🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- khalidbinkebe@gmail.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Law students Union ️️️ dan repost
የሰበር ውሳኔ.pdf
1.8Mb
Share የሰበር ውሳኔ.pdf


የሌላን ሰው መሬት አጥር አጥሮ በመያዝ ቤት ሳይሰሩ ባለቤቱ ሳይቃወመኝ ነው የሰራሁት በማለት የፍ/ህ/ቁ 1179 በመጥቀስ መከራከር አይቻልም። መ/ቁ 249348
ታህሳስ 28 ቀን2017 ዓ.ም የተወሰነ።






#የወንጀል_ክስ_መመስረቻ_ጊዜ
ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ስለመሆኑ፡፡

ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት ያለዉ ስለመሆኑ፡፡

ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 252231 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል


ስለ-ሕግ ⚖️ ABOUT-LAW dan repost
file number 29 1512.08 Meseret Taye.pdf
26.1Mb
አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት በህፃኑ በሕጋዊ መንገድ የተፈራ ንብረት ስለመሆኑ ግምት ሊወሰድ ይገባል፡፡ ፍርድ ቤቶች ህፃኑ ንብረቱን ከራሱ የሃብት ምንጭ ወጪ አድርጎ ስለመግዛቱ አላስረዳም በሚል ምክንያት ንብረቱን ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት አንጂ የህፃኑ አይደለም በማለት ወስነዋል፡፡ ባልና ሚስቱ ንብረቱን በራሳቸው ፈቃድ ከጋራ ንብረታቸው ወጪ በማድረግ አካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ስም ገዝተዋል፡፡ አንዲህ ዓይነት ህፃናትን የሚመለከቱ ጉዳዮች የህፃናትን ደህንነትና ጥቅም በቀደምትነት መታሰብ ያለበት እና ለህፃኑ ጥቅም ተብሎ አንደተገዛ (እንደተፈራ) ንብረት ተደርጎ ሊወሰን የሚገባው ነው በማለት ምክር ቤቱ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
(የፌ/ም/ቤት መዝገብ ቁጥር 41/10)

Credit- Yadeta G.


የመንግስት ቤት ተከራይ የሆነሰው የራሱን ቤት ሲሰራ የተከራየውን ቤት ለመንግስት የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡በቤቱ በዳባልነት ተመዝግቤ አለሁ እና ቤቱሊተላለፍልኝ ይገባል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ራሱን የቻለ እና በቅድሚያ ቤቱን
ለሚያስተዳድረው የአስተዳደር አካል ቀርቦ ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው የመብት ጥያቄ በመሆኑ ተጠሪ የሚያስተዳድረውን ቤት ለማስለቀቅ በቀበሌ ቤቱ ተከራዩ ላይ ካቀረበው ክስ ጋር ታይቶ ምላሽ የሚያ
ገኝ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ211043 ያልታተመ


ግራ ቀኙ ኢትዮጵያውያን ሆነው በውጭ ሀገር ሕግ መሰረት በዛው ሀገር ጋብቻ በመካከላቸው እንደተደረገ በመግለጽ አንደኛ አመልካች ጋብቻ እንዲፈርስ እንዲሁም የጋራ ንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ዳኝነት ሲጠይቅ ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ አቤቱታውን ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1) (ሀ) እና 11 መሰረት የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው።


#የወራሽነት_ማስረጃ_የወሰደ_ሰው_በሕግ_በታወቀ_ጋብቻ_ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት ግንኙነት ወይም ከሁለቱ በአንዱ በሕግ በሚታወቅ ግንኙነት ውስጥ #እንዳልተወለደ #ከተረጋገጠ #የሟች_ልጅ_እንደሆነ_በመግለጽ ከአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ነው ተብሎ የተሰጠ ማስረጃ ጸንቶ ሊቀጥል የሚችለው #ሟች_ልጄ_ነው #በማለት #የተቀበሉት ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 143 እና ተከታዮቹ መሠረት አባትነት #በፍርድ_ቤት #ውሳኔ #የሚታወቅባቸው_ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሲቀርብ መሆኑን: ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ የሚወስዱት መብት ለማቋቋም በማሰብ እንደመሆኑ ይህን ማስረጃ በመጠቀም በሚደረግ ተግባራት የሶስተኛ ወገኖች መብቶች ሊነካ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከግምት በማስገባት ማስረጃውን የሚሰጠው ፍርድ ቤትም የወራሽነት ማስረጃ ሲሰጥ ጠያቂዎቹ ከሟች ጋር አለን የሚሉትን ግንኙነት በተገቢው ማስረጃ እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሚኖርበት: በዚሕ አግባብ ተረጋግጦ የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መሆኑን ማስረጃው የተሰጠው ሰው ባላስረዳበት ሁኔታ ማስረጃውን በመቃወም ክስ ያቀረበ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው የመካድ ክስ እንዲያቀርብም ሊፈቀድለት አይገባም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

