ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


♦️⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት
⛪️ የንግስ መዝሙራት
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @kingo08bot ላይ ትገኛላችሁ=

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri


እንዴት አደራቹ ውድ ኦርቶዶክሳውያን?
የልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ሠላም ከሁላችንም ጋር ይሁን።

አጠገብህ ስለሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር፤ ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠህ ይቆጠራል።"
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

መልካም ቀን ውድ የተዋሕዶ ልጆች🙏

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው ያለው ማነው?


ማኔ ቴቄል ፋሬስ ተብሎ የተጻፈበት ንጉሥ ማነው?


በሃገራችን ኢትዮጲያ ለመጀመርያ ግዜ የተጠመቀ ማነው?ያጠመቀውስ ማነው?
So‘rovnoma
  •   ባኮስ፣ፊልጶስ
  •   ፊልጶስ፣ባኮስ
  •   ሁሉም ክርስትያኖች
  •   ሐዋርያት፣ቅዱስ ዮሐንስ


🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ሐሙስ
      #ቀን:- ጥር ፳፱ ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን

ባዕለ ወልድ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ አቡነ መዝርዐተክርስቶስ፣ አባ አፍጼ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ


አክብረን እና አስበን እንውላለን።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው ያለው ማነው?
So‘rovnoma
  •   ቅዱስ ጳውሎስ
  •   ንጉስ ዳዊት
  •   ኢየሱስ ክርስቶስ
  •   ቅዱስ ያዕቆብ
53 ta ovoz


አባታችን አብርሃም እና እናታችን ሣራ በስንት ዓመታቸው ነው ሥላሴን በድኳናቸው ተቀብለው ያስተናገዱት!?
So‘rovnoma
  •   አብርሃም በ99 ዓመቱ፥ሣራ በ89 ዓመቷ
  •   አብርሃም በ100ዓመቱ፥ሣራ በ80ዓመቷ
  •   አብርሐም በ99 ዓመቱ፥ሣራ በ79ዓመቷ
  •   ሣራ በ89 ዓመቷ ፥አብርሃም በ79ዓመቱ።
42 ta ovoz


#መሀረኒ_ድንግል

መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
አዝ...............
ይጠሩሻል ካህናቱ
ንዒ ይሉሻል በሳታቱ
ለለመነሽ የማትቀሪ
በልቤ ውስጥ ፀንተሽ ኑሪ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ

መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ

ያዲስ ኪዳን ኪሩ የሆንሽ
ለምኚልን ካንዱ ልጅሽ
ርግብየ ሰናይትየ
ነይ ወደኔ ነይ ወልድየ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
..............................................
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ 2×
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ
አዝ.........................
ባለም መኖር ሰልችቶኛል
መልካም መስራት አቅቶኛል
እጄን ይዘሽ ድንግል ምሪኝ
አዛኚቷ አትለይኝ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ

መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ 2×
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ

እበላለው ብዬ ማርያም
እመካለው ባንቺ አላፍርም
ካንቺ ወዴት እሄዳለው
ስምሽን ልጥራው እፅናናለው
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ

ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ 2×
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


" በፈጣሪ ልጄን አድኑልኝ😭😭😭"    #አባት

ይህ ቆንጅዬ ህፃን #አሚር የሱፍ  ይባላል!በተወለደ 4ኛ ወሩ ህመም ሲያሰቃየውና እንቅልፍ ሲከለክለው እናትና አባት ወደ ጥቁርአንበሳ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ!
ህፃን አሚር አንድ ወር አልጋ ይዞ ክትትል ካደረገ በኋላ ዶክተሮች "የልብ ክፍተት  ችግር አለበት፣ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል"ተባሉ!

