#Update #Axum
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።
ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።
159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።
በዚህም ምክንያት ተማሪዎቹ ከፈተና ውጭ
ጉዳይ በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።
ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?- በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።
- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።
- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።
- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።
- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል።
... ብለዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ታህሳስ 22 /2017 ዓ.ም ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤህ ህዝበ ሙስሊሙን በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 /2017 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
ከ2017 ዓ/ም የ12 ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።
@islam_in_school