ኢትዮጵያ አንድ ቢሊየነር አስመዘገበች።
ቢሊየነርስ አፍሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ 10 እጅግ የናጠጡ ሀብታሞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
መፅሔቱ ግብፅ፣ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ያላቸው ባለሀብቶችን ማፍራት የቻሉ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን ያላት ቢሊየነር አንድ ብቻ ነው፡፡ እሳቸውም ሼክ መሀመድ አልአሙዲ ናቸው፡፡
በመከተል በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉ በርካታ ሚሊየነሮች በኢትዮጵያ እንዳሉ ዘገባው አስረድቷል፡፡
አልአሙዲ በቁጥር አንድነት የተቀመጡ ሲሆን፣ የሀብታቸው መጠን 9.56 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡ በሁለተኛ የተቀመጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩትና የሳንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ናቸው፡፡
በቢሊየነርስ አፍሪካ ዝርዝር በሶስተኛነት የተቀመጡት የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ናቸው፡፡
በአራተኛ ደረጃ የተቀመጡት ደግሞ ከሀይል አቅርቦት እስከ ሸቀጣ ሸቀጥና ሪል ስቴት ዘርፍ ባሉ ስራዎች ላይ የተሰማሩት አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ ናቸው፡፡
መፅሄቱ በአምስተኛ ደረጃ ያስቀመጣቸው በዋሽንግተን ዲሲና ኒውዮርክ ከተሞች በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ያላቸውና በቨርጂኒያ የሪል ስቴት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን አቶ ኢዮብ ማሞ ነው፡፡
አቶ ከተማ ከበደ ስድስተኛ፣ አቶ አለማየሁ ከተማ ሰባተኛ፣ አቶ ብዙአየሁ ቢዘኑ ስምንተኛ፣ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ዘጠነኛ እንዲሁም የአቪየሽን ባለሙያው አቶ ግርማ ዋቄ አስረኛ ሁነው አጠናቀዋል፡፡ #billionairesafrica
@ThiqahEth