Buna Tech ቡና ቴክ

Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha

Welcome to our Buna Technology Telegram channel
It's a channel where you find the amazing and new things about Computer and technology that you don't know in photo and writing, you get a variety of funny surprises and you get knowledge. Thanks 🙏

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri

Microsoft Skype የተሰኘውን ፕላትፎርም ሊዘጋ ነው።

ከAugust 29, 2003 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የበረው Skype ከ21 አመት በኋላ ማለትም በmay 5, 2025 ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ ሊቋረጥ ነው።

Microsoft ይህንን ፕላትፎርም በ2011 $8.5 billion አውጥቶ ቢገዛውም አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተበለጠ መጥቷል።

የተጠቃሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱና Teams የተሰኘው የmicrosoft ፕላትፎርም ይበልጥ ውጤታማ መሆኑ ለskype መዘጋት እንደምክነያት ይጠቀሳሉ።

የskype ተጠቃሚዎችም skype ላይ ያላቸውን chat historyና መረጃዎች ወደ Microsoft Teams ማዘዋወር ይችላሉ ተብሏል።

በርካቶቻችን ለመጀመሪያ ጊዜ video call ከማውራት ጀምሮ በርካታ ትዝታዎች በዚህ ፕላትፎርም ላይ አሉን።

በዚህ መረጃ የተሰማችሁን አሳውቁን።

©bighabesha_softwares

ስልካችሁ SAMSUNG ከሆነ ያለበትን እያንዳንዱን ችግር ቼክ የምታደርጉበት app
Samsung members

Play store ላይ ስለማታገኙት በዚህ ሊንክ ማውረድ ትችላላችሁ።
https://t.me/big_habesha/287

ስለ አጠቃቀሙ ከደቂቃዎች በኋላ TikTok ላይ video post አደርጋለሁ።

የዲላ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት dan repost
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ፣

ካራት የካቲት 19/207 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና በቀሪ ግማሽ  ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አቶ ተካልኝ አክለውም ቢሮው በክልሉ ያሉ ዞኖች በዘርፉ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአንዳንድ ዞኖች  በጥንካሬ እየተመራ መሆኑን እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሚገባ እየተመራ ባለመሆኑ ኢኒሼቲቩን ለማሳካት በጉዳዩ ዙሪያ መምከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ወቅቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የዳበረ ሀገርን ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ቢሮው በክልሉ ዞኖች የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ  በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን እንደ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ እመቤት ተናግረዋል።

Biruk Afework dan repost
Welcome to My Channel!

Join me as I share insights from my work and personal life, including:

Work Projects

Personal Experiences

Milestones  Achievements

Inspirations  Motives

Book Reviews

Challenges  Failures

Lessons Learned Along the Way

Expect valuable recommendations on resources, engaging QA sessions, and exciting guest features. Let’s build a supportive community together as we explore our journeys.

Contact Me :@Biruk_Buraa

Join me: here
https://t.me/BirukAfework

Adobe Photoshop በSamsung Galaxy ስልኮች ላይ መስራት ሊጀምር ነው

ዝነኛው የፎቶ ማቀናበሪያ ሶፍትዌር Adobe Photoshopን ከአንዳንድ ገደቦች ጋር በስልክ መጠቀም ሊቻል ነው።ይህም ለጊዜው የታቀደው በgalaxy ስልኮች ላይ ነው።

ይህ መተግበሪያ በርካቶች ከሚውቁት የተለየ ሲሆን ለተጠቃሚዎችም ከዴስክቶፕ version አንፃር ቀላል እና ለአጠቃቀም ምቹ ነው።

የዴስክቶፕ versionኡን ሙሉ በሙሉ ባይተካም መሰረታዊ የሆኑ edits ለማድረግ ያስችላል።

አሁን ላይ ካሉት የስልክ editing softwares በእጅጉ የተለየ ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ብዙ በAI የተደገፉ features እንደሚያካትትም ተገልጿል።