ሰ.መ.ቁ 248877 ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ . ም-


#የፌደራል
ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 127313፣160867፣159451፣141081፣76909 እና በሌሎች የሰበር ውሳኔዎች ላይ አንድ ተከሳሽ የዐ/ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኃላ ወይም ተከላከል ከተባለ በኃላ በተከታታይ ቀጠሮ ካልቀረበ የቀረበበት የወንጀል ክስ በሌለበት የማይታይ ወንጀል ቢሆንም ፍ/ቤቱ ተከሳሽ የመከላከል መብቱን በራሱ እንደተወው ተቆጥሮና አልቀረበም በሚል ሰይሞ በቀጥታ ውሳኔ መስጠት እንጂ በሌለበት የሚታይ ጉዳይ አይደለም በማለት መዝገቡን መዘጋት እንደሌለበት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።
ይሁን እንጂ አንድ ተከሳሽ በዋስ ሆኖ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንዳለ የዕለት ከዕለት ሰራውን ለመስራት ከክልሉ ውጭ እንደሄደ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይም በሌላ ወንጀል ተጠርጥሮ ታስሮ በቆየበት ሁኔታ እንዲከላከል ብይን የሰጠው ፍ/ቤት ተከሳሹ የክርክሩን አዝማሚያ ካየ በኃላ ሆን ብሎ ከፍትህ ለመሸሽ ሲል እንደቀረ ወይም እንደጠፋ በመቁጠርና ከላይ የተጠቀሱትን የሰበር ውሳኔዎችን በመጥቀስ በቀጥታ የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ቢሰጥ ተከሳሽ በየትኛው የህግ ድንጋጌ የመከላከል መብቱን ሊያስከብር ይችላል ? ተከሳሽ በራሱ ባልሆነ ጥፋትና ከእርሱ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት በችሎት ባለመቅረቡ የተነሳ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 20(4) ስር የተመለከተውን የመከላከል መብት እንዲያጣ ማድረጉስ ተገቢ ነው ? የሰበር ውሳኔዎችስ በመሰል scenario ጊዜ ፍ/ቤቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ ወይ(454/97 አንቀፅ 2(4) አንፃር )? መሰል በቂ ምክንያት ያላቸው ተከሳሾች በመሰል scenarios መብታቸው በተጣበበ ጊዜ መብታቸውን የሚያስከብሩበት የወንጀል ስነ-ስርዓት ድንጋጌስ አለ ወይ?
የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 197፣198፣199 ድንጋጌዎች ተፈፃሚነታቸው በሌለበት ተብሎ ለተሰጠ ውሳኔ እንጂ ተከሳሽ ሙሉ ክርክሩን እንዳደረገ ወይም መብቱን በራሱ እንደተወው ተቀጥሮ አልቀረበም በሚል ለተሰጠ ውሳኔ ተፈፃሚነት የላቸውም። ከላይ የተሰጡት የሰበር ውሳኔዎች ከመሰል ችግሮች አንፃር unconstitutional decisions ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም ወይ? በዚህ ረገድ በቅፅ -7 በሰ/መ/ቁ 29325 የተሰጠው የሰበር ውሳኔ ከላይ ከተሰጡት የሰበር ውሳኔዎች አንፃር ሲታይ የተሻለ ችግር ፈችና በህገ-መንግስቱ የተመለከተውን የመከላከል መብት ሰፋ ባለ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ቢሆንም ከላይ ከተጠቀሱት የሰበር ውሳኔዎች ጋር የሚቃረና ሁሉም በ5 ዳኛ የተሰጡ ውሳኔዎች ከመሆቸው አኳያ ተግባራዊነቱን አስቸጋሪ አድርጎታል።


Minda Girma Law Office ምንዳ ግርማ ህግ ቢሮ dan repost
94-13.pdf
1.3Mb
የፌደሬሽን ም/ቤት ወሳኔ❗️
➤ 1. ሕፃናት በፍ/ቤት ለማስረጃነት የሚውል የዘረ መል (DNA) ምርመራ ለማድረግ አይገደዱም፤ ምርመራውን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብቻውንም እንደ በቂ ማስረጃ ተቆጥሮ "ሕፃኑን DNA ለማስመርመር ፈቃደኛ ያልተሆነው ልጁ የባልዬው ባይሆን ነው" የሚል የሕግ ግምት [የፍ/ሕ/ቁ. 22ን ልብ ይሏል] በመያዝ ባልዬው የልጁ አባት አይደለም ብሎ መወሰን ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው::

➤ 2. በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ልጄ አይደለም በማለት (አባትነትን ለመካድ) የሚቀርብ ክስ በጠባቡ ሊታይ የሚገባና የክስ ማቅረቢያ ጊዜውም ባልዬው የልጁን መወለደ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ባሉት 180 ቀናት ውስጥ የመሆኑ ይርጋ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሌሎች ይርጋዎች የተለየ ስለሆነ በአንድነት ሊታይ የማይገባ እና ተከራካሪ ወገኖች ባያነሡትም እንኳን ፍ/ቤቶች በራሳቸው አንሥተው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ ነው::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 94/13
ግንቦት 30/2013 ዓ.ም


⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖ dan repost
አቶ_ረዲ_አህመድ_እና_ወ_ሮ_መኪያ_ሀሰን_የሰ_መ_ቁ_175719.pdf
513.4Kb
ሰ.መ.ቁ.175719

የባልና ሚስት ጋብቻ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸርዓ ፍ/ቤት በፍቺ ዉሳኔ ከፈረሰ በኋላ የፍቺ ውጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ መደበኛ ፍ/ቤት ለማየት የሥረነገር የዳኝነት ስልጣን የለዉም።




ሰመ.ቁ. 219736 ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም የ ሁከት ተግባር ምንነት
የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) የሁከት ተግባርን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮችን ከመጥቀስ ባለፈ በራሱ “ሁከት” ለሚለው ቃል የሰጠው ግልፅ ትርጉም የለም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለውም የሁከት ተግባር የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት ሁለት ድርጊቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ባለይዞታው በሀብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም መብቱ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት አልያም የሚፈጠር እንቅፋት (Interferance) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በባለይዞታው እጅ የነበረን ንብረት/ይዞታ/ በሙሉ ወይም በከፊል በመውሰድ ባለይዞታውን በዚያው መጠን ይዞታ አልባ ማድረግን (Dispossession) የሚመለከት ነው፡፡

በሌላ በኩል የሁከት ተግባሩ በሁለት መንገድ ሊፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ ጥናቶች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ይዞታውን ከባለይዞታው እጅ በመውሰድ ወይም በይዞታው ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት ላይ በተጨባጭ/በተግባር/ የሚፈፀም ጣልቃ ገብነት /Disturbance in fact/ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በባለይዞታው የይዞታ መብት ላይ በህግ ረገድ የሚፈጠር ሁከት/Disturbance in law/ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የሁከት ዓይነት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው አስተዳደር ክፍል ይዞታውን በተመለከተ በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ በሌላ ወገን ጠያቂነት በተለያየ መንገድ የባለይዞታውን የይዞታ መብት በሚነካ መልኩ በሚወሰደው አስተዳዳራዊ እርምጃ ነው፡፡ ይህ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደየሁኔታው ባለይዞታው ይዞታውን በተመለከተ አንድን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም በማድረግ አልያም የባለሃብትነት መብቱን የሚያሳጣ ተግባር በመፈፀም ሊሆን ይችላል፡፡

በእነዚህ ሁኔታዎች በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ባለይዞታ የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድለት እና በድርጊቱ ስለደረሰው ጉዳት ኪሳራ እንዲሰጠው በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ እና ዳኞችም ይኸው ስለመፈፀሙ ሲያረጋገጡ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ እና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካሳ እንዲከፈል ሊወስኑ እንደሚችሉ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ሀበሻ advocates




👉 ሰ/መ/ቁ 188480
/ ያልታተመ/

↪️ተከራካሪ ወገኖች የተገፋባቸውን መሬት መጠን ትክክለኛ መለኪያ መጠን እንዲገልፁ የማይገደዱ ሲሆን መጠኑ በባለሙያ ሲለካ ከጠየቁት መጠን የበለጠ ቢሆንም የጠየቁት ብቻ ነዉ ዳኝነት ሊባል አይችልም።
በድንበር ግፊ ክርክር ከሳሽ የሆነ ወገን ምስክሮቹ ተከሳሹ መሬቱን መያዙን ካስረዳ የግድ በሜትር ስንት በስንት ተያዘ የሚለውን እንድያስረዱ አይጠበቅትም፡፡ ፍ/ቤቱ ከይዞታው ላይ ስንት በስንት ሜትር ተይዟል የሚለውን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 136 መሰረት በባለሞያ አጣርቶ መወሰን አለበት።




ዘወልድ የሕግ አገልግሎት dan repost
መንግስት አንድን የተቆቆመ አለፍነቱ የተወሰነ ማህበር ወራሽ ሆኖ ሊቀርብ ስለመቻሉ መንግስት በውርስ ጉዳይ መብትና ጥቅም እንዴት እንደሚኖረው ወራሽ ዘመድ የለውም የሚባልበት ሁኔታ እና ዘመድ ኖሮት ውርሱን አንቀበልም የማለት ውጤት እና ውርሱን ተቀባይ ሰለመኖሩ የሚያመጣው ለውጥ እና አንድ አላፉነቱ የተውሰነ ማህበር የማህበሩ አባል ሲሞት ማህበሩ ሰለመፍረስ አለመፈርስ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች አንድ አክስዩን ተሸጠ የሚባለው በሚን አይነት ሁኔታውችን ሲያሞላ ነው በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽፈት ቤት አለመመዝገቡ የሚያመጣው ውጤት ምን እንደሆነ ከንግድ ህጉ 524 ከአዋጅ ቁጥር 922/2008,334/95,እና ከፍ/ህ/ጉ 852,995,977 ጋር ተገናዝቦ የተወሰና አስተማሪ ጠቃሚ የሰበር ውሳኔ



19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.