🌍ተውሂድና ሱና ✍


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ቁርአንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተውሂድ፣ሲራ አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺ ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።ቻናሉን ይቀላቀሉ ኪታቦችን ይቅሩ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


➡️ጠንካራ ሙዕሚን ከደካማ ሙዕሚን በላጭና ከአላህ ዘንድም ይበልጥ ተወዳጅ ነው።

👉ሁሉም መልካም ቢሆኑም። የሚጠቅምህን ለመፈፀም ጉጉት ይኑርህ።
√በአላህ ታገዝ፤
√አትስነፍ።
√አንዳች (ክፉ) ነገር ሲገጥምህ፦
አትበል። ይልቁንም
👉 «በል» (ቢሆን ኖሮ) የሰይጣንን ሥራ ትከፍታለችና '' ነብዩ (ﷺ


"ሶሉ አለነቢይ"

"اللهم صل على محمد، وعلى آل محمد، كما صليت على آل إبراهيم، وبارك على محمد، وعلى آل محمد، كما باركت على آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد" 

"ሰላላህ አለይህ ወሰለም"


ትምህርት ሚኒስቴር መርዘኛ ኢስላም ጠሎች የተሰባሰቡበት ኋላ ቀር ተቋም ነው።


የካቲት 16 ለሚካሄደው የነሲሓ ኮንፈረንስ እየተዘጋጃችሁ ነው?

የመግቢያ ትኬት በዚህ ሊንክ ገብታችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። ባለፈ አመት ተመዝግባችሁ ከሆነ፤ አዲስ መመዝገብ ሳይጠበቅባችሁ የተመዘገባችሁበትን ስልክ ቁጥር በማስገባት ብቻ ትኬቱን ማግኘት ትችላላችሁ። ባለፈ አመት ካልተመዘገባችሁ ግን እንደ አዲስ ተመዝገቡና ውሰዱ።

ሊንኩ፦
https://conference.nesiha.tv

ላጤዎች! አሁንም በባዶ ልትገቡ¿ እስኪ ባለችው ቀን ተፍ ተፍ በሉ!


"የጥዋት ስንቅ"
#አቡበከር አል_ሻጥሪ
#ሱረቱል አል–ባዪና
«ቁርአንን አብዝታ የምታነብ፣ የምታዳምጥና ቁርአንን ጓደኛዋ ያደረገች ቀልብ፦

➜ አትረበሽም
➜ አትጨነቅም
➜ አታዝንም
➜ ሁሌም ደስተኛ ናት

«ከቁርአን ጋር እንኑር»


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


«ሐራምን ሐላል ያደረገ ሰው፤ ከፈፃሚው (ሐራሙን ከተገበረው) ሰው በላይ እጅግ በጣም ወንጀለኛ ነው።»


ኢብኑ ተይሚ-ይ'ያህ


[መጅሙዑ-ል-ፈታዋ: 20/280]