በዚህ ሀሳብ ዙሪያ አስተያየታችሁን አካፍሉን።

Meta ይቅርታ ጠይቋል።

ከትናት ጀምሮ የሚረብሹ የተለያዩ ቪዲዮዎች  reels ላይ በመምጣታቸው ምክንያት ብዙዎች X ላይ በመውጣት ሲነጋገሩበት ነበር። ይህንንም ችግር አሁን እንዳስተካከለው Meta አስታውቋል። በይፋም ይቅርታ ጠይቀዋል።

እኔ እራሴ check እንዳደረኩት Instagram reels ላይ ቪዲዮዎች ቢስተካከሉም የተለያዩ ችግሮች (bugs) ግን አሁንም አሉ።
ለምሳሌ
⚫ሁለት ወይም 3 ጊዜ scroll ካደረጋችሁ በኋላ scroll ማድረግ አትችሉም stack ያደርጋል።
⚫አንዳንድ ቪዲዮዎች ድምፃቸውን መዝጋት አትችሉም። አፕሊኬሽኑን ብትዘጉት እራሱ ድምፁ አይጠፋም። ስልካችሁን restart ወይም ዳታ እያበራችሁ ማጥፋት ይኖርባችኋል።

እናንተ ምን አስተዋላችሁ?

Instagram ምን እየሆነ ነው?

ከትናንት ጀምሮ Instagram reel ላይ እጅግ ለማየት የሚሰቀጥጡ የግድያ፣ የእራ*ን ማጥፋት እነዲሁም ሌሎች አደገኛ ቪዲዮዎች በብዛት እየተለቀቁ ነው።

ይህንንም በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ሲሆን ምክንያቱ ምን እንደሆነ Meta በይፋ ያለው ነገር የለም።

ይህ ነገር የሚረብሻችሁ ሰዎች ለተወሰነ ቀን Instagram ላይ ባትገቡ እመክራለሁ። ህጻናት ከሚጠቀሙበት ስልክ ላይም አፕሊኬሽኑን ብታጠፉት ይመከራል።

እንኳን ለህፃናት እኔንን እራሱ ዘገነነኝ።

አዲስ ነገር ካለ ተጨማሪ መረጃ አደርሳችኋለሁ።

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ፣

ካራት የካቲት 19/207 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና በቀሪ ግማሽ  ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አቶ ተካልኝ አክለውም ቢሮው በክልሉ ያሉ ዞኖች በዘርፉ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአንዳንድ ዞኖች  በጥንካሬ እየተመራ መሆኑን እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሚገባ እየተመራ ባለመሆኑ ኢኒሼቲቩን ለማሳካት በጉዳዩ ዙሪያ መምከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ወቅቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የዳበረ ሀገርን ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ቢሮው በክልሉ ዞኖች የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ  በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን እንደ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ እመቤት ተናግረዋል።

Biruk Afework dan repost
Welcome to My Channel!

Join me as I share insights from my work and personal life, including:

Work Projects

Personal Experiences

Milestones  Achievements

Inspirations  Motives

Book Reviews

Challenges  Failures

Lessons Learned Along the Way

Expect valuable recommendations on resources, engaging QA sessions, and exciting guest features. Let’s build a supportive community together as we explore our journeys.

Contact Me :@Biruk_Buraa

Join me: here
https://t.me/BirukAfework

ሴቶች ከወንዶች የበለጠ "አፒራንስ አንዛይቲ' ለተባለው የጭንቀት አይነት ተጋላጭ ናቸው አፒራንስ አንዛይቲ ማለት ስለ እራሳችን መልክ፣ ቁንጅና እና ውበት መጨነቅ ማለት ነው

❖ ወንዶች በአፒራንስ አንዛይቲ የማይጠቁበት አንዱ ምክንያት ለእራሳቸው የሚሰጡት ግምት እጅግ በጣም የተጋነነ በመሆኑ ነው ሲሉ የስነልቦና አዋቂዎች ይመሰክራሉ፡፡

#Share_x5
#Join
@bunatech
@bunatechdiscussion

✅ያውቁ ኖሯል ?

✅በአለማችን ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወደ አደገኛ ሀከሮች ኪስ በህገወጥ መንገድ በ Internet  አማካኝነት ገብቷል !

✅ወደ ፊትም ይህን መሰል ጥቃቶች ለመከላከል የተማረ የሰው ሀይል ያስፈልጋል፡፡

✅በተደረጉ ጥናቶች በነጮች 2021 በመረጃ ደህንነት እና ጥበቃ (Cyber Security ) ዘርፍ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ክፍት የስራ ቦታዎች ይኖራሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

✅እና ዝግጁ ናችሁ??

የሳይበር ጥቃት ሙከራ ቢደረግብዎ የመጀመሪያ ርምጃዎ ምንድን ነዉ?
የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነትና በመጠን እየጨመሩ ይገኛሉ። እነዚህ ጥቃቶች በሀገር ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ ነዉ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚገኘዉ የኢትዮጵያ የኮምፒዉተር አደጋ መከላከልና መላሽ መስጫ ቡድን(ethio-cert) ተቋቁሞ የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር ደህንነት በማስጠበቅ ሀገራዊ ሚናዉን እየተወጣ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛዉም አካል የትኛዉም አይነት የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ቢደርስቦት ወዲያዉኑ ለኢትዮ-ሰርት ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።
የሚከተሉትን የኮሚዩኒኬሽን አማራጮችን በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ እንደሚችል ለመግለጽ እንወዳለን።
👉ነጻ ጥሪ------------------------933
👉ስልክ ቁጥሮች--------------+251-993939270/993531965
👉ዋትሳፕ ቁጥር---------+251913255353
👉የኢሜይል አድራሻ -------- ethiocert@insa.gov.et
👉ፖስታ ሳጥን ቁጥር---------124498
👉ዌብ ሳይት------------ https://ethiocert.insa.gov.et

Wright ወንድማማቾች Orville Wright እና Wilbur Wright በአውሮፕላን አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፣ አንድላይ የተጓዙት ፣ ምክንያቱም ፣ አደጋ ከተከሰተ ፣ አንዱ ቢሞት ፣ አንደኛው ስራውን ለማስቀጠል በሚል ሀሳብ ። እነኚ ወንድማማቾች  አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሩት መሆናቸው ይታወቃል።

ቻይና በአዲሱን የ AI ሞዴልን Deep seek ለማበልፀግ 6 ሚሊዮን ዶላር አውጥታለች !

በአንፃሩ ሳዑዲ አረቢያ 7 ጨዋታዎችን ብቻ ለተጫወተው ኔይማር 90 ሚሊዮን ዶላር  ከፍላለች !

በኢትዮጵያ የተመረተ ኢ-ፓስፖርት ይፋ ሆነ

በTOPPAN Security Ethiopia እና በEthiopia investment holding የተመረተው ይህ ፖስፖርት የግለሰቡን የbiometric መረጃዎች የያዙ electronic chips ያካተተ ነው።

ይህ ፓስፖርት ደህንነትን ከማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያን ከማስተዋወቅ እና ለዜጎች ፈጥኖ ከመድረስ ረገድ አውንታዊ ተፅዕኖ እንዲሚኖረው ተመላክቷል።

በፊት አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ፓስፖርት የቆየ እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይወጣበት እንደነበርም ተመላክቷል።

ከዚህ በኋላ ፓስፖርት ለሚያወጡ ሰዎች አዲሱ ዲጅታል ፓስፖርት የሚሰጣቸው ሲሆን ለዚህም ሲባል 1.5 ከሚልዮን በላይ ኢ-ፓስፖርት ተዘጋጅቷል።

