በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Creator - @abela1987 📨
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


🔥Best folder disk channel🔥 dan repost
🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇




ችሮታ
(በእውቀቱ ስዩም)
ወዳጆቼ እንዴት ናችሁ? ትራምፕ ከተመረጠ ጊዜ ጀምሮ አልተገናኘንም፤ በነገራችን ላይ፥ ትራምፕ ማለት ለኔ የሜሲ ቦዲጋርድ ማለት ነው፤ የሜሲ ቦዲጋርድ ድንገት ከመሬት ተንስቶ ወደ ጨዋታው ሜዳ ሲሮጥ ታዩታላችሁ፤አሯሯጡ ደግሞ ፥ቀነኒሳ የይርጋ ጨፌን ቡና ጠጥቶ ቢሮጥ ብላችሁ አስቡት ፤ ሜሲ ከማርስ በመጡ ፍጡራን ታግቶ እሱን ለማስጣል የሚሮጥ ነው የሚመስለው፤ ምንጉድ ተፈጥሮ ነው ብየ አያለሁ፥የሆነ ብላቴና ልጅ ወደ ሜዳው ሰርጎ ገብቶ፥ ከሜሲ ጋር ሰልፊ ሊጠባጠብ እየሞከረ ነው፤ ቦዲጋርዱ ሮጦ ከደረሰ በሁዋላ ሰልፊ ጠያቂውን ልጅ እንደ በቆሎ በቁንጮው አንጠልጥሎ ያስወጣዋል ብየ ሳስብ፤ የሰልፊው ተሳታፊ ሆኖ ወደ ቦታው ተመለሰ፤ እምደንቅ ነው! እስከዚህ ድረስ ያለውን ለትራምፕ ቆርጣችሁ ላኩለት🙂

ስሙኝማ! አዚህ ከተማ ፥ጨዋ ጨዋ፥ የሚጫወቱ ሀብታሞች እየተበራከቱ ነው፤ ሚድያ ላይ ይወጡና ” በዚህ ድሀ ህዝብ ላይ የሀያ ሚሊዮን ብር መኪና አልነዳበትም ብየ ዱባይ ውስጥ ቀለል ያለ ሪልስቴት እየገነባሁ ነው፤ “ የሚል ይዘት ያለው ቃለመጠይቅ ይሰጣሉ፤ ግዴለህም በላብህ ካመጣኸው ሀብታምነት ምንም የሚያሸማቅቅ ነገር የለውም፤ ፈይሳ ሌሊሳ የተመኘልን ጋሪ በጎርፍ ከሚረጨን፥ የሃያ ሚሊዮን ብር መኪና ቢገጨን ለኛም ክብር ነው፤

እኔ ሀብታም መሆን እንደምፈልግ በተደጋጋሚ ተናግርያለሁ፤ ሱፐርማርኬቴ በር ላይ “ የግብር ከፋዩ ስም በእውቀቱ ስዩም የሚል ፥ በደብዛዛ ጉርድ ፎቶግራፌ የታጀበ ሰርተፍኬት ደቅ ብሎ ማየት እፈልጋለሁ፤

በተቻለኝ መጠን እቆጥባለሁ ፤ ያ ማለት ግን ትራምፕ እንደ ሰረራት አሜሪካ፥ ችሮታየን አቋርጫለሁ ማለት አይደለም፤ ሀበሻ ምስጋና አያውቀም እንጂ፥ እኔማ የተራበ ከማብላት የተጠማ ከማጠጣት ቦዝኜ አላውቅም:
:
በቀደም ደቻሳ ክትፎ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብየ ያዘዝኩትን ስጠብቅ ሁለት ጎረምሶች ከፊቴ ቁጭ ብለዋል፤

አንደኛው “ በውቄ ! የሎስ አንጀለሱ ሳያልቅ ጋብዘና “ አለኝ፤

“ በደስታ “ አልሁና በክትፎ ቤቱ በር የሚያልፈውን ቆሎ አዙዋሪ በፉጨት ጠርቼ፥
“ ከለውዙ አንዳንድ ማንኪያ፥ ከሽንብራው አንዳንድ ጭልፋ ስጥልኝ ” ብየ አዘዝኩት፤