ልጁን ለማሳከም የተጠየቁት 1500000 ብር ነው ከአቅም በላይ ስለሆነ ልጃቸውን ለማዳን እናንተን እየተማፀኑ ነው😭 እባካችሁ #እንድረስላቸው🙏  #በዱአ #ሼር እናግዛቸው🙏
                "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000304310937-ዩሱፍ ሀምደለ (አባት)
#ስልክ
0705740135

☞አድራሻ ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር

☞ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል


#ከማህፀን_እስከ_ሽምግልና

ከማህፀን እስከ ሽምግልና
ሚጠብቀኝ ምህረትህ ነውና
በምስጋና ወደ ቤትህ ልግባ
ልሰዋልህ የከንፈሬን መባ  (2×)


በኑሮ መስመር በሕይወት ጎዳና
ዕድል ፈንታየን የምታቀና
ስፈራ በትር ስዝል ምርኩዜ
ተቀኘሁልህ ባሰብከው ጊዜ

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ዘውዴ ልበልህ መከበሪያየ
ማዕረጌ ነህ መታፈሪያየ
ስምህን ይዤ ምን ጎሎብኛል
ባንተ ስላለሁ ሁሉ ተርፎኛል

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ሳትሳቀቅም ተሸክመኸኝ
ስንት ሸለቆ ጌታ አሳለፍከኝ
አልቆምም ነበር በራሴ ጉልበት
አንተ ባትሆነኝ ጽኑ ሰገነት

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ይህ ሁሉ ክብር ይህ ሁሉ ዝና
ያላንተ ፈቃድ መች ይሆንና
ይሁን ይደረግ ጌታየ ያልከው
እኔስ ያለኝ ቃል አሜን ብቻ ነው


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

4k 1 78 1 79



🌕 የማያሳፍር ተስፋ 🌕

ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው “የተስፋ አምላክ” ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? “ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ” ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16)

"ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ"

"ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!"

ዲያቆን አቤል ካሳሁን


#ዘጸዓት_ነው_ለሕዝቡ

ዘጸዓት ነው ለሕዝቡ
በደም ታስሯል ወጀቡ
ጽኑ ክብርን ያየነው
ኢየሱስን ይዘን ነው
ክርስቶስን ለብሰን ነው[፪]

የግብፁ ፈርኦን
በግፍ ሲያስጨንቀን
ክቡደ መዝራዕት ሙሴ
ተነሳና ከራምሴ
መንጋውን ይዞ ወጣ እየቀና
በኀቅለ ቃዴስ በሲና
ያ መንፈሳዊ መጠጥ ያ መንፈሳዊ መብል
ክርስቶስ ነበረ እኛን የሚከተል

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

በራፍዴም እንዳንቀር
ተወልን ምስክር
በኢያሱ ወልደ ነዌ
እያዳነን ከአርዌ
ከንዐን ሄደ ከፊት እየመራን
ስሙ መድኃኒት ሆነን
እስራኤል ዘነፍስ ነን ድል በአደረገው ጌታ
ኢያሪኮ ሲዖል ፈርሷል በእልልታ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

በፋርስ ነገሥታት
ወድቆብን ባርነት
በኤርምያስ የነውጽ በትር
እየታየን በምሥጢር
እንደ ብረት አምድ ቅጥር አድርጎን
የእሳቱን ወጀብ አለፍን
በምልክት በራዕይ ተስሎ በሰማይ
ማምለጫችን ሆነ በጎለጎታ ላይ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ከጠላታችን መዳፍ
መከራ ቢወነጨፍ
የጠበቅነው መሲህ ደርሷል
ሸክማችንም ተራግፏል
የመቤዠት ቀን ቀርቦ ዘጸዓት
ጠቅልለን ወጣን ከሞት
በደሙ አጊጠናል እርስቱን እንወርሳለን
በጽዬን ተራራ ለበጉ እየዘመርን


በዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


#በምስጋና_በውዳሴ

በምስጋና(2) ተማርኳል ልባችን
በውዳሴ(2) እረካችን ነፍሳችን
ስለወደድክ ስላፈቀርከን
ስለክብርህ እንዘምራለን /2/

ለዘላለም የማትረሳን የማትተወን
ቸርነትክን ምህረትክን ያረክልን
እንሰዋለን የምስጋና መስዋእት
በቀንና በለሊት

የሰራሃውን በጎነት ስናስብ
በመገረም በመደነቅ አልን እጹብ
ለአንተ ክብር ቅኔና ውዳሴ
እንደ አሮን እንደ ሙሴ

ተቀኘንልህ በመሰንቆ በበገና
ህዝብህ ቆሞ ለውዳሴ ለምስጋና
አይቱዋልና ቀራኒዮ ፍቅርህን
ሊያከብር ወጣ ስምህን

በስራህም ተገርመናል ተደንቀናል
ንጹህ ፍቅርህን ቀራኒዮ ላይ አይተናል
ስናመልክህ እኖራለን እስከሞት
አግኝተናል በአንተ ህይወት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