ይህ ኢ-ፓስፖርት ከ25 አመት በላይ ለሆናቸው የአገልግሎት ዘመኑ 10 አመት ነው። ዋጋውም ነባሩ ፓስፖርት ሲሰጥበት ከነበረው ዋጋ ጋር እኩል ነው።

በተጨማሪም ይህ ፓስፖርት አለም የደረሰበትን የፓስፖርት ቴክኖሎጂ መጠቀሙ እና በከፍተኛ ሁኔታ የደህንነት ችግሮችን መቀነሱ ከነባሩ ፓስፖርት የሚለይባቸው ምክንያቶች ናቸው።

በዚህ ፓስፖርት ዙሪያ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

የጌዴኦ ዞን ሳኢቴ መምሪያ ኃላፊ የ6ኛ ዙር ኮዲንግ ሰልጣኞችን ጎበኙ።

ዲላ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

ከተጀመረ ሶስተኛ ወሩን ያስቆጠረው 6ኛ ዙር የኮዲንግ ሰልጣኞችን የጌዴኦ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ #ደረጀ_ሾንጣ በዛሬው እለት በት/ቤታችን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

የማዕከሉ ኃላፊ እና የስልጠናው መምህር ስለ ስልጠናው ሰፊ ገለፃ የሰጠ ሲሆን አቶ ደረጀም በማዕከሉ ተገኝተው በተማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ ስራዎችን አይተዋል።

በ6ኛው ዙር 31 ወንዶች እና 29 ሴቶች በድምሩ 60 ህፃናት ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የተማሪዎችም የክፍል ደረጃቸው ከ6ኛ እስከ 10ኛ ነው። አጠቃላይ አራት ኮርሶችን በስልጠናው የሚመስዱ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ሁለት ኮርሶችን ጨርሰው አሁን ላይ python basic ኮርስ እየወሰዱ ይገኛሉ። በቀጣይ የድረ ገፅ ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን ከስልጠናው ጎን በጎን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በሐምሌ ወር የተጀመረው የ5ሚሊዮን ኮደርስ የኦን ላይን ስልጠና ተመዝግበው የሚወስዱ ይሆናል። በስልጠናውም አለምአቀፉዊ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።

አቶ ደረጀም ስለ ስልጠናው ለተማሪዎች ግንዛቤ የሰጡ ሲሆን ከመምሪያው ባለሙያዎችን በመመደብ ተማሪዎች ድጋፍ እንዲሚያገኙ ለተማሪዎቹ ቃል ገብተውላቸዋል ።

የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

Call me an isolated person, or whatever you want, but I don’t need to know
the stories of some random strangers on social media.

Source:#NOBODYCARES Dara ly

የሳይበር ጥቃት ሙከራ ቢደረግብዎ የመጀመሪያ ርምጃዎ ምንድን ነዉ?
የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነትና በመጠን እየጨመሩ ይገኛሉ። እነዚህ ጥቃቶች በሀገር ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ ነዉ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚገኘዉ የኢትዮጵያ የኮምፒዉተር አደጋ መከላከልና መላሽ መስጫ ቡድን(ethio-cert) ተቋቁሞ የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር ደህንነት በማስጠበቅ ሀገራዊ ሚናዉን እየተወጣ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛዉም አካል የትኛዉም አይነት የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ቢደርስቦት ወዲያዉኑ ለኢትዮ-ሰርት ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።
የሚከተሉትን የኮሚዩኒኬሽን አማራጮችን በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ እንደሚችል ለመግለጽ እንወዳለን።
👉ነጻ ጥሪ------------------------933
👉ስልክ ቁጥሮች--------------+251-993939270/993531965
👉ዋትሳፕ ቁጥር---------+251913255353
👉የኢሜይል አድራሻ -------- ethiocert@insa.gov.et
👉ፖስታ ሳጥን ቁጥር---------124498
👉ዌብ ሳይት------------ https://ethiocert.insa.gov.et

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.