በጋበዝኳቸው ለጠብ ተጋበዙ፤ ግማሹን የኮንደሚኒየም ነዋሪ ያሳተፈ ግልግል ተደርጎ ከሞትና ከቁስለት ተረፍኩ::

ከጥቂት ቀናት በፊት ደሞ፥ የረከቦትን ጎዳና ይዤ፥ በእግሬ ስዠልጠው፥ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የቀፈለኝ ልጅ ከጎን ከጎኔ ያጅበኝ ጀመር፤ “በውቄ ደብሮኛል "አለኝ፤

“ ዠለስ ፤ ቢኖረኝ ኖሮ፥ በዚህ ማጅራትና ግንባር አስተባብሮ በሚመታ ጠራራ ጸሀይ፤ በእግሬ እሄድ ነበር” ብለውም ሊፋታኝ አልቻለም:
:
ትንሽ እንደተራመድን፥ መንገዱ ዳር ካለው ካፌ አንድ የማውቀው ሰውየ ሲወጣ ተመለከትኩ፤
“በውቄ እንዴት ነህ፡ “ ብሎኝ ሊያልፍ ሲል፥ ቀረብ ብየ እጁን ያዝኩና አስቆምኩት፤

“በናትህ ይሄ ልጅ እየነዘነዘኝ ስለሆነ እንዲሄድልኝ ትንሽ አውራኝ “ አልሁት፤ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ወደሚጠብቀኝ ጎረምሳ እየጠቆምኩት፤

“ ብራዘሬ እኮ ነው፤ ከስራ ተቀንሶ እንጂ የሰው ፊት ማየት የሚወድ ሰው አልነበረም ” አለና ከቴስታ የማይተናነስ ግልምጫ አበረከተልኝ::

አቤት ! እንደ እንደ ድሮ ሻንጣ ሽምቅቅ ስል ይሰማኛል፤

“ በል ስራ እስኪያገኝ ድረስ ይሄ አንተ ጋ ይቀመጥለትና እየቀነስህ ስጠው”

አልሁና ድፍን መቶ ብር ሰጥቼው ጉዞየን ቀጠልኩ:;

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ጊዜ ሃያል ነው ። የከበደን ይቀላል ፣ ግራ የገባን መስመር ይይዛል፣ የምንፈራውን ስናየው ሳቅ ይታገለናል።

አሻግረን ብርሃን እናያለን ፤ጠንክረን እንሰራለን ፤ ያሸነፍን ሲመስለን አንታበይም ፤ በወደቀ ላይ አንፈርድም ፤በትንሽ በትልቁ አንማረርም ፤በረባው ባረባው አንቀደድም ፤ላለው አናሽቃብጥም ።

ስንገሰፅ እንሰማለን ፤ ቅር ያለንን እናሳያለን ፤ ስንወድ መውደዳችንን አንደብቅም ፤ ስናደንቅ አድንቆታችን ለሚገባው ሰው እንሰጣለን ።

ድክመት ድክመት ላይ አንመሰጥም ፤ ውድቀታችንን ጠቅልለን አናላክክም ፤ ይሉንታ ቢስ አንሆንም ።

ግፍን እንፈራለን ፤ ያዘነ ላይ አንስቅም፤ የጉብዝና ወራታችን ወቅት አንመፃደቅም ። መስገብገባችንን አደብ አናሲዘዋለን ፤ ውድድራችን ከራሳችን ትላንት ጋ ነው፤ ትግላችን ከህልማችን ጋ ነው።

ከትላንታችን እንማራለን ፤ ታላላቆቻችን እንሰማለን ታላላቆቻችን በምክንያት እንሞግታለን ፤ አድናቆታችን አምልኮት የለበትም ፤ ስኬታችንን በመርሃችን እንለካለን ፤ እራሳችንን እንገዛለን ።

