የህብረተሰብ እረኛ ናቸው። መሪዎች እነርሱ ናቸው። በተሰጣቸው ሀላፊነት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። በእርሷ ላይ አላህን ይፍሩ። ሰዎች ከእሳት በሚወጡበት ጉዳይ ላይ ይወያዩ። ከጥፋት ሰበቦች ያስጠንቅቁ። የአላህን እና የረሱልን ፍቅር በልቦቻቸው ውስጥ ይትከሉ። በአላህ ዲን ላይ ኢስቲቃማ እንዲኖራቸው ከፍተኛ ጥረት ያድርጉ። ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ አቅጣጫ ይስጡ። ከእሳት ጓዳና ያስጠንቅቁ- እሳት አስከፊ መመለሻ ናትና። ከእርሷ መጠንቀቅ ግድ ነው ፤ ከእርሷ ማስጠንቀቅም እንዲሁ።
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة