EOTC TV (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri




አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

መ/ር ጌታቸው በቀለ
                                                                                                                                                                 በ፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ እንደ ተመሠረተ በሚነገርለት በደብረ ዋሊ ወይም ዋልድባ ገዳም የተነሡ ስመ ጥር መነኩሴ መናኝና የጽድቅ መምህር ናቸው፤ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ሳሙኤል በመቶ ዓመታቸው ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ዋልድባ አብረንታት ዐርፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም የጻድቁን ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡

አቡነ ሳሙኤል የገዳማዊ ሕይወት እጅግ ተስፋፍቶ በነበረበት በ፲፫ኛው እና በ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣ ብፁዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ የእነዚህም የቆብ ልጅ በሆኑት በገዳመ በንኮል በአባ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ምንኩስናን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን በተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋ አገልግለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የተወለዱት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ አክሱም ሲሆን አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባሉ። ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ አባታቸው ለአክሱም ቄሰ ገበዝ እንደሰጧቸውና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጠናቀው ለአገልግሎትም ዲቁናን ተቀብለው በንቃትና በልባምነትም ቤተ ክርስቲያንን ለሰባት ዓመት ካገለገሉ በኋላ ጌታችን በወንጌል “ፍጹም ልትሆን ብትወድ…” /ማቴ.፲፱፥፳፩—፳፪/ ያለዉን ለመተግበር ለአክሱም ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ሚገኘው ደብረ በንኮል ገዳም ገብተው ከገዳሙ ሊቃውንት የብሉያትንና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል።/ገድለ አቡነ ሳሙኤል/፡፡

አባ ሳሙእል ዘዋልድባ አባ እንጦንስና መቃርስ የተከተሉትን የምንኩስና ሕይወት በሰፊው ተጓዘበት። ትጋቱንና የምናኔ ሕይወቱን ያዩ መናንያን አበው መነኮሳት የእነሱን የምንኩስና አክሊል እንዲቀበል ፈልገው የገዳሙን አበ ምኔት (ኃላፊ) አባ መድኃኒነ እግዚእን ይመክሩና ይለምኑ ነበር፡፡ አባ መድኃኒነ እግዚእም የሚያየውንና ከመነኮሳቱም የሰማዉን ተቀብሎ በወቅቱ ለምንኩስና ከተዘጋጁት ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ደቀ መዛሙርት ዉስጥ አንደኛው እንዲሆኑ ወስነው አመነኮሷቸው፡፡

በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሡ ቅዱሳን “ሳሙኤሎች” ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ ሳሙኤሎች ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል፣ ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና ያሳዩ የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም:-

1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው፡፡

“ፀሐይ ሳሙኤል ዘዋሊ”

አባ ሳሙኤል በገድላቸው እንደምንመለከተው “ፀሐይ ሳሙኤል ዘዋሊ” ይላል፡፡ ‘ዋሊ’ የዋልድባ ገዳም የቀድሞ መጠሪያ ስሙ ነው፡፡ ዋልድባ ገዳም በጣም ተዳክሞ በነበረበት ዘመን ተነሥተው ዋልድባን ከጥፋት የታደጉ፣ መናንያንን በማሰባሰብ እንደገና ያስፋፉ በመሆናቸው “ዘዋሊ” ይሏቸዋል፡፡  አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው ግርማ ሌሊቱን፣ ድምፀ አራዊቱን፣ ፀብዓ አጋንትን፣ የሌሊት ቁር፣ የቀን ሐሩርን ታግሰው የጽድቅን ጎዳና ተከትለው ብዙ ገድል በመሥራት ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርገዋል ይህም በገድልና በተአምራት መጽሐፋቸው በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል።

ብፁዕ አባታችን ዉዳሴዋን ቅዳሴዋን ሲያደርሱ እመቤታችን የፍቅሯ ምልክት ይሆን ዘንድ ነጭ እጣንና የሚያበራ እንቁ ሰጥታቸዋለች። አባታችንም “እነዚህን ስጦታዋች የምትሰጭኝ ምን ስላደረግሁ ነው?” ብለው በጠየቋት ጊዜ “እጣኑ የምኡዝ ክህነትህ፣ ዕንቁው የንጽሕናህ የድንግልናህ የቅድስናህ ናቸው” ብላ ተርጉማላቸዋለች። አባ ሳሙኤል ዘዋልድባን የዱር አራዊት ሁሉ ይገዙላቸውና ይታዘዙላቸው  እንደነበረ በዚሁ በገድል መጽሐፋቸው በሰፊዉ ተተንትኗል፤ ይልቁንም ሁለት አናብስት የሁል ጊዜ አገልጋዮቹ ነበሩ። ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም፣ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እሳቸው በአንዱ አንበሳ ተቀምጠው መጻሕፍቶቻቸውን በሌላው አንበሳ ላይ ጭነው እንደሚጓዙ ገድላቸው ያስረዳል። ሌሎቹም አራዊት አባታችንን ሲያዩአቸው እናቱን እንዳየ እንቦሳ በደስታ ይፈነጩ ነበር።

ጻድቁ አባታችን ወንጌልን ለማስፋፋት በየሀገሩ ዞረው አስተምረዋል፡፡ ብዙ የትሩፋትንም ሥራ ሠርተዋል ጣና ውስጥ በሚገኙ ገዳማትና ማን እንደአባ ያሳይ እንዲሁም ገሊላ ቦታዎች በምድር ዉስጥ ጉድጓድ ቆፍረው እየገቡ ከእህልና ዉኃ ተለይተው ሁለትና ሦስት ሱባኤ ይፈጽሙ ነበረ። ከሁለት ቅዱሳን ወንድሞቻቸው ከአባ ሳሙኤል ዘወገግና ከአባ ብንያም ዘታህታይ በጌምድር ጋር በመሆን ምድረ ከብድና ዝቋላ በመሔድ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር በተገናኙ ጊዜ ብዙ ተአምራት እንደተደረገላቸው መጽሐፈ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በኤርትራ የሚገኘዉን ገዳም ከመሠረቱት ከአቡነ ፊልጶስ ጋር እንደተገናኙና የእግዚአብሔርን ክብር ይጨዋወቱ እንደነበር በገድላቸው ተጽፏል።

የአባ ሳሙኤል የዕረፍት ጊዜ ሲደርስም በተወለዱ በአንድ መቶ ዓመት በምናኔ፣ በተባህትዎ እና በምንኩስና ከዚህ ዓለም ተለይተው ግርማ ሌሊትን፣ ድምፀ አራዊትን፣ ፀብአ አጋንንትን፣ የቀን ሐሩር፣ የሌሊት ቁሩን ታግሰው ራቡን ጥሙን ችለው መላ ዘመናቸውን የተቀበሉትን ፀዋትወ መከራ አይቶ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸው ዘንድ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችን ካሉበት በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማዕታትን አስከትሎ መጥቶ በሕይወት ሳሉ የሰጣቸዉን ቃል ኪዳን በዕረፍታቸዉም ደግሞ “ስምህን የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህ በአማላጅነትህ ያመነ፣ በመቃብርህ በመካነ አፅምህ የተማፀነ የአንተ ቤተሰብ ሆኖ አንተ የገባህበት አገባዋለሁ። ርስት መንግሥተ ሰማይን አወርሰዋለሁ” ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ንጽሕት ነፍሳቸው በእደ መላእክት፣ በመዓዛ ገነት ከሥጋዋ ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በነብዩ በዳዊት ቃል መዝ.፻፲፮፥፲፭ “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” እያሉ በታላቅ ዝማሬ፣ በይባቤ፣ በዕልልታና በሕይወት ወደ ዘለዓለም የዕረፍት ቦታ አስገቧት።

ጻድቁ አባታችን በተወለዱ በመቶ ዓመታቸው ታኅሣሥ ፲፪ ዋልድባ አብረንታንት ዐርፈዋል።  እንዲሁም ወር በገባ 12 ደግሞ ወርኃዊ በዓላቸው ነው።

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት፣ በረከት፣ አማላጅነት አይለየን!!
                          ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ዋቤ መጻሕፍት
      ✍️ ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
      ✍️ ዝክረ ዱሳን
      ✍️ Saints of The Orthodox Church










Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ታላቅ የንግሥ በዓል ጥሪ


ማስታወቂያ
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በመቶ ብር ትውልድ የሚታነጽበትን ፕሮጀክት እየደገፉ ይሸለሙ
- ሙሉ ወጪዎ ተችሎ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጉብኝት
- የግብጽ ገዳማት ጉብኝት
- የሀገር ውስጥ ገዳማት ጉብኝት
- የብራና ሥዕለ አድኅኖ
- የአንገት ወርቅ እና ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች ለባለ እድለኞች ተዘጋጅተዋል ይህ ሁሉ በ መቶ ብር ።

ገቢው ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማእከል እያስገነባ ላለው ባለ 12 ፎቅ የሕፃናት እና ወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማእከል እና አገልግሎት ማስፋፍያ የሚውል ።

የዚህ ሕንጻ ፕሮጀክት አስፈላጊነት በጥቂቱ
- በሁለት በኩል የተሳለ ትውልድ ማፍራት
- የግቢ ጉባኤ አገልግሎትን ማሳደግ
- የአብነት ትምህርትን ማስፋፋት
- ዘመኑን የዋጁ ካህናትና ሰባኪያን ማፍራት
- ኢ-አማንያንን ማስተማርና ማጥመቅ
- ሴተኛ አዳሪዎችን ካሉበት ሕይወት ማውጣት
-እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶች ለመደገፍ እና ለማስፋፋት በቋሚነት የቦታም ሆነ የፋይናንስ ችግር የሚፈታ የሕንጻ ፕሮጀክት ለመስራት የበኩልዎን ይወጡ

ትኬቶቹን :--
_ በሁሉም የአሐዱ ባንክ ቅርንጫፍ
_ በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች
_ በማኅበረ ቅዱሳን ንዋየተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ
_ በአጥብያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ት\ቤት ያገኙታል
ለዚህ የትውልድ መገንቢያ ሕንፃ ግንባታ የበረከት እጅዎን ይዘርጉ፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ
አሐዱ ባንክ. 0002505310101
ኢ.ንግድ ባንክ. 1000303949112
አቢሲንያ ባንክ. 68960665
አዋሽ ባንክ. 01304868950900
ዳሽን ባንክ 0088211311011
ዓባይ ባንክ 1891119601313011

ለበለጠ መረጃ
0902 50 11 31
0946 38 38 92






ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮለት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ከ37 ዓመት በኋላ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም እቅዳሴ ቤቱ እንደሚከበር ተገለጸ።።
ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ
(#EOTCTV ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሀገረ ስብከት በሶዶ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ እንደሚከበር የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ገልጸዋል።

ገዳሙ በብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት በ12ኛ ክ/ዘመን መጨረሻ በ13ኛዉ ክ/መ መጀመሪያ የተመሠረተ ኾኖ በርካታ ዓመታት ያስቆጠረ በዝባፈተን/ዳሞት/ ተራራ ሥር በዕድሜ ጠገብ አጸዶች የተከበበ ከአዲስ አበባ በ320 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ ታላቅና ታሪካዊ ገዳም መኾኑን ተነግሯል።

ገዳሙ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ጣዖትን አፍርሰዉ ቤተ መቅደስን የሠሩበት ንጉሥ ሞቶሎምን ከእነ ሠራዊቱ አስተምረው አሳምነው ያጠመቁበት፤ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ከእግዚአብሔር እጅ ጵጵስና የተሾሙበት እና 12 ዓመት ያገለገሉበት ጥንታዊ ገዳም እንደኾነ ተገልጿል።

ቅዱስ ቦታው የቤተክርስቲያን ባለ ውለታ የሆኑት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለበርካታ ዓመታት ያስተማሩበት እና ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት/ በቀድሞው ስማቸው አባ መላኩ ለፕትርክርና ከመጠራታቸዉ አስቀድሞ ለ42 ዓመታት ያክል እየጾሙና እየጸለዩ ወንጌል ያስተማሩበት ታሪካዊ ቦታ መኾኑን ተነግሯል።

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እንደገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ከሆኑ በኋላ 12 ብፁዓን አበውን አስከትለው ወደ ወላይታ ሐዋሪያዊ ጉዞ ያደረጉ ሲሆን በዕለቱ ማለትም ግንቦት 13 ቀን 1980 ዓ.ም ለአዲሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ህንጻውን ግን በእናታቸው ማህጸን ያሉ ህጻናትን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ልጆቼ ወደፊት ይሰሩታል ብለው በወቅቱ ቅዱስነታቸው ትንቢት ተናግረው እንደነበር ገልጸዋል።

በመኾኑም የቅዱስነታቸው ትንቢት ተፈጽሞ የዕረፍታቸው ቀን በሚታሰብበት መጪው ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር መርሐ ግብር መያዙን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ሕንጻውን ተጠናቅቆ በተያዘለት ቀን ለማስመረቅ ለሚቀሩትን ሥራዎች እና የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች በባለሙያዎች ተጠንቶ ወደ 42 ሚልዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን በተያዘለት ቀን እንዲመረቅ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የምትገኙ የተዋሕዶ ልጆች እጃችሁን እንድትዘረጉ በጻድቁ ስም እማጸናለሁ ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።
#የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ብቻ!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
ተቋሙን በገንዘብ ለማገዝ፡-

የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTC(BSA)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165122406
ዓባይ ባንክ 1462319237132015 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=




ማስታወቂያ
++++++++++++++++++++++++++++++++++
በመቶ ብር ትውልድ የሚታነጽበትን ፕሮጀክት እየደገፉ ይሸለሙ
- ሙሉ ወጪዎ ተችሎ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጉብኝት
- የግብጽ ገዳማት ጉብኝት
- የሀገር ውስጥ ገዳማት ጉብኝት
- የብራና ሥዕለ አድኅኖ
- የአንገት ወርቅ እና ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች ለባለ እድለኞች ተዘጋጅተዋል ይህ ሁሉ በ መቶ ብር ።

ገቢው ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማእከል እያስገነባ ላለው ባለ 12 ፎቅ የሕፃናት እና ወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማእከል እና አገልግሎት ማስፋፍያ የሚውል ።

የዚህ ሕንጻ ፕሮጀክት አስፈላጊነት በጥቂቱ
- በሁለት በኩል የተሳለ ትውልድ ማፍራት
- የግቢ ጉባኤ አገልግሎትን ማሳደግ
- የአብነት ትምህርትን ማስፋፋት
- ዘመኑን የዋጁ ካህናትና ሰባኪያን ማፍራት
- ኢ-አማንያንን ማስተማርና ማጥመቅ
- ሴተኛ አዳሪዎችን ካሉበት ሕይወት ማውጣት
-እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶች ለመደገፍ እና ለማስፋፋት በቋሚነት የቦታም ሆነ የፋይናንስ ችግር የሚፈታ የሕንጻ ፕሮጀክት ለመስራት የበኩልዎን ይወጡ

ትኬቶቹን :--
_ በሁሉም የአሐዱ ባንክ ቅርንጫፍ
_ በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች
_ በማኅበረ ቅዱሳን ንዋየተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ
_ በአጥብያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ት\ቤት ያገኙታል
ለዚህ የትውልድ መገንቢያ ሕንፃ ግንባታ የበረከት እጅዎን ይዘርጉ፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ
አሐዱ ባንክ. 0002505310101
ኢ.ንግድ ባንክ. 1000303949112
አቢሲንያ ባንክ. 68960665
አዋሽ ባንክ. 01304868950900
ዳሽን ባንክ 0088211311011
ዓባይ ባንክ 1891119601313011

ለበለጠ መረጃ
0902 50 11 31
0946 38 38 92


ግብጽን በወርኀ ጥር ለበዓለ መርቆሬዎስ ከኛ ጋር ይጎብኙ

🗓ከጥር 24 – የካቲት 4 2017 ዓ.ም
መላ ግብጽን ለ10ቀናት የምንጎበኝበት ልዩ የበረከት ጉዞ መርሐ ግብር ያዘጋጀን በመሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተጓዦችን በጉዞው እንዲሳተፉ ሲንጋብዝዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ቀድመው ይመዝገቡ
አሁኑኑ ይድወሉ፡-
📞
0942111213
📞
0930796578
📞
0903131313
📍  22 አክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ እንግኛለን፡፡


==========================

👉👉የማኅበራዊ  ትስስር ድረ ገጾቻችንን  ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/Pagumentoursc
Instagram: https://www.instagram.com/Pagumentoursc
Telegram: https://t.me/pagumensc
Youtube: https://youtube.com/@Pagumentoursc
Web: www.pagumen.com




ግብጽን በወርኀ ጥር ለበዓለ መርቆሬዎስ ከኛ ጋር ይጎብኙ

🗓ከጥር 24 – የካቲት 4 2017 ዓ.ም
መላ ግብጽን ለ10ቀናት የምንጎበኝበት ልዩ የበረከት ጉዞ መርሐ ግብር ያዘጋጀን በመሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተጓዦችን በጉዞው እንዲሳተፉ ሲንጋብዝዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ቀድመው ይመዝገቡ
አሁኑኑ ይድወሉ፡-
📞0942111213
📞 0930796578
📞0903131313
📍 22 አክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ እንግኛለን፡፡


==========================

👉👉የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Facebook: https://www.facebook.com/Pagumentoursc
Instagram: https://www.instagram.com/Pagumentoursc
Telegram: https://t.me/pagumensc
Youtube: https://youtube.com/@Pagumentoursc
Web: www.pagumen.com









20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.