Fuad Muna (Fuya)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot

ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


አስቸኳይ!

አንዲት ቤተሰቦቿ በከባድ ችግር ውስጥ ያሉ እህት አለች። ታሪኩ ረዥም ነው። ቤታቸው የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በችግር እየማቀቁ ነው። ቢያንስ በልተው ማደር ይችሉ ዘንድ ልጃቸውን ስራ በመቅጠር ማገዝ የሚፈልግ @fuadmuna ላይ በውስጥ ያናግረኝ።
.
@Fuadmu


ቅዳሜ ምሽት ጥር 17


ሀረማያ ተገኝተን 2015 ላይ በጎደሉ አሉ ፕሮጀክት የተቆፈረውን ሌላኛውን የውሀ ጉድጓድ ጎብኝተናል። ቪዲዮውን ተከታተሉ።

https://vm.tiktok.com/ZMkQx3jSa/


ከ2 ዓመታት በፊት ሀረማያ ላይ ያስቆፈራችሁት የውሀ ጉድጓድ ያለበትን ሁኔታ ለማየት ተጉዘን ነበር። የጉዟችንን ቪዲዮ በሊንኩ ተከታተሉ።
https://vm.tiktok.com/ZMkQeqnAS/


80k ደርሰናል 🥰🥰🥰

ዘመቻችን ቀጥሏል። የጎደለባችሁ ካለ ለጎደለባችሁ፣ ከሌለም ለራሳችሁ የቀብር ጎደሎ ሰደቀቱል ጃሪያ ተሻሙ!

አካውንት @fuadmuna ላይ መውሰድ ትችላላችሁ።

አትፍዘዙ!
.
@Fuadmu


ዱዓ አድርጉላት እስኪ ያ ጀመዓ!


የኔ ሰው
(ፉአድ ሙና)
.
መቶ ብር ለታክሲ
ሀምሳ ለማስቲካ፣
ካፌ ተሰብስቦ
ሞኝ ሲያውካካ።
መቶ ብር ለጀነት
አለች እጅ አውጥታ፣
ካፌ ትሰጣበት
ጊዜ መች አግኝታ።

መቶ ብር ለጀነት!

አይኗን አውቀዋለሁ
አያይም ደግ እንጂ፣
ጥርሷን አውቀዋለሁ
ነጭ የፍቅር ፈንጂ!
ሰለዋት ተሞልቶ
አይገዳትም ሆዷ፣
የጀነት ስራ ነው
የህይወት መንገዷ!


መቶ ብር ለጀነት!

የታሸገ ውሀ
ብትጠጣም አማርጣ፣
ጭንቀቷ ላጣው ነው
ይህን የሪዝቅ እጣ!
ያብሰለስላታል... 
እንቅልፍ ይነሳታል...
የወንድሟ ጥማት
የእህቷ መደፈር፣
በጠብታ ውሀ
የሚስኪኑ መክፈር።
ያማታል ቆንጆዬን
እንቅልፏስ መች መጥቶ፣
ከጀነት ሲጨለፍ
ሰው ደጋፊ አጥቶ።
ያስነባታል በጣም!

መቶ ብር ለጀነት!

ገረፋት የሰው ፊት
ብታደገው ብላ፣
ሺህ ሰው ረገጠው
ያንን ቅዱስ ጥላ።
መቶ ብር ለጀነት
ትላለች የኔ ሰው፣
ኩፖኗን ይዛ ነው
`ምትመላለሰው።

መቶ ብር ለጀነት!

በቆሻሻ ውሀ
በሽታ እየጠጣ፣
ህይወቱ ለሚያልፈው
ህክምና እያጣ!
ያ ረቢ ለሚለው
ገጠር ተቀምጦ፣
እንዳይጫንበት
እንዲያምን መርጦ!
ትሽከረከራለች
ከኩፖኗ ጋራ፣
ወትሮም አንደኛ ናት
ለጀነት ሰው ስራ!

መቶ ብር ለጀነት!
መቶ ብር ለኔ ሰው፣
ፊት እየገረፋት
ኩፖኖቿን ሸጣ ለምትመለሰው!
***
መታሰቢያነቱ
በየገጠሩ የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ኩፖን እየሸጡ የሰው ፊት ለሚገርፋቸው ኢፋድዮች ይሁንልኝ! የኔ ሰው እናንተ ናችሁ!
.
@Fuadmu

7.9k 0 97 17 139

ትዝ ይላችኋል?

በጎደሉ አሉ ጅማ ዞን ሳኮሩ ወረዳ 2015 ላይ ያስቆፈርነው የመጀመሪያው የውሀ ጉድጓድ ትዝ አላችሁ?

ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለመመልከት ወደ ቦታው ተጉዘን ነበር። ገንዘባችሁ ከሁለት ዓመት በኋላ ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ ይመስላችኋል።

አልሀምዱሊላህ በደንብ እየሰራ ነው።

ሊንኩን በመጫን የጉዟችንን ቪዲዮ ተመልከቱ።

https://vm.tiktok.com/ZMk5GQEPQ/


ኢፋዳ የስነ ፅሁፍ ምሽት!

ዛሬ እሁድ ከአስር እስከ መግሪብ ቤተል ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት በሚገኝበት ሚና የገበያ ማዕከል ይካሄዳል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

አድራሻ: ‐ ከመንዲዳ ወደ ቤተል ሲመጡ አለምባንክ መገንጠያ አስፓልት ጋር ያለው ሚና የገበያ ማዕከል (አል ቤክ ሬስቶራንት ያለበት ህንፃ)


ውሀ!

የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም እሁድ!


የኢፋዳ መፅሀፍ የመጨረሻዎቹ ኮፒዎች እየተሸጡ ነው። የገዛችሁ ቶሎ መፅሀፋችሁን ውሰዱ መፅሀፍ እያለቀ ነው።

መግዛት የምትፈልጉ @ifadasales ላይ መግዛት ትችላላችሁ።

መልካም ሸመታ!


ውሀ የሌለባቸውን ገጠራማ አካባቢዎች ውሀ ለማዳረስ የጎደሉ አሉ ብለን ፕሮጀክት ከጀመርን ቆየን!

በጅማ ሳኮሩ ወረዳ አንድ የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሐረማያ ሁለት የውሀ ጉድጓዶችን አስቆፈርን።

በመሀል እስረኞችን ነፃ በማውጣት የጎደሉ አሉ ሁለትን አካሂደን ነበር።

አሁን ሰዓቱ የውሀ ነው። የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም ጁሙዓ!


ዋ... ወንድነት!
(ፉአድ ሙና)
.
የኔ ቆንጆ... ለሁላችንም ያላቸውን ጥላቻ ባንቺ በኩል ለማስተንፈስ ሲሞክሩ እያየሽ ነው አይደል? የኔ ያልሻቸው ደም የተጋራሻቸው ሰዎች... እንወድሻለን ያሉሽ ቁሸቶች ጊዜ ጠብቀው ምን እንደሚደግሱልሽ ተረዳሽ? «ድህረ ሰላም... እስላም!» ብለው ከመጀመሪያው ዝተውልሽ ነበር አሉ!

ገና ከፌደራል መንግስቱ ጋር የያዙት ጦርነት ሳያልቅ የበቀል ክንዳቸውን እንዴት አንቺ ላይ እንደሚያሳርፉ ሲጎነጉኑ የነበሩ የፍጥረት አተላዎች ናቸው። ቀን በቀን የአላህን ንግግር እውነታነት ቢያስረግጡልሽ አትገረሚ!

የሚያስመልጥሽ ክንድ የለም። ይጋፋበት ክንድ ያለው አንድ እንኳን ሙስሊም ወንድ የለሽም። ሁሉም የበታች ነው። ሁሉም ወራዳ ባሪያ ነው። ርካሽ ነን የኔ አለም። አንቺን እናድንበት ድምፃችን ሰሏል። እንደቁስበት ክንዳችን ዝሏል። በፍርሀት ተሸብበን ሁኑ ያሉንን እየሆንን ነው የኔ ንግስት!

ጌታሽ ቀድሞ እነዚህ ጠላቶችሽ በደም አይደለም በስጋ አካል እንኳን ብትጋሩ እንደማይመለሱልሽ ነግሮሽ ነበር።

«وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡» (በቀራ፣ 120)

ድረስልኝ አትበይኝ የኔ ፍቅር! በስሜቴ የተተበተብኩ ርካሽ ነኝ! እንደ ሙዕተሲም አዘምትልሽ ጦር፤ እቆጣልሽ ወንድነት የለኝም። ሲልኩኝ ወዴት ሲጠሩኝ አቤት የምል ወራዳ ነኝና ወደኔ አትጣሪ። ወደ አላህ ጩሂ የኔ ውድ! ወደማይነጥፈው ንግስና ተጣሪ! የእርሱ ክንድ አይዝልም። እርሱ ይደርስልሻል ውዴ!


«فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ

«ወደ አላህም ሽሹ፤» (ዛሪያት፣ 50)

እኔ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ላልመለስኳቸው የድረስልኝ ጩኸቶችሽም አነባለሁ! ለራቀኝ ወንድነት... ለተሸከምኩት ወራዳነት እንሰቀሰቃለሁ። አንድ ቀን ጭንቅላቴ ቀና ይላል። ሲነኩሽ አይሆንም ብዬ አስቆምበት ክብር አገኛለሁ ብዬ ከጌታዬ እከጅላለሁ። እስከዛው ግን ውዴ ወደ ጌታሽ ጩሂ.... እኔ ወራዳ ሆኛለሁ።

በበዳዮች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ!
.
@Fuadmu

7.5k 0 17 11 116

50 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu


የረጀብ የመጀመሪያ ምሽት ላይ እንገኛለን።

በዚህች የረጀብ የመጀመሪያ ለሊት ዱዓ አይመለስም። የልብ የልባችሁን ለአላህ አቅርቡ።

አደራ ከላጤነትም ገላግለን ማለት አትርሱ!
.
@Fuadmu

6.6k 0 26 10 86

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ላጤ ሆይ!
በአማርኛ ፅሁፍ ስትመከር እንቢ ብለሀል።
እስኪ በአረብኛ ቪዲዮ ተመከር።
.
@Fuadmu

8.3k 0 39 28 67

40 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu


ለሰደቃ ባልተቤቶች ያማረ ጁሙዓን ተመኘሁ።

የጁሙዓ ሰደቃችሁን ለውሀ ጉድጓድ አውሉ። @Fuadmuna ላይ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ።


ዛሬ ቴሌግራም ላይ የምንተፋ ሊንኮች በብዛት እየተሰራጩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ስለሆነም ከምታውቁትም ሆነ ከማታውቁት ሰው የሚላኩላችሁን ሊንኮች ባለመክፈት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ።

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ @fuadmuna ላይ ጎራ ብላችሁ አካውንት መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu


ጥራዝ ነጠቆቹ
(ፉአድ ሙና)
.
ዛሬ ስለፍቅር ጋብ አድርገን ስለ ጥላቻ ብናወራስ? ስለነዚያ ቢችሉ የጀነትን በር ይዘው ሌላ ሰው እንዳይገባ ለማድረግ ስለሚሹት ሠዎች እንወያይ! ደግሞ የሆነ አራት ኪታብ ቀርተዋል። በእነሱ አለም በራስ ጭንቅላት ማሰብ ነውር ነው። በኡስታዛቸው ጭንቅላት ይነዳሉ።

ከተግባርህም ሆነ ከንግግርህ ውስጥ በጉጉት የሚጠብቁት ወደ ስህተት ሊተረጎም የሚችል ነገርን ነው። ስህተት መሆን አይጠበቅበትም። ከመሰለ ይበቃቸዋል። «አላህን ፍራ!» በሚል ተቀፅላ ጀምረው የስድብ ጥማታቸውን ያስታግሱብሀል።

እነዚህ ሰዎች ለመምሰል እንደሚሞክሩት ብፁዕም አይደሉም። በወንጀል እጅጉን ሊበልጡህ ይችላሉ። በማስመሰል ህይወታቸውን ይመራሉ የምቀኝነትና የቅናት ድግሪ አላቸው። የእነሱ የእስልምና ትርጓሜ  ሰውንም ሆነ ራስን ማስጨነቅ ነው።

እነዚህ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም? እስኪ የገጠማችሁን አካፍሉን!

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ለማስቆፈር ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው። ለመሳተፍ የምትፈልጉ @Fuadmuna ላይ አካውንት ጠይቁኝ።
.
@Fuadmu

7k 0 17 23 60
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.