አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ አማናዊ የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት የሆነ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ከብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ጋር በማነፃፀር “በበግ በጊደርና በላም ደም እነደነበረው እንደ ቀደሙት አባቶች መሥዋዕት አይደለም፤ እሳት ነው እንጂ፡፡ ፈቃዱን ለሚሠሩ ልቦናቸውን ላቀኑ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው፡፡ ስሙን ለሚክዱ ለዐመፀኞች ሰዎች የሚበላ እሳት ነው፡፡” እንዳለ የብሉይ ኪዳንን መሥዋዕት አሳልፎ ራሱን ለዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠ ጌታ የአይሁድ አለቆች በገንዘብ ወዳድነት መሥዋዕቱን ወዳቃለሉበት ቤተ መቅደስ በመምጣት ቤተ መቅደስን አነጻ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ በቤተመቅደሱ የሚሸጡ የሚለውጡ ሰዎችንና የሚሸጡ የሚለወጡ እንስሳትን አገኘ፡፡ የሚሸጡት እንስሳት እንደ ብሉይ ኪዳን ሥርዓት ለኃጢአት ማስተስረያ መስዋእትነት የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ የካህናት አለቆችና ግብር አበሮቻቸውም በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እንስሳት ለመሥዋዕት ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ በመስጠት በምትኩ ገንዘብ እየተቀበሉ አገልግሎቱ መልኩን ቀይሮ ንግድ ሆኖ ነበር፡፡ ለመስዋእት የሚሆኑትን እንስሳት የሚሸጡት ሰዎችም ስለሚያገኙት ትርፍ እንጅ ስለ መሥዋዕቱ ንጽሕና አልነበረም፤ ከጌታ የሚገኝ ሰማያዊ ጸጋን በመሸጥና በመለወጥ በሚያገኙት ትርፍ የቀየሩ ነበሩ፡፡ ቅዱስ አምብሮስ በትርጓሜው እንደገለጠው በሬዎችን ይሸጡ የነበሩት ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለሥጋዊ ክብርና ጥቅም ሲሉ “የሚያስተምሩ” ምንደኛ አገልጋዮችን ይመስላሉ፡፡ በጎችን ይሸጡ የነበሩት ሰዎች መልካም ነገርን ለውዳሴ ከንቱ ሲሉ የሚያደርጉ ጌታችን “ዋጋቸውን በምድር ተቀብለዋል” ያላቸውን ከንቱ ውዳሴ ፈላጊዎች ይመስላሉ፡፡ እንዲል፡፡ ርግቦችን የሚሸጡትም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉትን ሲሞናውያን ይመስላሉ፡፡
ከላይ በተገለጸው መልኩ ቤተመቅደሱ የንግድ ቦታ ሆኖ ነበር፡፡ ሊቃነ ካህናቱም የጥቅም ተካፋይ ስለነበሩ የሚመክርና የሚገስጽ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ጌታችን የሚሸጡና የሚለወጡትን ካስወጣ በኋላ “የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ አላቸው“፡፡ በዚህም አምላክ፣ ወልደ አምላክነቱን ገለጠ፡፡
እንደ ማጠቃለያ
ሊቃናተ አይሁድ በቤተመቅደሱ ሲሸጡና ሲለውጡ፣ ሥጋዊ የገንዘብ ትርፍና ዝና በማሳደድ የቤተመቅደሱን ክብር ሲያቃልሉ ያደረጉትን ሁሉ ለመንፈሳዊ ዓላማ ያደረጉት ለማስመሰል በቤተመቅደስ ለሚሸጡትና ለሚለወጡት የመሥዋዕት እንስሳትና ገንዘብ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ይሰጡ ነበር፡፡ ዛሬም በዘመናችን ተረፈ አይሁድ የሆኑ ምንደኛ አገልጋዮች አሉ፡፡ ንጹሑን መንፈሳውያን እሴቶቻችንን ለገንዘብ ማግኛነት ሲጠቀሙባቸው ዓላማቸውን መንፈሳዊ ለማስመሰል በመጣር የወሓንን ያሳስታሉ፡፡
ጌታችን “ከእኔ ተማሩ” ብሎናልና በዘመናችን ባሉ አንዳንድ ጥቅመኞች ትምህርተ ወንጌልን ለገንዘብ ማግኛነትና ለንግድ ሲያውሏቸው፣ ከመንፈሳዊ ሥርዓት ይልቅ ሥጋዊ ንግድና ደስታ ሲበዛ፣ ጸሎት ለማድረስ ገንዘብ የሚተምኑ ሰዎች ሲመጡ ልንቃወማቸው ይገባል፡፡ እኛ በይሉኝንታ፣ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ተይዘን ዝም ብንልም የቤተ መቅደሱ ባለቤት ዳግም ይመጣል፡፡ የሚመጣው ግን እንደ ቀደመው ለማንጻት ሳይሆን ለፍርድ ነው፡፡ ስለሆነም ከሚፈረድላቸው እንጅ ከሚፈረድባቸው ወገን እንዳንሆን አገልግሎታችን ለጽድቅና ለበረከት እንጅ ለገንዘብ፣ ለዝና፣ ለታይታ፣ ለከንቱ ውዳሴ አይሁን፡፡
ምንባባት መልዕክታት
✍️ ቆላ. ፪÷፲፮—፳፫
✍️ ያዕ.፭÷፲፬
ግብረ ሐዋርያት
✍️ የሐዋ.፲÷፩—፰
ምስባክ
✍️ መዝ. ፷፰፡፱
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