✍
የእነሱ መባላት ለእኛ ዕረፍትም ድልም ነው!!ከሃዲያኖች ላይ ከሚደረጉ ትላልቅ ዱዐዎች አንዱ
🤲
"اللهم اجعل بأسهم بينهم شديد"
"አላህ ሆይ! በመሃላቸው ያለው ፍትጊያ የበረታ አድርገው" የሚለው ትልቁ ዱዐ አንዱ ነው።
ይህ ዱዐ ወይም የከሃዲያኖች ዕርስ በዕርስ መባላት ለሙስሊሞች ምን ያህል ዕረፍት እና ስኬት እንደ ሚያመጣ በቲዎሪ ከማብራራት ይልቅ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዓለም ላይ እየሆኑ ያሉ ክስተቶች መመልከት የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣል።
"ሀያላን" በሚባሉ ከሃዲ አረመኔዎች የምትዘወረው ዓለም: ለሙስሊሞች እና ለመላው ምስኪን ጭቁኖች መከራ መሆኗ እሙን ነው። በመሆኑም እነዚህ ከሃዲያን መሪዎች በሚያስተዳድሯቸው ሀገሮች የሚኖሩ ሙስሊሞችም ይሁኑ በራሳቸው ሀገር እየኖሩ የከሃዲያኖች ሴራ የተሸረበባቸው የሙስሊም ሀገሮች የሚኖሩበት መከራ እና የሚያዩት ስቃይ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ይህ እየሆነ ባለበት: እነዚህ የዓለም ፖለቲካ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉ ሀያላን አረመኔዎች ዕርስ በዕርሳቸው የሚያባላ ጦርነት ውስጥ በሚገቡ ጊዜ በእነርሱ ሲጨቆኑ የነበሩ ንፁሃን ሁሉ "እፎይ" ይላሉ።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንኳ ብናይ፦
ኣሜሪካ ከቻይና፣
ኣሜሪካ ከራሺያ፣
ራሺያ ከዩክሬን
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተዋጉበት ያለው ጦር ሜዳ ከተከፈተ በኋላ ዓለም ላይ ያሉ ሙስሊሞችም ይሁኑ የሙስሊም ሀገሮች ያገኙት ሰላም እና ስኬት እጅግ በጣም ብዙ ነው።
መታወቅ ያለበት………
እኛ ሙስሊሞች ድላችንም ይሁን ሽንፈታችን በጠላቶቻችን ሁኔታ ላይ የሚመዘን አይደለም፤ የጠላቶቻችን መጠንከርም ይሁን መድከም እኛ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የለም። የምናሸንፈውም ይሁን የምንከስረው እኛው ጋ ባለው ሁኔታ መሰረት ነው። ባለን ኢማን እና ሰላሕ ልክ ድላችን ሲጠነክር፤ ኢማናችን ሲደክም እና ሰላሓችን ሲጠፋ ሽንፈት እንላበሳለን።
መሰረታዊው ነገር ይህ ከመሆኑም ጋ የጠላት ዕርስ በዕርስ መባላት የእኛ ሰላም እና ስኬት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
ደስታውን አጣጥመን ያልጨረስነው የሶሪያ ነፃነት እንዲመጣ ሰበብ ከሆኑ ክስተቶች አንዱ ይኸው ነው።
የራሺያው የኩፍር መንግስት ከዩክሬን አቻው ጋ ደም አፋሳሽ እና ዕልህ አስጨራሽ ጦርነት ውስጥ ይገኛል፤
በመሆኑም………
የረዥም ጊዜ ወዳጁ እና በ"ፀረ_ሙስሊም" ዘመቻ ላይ የጀርባ አጥንት ሆኖ ሲያግዘው ለነበረው ውሻ (በሻር አል_አሰድ) መድረስ አልቻለም።
የሙስሊም ማሊያ ለብሶ ሙስሊሞች ላይ ጭራቅ የሆነው "ሂዝቦላህ" የተባለው የ"ሂዝበላት" ቡድን ከየሁዷ ኢስራኤል ጋ የውሸትም ይሁን የምር ባልታወቀ ጦርነት ተጠምዷል፤
በመሆኑም………
ለወዳጁ እና ለቢጤው በሻር መድረስ አልቻለም።
የንፍቅና እና የክህደት ምሳሌ የሆነችዋ ኢራን: ከድብቅ ወዳጇ የአይሁድ ስብስብ ከሆነችዋ ኢስራኤል ሰጣ ገባ ውስጥ ትገኛለች፤
በመሆኑም………
ለባልደረባዋ በሻር መድረስ አልቻለችም።
ይህንን ገራሚ እና ምቹ አጋጣሚ ያገኙ ነቄ የሶሪያ ታጋዮች በከሃዲ ነገስታቶች ዕርዳታ ምስኪን ሙስሊሞችን ሀገራቸው ጀሀነም አድርጎባቸው የሰነበተው የሙጅሪሙ በሻር አል_አሰድን አገዛዝ ገርስሰው የኢስላም እና የሰላም ነፋስ እንዲነፍስ አደረጉ።
የኢማን እና የጥበብ መፍለቂያ፤ የዕውቀት እና የጀግንነት ውሃ ልክ በሆነችዋ የመን የተጀመረው ዘመቻ በዚሁ መንገድ አላህ ድሉ ለሙስሊሞች እንዲያደርገው እየተማፀንን: ከሀዲያኖች መሃል ያለው ጦርነት አላህ የበረታ እንዲያደርግባቸው፤ ዕርስ በዕርስ የሚጨራረሱበት አቅም እና ወኔ እንዲሰጣቸው ደግመን እንለምነዋለን!!🤲اللهم اجعل بأسهم بينهم شديد
🤲اللهم فرق جمعهم
🤲وشتت شملهم
🤲وخالف بين وجوههم وأفكارهم وآرائهم
🤲اللهم اجعل تدبيرهم تدميرا لهم🖊
ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!https://t.me/hamdquante