ያ ታላቅ “ ነብይ
! ﷺ ”
—
እስኪ ትንሽ ልበል - ሰለዛ ታላቅ ሠው፣
ትንሽ ቢሆን አቅሜ - ቦታው ባይመጥነው፣
ብቻ ላመላክት - ጥቂት በምችለው!
/
እሳቸውን መግለፅ - አልችልም በእውነት፣
ትክክል የሚያትት - የት ይገኛል ቃላት፣
እርሰዎን የሚገልፅ - የት ተገኝቶ አንደበት፣
ትልቅ ያረጋቸው - አላህ ሲፈጥረዎት፣
ፍፁም የተላኩ - ለአለማት እዝነት!
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ - ታላቅ ባለ ፀባይ፣
መልእክት የመጣቸው - ከሰማያት በላይ፣
መቋጫ የሆኑ - መደምደሚያው ነብይ!
በጨለማ ጉዞ - ይህ ዓለም ሲዋልል፣
የሰው ልጅ ሲሰምጥ - በክህደት ማዕበል፣
ሰይጣን አላማውን - ሲበትን ሲያታልል፣
ይሄን ለመታደግ - ለማምከን ያን ተንኮል፣
ምድርን ለማብራት - ከአላህ ተልከዋል!
የፊት ነብያቶች - ጉዟቸው ተረስቶ፣
መመሪያቸው ሁሉ - ተበርዞ ጠፍቶ፣
የሠው ልጅ እምነቱ - ጠፍቶት ተበላሽቶ፣
መጥፎ ልማድ ባህል - እጅግ ተበራክቶ፣
በሕይወቷ እያለች - ሴት ልጅ ስትቀበር፣
ሲተገበርባት - ብዙ ዘግናኝ ተግባር፣
ከብዙ ባሎች ጋር ፣ አንድት ሴት ስታድር፣
በኑሮዋ ሁሉ - በጣም ስትቸገር፣
ድንቁርና ህይወት - በሰፈነበት ወቅት፣
ነብያችን ﷺ መጡ - በዛ ጭንቅ ሰዓት፣
በጥሩ ስነ-ምግባር - ያን ትውልድ አነፁት፣
በተውሒድ ብርሃን - ያን ጨለማ አበሩት፣
ከምድር አጠፉ - ያን ባዓድ አምልኮት፣
መጥፎ አስተሳሰብን - ከስሩ አመክኑት!
ወደ ንጹሕ እምነት - ሠዎችን ተጣሩ፣
በቁርኣን መመሪያ - ሁሉን አሰተማሩ፣
በእውነት ለአማኞች - ጀነት አበሰሩ፣
ደግሞ ካሀዳንን - በእሳት አሰፈራሩ!
እሺ ያላቸውን - ጀነት አስከትለው፣
እምቢ ያላቸውን - እሳት እንዳይባላው፣
አስጠንቅቅ አበስር - የሚል ትዛዝ ይዘው፣
ትልቅ ሀላፊነት - አቅፈው ተሸክመው፣
ለሠው ልጅ የሚደርስ - መልእክት አስይዟቸው፣
እኝህ ታላቅ ነብይ ﷺ - ከፍ ያለ ሚና,ቸው፣
አሸናፊው ጌታ - አላህ የላካቸው!
ከሠው ዘር ሁሉ ምርጥ - ልዩ ድንቅ ፍጥረት፣
ደረጃቸው በላጭ - ከሁሉም ነብያት፣
እድሜያቸውን ሁሉ - ባሳለፉት ሕይወት፣
የሰይጣንን መንገድ - የጣዖትን እምነት፣
ድራሹን ያጠፉ - በጣም ያሳደዱት፣
እንኳን ትልቅ ሆነው - መጥቶላቸው መልእክት፣
ጅስማቸው ሳይጠና - ገና ከልጅነት፣
ተዓምር ነበሩ - አስገራሚ ትንግርት፣
እኩይ መጥፎ ድርጊት ጸያፍን ተግባራት፣
ዝክትልትል ቅርፃቅርፅ - አማልክት ጣኦት፣
ይፀየፉ ነበር - ገና በለጋነት!
ታላቅ ሞዴላችን - በሶብር በትእግስት፣
ለዚህ ለኢስላም ሲሉ - ለተፈጥሮው እምነት፣
ያነ ሁሉ ችግር - ፍዳ ሲያሳዎት፣
ከአፀያፊ ትቺት - እስከ ከባድ ጥቃት፣
ያልደረሰ የለም - ያልወረደ መዓት፣
ይቅር በለው ሲያልፉ - ግፉን ሲቋቋሙት፣
ታግሰው ግብ መቱ - በጠንካራ ፅናት!
ለሀቅ ጥላቱ - ብዙ ነው በፊትም፣
የበፊት ነብያት - ተፋልመዋል ሁሉም፣
ይሄን ጥሪ ይዘው - ሲመጡ እሳቸውም፣
የሰይጣን ሰራዊቶች- ሆነባቸው ህመም፣
አመፀኛው ሁሉ - ተነሳ ሊቃወም፣
ስም ማጥፋት ጀመሩ - ማንቋሸሽ ማጣመም!!
ምን የቀረ አለና - ያልተፈጠረ ጉድ፣
ለመግደል ሙከራ - ከሀገር ማሳደደድ፣
ብዙ ጫና ቢደርስ - ብዙ ጉድ ማስገደድ፣
ተራምደው አለፉት - ፍቅርን በማስለመድ!
ነብዩን ﷺ በመስደብ - ከሀቅ ለመከልከል፣
እውነት ለመሸፈን - የሚጣጣር አካል፣
አላማው ግልፅ ነው - በጀመርባው መርዝ አዝሏል፣
የሰይጣን ስራ አስኬያጅ - ክህደት ለማስቀጠል፣
ከአላህ ከመጣው - ከሀቁ ለማግለል፣
ቅጥፈት ቢደማመር - መች እውነት ይሆናል፣
ነቢን ﷺ ታላቁን ሰው - በመጥፎ የሚስል፣
እርሰዎን የሚሰድብ - እውነት ያ ሠው ታሟል፣
ውቂያኖስ በቁንጥር - እንደት ይቆሽሻል፣
የፀሀይ ብርሃን - መች በእጅ ይሸፈናል፣
አንጋጠው ቢተፉ - መልሶ አፍ ላይ ያርፋል!
—
✍ አብዱረህማን ዑመር
t.me/Abdurhman_oumer/9400