6.1k 1 111 1 92

#በስምህ_ታምኛለው

በስምህ ታምኛለሁ እን ዳትተወኝ
ለሚያሳድደኝ ጠላት ለሞት አትስጠኝ
ፀጥታዬ ነህ ጌታ ሰላም ዕረፍቴ
ጉዞዬን አንተ አቅናልኝ ቅደም ከፊቴ
            አዝ
በለስም ባታፈራ ዘይትም ባይኖር
የህሊና ሰላም አለኝ ካንተ ጋር ስኖር
በአባቶቼ በረከት የ ባረከኝ
የእስራኤል ታዳጊያቸው ክበርልኝ
ዘላለም ተመስገን ከፍ በልልኝ
          አዝ
የፈተናዬ መውጫ መልሴ ነህ
አንተ ጨለማውን አሻግረኝ እልፍኙን ከፍተህ
ስታፅናናኝ ኖሬአለሁ ለብዙ ዘመን
ተገፍቶ መች ይወድቃል በአንተ የሚታመን
አይሞትም ይኖራል በአንተ የሚታመን
           አዝ
ይቅርታና ምህረትህ እነሱ ይምሩኝ
ወጥመድና እንቅፋቱ እንዳያደክሙኝ
በጽድቅህ ሀሴት ላድርግ በአንተ ልበርታ
መተከዝ ማልቀስ ይብቃኝ አፅናናኝ ጌታ
ተነግሮ አያልቅም የአምላኬ ውለታ
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


የእናታችን_የአማላጃችን_የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰት እስከ ትንሣኤዋ ያሉት እውነታዎች:-
-  ነሐሴ ፯ ተፀነሰች ።
-  ግንቦት ፩ ተወለደች ።
-  ታህሣስ ፫ ወደ ቤተመቅደስ ገባች።
-  መጋቢት ፳፱ ቀን አምላክን በድንግልና ፀነሰች ።
-  ታህሣስ ፳፱ ቀን አምላክን በድንግልና ወለደች ።
-  የካቲት ፲፮ ቀን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከአምላካችን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀበለች (ኪዳነ - ምህረት)
-  ጥር ፳፩ ቀን በክብር አረፈች ።
-  ነሐሴ ፲፬ ቀን በክብር ተቀበረች ።
-  ነሐሴ ፲፮ ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነስታ በክብር አረገች ።

ክብር ምስጋና ለቅድስት ድንግል ማርያም

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


+ከአእላፋት ማግስት+

Credit: ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው (@yohannes_getachew1)

''ይሄን ስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት''

እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አሁንማ ገና እየደረሰ በመሆኑ፥ አእላፋት ዝማሬ ብቻ ሆኗል ወሬው እሱ ይረብሻታል።

ስለ እናቴ ትንሽ ላውራቹህ...

ኤልሳ ትባላለች። ሲበዛ ተጫዋች፥ ረጅም፥ በጣም ቀይ፥ ስትስቅ ጥርሷ የሚያምር፥ በዛ ላይ ዲምፕል ያላት ውብ ናት። አባቴ ደግሞ ሱራፌል ይባላል፤ ዲያቆን ነበር። በእርግጥ እኔ 16 አመቴ እያለ ነው የሞተው። ሰዎች ስለ እርሱ አውርተው አይጠግቡም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፥ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፥ ጸሎተኛ ነበር ፤ መምህሩ ሲቀሩ እርሱ ነበር ጉባኤ ዘርግቶ የሚያስተምረው። ሁሉም ነበር የሚወደው። እኔን ራሱ ውዳሴ ማርያም፥ ዳዊት፥ ቅዳሴ፥ ሰዓታት አስተምሮብኛል። '

