"ጋዛን መልሶ ለመገንባት ቢሊዮን ዶላሮች ያስፈልጋሉ" - ተ.መ.ድ
"ጋዛን መልሶ ለመገንባት ቢሊዮን ዶላሮች ያስፈልጋሉ" ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ።
የተ.መ.ድ ልማት ፕሮግራም በሁለቱ ወገኖች መካከል የነበረው ጦርነት ጋዛን 69 አመት ወደ ኋላ እንድትመለስ አድርጓታል ሲል አስታውቋል፡፡
በጋዛ የመጠለያ ቤቶችን ገንብቶ የማጠናቀቅ ስራ ብቻ እስከ 2040 ድረስ ሊወስድ እንሚችል ጠቁሟል፡፡
እስራዔልና ሀማስ ለ15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ቅዳሜለት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወቃል፡፡
በጦርነቱ 1200 እስራዔላውያንና 46,000 ፍልስጤማውያን ህይወታቸው ማለፉን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ከስምምነቱ በኋላ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። #dailytrust
@ThiqahEth