ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ፣
ካራት የካቲት 19/207 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማና በቀሪ ግማሽ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ተካልኝ አክለውም ቢሮው በክልሉ ያሉ ዞኖች በዘርፉ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአንዳንድ ዞኖች በጥንካሬ እየተመራ መሆኑን እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሚገባ እየተመራ ባለመሆኑ ኢኒሼቲቩን ለማሳካት በጉዳዩ ዙሪያ መምከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ወቅቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የዳበረ ሀገርን ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።
ቢሮው በክልሉ ዞኖች የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን እንደ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ወ/ሮ እመቤት ተናግረዋል።