'ሰበኔ... ሴት ሆንሽብኝ እንጂ አንቺን ዲያቆን ነበር የማደርግሽ'' የሁል ጊዜ ንግግሩ ነበር።

እናቴ አባቴ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መተማመን ይገርማታል። እኔ ልክ 15 አመት ሲሆነኝ አባቴ በጠና ታመመ። የሳንባ ካንሰር ያዘው። ከቤት መውጣት ከበደው፤ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው አልጋ ላይ መጽሐፈ መነኮሳትን እያነበበ ነበር። ትንሽ ህመሙ ባስ ሲልበት ደግሞ መጽሐፉን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሰአታት መተንፈስ የከብደው ነበር። ከእርሱ ህመም በኋላ ቤታችን ውስጥ ሳቅ የሚባል ጠፋ። እናቴ ቀይ ፊቷን ማድያት ወረሰው።

.......የሆነ ማክሰኞ ቀን ጠዋት ላይ ''ኡኡኡኡኡኡኡኡ'' የሚል ጩኸት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። እናቴ ነበረች። ብርድ ልብሱን ከራሴ ላይ በስርአት ሳላወልቅ ሮጥኩኝ። ኤልሲ አባቴን አቅፋ ፥-

"ጌታዬ ጉድ አታድረገኝ ባክህ ጉድ አታድርገኝ"

"እማ አባቴ ምን ሆነ?" ......እምባዬ ከየት እንደመጣ አላውቅም። ፊቴ ርሷል...

"የልጀነት ፍቅሬ ኧረ ተው" ትላለች።

"እማ አባቴ ምን ሆኗል?!"

"ጉድ አረከኝ! ብቻዬን ለማን ጥለከኝ! ኧረ ያላንተ አይሆንልኝም! ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ"

ጩኸታችንን የሰሙ ጎረቤቶቻችን ቤታችንን ሞሉት። በአንዴ ግማሹ ቲቪ ይሸፍናል፥ ግማሹ ስለ ድንኳን ያወራል......ራሴን ሳትኩ፤ ስነቃ ቀብር ሊሄዱ ህዝብ መጥቷል። ቤቱ ውጪው ግጥም ብሏል። ያ ሁሉ ህዝብ አንድ አባቴን አልሆን አለኝ.....

አባቴ ካረፈ ጊዜ ጀምሮ ቤታችን የማይቀሩ የማይቀሩ 3 ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእናቴ የስራ ባልደረቦች ታዲያ በመጡ ቁጥር ለእናቴ እንፀልይልሽ ብለዋት ነው የሚሄዱት፤ የሆነ ቀን ላይ ከታናናሾቼ ጋር ጸሎት እያደረግን "ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቤት ሃይማኖት ተቀይሯል!" አለችን።

"ወደምን?" አልን

"ጌታን ተቀብለናል! ነገ ትጠመቃላችሁ። አቁሙ አሁን!"

"እንዴ ኤልሲ! እኛ እኮ ልጅ እያለን ተጠምቀናል"

"አንቺ ልጅ! ተናገርኩ በቃ!"

"አልቀይርም! አባቴ ያስተማረኝ ያወረሰኝ ነው፤ አልቀይርም!" አልኩ።

ኤልሲም መልሳ "ነው? ከሆነ ከቤቴ ውጪ! እናንተም እንደዛ ነው?

ታናሽ እህቴም አዎ አለች።

"ውጡ! ችግር እና ረሃብ ሲፈራረቅባችሁ ትመጡ የለ!" አለችን በቁጣ።

ስልኬን አንስቼ ለአያቴ ደወልኩ። አያቴ ብቻዋን የምትኖር፥ በጣም ትልቅ ጊቢ ያላት፥ እሱ ላይ ወደ 20 ምናምን ቤት ሰርታ የምታከራይ ሴት ናት። ስደውል ኑ ኧረ ኑ አለች

......... እናቴ ሃይማኖቷን ቀየረች። ሁሉንም እኛ ክፍል የነበረ ስእለ አድኅኖ አውጥታ አቃጠለች። የአባቴን ግን ከበዳት። የእርሱን ዳዊት፥ የጸሎት መጻሕፍት፥ ሁሉን ነገሩን በአንድ ላይ አድርጋ አንድ ክፍል ውስጥ ቆለፈችበት። እኛም አያታችን ጋር መኖር ቀጠልን።

---------------------------------------------------

እናቴን ሃይማኖቷን ያስቀየሯት ሰዎች Theology እንድትማር አደረጉና ፓስተር ሆነች ።

ዛሬ...

