የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
سَيَقُولُ لَكَ الْمُخَلَّفُونَ مِنَ الْأَعْرَابِ شَغَلَتْنَا أَمْوَالُنَا وَأَهْلُونَا فَاسْتَغْفِرْ لَنَا ۚ يَقُولُونَ بِأَلْسِنَتِهِم مَّا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ لَكُم مِّنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ بِكُمْ ضَرًّا أَوْ أَرَادَ بِكُمْ نَفْعًا ۚ بَلْ كَانَ اللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
"ከአዕራብ ሰዎች እነዚያ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የቀሩት ለአንተ «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸገሩን፤ ስለዚህ ምሕረትን ለምንልን፤» ይሉሃል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ፡፡ (አላህ) «በእናንተ ላይ ጉዳትን ቢሻ ወይም በእናንተ መጥቀምን ቢሻ ከአላህ (ለማገድ) ለእናንተ አንዳችን የሚችል ማነው? በእውነቱ አላህ፤በምትሠሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡"
(ፈትህ ፡ 11)
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ
አላህ ﷻ በረሱል አንደበት በዲን ላይ ማክረርን ፤ በአምልኮ ወሰን ከማለፍና ያለአቅሟ በነፍስ ላይ ጫና መፍጠርን ከልክሏል፡፡ በዚህ ዙሪያ የመጣው መረጃ በርካታ ነው፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ፡ አመቱን ሙሉ ከመጾም ፣ ሌሊቱን ሁሉ ከመቆም አብደላ ኢብን አምርን የአሏህ መልክተኛ ﷺ
ከልክለውታል። ይህን ተግባር የከለከሉት ከሚስቱ እና ከሌሎችም ሀቆች ጋር በተያያዘ ቸልተኛነት እንዳያሳይ መሆኑን ልብ በል። ታዲያ ባሪያው ከሀቆች ሁሉ ትልቅ የሆነውን የአላህን ሀቅ እንዳያጓድል ፣ በዱንያ ወሰን ማለፍን መከልከሉ እንዴት ሊሆን ነው!?
ሁለተኛው ፡ ገንዘብ በመፈለግ ላይ ድንበር ካለፈ ሳያውቅ ወደሀራም ይጎትተዋል፡፡ ለዚህ ነው ነብያችን ﷺ በኡመታቸው ላይ የገንዘብ ጉዳይ ያስጨነቃቸው ፣ ያሳሰባቸው።
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት አምር ብን አውፍ የሚከተለውን ሀዲስ አስተላልፏል ፡
"والله ما الفقر أخشى عليكم ، ولكني أخشى أن تبسط عليكم الدنيا كما بسطت على من كان قبلكم ، فتنافسوها كما تنافسوها ، وتهلككم كما أهلكتهم "
“ወሏሂ ፣ በእናንተ ላይ ድህነትን አልፈራም ፣ ነገር ግን እኔ የምፈራው ከዚህ በፊት በነበሩት ላይ በስፋት እንደተለቀቀው በእናንተ ላይ ገንዘብ በስፋት ተለቆ ፣ እነርሱ እንደተፎካከሩት እናንተም ትፎካከራላችሁ ፣ እነርሱን እንዳጠፋች እናንተንም ታጠፋችኋለች ብየ ነው ፡፡”
አዎ ዛሬ ስለተጨናነቅን ወይም ኑሯችን መካከለኛ ስለሆነና በብዙ ነገሮች ስላልተጠመድን ልቦቻችን ወደአላህ እንዲሁም በአላህ ዙሪያ እውቀትን በመፈለግ ዞረው ሊሆን ይችላል። በዚህ ሰአት እንረጋጋለን ፣ በደንብ እናስተውላለን። ነገር ግን ዱንያ በተከፈተልን ጊዜ የመልካም በሮች በእኛ ላይ መዘጋታቸው ፣ ከመልካም ስራዎች አካላችን ሽባ መሆኑ ነው አስፈሪው፡፡
ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ አብደላ ብን አምር ብን አልአስ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል ፡
የአሏህ መልክተኛ ﷺ ለሶሀቦች የሚከተለውን ጥያቄ አቀረቡ :
"إذا فتحت عليكم فارس والروم أي قوم أنتم؟
“በእናንተ ላይ ፋርስ እና ሮም በተከፈተ ጊዜ እናንተ ያን ጊዜ ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ?”
አብዱረህማን ብን አውፍ የሚከተለውን ምላሽ ሰጠ “አላህ እንዳዘዘን እንሰራለን” አላቸው፡፡
የአላህ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናገሩ :-
"أو غير ذلك تتنافسون ، ثم تتحاسدون ، ثم تتدابرون ، ثم تتباغضون"
“ከዚህ ውጭ (በገንዘብ ..) አትፎካከሩምን?፣ ከዚያም አትመቀኛኙምን ?፣ ከዚያም አትዟዟሩምን? ፣ ከዚያም አትጠላሉምን?!”
አላህ ﷻ መጽሀፋቸውን በግራ የሚሰጡትን ሰዎች አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
مَا أَغْنَىٰ عَنِّي مَالِيَهْ ۜ
هَلَكَ عَنِّي سُلْطَانِيَهْ
«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡
(ሀቃህ ፡ 28-29)
ሸይኹል ኢስላም የሚከተለውን ተናገሩ ፡
"غاية مريد الرياسة أن يكون كفرعون ، وجامع المال أن يكون كقارون"
“ከፍተኛው የስልጣን ፈላጊ ልክ እንደፊርዓውን መሆን ነው፤ ከፍተኛው የገንዘብ ሰብሳቢ ደግሞ ልክ እንደቃሩን መሆን ነው"
ስለዚህ እያንዳንዱ ሙስሊም በመልካም እና በጥሩ ስነምግባር መጓዝ አለበት። በዲን ስም ዱንያውን እውቀቱን ማጥፋት የለበትም።
የሙስሊም መገለጫ የሚከተለው የረሱል ﷺ ንግግር ሊሆን ይገባል ፡
"أعط لكل ذي حق حقه"
“ለሁሉም የሀቅ ባለቤት ሀቁን ስጠው፡፡”
በእውቀት ስም በገንዘብ የተጠመደ አካል ከትክክለኛው ጎዳና ተጣሟል፡፡ ምክንያቱም ገንዘብን መሰብሰብ ስለአላህ ስለረሱል ሱና ከማወቅ ጋር አይስተካከልም፡፡
አልይ የሚከተለውን ተናግረዋል ፤
"العلم خير من المال، العلم يحرسك ، وأنت تحرس المال"
“እውቀት ከገንዘብ በላጭ ነው፡፡ እውቀት አንተን ይጠብቅሃል፤ አንተ ግን ገንዘብን ትጠብቃለህ፡፡”
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة