#Ethiopia #OromiaRegion
“ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተወሰዱት 50 ገቢያተኞቹ እስካሁን አልተመለሱም” - ነዋሪ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሰዎች ለቅሶና ገበያ ሲሄዱ ጭምር እየታገቱ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተግረዋል።
“ታጣቂዎች በየቦታው ሰው ይወስዳሉ” ያሉ አስተያየት ሰጪ በተለይም ሰው ገቢያም ሆነ ለቅሶ እንኳ ለመሄድ ስጋት እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ከደብረሊባኖስ አካባቢ ወደ ያያ ጉሌሌ ለገቢያ ሲጓዙ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ 50 ሰዎች ሳዲኒ ብዮ በሚባል የያያ ጉሉለ ወረዳ ታፍነው ከደተወሰዱ እንዳልተመለሱ ሌላኛው ነዋሪ ገልጸዋል።
“ገቢያ ስሄዱ የነበሩ አንድ ሙሉ መኪና አብዛኞቻቸው ነጋዴዎችና ገቢያተኞች የሚገኙባቸው ያለፈው ማክሰኞ ሳምንት ወደ ጉሌሌ ለገቢያ እየመጡ ሳለ ነው ሳዲኒ በሚባል ቀበሌ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት፡፡
ይህ ቦታ ከአንድ ወር በፊት አምስት የዞን ባለስልጣናትን ጨምሮ የመንግስት ሰራተኞች የተገደሉበትም ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተወሰዱት ወደ 50 የሚሆኑት ገቢያተኞቹ እስካሁን አልተመለሱም፡፡ ሾፈርም አብሮ እንደተወሰደ ነው” ብለዋል፡፡ #DW-Amharic
@ThiqahEth