"እሺ ባክሽ... አእላፋት ምናምን እያላችሁ ነው ደግሞ በነጭ ልብስ ጣኦት ልታመልኩ"

"ተይ እንጂ እማዬ... የማይሆን አትናገሪ። ለምን ዛሬ አብረን አንሄድም?"

"ማን? እኔ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ... ሥራ አልፈታሁም"

"ምን ችግር አለው? ከደበረሽ ቶሎ እንወጣለን።"

"ቆይይይይይ እሄዳለው። የምሄደው ግን እንዴት ልክ እንዳልሆናችሁ ላሳይሽ ነው!"

ሁላችንም ለባብሰን ወጣን። በጊዜ ነበር የደረስነው፤ ቦሌ መድኃኔዓለም ሞልቷል። እንደምንም ብለን ፊት ተጠጋን። ዲያቆኑ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" ይላል። ቁርጥ የአባቴን ድምፅ! ኤልሲ ደነገጠች። አባቴን ያየችው መስሏት ተንጠራርታ ፈለገችው፤ የለም። የሚፀየውን ጸሎት በግእዝም በአማርኛም ስታየው ቆየች። እምባዋ ይፈስ ጀመር። ጸሎቱ ተጠናቆ ነጫጭ የለበሱ ዘማሪያን መድረኩን ሞሉት። መዝሙር ቀጠለ። ቸሩ ሆይ የሚለው መዝሙር ዘማሪዎቹ መዘመር ጀመሩ። የአባቴ የሚወደው መዝሙር ነበር። የሲቃ ድምጽ አውጥታ አለቀሰች። አሳዘነችኝ ደስም አለኝ። መዝሙሩ አለቀ። በአባቶች ብራኬ ተጠናቀቀ። ኤልሲ ሙሉ ሰአት እያለቀሰች ነበር ።

"ኤልሲዬ በቃ አንቺ ሂጂ፥ እኛ እናስቀድሳለን።"

"ልምጣ?"

"የምርሽን ነው?"

"አዎ ልምጣ"

"ነይ" ድንጋጤዬ ያስታውቃል።

ማህሌቱ አልቆ፥ ቅዳሴው አልቆ፥ ቤት ገባን። እኛ ቤት ከመጣሁ 10 አመት አልፎኝ ነበር። ያው ነው፥ ምንም አልተቀየረም። እናቴ ሮጣ ጸሎት ቤት ገባች። ሁሉ ነገሩ አባቴን አባቴን ይላል። ትልቅ የእመቤታችን ምስለ ስዕል ፊት ወድቃ አለቀሰች።

"ሰበኔ አሁን ገባኝ! ልቤ ተሰብሬ ሲያገኙኝ ዓለም ገደል ስትሆንብኝ አግኝተውኝ ነው! ልጆቼ ይቅር በሉኝ! በጎደለኝ በኩል ሲቆሙ ወዳጆች መሰሉኝ ......"

ተቃቅፈን ተላቀስን። ምን ተረዳሁ መሰላችሁ? እግዚአብሔር ስራው Mysterious ነው። እንዲህ ነው ብለን Define የማይደረግ። ዛሬ ላይ ቤተሰቤ ሙሉ ሆኗል፤ እናቴም ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርት ለመማር ከመምህሬ ጋር አገናኝቻለሁ። ከ 10 ዓመት ከብዙ ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ። እጆቼን ከፍ አድርጌ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ...

"የእኔን እምባ ያቆምክ እግዚአብሔር... እምባቸውን ለሚያወጡ ድረስ" ብዬ። "ሰላም ለናፈቁ ሁሉ ሰላም ስጥ። አባቴ የደከሙ ልቦችን አሳርፍ፥ ፈገግታን የናፈቁን ሁሉ ሳቅ አጥግብ፥ ለደስታ የተግደረደሩትን ሁሉ አላምዳቸው ...ባለቀሱበት ቦታ እንባቸውን አብስ። ሁሉን ቻይ ሆይ፥ የመዳናቸውን ቀን አታርቅ።"

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው
ጥር 1 / 2017 ዓ.ም

7.2k 1 36 9 144



🗓 #ነገ ማለትም
🔣#ዕለት:- ረቡዕ
      #ቀን:- ጥር ፳፩ ፳፻፲፯(21/5/17) ዓ.ም
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን

እመቤታችን በዓለ ረፍት✔️
ነቢዩ ኢዩኤል፣ አቡነበትረ ማርያም፣ ቅድስት ሔራኒ፣ ጻድቁ ቆጵርያኖስ
አክብረን እና አስበን እንውላለን:

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏



🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


የጥምቀት መዝሙሮች


#ሃሌ_ሃሌ_ሃሌ_ሉያ
#ኀዲጎ_ተሰአ
#መፃ_ቃል
#ጥምቀተ_ባሕር
'https://t.me/NEY_NEY_EMYE_MARYAM/64https://t.me/NEY_NEY_EMYE_MARYAM/64' rel='nofollow'>#በዕደ_ዮሐንስ
#በጎል_በጎል
#ኢየሱስ_ሖረ
#የዓለምን_በደል
#የኛ_ነው_ዋሻው_እምነቱ_ፀበሉ
#ዮሐንስኒ_ያጠመቀ
#ዮሐንስ_አጥመቆ_ለኢየሱስ
#ዮርዳኖስ_ደስ_ይበልሽ
#ጌታ_ተጠመቀ

የንሰሐ መዝሙሮች


#ለድሆች_ወንጌልን
#መሠረቷ_ጉልላቷ
#መች_ይረሳል
#መፃጉዕ
#ማረኝ_መመኪያዬ
#ሰላሜ_ነህ_ፀጥታዬ
#ርግብና_ዋኔን
#በርጠሚዮስ_ነኝ
#በብርሀን_ፀዳል
#በቤተ_መቅደስህ
#በሚፈርደው_ፈረዱበት
#በፈቃዱ_ለሕማም_ተሰጠ
#በፍቅር_ላዚምህ
#ታላቅ_መሆን_የፈለገ
#ና_ና_የምስጋና_ጌታ
#እውነት_ስለሆነ
#እንተ_በህሊና
#እኔ_አንተ_ቤት
#እኔ_እሆንን
#እጠበኝ_ቆሽሻለሁ
#እኔን_ደካማውን
#ዓለምን_ለማዳን
#የሉም_ከሳሾቼ
#ያንተ_ይሁን_ምርጫዬ
#ይቅር_ስላልከኝ_ነው
#ደም_ግባት_አልባ
#ፈቃዴ_ነው_የሰውን_ነገር_ላልናገር
#ፈራሁ


የሰርግ መዝሙሮች


#ሐመልማለ_ወርቅ
#ቃና_ዘገሊላ
#በቃና_ዘገሊላ|
#አጅቡት_በእልልታ
#አካልሽ_ከአካሌ
#እልል_እልል_የሰርግ
#እልል_እልል_ደስ_ይበለን_የሰርግ_በረጅሙ
#እመቤታችን_በአንቺ_ምልጃ
#ደመቀ_አበራልን
#ዘወይነ_ዘወይነ

ኦሮሚኛ መዝሙሮች


#ቲክሴ_ጋሪ_ቀባ
#ዱጉማ_ዱጋዳህ
#ALFAA_FI_OMEEGAA
#Mana_kee_keessatti

ኦሮሚኛ የንሰሀ መዝሙሮች


#Jireenya_fayyinaaf(ለመዳኑ ሕይወት)

የብፁሃን አባቶች ትምህርት

#መጻጉዕ
#ቅዱስ_ቄርሎስ_ሳድሳዊ
#ቅዱስ_ኤፍሬም
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ2
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ3
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
#ነበርኩ_መች_ያድናል
#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

መዝሙራቱ ለፍለጋ እንዲመቹ በፊደል ተርታ የተቀመጡ ሲሆን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የፈለጋችሁትን መዝሙር ስትነኩት ከስር ቀስት ያመጣላችኋል ቀስቱን በምትነኩበት ሰአት ቦታው ላይ ይወስዳችኋል

እንዲሁም ከዚህ ከማውጫው ግርጌ leave a comment  የምትል ቦታ አለች እሱን ቦታ በመንካት አስተያየት መስጠት እና ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ።
የአባቶ ች አስተማሪ ትምህርቶች

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.