ወሎ የመቻቻል ወይስ የግፍ ምድር?
~
"ወሎ ሌት እስላም፣ ቀን ክርስቲያን" ሲባል ሰምተሀል ወንድሜ? ዛሬ ሰው እየሳቀ ያወራዋል። በውስጡ ያዘለው መልእክት ግን የሚያስለቅስ እንጂ የሚያስቅ አይደለም። በተከፈተበት አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ሳቢያ ሞት የተጋረጠበት ህይወቱን ለማትረፍ ሲል ቀን ላይ "ክርስቲያን ነኝ" የሚልበትን፤ ሌት ላይ አራ -ጆቹ ከፊቱ ዞር ሲሉለት እለታዊ የእምነቱን ሕግጋት ሲፈፅም የነበረበትን ዘመን ነው የሚያስታውሰው። በዚህ ሳቢያ ነበር "ወሎ ሌት እስላም፣ ቀን ክርስቲያን" የተባለው።
ሌት ላይ በድብቅ ፆም ለመያዝ እሳት ሲያቀጣጥል ታይቶ የተንገላታው ስንቱ ነው?! ትላንት በዚህ አይነት ትንቅንቅ ነበር እምነቱን ያቆየው።
·
የትላንቷ ሙስሊማ ሃይማኖቷን መቀየሯን ያላመኑ ጉልበተኛ አጥማቂዎች ሲያስጨንቋት "ወላሂ ክርስቲያን ነኝ" ስትል ነበር። ሕይወቷን ለማትረፍ "ክርስቲያን ነኝ" ትላለች። ከስጋዋ ጋር የተዋሀደው ኢስላሟ ግን በጎን ሾልኮ እየወጣ ሂወቷን ስጋት ላይ ይጥልባታል። "ወላሂ" ትላለች። አነጋገሯ አስቆህ ከሆነ ሞኝ ነህ። ይሄ የሚያስለቅስ እንጂ የሚያስቅ አይደለም።
·
ይህ ሁሉ ከመፈፀሙ ጋር "ወሎ የመቻቻል ተምሳሌት" እያለ የሚወሸክት አለ። ወሎ የመቻቻል ሃገር ሳይሆን በአንድ ህዝብ ላይ የተፈፀመ መጠነ ሰፊ ሃይማኖት ተኮር ግፍ በገሃድ የሚታይበት ምድር ነው። በዮሀንስ፣ በምንሊክና በራስ ሚካኤል የተባበረ ክንድ እልፍ አእላፍ ሙስሊም በግፍ ተጨፍ ~ `ጭፏል። ከርስቱ ከመሬቱ ብቻም ሳይሆን እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር ተፈናቅሎ በየጥሻው ቀርቷል። የአሞራና የጅብ ቀለብ ሆኗል። በረሃብ በቸነፈር እንደ ቅጠል ረግፏል።  ጠኔ ባደከማቸው ከሲታ እግሮቹ የወራት መንገዶችን አቆራርጦ ወደማያውቀው ምድር ተሰዷል። እጅግ ብዙው ካለመበትም ሳይደርስ አንድም በሚያሳድደው ጥጋበኛ የኩ ^ f ር ሰራዊት፣ አለያም በረሃብና በወረርሽኝ መንገድ ላይ ቀርቷል።
የተረፈው አይናቸውን በጨው አጥበው "ኢስላም በሰይፍ ነው የተስፋፋው" እያሉ በሚከሱ ሃፍረተ ቢሶች ያለ ምርጫው በሃይል ተጠምቋል። በገዛ እጁ መስጂዱን እያፈረሰ ቤተ ክርስቲያን እንዲገነባ ተደርጓል። የማወራው እዚችው የግፍ ምድር ላይ ስለተፈፀመ ግፍ ነው። ስለ መቻቻል ሰርክ የሚዜምላት ኢትዮጵያ!
·
አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻው ካለፈ በኋላም በሙስሊሙ ላይ የሚፈፀመው ግፍ መልኩን ቀይሮ እንደቀጠለ ነበር። ህዝበ ሙስሊሙ ለገዛ እምነቱ ባይተዋር እንዲሆን፣ የነሱ ባእላት አድማቂ እንዲሆን ተደርጓል። በተፈፀመበት የረጅም ጊዜ ሴራ የተነሳ ጥምቀት እና ገና የሚያከብር፣ ደመራ የሚያቃጥል፣ "አልሐምዱ ሊላሂ ታቦታችን ገባ" እያለ ታቦት የሚሸኝ፣ ፀበል የሚመላለስ፣ ማንነቱ የተደባለቀበት ትውልድ ተፈጥሯል። ይሄ ግን  አንዳንድ ቅቤ አንጓቾች እንደሚያስተጋቡት የመቻቻል ውጤት አይደለም። ይልቁንም አስገድዶ ከማጥመቅ የቀጠለው ማንነትን የማደባለቅ ዘመቻ ውጤት ነው።
ይህን ያዩ ሸይኽ ነበሩ እንዲህ ሲሉ የገጠሙት:–
·
"እራሴን ወገቤን ብሎ ሳይናገር
እንዲህ ሆኖ ቀረ የወሎማ ነገር!"
·
ዛሬ "በብሄሬ ሰበብ ተገፋሁ" ብሎ የብሶት ፖለቲካ የሚያራምደው ስንቱ ነው? ዛሬ "በማንነቴ ተበድያለሁ" ብሎ የቂም ታሪክ የሚያስተጋባው ስንት ነው? ግን በዚች የግፍ ምድር ላይ እንደ ሙስሊሙ የተገፋ አለ ወይ? እንደ ሙስሊሙ በጅምላ የታ -ረደ አለ? እንደ ሙስሊሙ በግፍ የተፈናቀለ አለ? እንደ ሙስሊሙ የታሪክ ደባ የተፈፀመበት አለ?! በፍፁም!
"ኢትዮጵያ የመቻቻል ሃገር ናት" የሚለው አባባል በሃገሪቱ በፖለቲከኞችና በጋዜጠኞች ከመደጋገሙ የተነሳ እውነት የመሰለ ትልቅ ውሸት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ መቻቻል እንዳልነበረ አንድ ሺ አንድ ማስረጃዎችን መደርደር ይቻላል። ትላንት ቀርቶ ዛሬም መቻቻል የለም። ነገር ግን መብቱን የሚጠይቀውን ሁሉ "ፀረ መቻቻል" አድርጎ በመሳል ነባሩን አግላይ አካሄድ ቀባብተው ማስቀጠል ነው ህልማቸው። ትላንት ያልነበረውን፣ ዛሬም የሌለውን መቻቻል እያዜሙ!
·
መስጂዶች ሲፈርሱና ሲቃጠሉ፣ ለመስገጃ ኩርባን መሬት ሲከለከል፣ ሙስሊም ተማሪዎች በሃይማኖታቸው ሳቢያ ከትምህርት ገበታ ሲባረሩ ከግል እስከ መንግስት ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች፣ እስከ አክቲቪስቶች ድረስ ኮሽታ አያሰሙም። ይልቁንም አንተ ቤተ ክርስቲያን ስታፀዳ፣ የኩ ^ፍ -ር በአል ስታደምቅ፣ ለቤተ ክርስቲያን መገንቢያ ገንዘብ ስታስገባ በመቻቻል ስብከት ያደነዝዙሀል። "ጥምቀት የክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሙስሊሙም ነው፣ የሁሉም ነው" እያሉ ከጋዜጠኝነት ባሻገር ሰባኪ ሰባኪ ይጫወቱልሀል። እነሱ ስራቸውን እየሰሩ ነው። ሃይለ ሥላሴ በሙስሊሙ ላይ ስውር ደባ ሲፈፅምም "ሃገር የጋራ፣ ሃይማኖት የግል ነው" የሚል መሸንገያ ነበረው። ዛሬም እንዲሁ እየተፈፀመ ነው። በምላስ እየሸነገሉ በተግባር መውጋት! "አዋህም ከም ዴ ሲል የሞዴ" አለ አርጎባ። "አባትህም እንዲህ ሲል ነው የሞተው!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 27/2011)


"የጠዋት አዝካር"


اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنا وَبِكَ أَمْسَينا، وَبِكَ نَحْيا وَبِكَ نَمُوتُ وَإِلَيْكَ النُّشُور.


👉"አላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሳይና፤ ወቢከ ነሕያ ወቢክ ነሙት፤ ወኢለይከ ኑሹር"


👉 "አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
/ ቲርሙዝይ/


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የምሽት ዝክሮች


ሳዑዲ አረቢያ ሶሪያን መልሶ ለመገንባት በሚደርገው ሂደት ላይ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች!

- ሀሩን ሚድያ፣ ጥር 26/2017

የሶሪያ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አሕመድ አሸረዕ በትላንትናው ዕለት ከልዑል አልጋወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ጋር ሪያድ በመገኘት ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሳዑዲ አረቢያ ሶሪያን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ሂደት እንደምትደግፍ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ተናግረዋል።

የሶሪያ ፕሬዝዳንት አሕመድ አሸረዕ በበኩላቸው ሶሪያን እንደቀደመው ሁሉ ገናና ለማድረግ ከሙስሊሙ ሀገራት መሪዎች ጋር በትብብር እንደሚሰሩ በማንሳት የሶሪያን ሰላም ወደቀደመው እንዲመለስ ለማድረግ እንደሚጥሩ ገልፀዋል።

አሕመድ አሸረዕ በዛሬው ዕለት ኡመራ ለመፈፀም መካ እንደሚገኙም የሳዑዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


ጥንታውያኑ ቻይናውያን በሰላም መኖር ቢያምራቸው ታላቁን የቻይና ግንብ ገነቡ። ቁመቱ ክፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ማንም አይወጣበትም፣ ማንም አይደርስብንም ብለው አምነዋል። ነገር ግን...
ግንቡ በተገነባ የመጀመሪያው መቶ አመት ውስጥ ብቻ ቻይና ሶስት ጊዜ ለጠላት ወረራ ተጋለጠች። በያንዳንዱ ወረራ ጊዜ ግዙፉ ወራሪ ሀይል ታላቁን የቻይና ግንብ መስበርም መንጠላጠልም አላስፈለገውም ነበር። እናስ? ሰተት ብለው ነበር በበሩ የሚገቡት። እንዴት አድርገው? ቀላል ነበር። ለግንቡ በረኞች፣ ለዘበኞቹ ጉቦ ይሰጣሉ። ከዚያ ነገሩ ሁሉ ያልቃል።

ቻይናውያን በዙሪያቸው ግዙፍ ግንብ በመገንባት ሲጠመዱ ዘበኛ መገንባት ግን ዘንግተዋል። ስብእናን መገንባት ሌሎች ነገሮችን ከመገንባት የሚቀድም ነገር ነው። ይሄ ጉዳይ ትኩረት ሊቸረው የሚገባ ጉዳይ ነው። አንዱ የምስራቁን ታሪክና ትውፊት የሚያጠና ተመራማሪ እንዲህ ይላል፡-

“የአንድን ህዝብ ስልጣኔ ማፈራረስ ከፈልግክ ሶስት መንገዶች አሉልህ፡-
1. ቤተሰብን ማፍረስ
2. የትምህርት ስርአቱን ማፍረስ
3. መልካም ምሳሌና አርኣያ የሆኑ ሰዎችን ስብእናቸውን ማጠልሸት

* ቤተሰብን ለማፍረስ እናት ሚናዋን እንዳትወጣ አድርጋት። “የቤት እመቤት” በመባሏ እንድታፍር አድርጋት።
* የትምህርት ስርኣቱን ለማፍረስ አስተማሪው ላይ አነጣጥር። ህብረተሰቡ ጋር ያለውን ቦታ አሳጣው። ተማሪዎቹ ይንቁት ዘንድ ደረጃውን አውርደው። * አርአያዎችን ለማፍረስ ዓሊሞች ላይ አነጣጥር። አንቋሻቸው። ዋጋ አሳጣቸው። ማንነታቸውን ሰዎች እንዲጠራጠሩ አድርግ። ያኔ ሰዎች አይሰሟቸውም። ምሳሌም አያደርጓቸውም።

• አስተዋይ እናት ከጠፋች
• ከልቡ የሚሰራ አስተማሪ ከጠፋ
• ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ዋጋ ካጡ
ማነው ትውልዱን በመልካም ስነ-ምግባር የሚያንፀው?!

ከዐረብኛ የተመለሰ
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 25/ 2007)


ሂንድ ቢንት አቢ ኡመየህ አል መኽዙሚ የነቢዩ ሚስቶች ክፍል 5


👉ሂንድ ቢንት አቢ ኡመየህ ቢን አልሙጊረህ አልመኽዙሚይ እናቷ: ዓቲከህ ቢንት ዓሚር አልከናኒየህ አባቷ: አቡ ኡመየህ ሱሀይል ቢን ሙጊራህ አልመኽዙሚ የመካ ሰዎች ዛዱራኪብ/የተጓዦች ስንቅ/ ይሉታል ምክኒያቱም ከተጓዦች ጋር አብሮ ከወጣ ስንቃቸው በሱ ወጪ ስለሚያደርግ ነው፡፡

👉ክብሯ: እሷና የቀድሞው ባሏ አቡሰለማ ለዲናቸው ሲሉ ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ውስጥ ናቸው ከዛም የሁለተኛውን ስደት ወደ መዲናም ተሰደዋል አቡ ሰለማ የነቢዩ/ ﷺ / የአጎቱ ልጅ እና የጡት ወንድማማች ናቸው ባሏም ሲሞት ነብዩ / ﷺ / አገቧት ነብዩ / ﷺ /ጋር አብራ ከፊሉን ጅሀድ ወታለች እሷም የአማኞች ሁሉ እናት ናት።

👉መሕሯ: ከተምር ቅጠል የተሰራ ፍራሽ፡ጆክ፡ትሪ እና ጥቂት ምግብ

👉የስነ-ምግባሯ ባሕሪ:
አሏህን ተጠንቃቂ አማኝ፡ታጋይ፡ለባሏ ታዛዥ፡አርቆ አሳቢ እና ታጋሽ ናት ልጆቿ: ከነብዩ / ﷺ / ልጅ አልወለደችም ከቀድሞው ባሏ/አቡሰለማ/ የወለደቻቸው ሰለመህ፡ ዑመር፡ዘይነብ እና ሩቀየህ ናቸው እነሱም ከነብዩ / ﷺ /በሆነ እንክብካቤ ነው ያደጉት ህልፈቷ: በ ዚልቂዕዳ ወር በ59ኛው አመተ ሂጅራ ላይ አረፈች ያስተላለፈችው ሀዲስ: 378 ሀዲሶችን አስተላልፋለች


"የ25 ነቢያት የህይወት ታሪክ ክፍል"
ነብዩሏህ ኑህ علايه السلام
"

👉የነብዩሏህ ኑህ علايه السلام*... አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከነዝያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ። ኑህም ህዝባቸውን ሰበሰቡ'ና፥'' እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡ በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ(ክፍያ) አልጠይቃችሁም። ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" ብለው ህዝባቸውን ተጣሩ። ይህን ሲሰሙ አስተባበሉት ምንም ሊያምኑለት አላቻሉም።እንዲያውም ያፌዙበት ጀመር።

👉ኑህ علايه السلام ያለመሰላቸት ዘወትር ጥሪም ያደርግላቸውም ነበር። የህዝቦቹ ማፌዝ እና ማላገጥ በበዛበትም ግዜ'' ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ።

👉የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ።'' አላቸው። የኑህን ዐ ሰ ንግግር በሰሙ ግዜ በጣም በመገረም " አንተ ነህ!!! አንተ እኮ እንደኛው ሰው ነህ እንዴት ነው መልዕክተኛ ነኝ ምትለው? በዛ ላይ ጥቂት ተከታዮች አሉህ ሁሉም ግን ድሀ እና ኮሳሳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው። ደግሞም በሀብትም ሆነ በክብር ከኛ ጋር አትመጣጠኑም" ብለውሞ አስተባበሉ። ያም አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ በሚፈፅሙት የሀውልት አምልኮ እንዲፀኑ ይመካከሩም ጀመር፡፡ ኑህም የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው በመለማመጥ መልኩ፥አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን'' እያለ ቢያግባባቸውም ክህደታቸው ይበልጥ እየጨመረ እንጂ ምንም አይቀንስም ነበር።

👉ምንም እንኳን ኑህ( علايه السلام) የህዝቡ ነገር ተስፋ ቢያስቆርጣቸውም ተልዕኮዋቸውን በሚገባ በማድረስ ላይ ቀጥለዋል። እናም ሁሌ ቀን እና ማታ ህዝባቸወን ስለ አላህ ሲያስታውሷቸው ህዝባቸው የነቢያቸውን ዳዕዋ ከመስማት ጆሮዋቸውን መያዝ ጀመሩ።ጆሮዋቸውን ይዘው መስማት እንቢ ሲሉ ኑህ (علايه السلام) በምልክት ይነግሯቸው ነበር። ኑህም በምልክት ሲነግሯቸው ህዝቡ ግን አይኖቻቸውን በልብሶቻቸው ይሸፍኑ ነበር።


ዳዕዋ ሰለፍያ በሶባ(አሸዋዉ) ✈ dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
⭕️👉አሏህን የተገናኘ ሰው የቂያማ እለት (የውመል ቂያማ) ፦

ሸይኽን እያመለከ ❌

በቀብር ተበሩክ እያደረገ ከቀብር በረካን እየፈለገ❌

በተሚማ አንጠልጥሎ ተበሩክ እያደረገ❌

አሏህን የተገናኘ።

መልካም ስራ የለውም ፣ ሰባት ገዜ ሀጂ ቢያደርግ ፣ ብዙ የሆኑ የረመዷን ወሮችን ቢፃም፣በጣም ብዙ ሶላቶችን ቢሰግድ አይጠቅመውም።

አሏህ እንዲህ ብሏል፦
وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡

ይሄ ሽርክ ለዚች አገር መከራ ነው

🎤 ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂር (ሀፊዘሁሏህ)



👉⭕️አወ ጀማ ንጉስን፣ ማምለክ ፣ገታን ማምለክ ፣ማይባርን ማምለክ ፣አርባ ጫማን ማምለክ፣የቦረናውን ሸይኽ ማምለክ ፣አናን ማምለክ ፣ዳናን ማምለክ ፣ቁጥብን ከማምለክ ሰይፉ ጨንገሬን ማምለክ፣ ጭሌን ማምለክ፣ ለዛፍ ማረድ፣ በየ ሾላው ስር ከማረድ፣በየ ወንዙ ዳር ከመገበር፣በየሜዳው ላይ ለባድገዝ ድንኳን ጥሎ ከማጫጫስ፣ለጅን መገበር፣ ማረድ፣ቃልማ እያሉ መስከረም መስከረም ጥቁር በግ ገነጣጥሎ ማጫጫስ፣ ነጭ ፍየል ገዝቶ ቃልማ ብሎ ሀገሩን ማዞር፣መቃም ወ~ዘ~ተ የዚች ሀገር በተለይ የወሎ ሙሲባ ማነቆ መከራ ችግር ነው

ነጃ መውጣት ከፈለግን ይህንን አጉል ኮተት እምነት ህዝባችን እንዲተወው መስራት አለብን በተለይ በገጠር ለእናት ለአባቶቻችን ማስተማር ለወገናችን ማሰብ ይኖርብናል።

ወንድም አቡ ሹራ አህመድ

ለተጨማሪ ጠቅ አርጓት👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/5064
https://t.me/Sobabilalmesjid/5064


የዘንድሮውን ረመዳን የሚያደምቁልን ብርቅዬ ቃሪኦች
የዘንድሮ 1446 (2025) የወርሃ ረመዿን በመከተ-ል-ሙከረማህ መስጂደ-ል-ሐረም ተራዊሕና ተሀጁድ የሚያሰግዱት ኢማሞች ስም ዝርዝር ወጥቷል።

1- ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ዐብዱ-ር'ረሕማን ሱደይስ
2- ሸይኽ ማሂር አል-ሙዐይቂሊ
3- ሸይኽ ዐብደልሏህ ጁሀኒይ
4- ሸይኽ በንዲር በሊላህ
5- ሸይኽ ያሲር ደውሳሪ
6- ሸይኽ በድር አል-ቱርኪ
7- ሸይኽ ወሊድ አል-ሸምሳን

አላህ ረመዿንን በሰላም ያድርሰን።
t.me/tewhidnasuna


"የጥዋት ዚክሮች"

ከአፋችን መጥፋት የሌለባቸው ዝክሮች
👉ሱብሃነላህ
👉አልሀምዱሊላህ
👉ላኢላህኢለሏህ
👉አላሁአክበር


ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

💡 فضل  شهر شعبان🌙

🌙"የሻዕባን ወር ቱሩፋት" 💡🎴በሚል ርዕስ፡

🟢በወንድም አቡ ዑሰይሚን [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።

🔜ሰአት➡️ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤0️⃣0️⃣ጀምሮ።

            📌የሚተላለፍበት ቻናል፡
                  ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

🎴  https://t.me/Yeselefoch

           🌹በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🌹


በወርሃ ሸዕባን ምን እናድርግ?… 
⚀ ጾም ማብዛት። ሰኞና ሀሙስ እና ሌላውንም መለማመድ። ለረመዳን መዘጋጀት።… 
⚁ በቀደሙ ረመዳኖች ያመለጡንን ቀዷ ማውጣት።… 
⚂ ከሰዎች ጋር እርቅ መፍጠር። ጥላቻና ቂምን መተው። የሰዎችን ሐቅ መመለስ። የረመዳንን በረከት ከሚያሳጡ መካከል መጥፎ ስነምግባር እና  የሰዎችን ሐቅ መጣስና በደል መፈፀም  ዋነኞቹ ናቸው።

«አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ሸዕባን ወበሊግና ረመዳን።»



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.