የማይነጋ ጨለማ የለም... ይነጋል ፣ የጠወለገው ይለመልማል ፣ የጎደለው ይሞላል ።

አሜን ❤🙏
Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


Forex Free Signal
💰 ኑ አብረን ገንዘብ እንስራ
💵
Join us 👇👇👇


#የአባት_ሀዘን

ሙላቴ ጎሏል በሀዘን
ፍካቴ ፀልሟል ባባ፣
ግማሹን የእኔ አካል
ይዞት ከጉድጓድ ገባ፤

ፈጣሪ ፈቅዶ እንደልጅ
ተንከባክቤ ሳልጦረው፣
የምድርን ትቢያ አልብሶ
እንዳይመለስ አስቀረው፤

ጎደልኩኝ መቼም ላልካስ
እወደው ነበረ በጣም፣
እህህ.. ማለቴም ከንቱ
ሀዘኔ መቼም አይወጣም፤

አቃተኝ እውነቱን ማመን
ውል አለኝ ሳቁ እና ድምፁ፣
ፈለኩት በሰዎች መሀል
ናፈቀኝ ኮስታራው ገፁ፤

በእንባ ቢታጠብ ገላዬ
ሁለመናዬ የሱ አምሳል፣
ለቅሶስ በምን ስልጣኑ
ያባትን ሀዘን ያስረሳል?

መፅናናት በምን ይቻለኝ
ልጠንክር እንዴት አባቴ፣
ስረታ የሚያጎብዘኝ
እርሱኮ ነበር ብርታቴ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ሌላ ሴት አሳዩን

ፈጣሪዋን ወልዳ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ጡቶቿን የጠባ
ማርያም ማርያም ፥ አንበል ነጋጠባ ።

አምላኳን ታቅፋ ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ በእጆቿ መሐል
በማርያም ተገርመን ፥ ተደንቀን አንዋል።

ፈጣሪዋ የነሳው ፥
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ከእሷ ሥጋና ነብስ
ማርያምን ከንግዲ ፥ እናቁም ማወደስ።

እናንተ ምታቋት ፥
ያለዘር ፀንሳ ፥ ቃሉን ብቻ ሰምታ
የድንግልናዋ ፥ ማህተም ሳይፈታ
ሌላ ሴት አሳዩን ፥ ካለች ያያችሁት
ማርያምን ማመስገን ፥ እንተው እንዳላችሁት ።


✍ አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ብርድ ባይደቁስው ምን ጠግቦ ቢበላም
ወንድ ልጅ ብቻውን አንድ ቤት አይሞላም
ነይ አብረን እንኑር
ነይ አብረን እንሁን
ከቤቴ ግቢ እና ጎጆየን አድምቂ
አለሁልህ ብለሽ ሀዘኔን አርቂ
የብቸኝነትሽን ኮፈኑን አውልቂ
ነይ አብረን እንኑር
ነይ አብረን እንሁን
ደረቴ ላይ ተኚ አለምን እንርሳ
ከጡትሽ ላይ ልደር ላፍታ ሳልነሳ
ነይ አብረን እንኑር
ነይ አብረን እንሁን
ብቻ ማደር ክፉ በናፍቆት ይገድላል
ለእኛም ለፈጣሪም አብሮነት ይሻላል
👫👫👫👫👫👫
ነይ አብረን እንሁን

✍ ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።

#ተፃፈ_በዳዊት
@Davunin

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


👍ታላቅ ቅናሽ ለታላቁ ጥምቀት
ከ99,935 ወደ 93,357 ብር ቅናሽ አድርገናል

የሚመኙት ያማረ ነገ እውን ይሆን ዘንድ
ዘመናዊ የሆኑትን የአያት አፓርታማዎች
ከ522 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ
በኢትዮጵያ ብር ተዋውለው
የቤት ባለቤት ይሁኑ

🙏   በካሬ 93,357 ብር
🙏    ከ70 ካሬ እስከ 150 ካሬ
🙏    ከባለ አንድ መኝታ  እስከ ባለ አራት መኝታ
🙏    100% ለሚከፍል 15% ቅናሽ


🏩  በCMC ምካኤል
🏩  መሪ
🏩  በአያት72
🏩  በአያት ባቡር ጣቢያ
🏩  በአያት ሎሚያድ


ያማረ ነገዎን ይገንቡ!

የበዓል ቅናሽ እንዳያመልጠወ ።


ለበለጠ መረጃ:

☎️ 0911468394
@abela1987


አጓጉል ባልንጀርነት

ምናይት አመል ነው እናንተዬ!?

የሆነች ጓደኛ ነበረችኝ። ምንም ነገር ብነግራት ከሌላ ወገን ካላረጋገጠች እኔ በነገርኳት ብቻ አታምንም። ቀድሜ ስላነበብኩት ታሪክ ወይም ገጠመኝ ብነግራት ከቻለች ያነበብኩትን አግኝታ አንብባ ታረጋግጣለች ካልሆነ እኔን ባለማመን ውስጥ ትሰነብታለች። ከእከሌ ጋር ሆነን ስለበላነው ምግብ ሳወራት እከሌን በሆነ አጋጣሚ ስታገኘው

“አብራችሁ በላችሁ አይደል? “

ብላ ትጠይቃለች። የሆነ ቦታ ልንሄድ ነው ስላት አብረውኝ የሚሄዱትን

“ልትሄዱ ነው እንዴ?”

የገዛሁት ልብስ አልሆነኝም ስላት ወደ ልጆቼ ዞራ

“አልሆናትም እንዴ? ትላቸዋለች።

አድራሻ ስነግራት ማፕ አውጥታ ታረጋግጣለች። ይሄ ከተማ የሚገኘው ከዚህኛው ከተማ ቀጥሎ ነው ካልኳት ጉግል አድርጋ ታረጋግጣለች።

ቀድሜ በቲቪ አይቼ ነገ ዝናብ አለ ካልኩ “Siri” ብላ አርተፊሻሏን ትጠይቃለች።

በዝናብ ምክኒያት የሰርግ ቦታና ሰዓት የቀይሯል ስላት ሌላ ሰው ጋር ደውላ መቀየሩን ጠይቃ ታረጋግጣለች።

በቃ ምን አለፋችሁ ምንም ምንም ነው የማታምነኝ እና የምሰጣትን መረጃ በቀጥታ የማትጠቀምበት! ለብዙ ግዜ ግራ እየገባኝም ቢሆን ዝም ነበር የምለው። ይሄ አመሏ ግን እኔ ላይ ብቻ ነው ለሁሉም ሰው ይሆን? ብዬ የራሴን ጥናት ማድረግ ጀመርኩ። ለማመን አረፍተ ነገሩን እስኪጨርስ እንኳን እንደማትጠብቅ አስተዋልኩ።

ማታ በስልክ እንዳመመኝ ነግሬአት በነጋታው “ተሻለሽ ወይ?” ብላ በመጠየቅ ፋንታ “ዛሬ ድነሻል!” ብላ ወሬ ትጀምራለች። አሞኛል ያልኳትን አላመነችም ማለት ነው? እላለሁ ለራሴ። እየቆየሁ ግን ያመኝ ጀመር! ምናልባት ብታሻሽል ብዬ የሆነ ነገር እነግራትና Siriን ጠይቂያት፣ ከእከሌ አረጋግጪ ስላት ባልሰማ ታልፋለች እንጂ ለምን አትለኝም። አንዳንዴ የሆነ ነገር በሰው አስነግራትና የሰማችውን ወዲያው አምና እንዲህ ሆኗል ብላ ለኔ ትነግረኛለች። ቀድሜ የነገርኳት እኔ ብሆን ኖሮ ግን ሌላ ማረጋገጫ ትፈልግ ነበር። አንዴ ደግሞ እነሱ ሰፈር ያለ ስቶር እኔ በጣም የምፈልገው ዕቃ ላይ የአጭር ግዜ ሃይለኛ ቅናሽ አድርጎ በፅሁፍ መልዕክት እባክሽን ከስራ ስትመለሺ እግረ መንገድሽን ይህን ዕቃ አንሺልኝ ብሩን Cash up አደርግልሻለሁ አልኳት። ሁለት ቀን ሲያልፍ ደውዬ ገዛሽልኝ? ስላት

“አይ ገና አልሄድኩም”

ለምን? የምትጠይቂው ሰው በቅርብ ካላገኘሽ ጉግል አታደርጊም ነበር? ካልቻልሽ ደግሞ አልችልም አትይኝም ነበር? አልኳት።

“የባሏን ስም ጠቅሳ እሱን ጠይቄው ነበር ስላልመለሰልኝ ነው” አትለኝም?

እውነት ለመናገር ከሆዴ ውስጥ የተቃጠለ ጪስ በጉሮሮዬ በኩል መውጣት ጀምሮ ነበር። እሺ ችግር የለም! ብዬ ስልኩን ዘግቼ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ነድቼ ሄጄ ለመግዛት ብዬ መኪናዬን አስነስቼ ለማንኛውም ብዬ ወደ ዌብሳይቱ ስገባ እቃው sold out ሆኗል።

በፊቱኑም ያን ያህል ሩቅ ሆኖ ሳይሆን ለሷ ስለሚቀርባት እና በደጃፉ ስለምትመላለስ ዕድሉን ለመጠቀም ነበር። ወዳጄ በገንኩ አይገልፀውም!! ዕቃው ስላመለጠኝ እንዳይመስላችሁ የበገንኩት። የእሷ እኔን ያለማመንን ልክ እና ለዚያ ያደረሳት የደበቀችኝ ምክኒያት ምን ይሆን የሚለው ጉዳይ በጨጓራዬ ውስጥ ጉልቻ ደርድሮ፣ ማገዶ ሰትሮ እሳት ማንደድ መጀመሩ ተሰማኝ። እኔን ያለማመንን በአደራ እንደተቀበለችው ዕቃ ነው የምትቆጥረው። አትጥለውም፣ አታዝረከርከውም፣ ለአፍታ እንኳን አትተወውም።

እየደከመኝ ሄደ? ውስጤ ጓደኝነታችንን ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ጀመረ። ማለቴ በየወንዙ እየተማማልን እንዴት ነው የልብ ጓደኛ ሆነን የምንቀጥለው? እያልኩ ማብሰልሰል ያዝኩኝ። ሌላ የማስብበትን ግዜ ተሻማብኝ። ደጋግሜ ሌላ ማረጋገጫ የምትፈልግለትን ነገር እንዳትጠይቀኝ ብነግራትም አልሰማ አለች። ልቤ ምክር ሳይጠይቀኝ እየራቃት ሄደ። አንድ ቀን ግን ተስፋ ቆረጥኩ! አብረን ሆነን አመመኝ። ለባሌ ደውላ

“ታማለች እንዴ?” አለችው!!

ይኸው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከተለየሁዋት አምስት አመት ሆነኝ። ደሜ በትክከ‍ል መዘዋወር ጀምሯል። 😄አንዳንድ ጉድኝቶች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዝናልና ይፈተሹ ለማለት ነው።

ዛሬ ፎቶ አይቼ ትዝ ብላኝ ነው። ምፅ! 😴😴

አይዳ (ቃል እና ቀለም)

ፉት እያልን☕️

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


🎁 አሸናፋዎቹ  ዛሬ ይታወቃሉ⁉️

ለጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው✅

⭐️500STAR ለ 5 እድለኛ ሰዎች, አሸናፊውን TELEGRAM RANDOM ይመርጣል  ለመሳተፍ 4 ቱን ቻናሎች የግድ መቀላቀል ይኖርባቹሀል። Share ስታደርጉ ደግሞ እድላችሁ ይሰፋል

🎁መልካም እድል 🙏

የኛ ቤተሰብ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን 👍

ሞቅ ሞቅ አርጉት እንጂ👍🔥

መልካም እድል


Dubai Furniture Ethiopia ዱባይ ፈርኒቸር ኢትዩጵያ🇪🇹 dan repost
Розыгрыш 500 Telegram Stars, которые будут распределены среди 5 победителей
Условия участия:
  • В розыгрыше участвуют все подписчики
  • Необходимо быть подписчиком 5 kanal
  • Конец розыгрыша: 07.02.2025 22:20


❤እህት!❤

አዛኝ እሩህሩህ ደግ ልብ ያላት
ሲከፋህ ምታዝን ሆና እንደ እናት።
ደክማ ምታሳድግ በችግር ተቃጥላ
መሸሸጊያ ነች የክፉ ቀን ጥላ።

✍️ገጣሚ ዘሪሁን
ጥር 28/2017

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


“ያድርስልህ ለሰው”
————-//———-

አርከፍክፍ እንባህን፣ ስሜትህን ማግደው
በቁስልህ ምድጃ ህመምህን አንድደው፤

ይንተክተክ ውስጠትህ ቱግ ቱግ እያለ!
መግላሊቱን ይግፋ እየገነፈለ፤
ይብሰል! እሳት ይምታው እንዲ’በላ ጣፍጦ
ጥልል ይበል ስቡ ይታይ ተቅለጥልጦ
ልብህ ደዌ ችሎ፣ ስቃይ አጣጥሞ
እግርህ ሰላ ብሎ፣ ከናድህ ፈርጥሞ
ራዕይ ለመሞላት እንዲወስድህ ፍጥሞ፤

ቁስልህን ጉልቻ፣ መከፋትህን ድስት
እንባህ ቤንዚን ይሁን፣ ማቃሰትህ ክብሪት
የመድረሻ አቅጣጫ እንዲሰጥህ ምሪት፤

ስሜትህን ማግደህ ሰባራው ልብህ ላይ
ለኩሰው እሳቱን፣ አጢያጢሰው
ጢሱን ይሂድ ወደ ሰማይ!

አግመው ነዲዱን ይትጎልጎል ቆስቁሰው
አውሎውን አንፍሰው! አየሩን አምሰው!!
የልብህን መሻት ላልተገነዘቡት
ያሳውቅ ለአገር፣ ያድርስልህ ለሰው።

ስማኝማ አንተዬ!!

አልያ እንኳን እቀድ የም’ተገብረው
እንኳን የድል ዜማ የምትዘምረው
ስለ መዳረሻህ የምትፈክረው
ስጋና እስትንፋስም ከደዌህ አብረው
ከማትስማማቸው፣ ከጠሉህ ተባብረው
ይዶልቱብሃል ሊሸኙህ አሻግረው!!

አይዳ (ቃል እና ቀለም)

ተፃፈ በቀን 12/4/2024
Break Room በምሳ ሰዓት

ግጥሙን ለመፃፍ ውስዋስ የሆነኝ

“TURN YOUR PAIN IN TO POWER”

የሚል ባለቤቱን ያላወቅሁት ጥቅስ ነው።

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ደጉ ጠላቴ
*///
ነፍስና ሥጋዬን ሊቀጣ፣
መከራዬ
እንደ መብረቅ መጣ፡፡
ለዘለዓለም ሊያጠፋኝ፣
በፍላጻው መታኝ፡፡
ይገርማል!
ጠላቴ ሳይገባው
መልካም ሥራን ለመደ
ሊነቅለኝ መጣና
ጭራሽ ተክሎኝ ሄደ፡፡
****
ገጣሚ፦ዳዊት ፀጋዬ፣አርነት የወጡ ሐሳቦች

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


Forex Free Signal
💰 ኑ አብረን ገንዘብ እንስራ
💵
Join us 👇👇👇


ምንም ነገር ትስራ የትም ቦታ ትታይ
ይከፋኛልና ሴት ልጅ ወድቃ እንዳላይ

✍ ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


አካል ቡጢን ፈርቶ
በምላሴ ሸጥኳት
እህቴ ናት ብዬ
እኔው ሚስቴን ዳርኳት

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19


ክርስቶስን

ከአይሁድ ጅራፍ በላይ ፥ ጉንጮቹን የሳሙት
የይሁዳ ከንፈሮች ፥ ናቸው ያሳመሙት።

ከጠላትህ ይልቅ ፥ የነከሰህ ያኃል
ወዳጅ በሽንገላ ፥ ሲስምህ ያምኃል።

✍ አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.